አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አንድ አንድ ነጥቦች ስለ ቼክ እና በተግባር የሚያጋጥሙ የሕግና የአሰራር ችግሮች

ቼክ በተግባር በሰፊው ከሚሰራባቸውና በሕግ ከተቀመጡት ንግድ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በቼክ ላይ እምነት የሚታጣበት ከሆነ የንግድ ዝውውር ደህንነት (security of transaction) ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የንግድ ሥራው እያደገ በመጣ ቁጥር በቼክ የሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሚጨምሩ እንደሚሆን የሚታመንና በተግባርም የሚታይ ነው፡፡ የቼክ ዝውውር እየጨረ እንደመጣም መገመት አያዳግትም፡፡ እየጨመረ የመጣውን የቼክን ዝውውር አስተማማኝነት ለማሳደግ ሕጎች ሥርዓቱን ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡ በዚህም መሠረት በእኛ ሀገር የንግድ ሕጉ እና የወንጀል ሕጉ ይህንኑ የቼክ ጉዳይ በዋናነት ይህን ሥርዓት ዘርግተው ይገኛሉ፡፡ ባብዛኛው የቼክ ጉዳይ የሚያከራክር ጉዳይ የሌለበት ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን አከራካሪ ጉዳዮች መታየታቸው አልቀረም፡፡ ይህ ጽሑፍ ዓላማውም በቼክ ዙሪያ ያሉትን አስፈላጊ የሕግ ድንጋጌዎችንና አስገዳጅ የፍርድ ውሳኔዎችን ማሳወቅና በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለአከራካሪ ጉዳዮች የጸሐፊውን እይታ ማንፀባረቅ ነው፡፡
ቼክ ምንድ ነው?
በንግድ ሕጉ ላይ የቼክ ዓይነቶች፡ የስርዝ ምልክት ያለበት ቼክ (crossed cheque)፣ ከሂሳብ ውስጥ የሚገባ ቼክ (cheques payable in account) እንዲሁም የመንገድ ቼክ(travellers cheque) የሚባሉ ሲኖሩ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግን እነዚህን ወደ ጎን በመተው በንግድ ሕጉ ቁጥር 827 ጀምሮ የተቀመጠውን መደበኛ የቼክ ዓይነት ላይ ያተኩራል፡፡
ቼክ በንግድ ሕጉ መሠረት በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉ የንግድ ወረቀቶች (commercial instruments) አንዱ ሲሆን የንድግ ወረቀት ማለት ደግሞ በገንዘብ መከፈል የሚሆነውን ግዴታ የሚናገሩ የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች ናቸው፡፡ የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ (negotiable instruments) ማለት ደግሞ መብቱ ከሰነዱ ተለይቶ ሊሰራበት ወይም ሊተላለፍ የማይችል መብት ያለበት ሰነድ ሁሉ ማለት ነው (የንግድ ሕግ ቁጥር 715)፡፡ በዚህም መሠረት እንግዲህ ቼክ በቼኩ ላይ ያለን መብት ከቼኩ ተለይቶ ሊሰራበት ወይም ሊተላለፍ አይችልም ማለት ነው፡፡ ቼኩ አብሮ ካልተሰጠ በስተቀር ሌላኛው ወገን ያለበትን ግዴታ እንዲፈፅም አይገደድም ግዴታው ወይም መብቱ ከቼኩ ጋር ተነጣጥሎ መተላለፍ አይችልም፡፡ የገንዘብ ሰነድ የሆነውን ቼክ ከፋይ ሊሆን የሚችለው ባንክ ወይም በሕግ እንደ ባንክ በታወቀ ባንድ ሥራ ማስኬጃ ብቻ ነው (የንግድ ሕጉ ቁጥር 829)፡፡ ስለዚህ ለምሳሌ ግለሰብ ባለኃብቶች ቼክን የመክፈል ሥራ ሊሰሩ አይችሉም ወይም በቼክ ላይ ከፋይ የሚለው ቦታ ላይ ስማቸው ሊሰፍር አይችሉም ማለት ነው፡፡ የገንዘብ ሰነድ የሆነው ቼክ ደግሞ ቼክ ነው ተብሎ ስለ ቼክ በተደነገገው የንግድ ሕግ ስር መብትና ግዴታ እንዲጥል ቼኩ ሊያሟላ የሚገባው መግለጫዎች ይኖራሉ፡፡
ቼክ ሊያሟላ የሚገባቸው አስፈላጊ መግለጫዎች ምንድ ናቸው?
