በአሰራር ሂደት የሚከሰቱ ስህተቶች ለዳኝነት ነጻነት አለመኖር ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ እንደማይገባ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
ሰሞኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር አጣሪ ችሎት በቀረበ አንድ የፍትሐ-ብሔር ጉዳይ ላይ በአመራሩ ጣልቃ ገብነት ሁለት ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንደተሰጠ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ በፍርድ ቤቱ ዳታ ቤዝ ባለሙያዎች በተፈጠረ የአሰራር ስህተት ምክንያት መሆኑን ጉዳዩን ያጣራው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
በፍርድ ቤቱ አመራር ጣልቃ ገብነት የዳኝነት ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የጠቅላይ ፍ/ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን ለማጣራት ባካሄደው ምርመራ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች የሰበር አጣሪው ችሎት በአምስት ዳኞች ውሳኔ የሰጠበትን ጉዳይ ቀደም ሲል “አያስቀርብም” ለማለት በመዝገቡ ውስጥ ተያይዞ የቀረበን ቅጽ በመመልከት ውሳኔ እንደሰጠ የሚገልጽ የተሳሳተ መረጃ በመረጃ ቋት (Database) ውስጥ በማስገባታቸው ምክንያት የተፈጠረ ችግርን መነሻ በማድረግ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የፍርድ ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ችግሩን የፈጠሩት ባለሙያዎችንና የችግሩን ስረ ነገር ለመለየት የማጣራት ስራውን የቀጠለ ሲሆን በዚህ ያልተገባና ሃላፊነት በጎደለው ተግባር ላይ ድርሻ ያላቸው ባለሙያዎች ለተፈጠረው ስህተት በዲሲፕሊን እንዲጠየቁና በፍርድ ቤቱ በተዘረጋው የተጠያቂነት ስርዓት ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡም የዳኝነት ነጻነት የለም፤ የዳኝነት አካሉ አሁንም ከጣልቃ ገብነት ነጻ አልወጣም እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚተላለፈው መረጃ ከእውነት የራቀና መሰረት የሌለው መሆኑን ተረድቶ በዳኝነት አካሉ ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም አስተያየቶችና የሚቀርቡ ትችቶችን በጥንቃቄ እንዲመዝናቸው ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቶች ዜጎች ፍትህ ለማግኘት ጠንካራ ተስፋ የሚጥሉባቸው ተቋማት ናቸው ያለው ዳይሬክቶሬቱ የፍ/ቤቶች መልካም ገጽታን የማጠልሸትና የህዝቡን አመኔታ በመሸርሸር አሉታዊ ውጤት ያላቸው መረጃዎችን በማንጨት የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ቆም ብለው ጥቅምና ጉዳቱን እንዲያመዛዝኑም መክሯል፡፡ የምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የደረሰበትን የምርመራ ውጤትም እንዲህ አብራርቷል፡፡
ጉዳዩ በጄፎር ኮንስትራክሽን እና አስማማው ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የውል ክርክር ሲደረግበት የቆየ ነው፡፡ አመልካች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ችሎት ዳኝነት በጠየቁበት ጉዳያቸው ላይ የሰጠው ውሳኔ የህግ ትርጉም ስህተት ያለው መሆኑን ጠቅሰው የሰበር ችሎቱ ጉዳዩን አይቶ እንዲያርምላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የአቤቱታውን ተገቢነት እንዲያጣራ በመዝገብ ቁጥር 185837 ጉዳዩ የቀረበለት 1ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን ሰምቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በጉዳዩ ላይ የችሎቱ ሁለቱ ደኞች የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡበት እና አንድ ዳኛ ግን በጉዳዩ ላይ እንነጋገርበት ማለታቸውን የሚያሳይ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሞላ የውሳኔ ቅጽ ተያይዟል፡፡ በዚህም ምክንያት ችሎቱ ውሳኔ ያልሰጠ መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል፡፡
አቤቱታ አቅራቢው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጉዳያቸው ውሳኔ ሳይሰጠው ረጅም ጊዜ መውሰዱን፤ መዝገባቸውም ቀጠሮ ሳያገኝ መቆየቱንና በዚሀም ምክንያት ጉዳያቸው በምን ደረጃ ላይ እንደለ መረጃ ማግኘት ያልቻሉ መሆኑን ጠቅሰው መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንትም ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፡፡ ከችሎቱ ዳኞች ጋርም ባካሄዱት ውይይት ክብርት ፕሬዝደንቷ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 21 (1) በተሰጣቸው ስልጣንና በችሎቱ ዳኞች ስምምነት ጉዳዩ በሶስት ዳኞች ከሚታይ ይልቅ በአምስት ዳኞች እንዲታይ የስራ መመሪያ ይሰጣሉ፡፡
