‹‹ …. ጤነኛ የሆንን እና የገቢ ምንጭ ያለን ስዎች እስኪ በአካባቢያችን ቢያንስ አንድ የተቸገረ ሰው እንርዳ። በየአካባቢያችን እንደዚህ ያሉ የእኛን እርዳታ የሚሹ ብዙ ናቸው። አይኖቻችንን ከፍተን በፍቅር እና በርህራሄ እንያቸው፣ እንርዳቸው! ..››
ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ለአገራችን ህዝብ ሰላም እና ደህንነት ሽብርተኝነትን በጋር እንከላከል
_______________
አገራችን የሰላም እና የልማት እንጅ የጦርነት አውድማ አይደለችም፡፡ ትልልቅ አገራዊ የለውጥ እና የልማት ሀሳብ ይዘን በትንንሽ ጉዳዮች የለውጥ ጊዜን አናባክን፡፡
የሰከነ ሀሳብ ለአገራችን ለውጥ መደሃኒት በመሆኑ ዛሬን ከነገ የተሻለ ለማድረግ አስተውለንና በአንድነት ተባብረን መራመድ ይገባል፡፡
አንድ ስንሆን ስንተባበር ካሰብነው እና ካቀድነው አላማ እንደርሳለን፡፡ ውድ አንባቢያን!! ሽብርተኝነት በመላው አለም በሰው ልጆች ላይ ጻታ፣ ሀይማኖት፣ ዘርና አካባቢ ሳይለይ የተቃጣ ግልፅ ጦርነት ነው፡፡
በመሆኑም ከአሁን በፊት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ወጥቶ የነበረው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2009 በይዘትና አፈጻጸም ክፍተቶች የነበሩበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
አጥፊዎች ከድርጊታቸው ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ የሚያስችል፣ የግለሰቦችን መብቶችና ነፃነቶች በበቂ ሁኔታ ሊያስጠብቅና የሕግ አሰፈጻሚ አካላትን ተጠያቂነት የሚያሰፍን ሕግ መተካት በማስፈለጉ እና የሽብር ድርጊት ተጎጂዎች የህክምና፣ መልሶ ማቋቋምና መሰል ተግባራት ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ለመፍጠር የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሸሽሎ የወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በአዋጁ ድንጋጌ መሰርት ማንኛውም ሰው የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብን ክፍል ለማሸበር ወይም መንግስትን፣ የውጭ አገር መንግስትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ፡-በሰው አካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ የሰውን ሕይወት ለአደጋ ያጋለጠ፤ ሰውን ያገተ ወይም የጠለፈ፤ በንብረት፣ በተፈጥሮ ሃብት ወይም አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ፤ ወይም የሕዝብ ወይም ማህበራዊ አገልግሎት እንዳይሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ ያስተጓጎለ እንደሆነ ከ15 እስከ 18 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ያስቀምጣል፡፡
በሽብር ድርጊቱ የተፈጸመው ተግባር ሰውን መግደል፣ በታሪካዊና የባሕል ቅርስ ወይም የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እንደሆነ ከ15 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡
በመሆኑም ወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ እና ምርጫ ጋር በተያያዘ ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት የሽብረተኝነት ተግባር የተጠናወታቸው አካልት ሰላማችን እንዳይነጥቁን ነቃትን መጠበቅና ሕግን ማስከበር የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆን አለበት፡፡
https://telegram.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ #ውሳኔ አሳልፏል!
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 1441ኛውን የኢድ - አል - ፊጥር በዓል ምክንያት በማደረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋል።
******************************
ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው ይህ በዓል ምስጋና፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ይቅርታ የተሞላበት እንዲሆን በመመኘት በዓሉን ስናከብር አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችንን በመርዳት እና የደስታችን ተካፋይ በማድረግ ደስታ እና በዓል የማያውቀውን የኮሮና ወረርሽኝ ሳንረሳ ለእራሳችን እና ለቤተሰቦቻችን ከፍተኛውን ጥንቃቄ ማድረግ እና ህጎቹን ማክበር እንዳንዘናጋ አደራ በማለት አሳስበዋል።
በሌላ በኩልም በትላንትናው ዕለት ምሽት በአዲስ አበባ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ስፍራ በመገኘት በልይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዩች እና ይህን ውረርሽኝ ለመከላከል በግንባር ቀደምነት ለተስለፉ ህክምና ባለሙያዎች ና የጽጥታ አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ በስፍራው ለሚገኙ አካላት የበአል ስጦታ በጎችን አስረክቧል።
ኢድ ሙባረክ!

ለእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያት በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው ኢድ-አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ ... አደረሠን!!! ኢድ- ሙባረክ!!!
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች በተለያዩ ምድብ ችሎቶች በመዘዋወር የመስክ ምልከታ አድረገዋል
………………………………………………………………
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች ግንቦት 13/2012 ዓ.ም የተለያዩ ምድብ ችሎቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቱ በከፍል ዝግ በሆነበት በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ በአዲስ ከተማ፤አራዳ፤መናገሻ እና ልደታ ምድብ ችሎቶች በመገኘት ዳኞች እና ሰራተኞች እራሳቸዉን ከወረርሽኙ እየጠበቁ በአግባቡ ባለጉዳዮችን እያሰተናገዱ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡ በመስክ ምልከታዉ ወቅትም በየምድብ ችሎቶቹ ከሚገኙ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና ሰራተኞች ጋር የተወያዩ ሲሆን በዚህም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በፍርድ ቤቱ በኩል እሰከ አሁን የተወሰዱ እርምጃዎች የሚበረታቱ መሆናቸው ተገልጷል፡፡
በቀጣይነትም ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲያስችል በቂ አቀርቦት እና የስርጭት ስርዓት ሊኖር የሚችልበት አግባብ ላይ የፍርድ ቤቱ አመራሮች ከዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና ሰራተኞች ጋር ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
በሌላ በኩል የወረርሽኙን መስፋፋት ለመቀነስ ሁሉም ወደ ፍርድ ቤቱ የሚመጡ ባለጉዳዮች የመግብያ በር ላይ እጃችዉን በአግባቡ በዉሃ እና ሳሙና በመታጠብ ፣ አካላዊ ሪቀታቸዉን በመጠበቅ እና የአፍ መሸፈኛ ማስክ በማድረግ እየተስተናገዱ የሚገኙ መሆናቸውን መመልከት ተችሏል፡፡
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ክፍል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
-------------------------------
የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ማጥበቅና ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም በተመለከተ እንደገለጹት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ከጊዜ ወደጊዜ ወጥነት ባለው መልኩ እየተሻሻለ ኮሮናቫይረስን እንዳይስፋፋ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታየ በመሆኑና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ዜጎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑ የተሰጠውን ትኩረት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።
“በመሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያወጣቸውን ዝርዝር ደንቦች በትክክል እንዲተገበሩ በጥብቅ መከታተል ያስፈልጋል” ብለዋል።
“በተለይ በትራንስፖርትና ሌሎች ዘርፎች ላይ የአዋጁን ደንቦች በሚገባ ለማስፈፀም እንዲያስችል ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ አዋጁን ማየት እንዳለብን ተመልክተናል” ሲሉ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።
“አዋጁን በትክክል ተረድቶ ከመፈፀምም ይሁን ከማስፈፀም ስህተቶች ሊገጥሙ ይችላሉ” ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ፤ የአዋጁ አስፈፃሚዎች የሚያደርጉት ክልከላዎች የዜጎችን ህይወት ለማዳን እንደሆነ በመገንዘብ ደንቦቹን መተግበር ከሁሉም እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
በተለይም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ከማድረግና ካለማድረግ ጋር ሰዎች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ከሚለው ቅሬታ ጋር አያይዘውም “ህዝቡ ሰዎች በሚበዛባቸው ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በማናቸውም ቦታዎች ማስክ ቢያደርግ ይጠቀም እንደሆን እንጂ አይጎዳም” ሲሉ መክረዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስከበር ሽፋን ውስጥ የሙስና ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ መንግስት እንዴት ይከላከላል? ለሚለው ጥያቄም “ህዝቡ ህይወቱን አስይዞ መደራደር የለበትም” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ግን ወደ አላስፈላጊ ድርድር የሚገባ ህግ አስከባሪ ካለ ጥቆማ በመስጠት የዜጎችን ህይወትና የሙስና ወንጀልንም ከመንግስት ጎን ሆኖ እንዲከላከል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች ከዳኞች እና ሬጅስትራሮች የተሰበሰበ ገንዘብ ለክብርት ዳኛ ምጥን ከፈኔ ቤተሰቦች ሰጡ ፡፡