አንድ ቼክ ሊያሟላ ይገባዋል ተብሎ በንድግ ሕጉ ላይ የተቀመጡ መግለጫዎች አሉ፡፡ እነዚህም
1.የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሀተታ የሌለበት ትዕዛዝ፣
2.መክፈል የሚገባው ከፋይ ስም (ባንክ ወይም በሕግ እንደ ባንክ የታወቀ ሌላ አካል ብቻ)
3.ገንዘብ የሚከፈልበት ቦታ
4.ቼኩ የወጣበት ቦታና ግዜ
5.ቼኩን ያወጣው ሰው ፊርማ መሆናቸውን የንግድ ሕጉ ቁጥር 827 በግልፅ አስቀምጧል፡፡
በዚህም መሠረት አንድ ቼክ በቼኩ አማካይነት የሚከፈለውን ገንዘብ መጠን እንዲከፈል የሚል ትዕዛዝ ሊኖር ይገባል፡፡ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል በዚህ መልኩ ትዕዛዝ የሌለው እንደሆነ ቼክ ሊባል አይችልም ማለት ነው፡፡ መክፈል የሚገባውን ከፋይ በተመለከተ ከፋይ ተብለው በቼክ ላይ ሊፃፉ የሚባገው ባንኮች ወይም በሕግ እንደ ባንክ የሚቆጠሩ የፋይናንስ ተቋማት ብቻ ናቸው (የንግድ ሕጉ ቁጥር 829)፡፡ ከነዚህ ውጭ የቼክ ከፋይ ሊኖር አይችልም፡፡ ገንዘብ የሚከፈልበት ቦታ በዚሁ መሠረት ሊቀመጥ ይገባዋል፡፡ ቼኩ የወጣበት ቦታና ግዜን በሚመለከት ቼኩ የወጣበት ቦታና ግዜን ያስቀምጣል፡፡ ቼኩ የሚወጣበት ቀንና ለክፍያ የሚቀርብበት ቀን አንድ ነው ወይስ ልዩነት አለው በሚለው ላይ ይህ ንዑስ አንቀፅ የሚጠቁመው ነገር ባይኖርም የንግድ ሕጉ ቁጥር 855 ግን ልዩነት ያላቸው ቀናት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል፡፡ እዚህ ላይ ቼኩ ለክፍያ የሚቀርብበትን ቀን እንደ ዋና መግለጫ አለመወሰዱ ተገቢና ትክክል አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ለክፍያ የሚቀርብበት ቀን የሌለው ቼክ ባዶ የሆነ ነገር ማለት ነው፤ ሕጉም እንዳስቀመጠው ቼኩ የወጣበት ቀን ከግምት ውስጥ ሳይገባ ነው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን ጀምሮ ለስድስት ወራት ተከፋይ የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ቼኩ የወጣበት ቀን ከአከፋፈል ጋር በተያያዘ አስፈላጊ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምናልባትም መሻሻል ካለባቸው የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች መኃል አንደኛው ይህ ሊሆን ይገባል፡፡ በተግባር እየተሰራበት ያለው ግን በቼኩ ላይ የሚፃፈው ቼኩ የወጣበት ቀን ሳይሆን ለክፍያ መቅረብ ያለበትን ቀን ነው፡፡ ሲጀመር በቼክ ላይ ሁለት ቀን መፃፊያ ቦታም የለውም (ለምሳሌ በወንጀል ጉዳይ ላይ ማስረጃ ሲቀርብ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ያለበትን ቀን በተመለከተ ከሌሎች ማስረጃዎች በተጨማሪ በዋናነት ቼኩ እራሱ ማስረጃ ሲሆን ቼኩ የወጣበትን ቀን በተመለከተ ግን የግል ተበዳይ (የሰው ምስክር) እና ሌሎች የሰው ምስክሮች ናቸው በዋናነት ይህንን ጉዳይ የሚያስረዱት ምክንያቱም ይህ ሁኔታ በቼኩ ላይ ስለማይፃፍ)፡፡ ሌላው ጉዳይ ቼኩን ያወጣው ሰው ፊርማ መኖር ይኖርበታል፡፡ ፊርማው ቼኩን ያወጣው ሰው ይሁን እንጂ ሌሎቹ ነገሮች ከላይ የቀረቡት በአውጪው እንዲፃፉ አያስገድድም፡፡ ሌላ ሰው ፅፎት አውጪው ከፈረመበት ቼኩ የተሟላ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ፊርማው ከጽሑፎቹ በኋላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም በጽሑፎቹ፣ በገንዘብ መጠኑ ተስማምቻለሁ የሚል ኃሳብ ያዘለም ስለሚሆን፡፡ ነገር ግን ቼኩ ላይ ፊርማ ካረፈ በኃላ በቼኩ የሚፃፉ ጉዳዮች ፈራሚው ተስማምቷል ፋቅዳል ለማለት የማያስችል እና በቼክ ዙሪያ የሚደረግ ስምምነቶችም የውል ሕግ መሰረታዊ መርሆዎችን መጠበቅ ያለባቸው ስለሚሆንና በዚህ ሁኔታ ግን አውጪው ለዝርዝር የስምንምነቱ ሁኔታ ሙሉ ፈቃዱን ሰጥቷል ለማለት ስለማያስችል (የሰበር መዝገብ ቁጥር 20232 ቅፅ 7 ቼክ መሰረታዊ የውል ሕግ መርሆዎችን ሊያሟላ እንደሚገባ ያስቀምጣል) በሰነዱ ላይ በተቀመጡት ጉዳዮች ፈራሚው ይገደዳል ለማለት አያስችልም፡፡ ምንም እንኳን የተለየ ባህሪ ያለው ቢሆንም ይህንን በተመለከተ ሌሎች የውል ስምምነቶችንም ቢሆን ተዋዋዩ ወገን በራሱ ፃፋቸውም አልፃፋቸውም በውል ስምምነቱ ላይ በሙሉ ፈቃዱ የተፃፈውን ነገር አንብቦ ፊርማውን እስካኖረና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች እሰከተሟሉ ድረስ ውሎች የሕግ ያክል በተዋወዮቹ ላይ ገዢነት ይኖራቸዋል በተለየ በሕግ ላይ እራሱ እንዲፅፋቸው እስካልተደነገገ ድረስ፡፡ ቼክንም በግልፅ በሕጉ ላይ በተቃራኒ እንዲሆን እስካልተደነገገ ድረስ ይህንኑ አካሄድ መከተል የሚያስኬድ ይሆናል፡፡ ብዙ ግዜ ከሚነሱ መከራከሪያዎች አንዱም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆንም ፅሁፉን ሌላ አካል (ለምሳሌ የተከፋዩን ስም) ፅፎት አውጪውም ፅሁፉን ተመልከቶ የፈረመ እንደሆነ አውጪው ፅሁፉን ስላልፃፈው አይገደድም ሊባል አይችልም፡፡
አስፈላጊ የሆኑ የቼክ መግለጫዎች ጉድለት የሚያስከትለው ውጤት ምንድ ነው?