አምስቱ ዳኞችም መዝገቡን መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም አስቀርበው ጉዳዩን መርምረዋል፡፡ በመጨረሻም ሰበር ችሎቱ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ ሊያያቸው የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮች ያሉበት ነው በማለት “ያስቀርባል” የሚል ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ያሳልፋል፡፡
በዚህ ሂደት መዝገቡ ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ዳታ ቤት በመሄዱ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች መጀመሪያ የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበትን ነገር ግን ውሳኔ ያላረፈበትን ቅጽ በመመልከት ጉዳዩ “አያስቀርብም” ተብሎ መወሰኑን የሚገልጽ መረጃ መረጃ ቋት (Database) ውስጥ በስህተት ያስገባሉ፡፡ ይህም መረጃ ለባለጉዳዮች በ992 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይደርሳቸዋል፡፡ ባለጉዳዮቹም ውሳኔውን ተቀብለው በዝምታ ያልፋሉ፡፡ በሌላ በኩል በበችሎቱ ውሳኔ መሰረት በሪጂስትራር በኩል የአመልካች የሰበር አቤቱታ ከፍርድ ቤቱ መጥሪያ ጋር ለተጠሪ እንዲደርስ በታዘዘው መሰረት መጥሪያው እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
የተፈጠረውን ስህተት ለማረም በመረጃ ቋት (Database) በገባው ትክክለኛ መረጃ መሰረት ለባለጉዳዮቹ መዝገቡ ያስቀርባል ተብሎ መወሰኑን እንዲሁም ለምርመራ እና የመልስ መቀባበያ ቀጠሮ መሰጡተን የሚገልጽ መረጃ በ992 አጭር የጽሁፍ መልእክት በድጋሚ ይደርሳቸዋል፡፡
በአንድ ጉዳይ ላይ አንድ ችሎት በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንዴት ሊሰጥ ይችላል የሚል ተገቢነት ያለው ጥያቄ ምናልባትም ከግራና ቀኝ ተከራካሪ ባለጉዳዮች መካከል አንዱ ያነሳሉ፡፡ ለዚህም ጥያቄ አሁን ላይ ማንነታቸው ተለይቶ ያልታወቁ አካላት ያልተገባና እውነታነት የሌለው ምክንያት በመስጠት የዳኝነት ነጻነት በአመራሩ ጣልቃ ገብነት መጣሱንና የውሳኔ ለውጥ መደረጉን የሚገልጽ መረጃ መሰራጨት መጀመሩን የምርመራ ክፍሉ አመልክቷል፡፡ ነገር ግን አቤቱታ አቅራቢው ባለጉዳይ ከላይ እንደተገለጸው ለፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ውሳኔ ዘገየብኝ፤ መዝገቡም ቀጠሮ ባለመያዙ ጉዳያቸው ያለበትን ደረጃ ማወቅ አለመቻላቸውን የሚገልጽ መሆኑን ከመዝገቡ ጋር የተያያዘው ማስረጃ ያሳያል፡፡
ይህን አይነት የተለመደ አቤቱታ የመቀበልና አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠት አሰራር በተሳሳተ ግንዛቤ ዓላማውን እንዲስት በማድረግ አቤቱታው ውሳኔ እንዲሻሻል የቀረበ በማስመሰልና ከእውነት የራቀ መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን የምርመራ ክፍሉ ጠቁሟል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በዲሲፕሊን የሚጠየቁ አካላትን ለይቶ ተገቢው አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን በማረጋገጥ ጉዳዩን ለማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም የመዝገቡን ሙሉ ግልባጭ በማግኘት ማጣራት እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ ፕሬስ መግለጫ
#Ethiopia : በአገራችን የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ በመንግስትና በባለድርሻ አካላት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን ትዕዛዞች፣ ክልከላዎችና መልዕክቶች እየተላለፉ ነዉ፡፡ እነዚህን መልእክቶችና ትእዛዞች ሰምቶ ለራስ በመፈጸምና ሌሎችን እንዲፈፅሙት በማድረግ በኩል በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም ነገር ግን በርካታ በሚባለዉ ህብረተሰቡ ዘንድ የመዘናጋት፣ የቸልተኝነትና በሽታዉን አስመልክቶ የሚሰጡ ትእዛዛቶች ወደ ጎን በመተዉ የሚሰጡ መግለጫዎችን የመላመድና ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታዎች እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ በቅርቡ በመንግስት ተቋማት፣ በልማት ድርጅቶችና በግል ተቋማት ወሰጥ ያደረግነዉ ምልከታ ከቅደመ ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ የመዘናጋት፣ ትኩረት ያለመሰጠት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ማህበረሰባችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተለይም በግብዓት ቦታዎችና በትራንስፖርት አገልግሎት መሰጫ አካባቢ እያሳየ ያለዉ መዘናጋትና ህጎቹን ያለማክበር ጉዳይ አሳሳቢ ነዉ፡፡ ይህ የኮሮና ቫይረስ በአገራችን በተገኘበት እና የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ሰሞን የነበሩ ጥንቃቄዎች ጋር ሰነጻጸር እየቀነሰ መዘናጋት እየጨመረ ሲሆን በተቃራኒዉ አሁንም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እጅጉን አሳሳቢና ዋጋ የሚያስከፍል ጉዳይ እየሆነ ይገኛል፡፡ መንግስት በሽታዉን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዉጆ ደንብና መመሪያዎችን በማዉጣት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ከዚህ ቀደም የወጡ መመሪያ ቁጥር 1/2012 እና መመሪያ ቁጥር 2/2012 ማሻሻያዎችን የያዘ መመሪያ ቁጥር 4/2012ን አፅድቆ ስራ ላይ እንዲዉል አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡
በዚሁ መሰረትም በመመሪያ ቁጥር 4 በኮድ 2 በቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ ከፊል የእንቅስቃሴ ክልከላ ፣የማሰክ አጠቃቀም ፣ በአገር አቋራጭ የህዝብ ተሸከርካሪዎች ላይ እንዲሆም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች መግቢያና መዉጫ ስአት ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
የኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ላይ መጣል የሚገባው የትራንስፖርት ሚኒስቴር በኩል የተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ በከፊል በመገደብ ግለሰቦች ቤታቸዉ እንዲዉሉ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ታሳቢ ተደርጎ በሙሉና በጎዶሎ መለያ ቁጥር ከፊል እገዳ ተጥሎ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ሆኖም የኮድ 2 ተሸከርካሪ ባለቤቶች በታሰበዉ መልኩ ቤታቸዉ ከመዋል ይልቅ የህዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም እና ታርጋዎችን እየቀያየሩ የመጠቀም ሁኔታ መታየቱ እንዲሁም ተራቸዉ ባልሆነ ቀን ቤታቸዉ ከመዋል ይልቅ በሰፊዉ የመንቀሳቀስ ሁኔታ የተስተዋለ መሆኑ ክልከላዉን መልክ መቀየር አሰፈላጊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ በኮድ ሁለት የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነስቶ አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል አማራጭ ክልከላ እንድተገበር የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወስኗል፡፡
የእንቅስቃሴ ገደብ መቀነሻ አሰራሮች አንዱ የሆነዉ በሀገር አቋራጭ ተሸከሪካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡
የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ለመገደብ አስተዋጽኦ እንደሚያደረግ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የተደረገው ጥናት ያመላክታል፡፡ በዚሁ መሰረት አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ የወንበር አቅማቸዉ ከ45(አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ ተወሰኗል፡፡ በተያያዘ የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት የማስክ አጠቃቀምን አስመልክቶ ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግን ግዴታ እንዲሆን ወስኗል፡፡ የአፍና አፈንጫ መሸፈኛ ማሰክ በፋብሪካዎች የተሰራ ወይም ባህላዊ ጨርቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ግዴታ በማስፈጸም ረገድ የጸጥታ መዋቅሩ ኃላፊነት እንዳለበት ተወሰኗል፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ስአት 1፡30 እንዲሆን የተቀመጠ ሲሆን መዉጫ ስአቱም 9፡30 እንዲሆን ተደርጎ ተሸጋሽጓል፡፡ ይህም የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመቀነስ ነው፡፡ በአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት በመሆኑ የሚታዩ መዘናጋቶችን እና ችላ ባይነትን በመቅረፍ ሁላችንም ህግና ሥርዓቱን ማክበር ግዴታ እንደሆነ በመገንዘብ መላዉ የሀገራችን ህዝብ እራሱ፣ቤተሰቡንና ሀገሩን የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትለው ጉዳት ለአፍታም ሳይዘናጋ ለመጠበቅ ርብርብ እንዲያደረግ ጥሪያችንን እናቀረባለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
ቀን፡- ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

BEYOND LAW ENFORCEMENT
Human Rights Violation By Ethiopia Security Forces In AMHARA AND ORMOMIA
AMNESTY INTERNATIONAL

COVID-19 Pandemic Multinational Cross-sectional Study
Dear Colleagues:
This is a multinational project/ study containing more than 20 countries measuring the knowledge, attitude and practices towards COVID-19 Pandemic and it will be published in high ranking journal. I am one the researches who are engaged in conducting the research and here I tried to collect the questionnaire via online from respondents.