**********************************************
የፍርድ ቤቱ አመራሮች ዛሬ ግንቦት 18/2012 በግንቦት 14/2012 ዓ.ም ያረፈችውን ክብርት ዳኛ ምጥን ከፈኔ ቤተሰቦች ጋር በመሄድ አጽናንተዋል፡፡
አመራሮቹ ክብርት ዳኛ ምጥን ከፈኔ በህመም ላይ በነበረችበት ግዜ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እና የዋና መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ለህክምና እንዲውል የገንዘብ መዋጮ ያወጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዳኞች በቀጥታ አካውንት ያስገቡት እና ከግንቦት ወር ደመውዝ የሚቆረጠው ገንዘብ እንደጠበቀ ሆኖ 79,950 (ሰባ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ) ብር በጥሬ የተሰበሰበ ገንዘብ አመራሮቹ ለክብርት ዳኛ ምጥን ከፈኔ ቤተሰቦች ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይነትም ለክብርት ዳኛ ምጥን ልጆች አስፈላጊ እና አቅም በፈቀደ መልኩ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አመራሮቹ ገልጸዋል፡፡

ህዝባችንን ከኮሮና ወረርሽኝ ለመጠበቅ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ለነገ የማይባል ተግባር ነዉ!
-------------------------------------
ህዝባችንን ከኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ ለመጠበቅና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እንዲያስችል የተቀመጡ ግዴታዎችን ህብረተሰቡ አዉቆ እንዲተገብራቸዉ ከማድረግ በተጨማሪ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአንዳንድ ግዴለሽ ግለሰቦች የህብረተሰባችን ጤናና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በደንብ እና በመመሪያዎች የተቀመጡ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን እንዲተገብሩ በማድረግ የህግ የበላይነት ጥያቄ ዉስጥ በማይገባበት መልኩ የህዝባችንን ሰብአዊ መብት በመጠበቅ ህግን ለማስከበር ከመቼዉም ጊዜ በላይ መረባረብ የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ የህግ የበላይነትን በማስከበር የህዝባችንን ህይዎት ለመታደግ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፡፡
በመሆኑም ከጤና ባለሙያዎችና ከሐይማኖት አባቶች የሚሰጡ ምክሮችን የሚሰሙ፤ ከመንግስት የሚተላለፉ ህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን የሚተገብሩ የሚያከብሩ አልፎም የሚያስከብሩ በጎ ፈቃደኞችና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒዉ ደግሞ በግዴለሽነትና በመዘናጋት ምክሮችንና ግዴታዎችን ጭምር የማይተገብሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸዉ የሌሎችን በጤና የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥሉና የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ መልኩ የሚጨምሩ በመሆናቸዉ የቫይረሱ ስርጭት አሁን ካለበት ፍጥነት በከፋ መልኩ ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ በፊት እነዚህ አካላት ላይ ጠበቅ ያለና የወጡ ህጎችን የማስከበር ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ብሎም ሌሎችን ከመጠበቅ በዘለለ ከህግ አስከባሪዎች ጎን በመቆም ለራሱ ጤና ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡
https://telegram.me/lawsocieties
-------------------------------------
ህዝባችንን ከኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ ለመጠበቅና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እንዲያስችል የተቀመጡ ግዴታዎችን ህብረተሰቡ አዉቆ እንዲተገብራቸዉ ከማድረግ በተጨማሪ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአንዳንድ ግዴለሽ ግለሰቦች የህብረተሰባችን ጤናና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በደንብ እና በመመሪያዎች የተቀመጡ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን እንዲተገብሩ በማድረግ የህግ የበላይነት ጥያቄ ዉስጥ በማይገባበት መልኩ የህዝባችንን ሰብአዊ መብት በመጠበቅ ህግን ለማስከበር ከመቼዉም ጊዜ በላይ መረባረብ የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ የህግ የበላይነትን በማስከበር የህዝባችንን ህይዎት ለመታደግ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፡፡