በመርህ ደረጃ
በንግድ ሕጉ ቁጥር 827 ላይ የተመለከቱት መግለጫዎች (አምስት መግለጫዎች) አንዱ እንኳን የሌለበት (የጎደለው) ሰነድ እንጂ እንደ ቼክ አይቆጠርም ይላል የንግድ ሕጉ ቁጥር 828፡፡ ነገር ግን ሁለት ልዩ ሁኔታዎች ደግሞ መኖራቸውን ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ እነዚህም
1. በልዩ የተመለከተ ቦታ ከሌለ በከፋዩ ስም አጠገብ የተጠቀሰው ቦታ የመክፈያ ቦታ ሆኖ ይቆጠራል፡፡ በከፋዩ ስም አጠገብ ብዙ ቦታዎች ተመልክተው እንደሆነ መጀመሪያ በተመለከተው ቦታ ቼኩ ተከፋይ ይሆናል፡፡
2. እነዚህ ማመልከቻዎች ወይም ማናቸውም ሌላ ማመልከቻዎች ከሌሉ የከፋዩ ዋና ሥራ ማካሄጃ በሆነው ቦታ ቼኩ ተከፋይ ይሆናል፡፡ ስለዚህም በእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር አንድን ሰነድ ቼክ የሚያደርገው በንግድ ሕጉ ቁጥር 827 ስር የተዘረዘሩት አስፈላጊ ሁኔታዎች መሟላታቸው ነው፡፡ በዚህ አንቀፅ ስር ከተቀመጡት አንዱ እንኳን ቢጎድል ሰነድ እንጂ ቼክ እንደማይባል ይህንንም ተከትሎ ቼክን በተመለከተ የተሰጠን መብትና ግዴታ ለመጠቀም የማያስችልና በሌሎች የሕግ ክፍሎች በተቀመጡት ድንጋጌዎች ብቻ መብትና ግዴታ ሊገኝ እንደሚችል ያመላክታል፡፡ ስለዚህም የቼክ ተከፋይ (payee) በቼክ ሲገበያይ ማድረግ ከሚገባው መሰረታዊ ነገሮች አንዱና ዋነኛው ካለይ የጠቀስናቸውን ዋና ዋና መግለጫዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡ የአንዱ መግለጫ ጉድለት ቼኩን እንደ ቼክ ዋጋ ሊያሳጣውና ሰነድ ብቻ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሰነድ ከተባለ ሌሎች ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው ከፋዩ እንዲከፍል አይገገድም፡፡ ከፋዩ እንዲከፍል የሚገደደው ቼክ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የቼክ ሁኔታዎችን አሟልቶ ከፋዩ ክፍያ እንዳይፈፅም የሚያስገድድ ምክንያት በሌለበት አልከፍልም ቢል ባለመክፈሉ ለሚደርሰው ጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡ በቅን ልቦና፣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጎ፣ የተለመደውን አሰራር ተከትሎ እና ተቃራኒ መረጃ ሳይደርሰው ለሚፈፅመው የቼክ ክፍያ በሚደርስ ጉዳት ከፋዩ ከተጠያቂነት ነፃ ነው(የንግድ ሕግ ቁጥር 861)፡፡
የቼክ አውጪው ዋና ዋና ሃላፊነቶች ምንድ ናቸው?
የቼክ አውጪው ዋናው ግዴታው ለቼኩ አከፋፈል የሚሆን የገንዘብ ስንቅ አስቀድሞ በሂሳቡ ውስጥ እንዲኖር ሲሆን ይህም ማለት አውጪው(the drawer) ለራሱ ተቀማጭ በከፋዩ ዘንድ(payer) ያለውና በግልፅ ወይም በዝምታ ባንድ ስምምነት መሠረት አውጪው ገንዘቡን በቼክ እንዲያዝበት መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል(የንግድ ሕጉ ቁጥር 830)፡፡ በቂ ስንቅ መኖሩን ማረጋገጥ ያለበት ቼኩ ከወጣበት ጀምሮ ለክፍያ እስከሚቀርብ ድረስ ነው፡፡ ይህን መተላለፍም በወንጀል ጭምር የሚያስቀጣ ነው(የወንጀል ሕግ 693)፡፡ ነገር ግን በቼኩ ውስጥ ሂሳብ አለመኖሩ የቼኩን ዋጋ የሚያሳጣ አይሆንም ይልቁንም በፍትሐብሔርም በወንጀልም ተጠያቂነትን ያስከተላል፡፡ ባጠቃላይም አውጪው ለቼኩ አከፋፈል ዋስ ነው፤ከዚህ ዋስትና ኃላፊነት የሚያድነው ስምምነት መፈፀም በሕግ የተከለከለ ነው ቼኩ ላይ የዛን ዓይነት ነገር ሰፍሮም ከሆነ እንዳልተፃፈ ይቆጠራል(የንግድ ሕግ ቁጥር 840)፡፡ የመዋዋል ነፃነት(freedom of contract) የቼክ ዋስትና ግዴታን በተመለከተ የማይሰራ ጉዳይ ይሆናል፡፡ በዚህ ዙሪያ ስምምነት ቢደረግም በሕግ ተቀባይነት የለውም የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡
ቼክ ወጪ የተደረገበትና ለክፍያ የሚቀርብበት ቀናት ሊለያዩ ይችላሉ ወይ?