The questionnaire will be disseminated online so it will be easy. Here is my copy https://docs.google.com/forms/d/1M5m9vbTNNPwxdIhvRzXNfiQ-KHRjdlmVkaesUkbGyws/edit?usp=sharing to you. kindly share it with only people living in Ethiopia. The form is in Amharic, Afan Omoro, and English languages. Remember that I am obliged to collect at least 150 responses from respondents. There is the need to collect at least 900 responses from the whole country (Ethiopia) including mine part. The deadline of data collection will be 30/5/2020. The deadline is very close so do your best to fill the questionnaire within the given period of time. In my online profile and on commonly used platforms in Ethiopia, it is explained about the purpose of the the study. You can see the impact and objective of the study.
I kindly request you to take three to five minutes to fill the questionnaire online and finally submit it. The questionnaire is prepared in Affan Oromo, Amharic and English languages; and you can use any of the three languages to fill the questionnaire. I also kindly request you to share the message (Web Link) for your colleagues and families (any one you have his/ her email) to fill the questionnaire too. If you have any question regarding the questionnaire, do not hesitate to contact me via mail. I will respond you soon.
Stay home, stay safe

Google Docs
Madalli Beekumsa, Ilaalchaa fi Bartee dhibee weerara COVID-19 irratti qabdan/ በኮሮና-19 የወረርሽኝ በሽታን በተመለከተ የህብረተሰቡ ግንዛቤ፤ አመለካከትና…
Qorannaan kun Tilmaama,Beekumsa, Ilaalcha fi Bartee dhibee COVID-19 iratti ummatni qaban kan qoraatu yoo ta’u kunis kan kophaa’ee garee projectii reserchii adunyaalessatiin. Deebiin keessaan nuufis ta’e addunyaadhaaf bayyee barbaachisa. Qoranno kana irratti…
#COVID19Ethiopia
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሁለት የሞባይል መተግበርያ (አፕሊኬሽኖችን) አገልግሎት ላይ ማዋሉን አስታውቋል።
ከሞባይል መትግበርያዎቹ የአንደኛው የጤና ባለሞያዎችን እውቀት ለማሳድግ የሚያስችል ሲሆን ሌላው ኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መለየት የሚያስችል ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት አራዘሙ
***
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ፍርድ ቤቶቹ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ መወሰናቸውን ለኢቢሲ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩና አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲመለከቱ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የወረርሽኙ ስርጭት እየተስፋፋ በመምጣቱ ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረና የስርጭት አድማስም እየሰፋ መምጣቱን የጤና ጥብቃ ሚኒስቴር በየጊዜው ከሚያስራጫቸው መረጃዎች የፍርድ ቤቱ አመራር መገንዘብ ችሏል፡፡
አመራሩ ባካሄደው ስብሰባ የዳኝነት አገልግሎት ለማግኘት ከክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተሞች ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ባለጉዳዮች ቁጥራቸው በርካታ በመሆኑና የእነዚህ ባለጉዳዮች ለቫይረሱ ስርጭት ያላቸወን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ዳኞችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ ወስኗል፡፡