በመሆኑም ከጤና ባለሙያዎችና ከሐይማኖት አባቶች የሚሰጡ ምክሮችን የሚሰሙ፤ ከመንግስት የሚተላለፉ ህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን የሚተገብሩ የሚያከብሩ አልፎም የሚያስከብሩ በጎ ፈቃደኞችና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒዉ ደግሞ በግዴለሽነትና በመዘናጋት ምክሮችንና ግዴታዎችን ጭምር የማይተገብሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸዉ የሌሎችን በጤና የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥሉና የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ መልኩ የሚጨምሩ በመሆናቸዉ የቫይረሱ ስርጭት አሁን ካለበት ፍጥነት በከፋ መልኩ ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ በፊት እነዚህ አካላት ላይ ጠበቅ ያለና የወጡ ህጎችን የማስከበር ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ብሎም ሌሎችን ከመጠበቅ በዘለለ ከህግ አስከባሪዎች ጎን በመቆም ለራሱ ጤና ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡
https://telegram.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
በሚኒሶታ በነጭ ፖሊስ ታንቆ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ በነጭ ፖሊስ የተገደለውን ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ መመርመር ጀምሯል፡፡
ክስተቱ ባሳለፍነው ሰኞ የተፈጸመ ሲሆን አንድ ነጭ የፖሊስ መኮንን ጥቁር አሜሪካዊን በእግሩ ጉልበት አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ መተንፈስ አቅቶት ሲዝለፈለፍ ያሳያል።
ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ በአስደንጋጭ ፍጥነት በተዘዋወረው ምሥል ላይ ነጭ ፖሊስ የዚህን ጥቁር አሜሪካዊ አንገት በጉልበቱ ተጭኖት እያለ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ተጠርጣሪው በበኩሉ ‹‹መተንፈስ አልቻልኩም እባክህን አትግደለኝ›› እያለ ሲማጸነው ይሰማል፡፡
ሟቹ የ40 ዓመት ጎልማሳ ጥቁር አሜረካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ይባላል።
ሆኖም ተጠርጣሪው በፎርጂድ ምርት ተግባር ላይ እንደተሰማራ ጥቆማ ደርሶት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሊያውለው እንደመጣ ተጠቅሷል፡፡ይህ ዘግናኝ ክስተት ከዓመታት በፊት በተመሳሳይ ቁጣን የቀሰቀሰውና በነጭ ፖሊስ ጭካኔ የሞተውን ኤሪክ ጋርነርን ያስታወሰ ሆኗል፡፡ ኤሪክ በወቅቱ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ ‹‹እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም›› እየለ በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር የሞተው፡፡ https://www.bbc.com/amharic/news-52816678 @bbc_amharic1

BBC News አማርኛ
በሚኒሶታ በነጭ ፖሊስ ታንቆ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ

Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
#NewsAlert ‼️
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ ፀደቀ! ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ መፅደቁን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
"ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለወገን እና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ጥንቃቄአችንን ከበፊቱ በላይ እናጠናክር" ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።
ህብረተሰቡ ለራሱ ሲል በመንግስት እና በባለሞያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መመሪያዎች ችላ ሳይል እንዲተገብርና ለህግ አስከባሪው አካል እንዲታዘዝም አሳስበዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት የሚያስገድድ መመሪያ መጽደቁ ተገለጸ፡፡
**********************************************************
አዲስ አበባ ግንቦት 19 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እንዳለበት ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቀ።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት ህይወት ለመታደግ ሲባል ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀሳቀስ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማድረግ ግዴታ የሚጥል መመሪያ ጸደቋል።
ወ/ሮ አዳነች እንዳሉት ከሌላው ስህተት መማር ብልህነት ነው !የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝን በተመለከተ ብራዚል ዉስጥ የነበረው መዘናጋት፣ ቸልተኝንት፣ የተላለፉትን ድንብ እና መመሪያዎችን አለማክበር ዛሬ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው።
ለእራሳችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለወገናችንና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ወረርሽኙን መከላከል አለብን ብለዋል። በመንግስት እና በባለሞያዎች የተላለፈውን የጥንቃቄ መመሪያዎችንም ችላ ሳንል እንተግበራቸው። ለህግ አስከባሪው አካል እንታዘዝ። ከማንም በላይ ጥቅሙ ለራስ ነው ሲሉ ጠቅላይ አቃቤ ህጓ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው፡፡