አስፈላጊ ስለሆኑት የቼክ መግለጫዎች የሚያትተው የንግድ ሕጉ ቁጥር 827 ይህንን በተመለከተ ምንም ያለው ነገር ባይኖርም የንግድ ሕጉ ቁጥር 855 ግን ጠቋሚ ነገር ያስቀምጣል፡፡ ቼኩ የወጣበት ቀን ከግምት ውስጥ ሳይገባ በቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት ስድስት ወራት ውሰጥ እንዲከፈልበት መቅረብ አለበት የሚለው የሕጉ ድንጋጌ ቼኩ ወጪ የሚደረግበትና ለክፍያ እንዲቀርብ የሚፃፈው ቀን ሊለያዩ እንደሚችሉ የሚጠቁም አንቀፅ ነው፡፡ ስለዚህም አውጪው ከቅን ልቦና ውጪ የተከፋዩን ጥቅም ለመጉዳት አስቦ ለክፍያ የሚቀርብበት ግዜው እንዲያልፍበት (ማለትም ለክፍያ መቅረብ ያለበትን ግዜ ከ 6 ወር ወደኃላ በማድረግ) አስቦ ካልተደረገ በስተቀር የክፍያ ቀኑን ከሚወጣበት(date of issuance) የመከፈያ ቀኑን ወደኃላ ማድረግም(pre-date) ወይም ወደ ፊት(post-date) ማድረግ ይቻላል ይህን በመደረጉ ምክንያት ቼኩም ዋጋ አያጣም ማለት ነው፡፡ ቼኩ እንደ ቼክ ዋጋ የሚያጣው አውጪው ቼኩ ከወጣበት 6 ወር ለበለጠ ግዜ ወደ ኃላ እንዲከፈል አድርጎ ቼኩ ላይ ከተፃፈ ሊከፈል ከሚገባው ቀን አንስቶ 6 ወር ያለፈው ቼክ ስለማይከፈል ቼኩ ዋጋ አይኖረውም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዐይነት ሁኔታ የሚጋጥመው ተከፋይ በሌሎች የሕግ ክፍሎች በተቀመጡት መብት ማስከበሪያ መንገዶች መብቱን ሊያስከብር ይገደዳል፡፡ የንግድ ሕጉ ቁጥር 789 እንደሚያስቀምጠውም የቼኩ ተከፋይ በፍትሐብሔር ሕጉ ላይ በተደነገገው አላግባብ ስለመበልፀግ የተቀመጠውን ድንጋጌ ተከትሎ የፍትሐብሔር መብቱን ሊያስከብር ይችላል፡፡ በወንጀል ሆን ተብሎ ከቅን ልቦና ውጭ የተደረጉ እስከሆኑ ድረስ የቼክ ወንጀልን(የወንጀል ሕግ 693/1) ባያያቋቁሙም በወንጀል ሕግ አንቀፅ 692 ስር በተደነነገገው የማታለል ወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል ስለሆነ ይህንኑ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ማመልከት ያስፈልጋል፡፡ ሆነ ተብሎ ተደርጓል አልተደረገም የሚለው ከአጠቃላይ ድርጊት አፈፃፀሙ ጋር ተስተያይቶ የሚረጋገት(infer የሚደረግ) ጉዳይ ነው፡፡
የሌሎች ሀገራት የቼክ ሕግጋትና አሠራር ከኢትዮጰያ ሕግና አሠራር ጋር በንፅፅር
ካናዳ
ካናዳ በዓለማችን ላይ ካሉ ውጤታማ ቼክ የማጥራት ሥርዓት (efficient cheque clearing system) ካላቸው ሀገራ መካከል አንዷ ናት፡፡ ምንም እንኳን የኤሌክትሮኒክስና የካርድ ክፍያዎች ሥርዓት መስፋፋት የቼክ አጠቃቀሟን እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም ድረስ ግን እሰከ 1 ቢሊዮን ቼክ በዓመት የማዘዋወርና የመገበያየት ሥራ ይሰራበታል፡፡ በካናዳ ቼክ አውጪው ላወጣው ቼክ በቂ ስንቅ ሳይኖረው ሲቀር ባንኩ ለተፋዩ ክፍያ ሊፈፅም ይችላል፡፡ ከዛ በኃላ ግን ያንን ላደረገበት ተጨማሪ ክፍያ ወይም (non sufficient fund fee(nsff)) ከአውጪው ያስከፍላል፡፡ አውጪው በቂ ሂሳብ እንዲኖረው ማረጋገጥ ያለበት ተጨማሪ ክፍያዋን(nsf fee) ላለመክፈልም ሲል ጭምር ነው፡፡ የዚህን ዐይነት አሰራር በኢትዮጵያ ባንኮች አይሰራበትም የሕግ ድጋፍም የለውም፡፡ ሌላው በካናዳ ወደ ፊት ለክፍያ እንዲቀርቡ(post-dated cheques) ቀድሞ ሊከፈል የሚችልበት አሰራርም አለ፡፡ ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከፈል ከተፃፈበት ቀን በፊት የመክፈል በሕግ የተቀመጠም ነገር የለም የዚህን ዓይነት አሰራርም ባንኮች አይከተሉም፡፡ ምናልባትም የንግድ ሕጉ ቁጥር 899 ካለው በላይ ማውጣት ስለመከልከሉ በሚለው አንቀፅ ስር “ገንዘቡን በአደራ የማስቀመጥ ውል ካለው ከተቀማጭ ገንዘብ በላይ የማውጣት መብትን አይሰጥም” በማለት አውጪው በሂሳብ ውስጥ ካለው በላይ ገንዘብን ቢያዝ ሊያወጣ እንደማይችል ጠቋሚ ይመስላል፡፡ የሁለቱ ጉዳዮች ልዩነት የመጣው በካናዳ ካለው ጠንካራ የፋይናስ ሥርዓት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ገና በማደግ ላይ የሚገኝ የፋይናነስ ሥራዓት መኖሩ አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ታይላንድ