ፍ/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩበት ጊዜ በተረኛ ችሎት እንዲታዩ ከተለዩት ጉዳዮች በተጨማሪ አነስተኛ የተገልጋይ ቁጥር ያላቸው ሌሎች የዳኝነት አገልግሎት ሊሰጥባቸው የሚችሉ የጉዳዮችን በመለየት አገልግሎቱን በየጊዜው ቀስ በቀስ ለባለጉዳዮች ክፍት እየተደረገ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም በአመራሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜ፡-
1. ከሰኔ 30/2011 ዓ/ም በፊት የተከፈቱ ዉዝፍ ይግባኝ መዝገቦችን ለመወሰን በችሎት ባለጉዳዮችን የመስማት አስፈላጊነት የታመኑባቸው ጉዳዮች ተለይተው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
2. የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተከራካሪ ወገኖች ይሰማሉ፤ እንደየሁኔታው ከባለጉዳዮች ጋር በመነጋገር የቃል ክርክራቸውን በጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን ወሳኔ እንዲያገኙም ይደረጋል፡፡
3. የፍታብሔር ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ባለጉዳዮችን መስማት አስፈላጊነቱ በዳኞች ከታመነባቸው ጉዳዮች ውጭ የሆኑ መዛግብት እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል።
4. አስቸኳይ በሆኑ ጉዳችዮች በተረኛ ችሎት የተሰጠውን ትዕዛዝ፣ ብይን እና ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ የይግባኝ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት የሚሰጣቸው ይሆናል፣
5. አስቸኳነት ያላቸው ጉዳዮች ማለትም ከህጻናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፣ የዋስትና ጉዳይ፣ የአሰሪና ሰራተኞች ጉዳይ፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይሆናሉ፡፡
6. የፌዴራልና የክልል ጉዳዮች ውሳኔን መሰረት በማድረግ ተከፍተው በሂደት ላይ የነበሩ የአፈጻጸም ጉዳዮች የስራና አፈጻጸም አቅጣጫ እስከሚሰጥባቸው ጊዜ ድረስ በደረሱበት ደረጃ ቆመው የሚቆዩ ይሆናል፡፡
7. በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ተዘጋጅቶ በሚገለጸው መርሃ-ግብር መሰረት የውሳኔ፣ የትዕዛዝ፣ የብይንና የመዝገብ ግልባጭ የመስጠት ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ የሚገቡና የሚስተናገዱት ባለጉዳዮቹ ብቻ ይሆናሉ፡፡
ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ እንዲሁም በመግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ እጅ መታጠቢያ እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የእርስ በእርስ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንዲስተናገዱ የፍርድ ቤቱ አመራር አሳስቧል፡፡ የመከላከያ ጥንቃቄዎችን በአግባቡ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያደርሰው አስከፊ ጥቃት ህብረተሰቡ አራሱን እንዲከላከል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
#EBC

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ
ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት አራዘሙ፡፡
የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩና አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲመለከቱ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች በፍርድ ቤቶች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ ባካሄዱት ስብሰባ ገምግመዋል፡፡

3. የፍታብሔር ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ባለጉዳዮችን መስማት አስፈላጊነቱ በዳኞች ከታመነባቸው ጉዳዮች ውጭ የሆኑ መዛግብት እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

7. በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ተዘጋጅቶ በሚገለጸው መርሃ-ግብር መሰረት የውሳኔ፣ የትዕዛዝ፣ የብይንና የመዝገብ ግልባጭ የመስጠት ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ የሚገቡና የሚስተናገዱት ባለጉዳዮቹ ብቻ ይሆናሉ፡፡ ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ እንዲሁም በመግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ እጅ መታጠቢያ እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የእርስ በእርስ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንዲስተናገዱ የፍርድ ቤቱ አመራር አሳስቧል፡፡
የመከላከያ ጥንቃቄዎችን በአግባቡ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያደርሰው አስከፊ ጥቃት ህብረተሰቡ አራሱን እንዲከላከል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

Hi Ale, investment, human rights, teaching materials laklign ebakh
አለመፍራታችን ያስፈራል!