በታይላንድ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በወንጀል የሚያስጠይቅ ሲሆን የቅጣት መጠኑ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ያነሰ ነው፡፡ በዚህም የወንጀል ድርጊት አውጪው
👍2
ማኖሩ ነው፡፡ ፊርማ ብቻ ያለበት ቼክ ለተከፋዩ ቢሰጥና ተከፋዩ የመሰለውን ነገር ቢሞላበት የተሟላ ቼክ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ከዚሁ ጋር በተገናኛ ፊርማው የእኔ አይደለም የሚል መከራከሪያም ይነሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ ምንም አያከራክርም አውጪው ፊርማው ከሌለበት ወይም የእሱ ካልሆነ ሰነድ እንዲ ቼክ አይባልም፡፡ ነገር ግን መርሳት የሌለብን አውጪው ለተከፋዩ ፊርማው የእኔ ነው ብሎ አሳሳች ነገር ተናግሮ ቼኩን ሰጥቶት እንደሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 692 ስር በተገነነገገው የማታለል ወንጀል ተጠያቂ መሆኑ አይቀርለትም ምንም እንኳን አንቀፅ 693 ስር ተጠያቂ ባይሆንም ማለት ነው(ከፍትሐበሔር ተጠያቂነት ጎን ለጎን አላግባብ ስለመበልፀግ በተደነገገው መሠረት)
ከቼክ ጋር በተገናኘ በሰበር ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች
ከቼክ ጋር በተገናኘ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰጣቸው ውሳኔዎች መኃል የተወሰኑትን ማንሳቱ ጠቃሚ መሆኑን በማመን የተወሰኑትን እንመለከታለን፡፡
የሰበር መዝገብ ቁጥር 67947 ቅፅ 12 ላይ እንደተወሰነው የሚያዝበት ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በሚል በወንጀል ሕጉ ውስጥ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ለማቋቋም ቼኩ ለክፍያ ባንክ በቀረበበት ጊዜ በቂ ስንቅ የሌለው መሆኑን/አለመሆኑን / ማረጋገጥ ብቻ በቂ መሆኑን አስገዳጅ በሆነው ውሳኔው ላይ አስቀምጦታል፡፡ በዚህ ውሳኔ መሠረትም ለዋስትና ነው ቼኩን የሰጠሁት፤ቼኩ ለክፍያ ሲቀርብ በቂ ሂሳብ እንደማይኖረው ለተከፋዩ ስላሳወኩት የማታለል ጉዳይ የሌለ ስለሆነ በቼክ ማታለል ልጠየቅ አይገባም የሚሉ መከራከሪያዎች ተቀባይነት እንደሌለው ብቻም ሳይሆን ከላይ የጠቀስነውን የድራፍቲንግ ችግር ይህም ውሳኔ ያረጋገጠው ጉዳይ ሆኗል ማለት ነው፡፡
የሰበር መዝገብ ቁጥር 20232 ቅፅ 7 ላይ እንደተወሰነው የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች (ቼክን ጨምሮ ማለት ነው) የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዴታ የሚረጋገጥባቸው በመሆናቸው የውል ሕግ መሰረታዊ ድንጋጌዎች መሟላታቸው አስፈላጊ ስለመሆኑ አስገዳጅ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ ይህም ማለት ውልን ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑት መግለጫዎች መኖር ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በኃይልና ማስገደድ የተገኘ ቼክ ይህ እስከተረጋገጠ ድረስ መብትሀና ግዴታ እንዳይጥል በፍርድ ቤት ማስወሰን ይቻላል ማለት ነው፡፡ ምክንያት በቼክ ዝውውር ግንኙነቱ ውስጥ የውል ሕግ መሰረታዊ ድንጋጌዎች አለመሟላታቸው፡፡
እንግዲህ በዚህ ጽሑፍ ላይ የተነሱት ሀሳቦች አጠቃላይ የሕግ ይዘትና በአከራካሪ ጉዳዮቹ ዙሪያ የግል አስተያየትም ጭምር ያለባቸው ስለሆኑ አንባቢው በበኩሉ የሚመስለውን ወይም መሆን አለበት የሚለውን ሊያካፍል ይችላል፡፡
By Federal Justice and Legal Research Institute.
ሊቀጣ የሚቸለው 1 አመት ባልበለጠ እሥራት እና አስከ 60 ሺህ የታይላንድ ባህትሰ (bahts) ባልበለጠ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታስቦ የሚፈፀም በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼክ ማውጣት በቀላል እሥራት ወይም እንደነገሩ ከባድነት እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ሊያስቀጣ ይችላል፤ በቸልተኝነት ሲሆን ደግሞ በመቀጮ ወይም 1 አመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት ያስቀጣል፡፡ የቅጣት ሁኔታ በዛች ሀገር ላይ ያለውን የወንጀሉን ተፅዕኖ እንዲሁም የቅጣቱ አስተማሪነት እንደ ሀገሪቱ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ ስለሚጣል ልዩነቱ መኖሩ አስገራሚ ላይሆን ይችላል፡፡ ሌላው ልዩነት የወንጀል ህጋችን ቼኩ በሚወጣበት ወይም ለክፍያ በሚቀርብበት ግዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ ከሌለው የወንጀል ተጠያቂነት እንዳለ ሲያስቀምጥ ታይላንድ ለክፍያ በሚቀርብበት ብቻ የሚለውን ነው የሚያስቀምጠው፡፡ በዚህ ረገድ የእኛ የወንጀል ሕግ ክፍተቶችን በመዝጋት ረገድ የተሻለ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም አንድ አንድ ግዜ ሂሳቡ ወጪ በሚሆንበት ሰዓት ሂሳብ ላስገባ ስል ሂሳቤ ተዘግቷል ተባልኩኝ የሚል መከራከሪያን ዝግ ያደርጋል፡፡ ይህን ማድረጉም የቼክ ክፍያ የግብይት ደህንነትን(security of transaction) ያጠናክረዋል፡፡ ቼክ አውጪዎችም የሕግ ቀዳዳ በመፈለግ ለማምለጥ የሚያደርጉትን ጥረት ዝግ በማድረግ ስለ ቼኩ አከፋፈል በቂ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያደርጋቸዋል፡፡
ቼክ ከወንጀል ጋር በተያያዘ
ከወንጀል ጋር በተያያዘ በቼክ ወንጀል ስለመፈፀም የሚደነግገው የሕግ አንቀፅ ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች ከሚለው ክፍል ስር ሲሆን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 693/1 “ማንም ሰው ቼክ በሚወጣበት ወይም ቼኩ ለባንክ በሚቀርብበት ጊዜ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ያወጣ/የሰጠ/ እንደሆነ በቀላል እሥራት ወይም እንደነገሩ ከባድነት ከ10 አመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራትና በመቀጮ ይቀጣል” በማለት ያስቀምጣል፡፡ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች በዚህ አንቀፅ ውስጥ ማውጣት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው ቼኩ ለክፍያ ሊቀርብ ከሚችልበት ግዜ(ምክያቱም ከዛ በፊት ወደ ፊት እንዲከፈል የተሰጠን ቼክ በተመለከተ ክፍያ መጠየቅ የሚያስችል ሕግም አሰራርም ስለሌለ ማለት ነው) ጀምሮ ለባንክ ለክፍያ እስከሚቀርብበት ግዜ ድረስ በባንክ ሂሳብ ውሰጥ በቼኩ ላይ ለተፃፈው ገንዘብ ክፍያ የሚሆን በቂ ሂሳብ መኖሩን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ስለዚህ ለምሳሌ ተከፋዩ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ካለበት ግዜ 5 ወር እንኳን ዘግይቶ ቢሄድ በዚህ የወንጀል ሕግ ድንጋጌ መሠረት አምስተኛው ወር ቢሆንም አውጪው ሂሳብ ውሰጥ ለቼኩ ክፍያ የሚሆን በቂ ሂሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህ ሳይሆን የቀረ እንደሆነ ግን የወንጀል ሕጉ ደንጋጌ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ጉዳይ ፍርድ ቤት ቅጣቱን በመወሰን ረገድ ሁለት አመራጭ ያለው መሆኑ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩ ከባድ አይደለም በማለት የሚወስድ እንደሆነ በቀላል እሥራት ማለትም ከ10 ቀን አስከ 3 ዓመት ሊደርስ በሚችል እሥራት ቅጣት ሊጥል ይችላል ማለት ሲሆን ነገሩን ከባድ ነው ብሎ የወሰደው እንደሆነ ግን ከ 10 አመት በማይበልጥ ፅኑ እሥራት ብቻ ሳይሆን በመቀጮም ጭምር የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡ ዝርዝር የቅጣት ሁኔታውም ተሻሽሎ በወጣው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 2/2006 መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ አንድ አንድ ግዜ ፍርድ ቤቱ የቀላል እሥራት አማራጭ ይወስድና የቅጣት አወሳሰን መመሪያው ላይ ግን የገንዘብ መጠኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ሲታይ ቅጣቱ በገንዘብም ጭምር እንዲሆን የሚያስመስል ቢሆንም መመሪያ ሕግን ሊጥስ አይችልምና ቀላል እሥራት አማራጭ ከገንዘብ መቀጮ ጋር አብሮ ሊወሰን ስለማይችል መመሪያው የሚያስቀምጠውን የገንዘብ መቀጮ ወደ ጎን መተው ተገቢ ይሆናል፡፡ ባጭሩም ቀላል እሥራት ከሆነ እሥራቱ ብቻውን ነው የፅኑ እሥራት አማራጭ ከሆነ ግን እሥራቱ ከመቀጮ ጋር ነው ማለት ነው፡፡