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)
የኮሮና ቫይረስ ወደ ሃገራችን ከገባ ድፍን ሶስት ወር ሊሞላው ተቃርቧል። ነገር ግን ከዛሬ ሶስት ወር በፊት እና አሁን ላይ ያለን የማህበራዊ ህይወት እምብዛም ልዩነቱ አይታይበትም።
ያኔ ገና አንድ ብለን ስንጀምር በብዙ መሸበር እና ግራ መጋባት እንዳልነበርን አሁን ላይ በቀን ውስጥ በመቶዎች ስናስቆጥር ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነን ደንገጥ አለማለታችን ያስፈራል። ጉዳዩን የቁጥር አድርገነዋል። ዛሬ ላይ የምንሰማው ከትላንቱ በአንድ እንኳን ካነሰ 'የዛሬውስ ይሻላል' እያልን ጥንቃቄያችንን በቁጥር ላይ መሰረት አድርገን እየተዘናጋን ነው። ጉዳዩ ግን የቁጥር እና የንፅፅር አይደለም።
በየቦታው የተሰቀሉት የእጅ መታጠቢያ ጄሪካኖች አሁን ላይ ከቦታቸው ተነስተዋል፣ አካላዊ እርቀቱ ተረስቶ እንደቀድሞው ሆነናል፣ የፊት ጭምብል ለአገጭ እና ለግንባር የተሰራ አስመስለነዋል፣ባጠቃላይ የመጀመሪያው ፍርሃታችን እና ጥንቃቄያችን የለም።
አንድ ሲባል እንዳልደነገጥን አሁን ላይ 100 በላይ ሲባል ምንም አልመስል ብሎናል፥ በፊት የምንወስዳቸው ጥንቃቄዎች ወረት ሆኖብን መድሃኒቱን ያገኘነው እስኪመስል ድረስ ቸልተኞች ሆነናል።
ነገር ግን የመጀመሪያውን ፍርሃታችንን ልንመልሰውና ወደ ጥንቃቄ ልንቀይረው ይገባል። ኮሮና ቫይረስን በምናብ የተሳለ ተረት አናድርገው፣ሲደርስብን ብቻ ለመንቃት አንሞክር።
መዘናጋታችን አሁንም ከዚህ በላይ ዋጋ ሳያስከፍለን ነቅተን አንዳችን ለአንዳችን ዘብ ልንቆም ይገባል። አሁን በደጉ ጊዜ ካለንበት ከቁጥር ዓለም እንንቃ እና ጥንቃቄ እናድርግ።
ፍርሃታችንን ወደ ጥንቃቄ በመለወጥ አድርጉ የተባልነውን ብቻ በማድረግ ሃገራችንን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንታደጋት።
''የአንተ/ያንቺ ጥንቃቄ ነገ ለእኛ ህይወት ነው''
via Tikvah

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 190 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው ፤አምስት ተጨማሪ ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል፡፡
https://amharaweb.com/በኢትዮጵያ-ተጨማሪ-190-ሰዎች-የኮሮናቫይረስ/
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4 ሺህ 599 የላቦራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዚህም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 2ሺህ 336 አድርሶታል፡፡
አምስት ተጨማሪ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፤ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል 135 ወንዶች ናቸው፡፡ ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ 89 ዓመት እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ቫይረሱ በአዲስ የተገኘባቸው…

Hello every body! Hopefully all you are fine ! Pealse could one of you help me in attaching the format of externship program. Thank u in advance!