ከወንጀል ጋር በተገናኘ መነሳት ካለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች መካከል በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 693 ስር ተጠያቂ ለመሆን በመጀመሪያ ቼኩ በንግድ ሕጉ ላይ የተቀመጠውን አስፈላጊ የሆኑ የቼክ መግለጫዎች ያሟላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለምሳሌ የገንዘብ መጠኑ ባልተጠቀሰ፣አውጪው የራሱ የሆነ ፊርማውን ካላሳረፈበትና የመሳሰሉትን ያላሟላ ከሆነ ቼክ ነው ተብሎ በቂ ሂሳብ አለው የለውም ወደሚል ሁኔታ ውስጥ ሊገባበት አይችልም፣አይገባምም፡፡ የወንጀል ሕጉም ከቼክ ጋር በተገናኘ ተጠያቂነትን በቂ ሂሳብ ከመኖርና ካለመኖር ጋር ነው ያያዘው፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚፈፀም ወንጀልም ካለ በንግድ ሕጉ ድንጋጌ መሠረት በሰነድ የተፈፀመ ወንጀል እንጂ በቼክ ላይ የተፈፀመ ሊባል አይችልም(የንግድ ሕጉን ቁጥር 828 መመልከት ይቻላል)፡፡ ይልቁንም በዚህን ግዜ ሌሎች የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን ለምሳሌ የማታለል ወንጀልን የሚያቋቁሙበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡
ሌላው ትልቁ ጉዳይ የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 693ን ለማቋቋም ድርጊቱ የማታለል ሁኔታን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ወይ?ይህንን ጥያቄ እንድናነሳ የሚያደርገን አንቀፅ 693 ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች ከሚል ክፍል ስር መካከተቱ ነው፡፡ በእኔ በኩል የማታለል ጉዳይ ግን መኖር የለበትም የሚል አቋም አለኝ፡፡ ምክንያት በዚሁ የማታለል ወንጀሎችን የሚመለከቱ ወንጀሎች ከሚለው ክፍል ስር ከሚገኙ የወንጀል ድንጋጌዎች መካከል የማታለል ይዘት የሌላቸው ወንጀሎች መኖራቸው ለምሳሌም በአንቀፅ 702(1) እና (2) ላይ የተደነገገው በሌላ ሰው ጥቅም የሥራ አመራር ላይ የተፈፀመ ጉዳት የሚለው የወንጀል ድርጊት በውስጣቸው የማታለል ድርጊት የሚይዙ አንቀፆች አይደሉም፡፡ ሌላኛው ምክንያት ወደኃላ ላይ በዝርዝር የምናነሳው የሰበር ውሳኔ መዝገብ ቁጥር 67947 ቅፅ 12 የቼክ ወንጀልን ለማቋቋም ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የማያስፈልግ መሆኑን የወሰነበት መዝገብ መኖሩ ነው፡፡ በዚህም አጋጣሚ የወንጀል ሕጉ ድራፍት የተደረገበት መንገድ ላይም ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ የማታለል ጉዳይን ያልያዙ ወንጀሎችን ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች በሚል የሕግ ክፍል ስር ማካተት የድራፍቲንግ(poor draftsmanship) ችግር ነው፡፡ በቼክ የሚፈፀም ወንጀል የማታለል ይዘት ሊኖረው ይገባል ከተባለ ብዙ ልዩነቶችን ያመጣል፡፡ ለምሳሌ አንድ ቼክ ወጪ በሚደረግበት ወይም ለክፍያ በሚቀርብበት ቀን አውጪው ለተካፋዩ በሂሳብ ውስጥ በቂ ሂሳብ እንደማይኖረው ነገር ግን ለመተማመኛ ብቻ ብሎ የሰጠው እንደሆነ በዚህ ሁኔታ የማታለል ጉዳይ ስለሌለው በሂሳብ ውስጥ በቂ ስንቅ የለውም እንኳን ቢባል በአንቀፅ 693 ስር የወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ አያስችልም ማለት ነው፡፡ የሕጉ ዓላማ ደግሞ የቼክ ዝውውር አስተማማኝ ሆኖ ዝውውሩ የተቀላጠፈ እንዲሆን ከማሰብ አንፃር ስለሆነ ከላይ ባቀረብነው መከራከሪያ ነጥብም ምክንያት የግድ የማታለል ጉዳይ ሊኖረው አይገባም፡፡ የንግድ ሕጉም በዚህ ረገድ የሚያስቀምጠው ነገር ወደ ፊት እንዲከፈል ከወጣ ቼክ ውጪ ቼክ እንደ ቀረበ የሚከፈልበት ነው(የንግድ ሕጉ ቁጥር 854 እና 855)(other than post dated cheques, cheques are always payable at sight)፡፡ ስለዚህ ቼክ እንዲከፈል በተፃፈበት ቀን ጀምሮ እንደቀረበ እንዲከል(payable at sight) የሚያስፈልገው የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉም ዓላማ በዚሁ አተያይ ስር መተርጎምና መታየት ይኖርበታል፡፡
የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮች ምንድ ናቸው?
ከቼክ ጋር በተ
1
ገናኘ የሚነሱ አንድ አንድ ችግሮች አሉ፡፡ ከሚነሱት የሕግ እና የአሰራር ችግሮች መኃል ከላይ የተነካኩና የጸሐፊው ሀሳቦችም ጭምር ተገልጧል፡፡ የቀሩትን በችግርነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ነጥቦች ደግሞ አሁን እናነሳለን፡፡
1. ቼክን ለክፍያ እንዲቀርብ ሳይሆን ለዋስትና ወይም እንደመተማመኛ ነው የሰጠሁት የሚል መከራከሪያ ይነሳል በተለይም በወንጀል ጉዳይ ተጠያቂ ላለመሆን የሚነሳ ጥያቄ ነው፡፡ ከላይ ባነሳነው መከራከሪያ ነጥብ መሠረት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 693 የማታለል ይዘት በድርጊት ውስጥ መኖሩ መረጋገጥ አስፈላጊ አይሆንም ባልነው መሠረት ቼኩ ለተከፋዩ የተሰጠው እንደዋስትና እንኳን ቢሆን በሂሳብ ውሰጥ በቂ ሂሳብ እስከሌለው ድረስ የወንጀል ተጠያቂነት ማስቀረት አይችልም፡፡ የማታለል ጉዳይ በዚህ ግንኙነት መኖሩ ግድ ነው የሚባል ከሆነ ግን የዚህን ዓይነት መከራከሪያዎች ሚዛን የሚደፉ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሰበር መዝገብ ቁጥር 67947 ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሂሳብ ውስጥ በቂ ሂሳብ ከሌለ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል አስቀጧል፡፡ ዝርዝር ጉዳዩን ወደታች እንመለከተዋለን፡፡
2. ሌላው መከራከሪያ ጉዳይ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼክ ወጪ ከተደረገ በኃላ ባንኩ የአውጪውን የቼኩ ሂሳብ መዝጋት፡፡ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ለ 3 ግዜ በቂ ሂሳብ ሳይኖረው ቼክ የፃፈ ግለሰብ በባንኩ ሂሳቡ እንደሚዘጋበት ያስቀምጣል፡፡ ሁለት መሰረታዊ ልዩነቶችን ግልፅ እናድርግ፡፡ የመጀመሪያው ሂሳቡ በባንኩ የተዘጋው ቼኩን አውጪው ከመስጠቱ በፊት እና ሂሳቡ ከመዘጋቱ በፊት የተሠጠ ቼክ ብለን ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያውን ሁኔታ ለሁለት በድጋሜ ከፋፍሎ ማየት ነገሩን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ቼኩ ቀድሞ ስለመዘጋቱ በባንኩ ለአውጪው የተነገረና በባንኩ ያልተነገረበት ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ ሁለተኛውን ሁኔታም በድጋሜ ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ በዚህም መሠረት ለክፍያ ቼኩ በሚቀርብበት ግዜ በቂ ሂሳብ በአካውንቱ የነበረውና ያልነበረው ተብሎ ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያውን ሁኔታ ማለትም ቼኩ ወጪ የሆነው ቼኩ ከተዘጋ በኃላ ሲሆንና ባንኩም ለአውጪው ቼኩ መዘጋቱን የገለፀለት እንደሆነ ክፍያ ሊፈፀም የማይችልበት ሰነድ ነው የሰጠው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ሁኔታም በድርጊቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙም ግልፅ ይሆናል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ግን አንቀፅ 692 የመታለል ወንጀል ነው፡፡ ምክያቱም ክፍያ ሊፈፀም እንደማይችልና ችኩ መዘጋቱን በመደበቅ ነው ቼኩን ፅፎ የሰጠው፡፡ ከባንኩ ጋር ያለው ስምምነት የተቋረጠ ስለሆነ ክፍያ መጠየቅ አይቻልም፡፡ ለሌላኛው እና አከራካሪው ጉዳይ ቼኩ መዘጋቱ ሳይገለፅለት ሂሳቡ ከተዘጋ በኃላ ቼክ ፅፎ የሰጠ እንደሆነ ምን ይከሰታል?በወንጀልስ ተጠያቂነት አለበት ወይ?የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ በተወሰነ መልኩም ቢሆን አስቸጋሪነት አለው፡፡ የወንጀል ተጠያቂነትን ለማስከተል እውቀት ወይም የጥንቃቄ ጉድለት(ቸልተኝነት)ይጠይቃል፡፡ ገንዘብ እንዳያስገባ ሂሳቡ ተዘግቷል በዚህ ሁኔታ አከራካሪና አጠራጣሪ ሁኔታ መፈጠሩን ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ደግሞ ወደ ተከሳሽ ማድላት እንደሚኖርብን የወንጀል ሕግ አንደኛው መርህ ስለሆነ በወንጀል ጥፋተኛ ወዳለማድረጉ ማድላት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ባንኮች የቼክ ሂሳብ ሲዘጉ የማሳወቅ አሰራርን የሚከተሉት፡፡ የማያሳውቁ ከሆነ ግን እራሱን የቻለ መከራከሪያ ነጥብ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ በሁለተኛው ሁኔታ ግን ሂሳቡ የተዘጋው ቼኩ ወጪ ከሆነ በኃላ ከሆነ የማታለል ጉዳይ ለማቋቋም ያስቸግራል፡፡ በዚህ ሁኔታ መሆን የሚኖርበት ሂሳቡ በሚዘጋ ወቅት በቂ ሂሳብ ነበረው ወይስ አልነበረውም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ሂሳብ ካልነበረው አንቀፅ 693 ስር የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ቼኩ በቂ ሂሳብ እንዲኖረው የሚያስፈልገው ቼኩ ወጪ በሆነበት ወይም ለክፍያ በሚቀርብበት ግዜ ስለሆነ ወጪ ከተደረገ በኃላ በቂ ሂሳብ እንደሌለው የሚያሳይ ስለሚሆን የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል፡፡ ነገር ግን በሂሳቡ ውስጥ ሂሳቡ ሲዘጋ የነበረው ገንዘብ መጠን በቼኩ ላይ የተፃፈውን ለመሸፈን የሚያስችል ከሆነ ይህንን ቼክ በተመለከተ አውጪው በወንጀል ሊጠየቅ አይገባም፡፡ ምክያቱም የማታለል ጉዳይ የሌለበትና(አንቀፅ 692)የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትለው በቂ ሂሳብ በሂሳብ ውስጥ ያለመኖር ስለሆነ(አንቀፅ 693/1/ን በተመለከተ)፡፡ በዚህም አጋጣሚ ቼክ የፃፈና ሂሳቡ ግን ከባንክ ባለመከፈሉ ምክንያት የወንጀል ተጠያቂነት ያለ ቢሆንም ሁልግዜም ያለመሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ይህ ማለት ግን የፍትሐብሔር ተጠያቂነትን በምንም መንገድ አያስቀርም(ያላግባብ ስለመበልፀግ በተደነገጉት የሕግ አንቀፆች መሠረት)፡፡
3. በቂ ሂሳብ እያለ ቼኩ ከተሰጠ በኃላ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ቼኩን ማሳገድ፡፡ የንግድ ሕጉ አንቀፅ 857 ቼኩ ከመከፈሉ አስቀድሞ አውጪው እንዳትከፍል ብሎ የነገረው እንደሆነ ባንኩ የቼኩን ዋጋ አልከፍልም ለማለት ይችላል ብሎ በማስቀመጥ ይህንን መብት አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ ከንግድ ሕጉ መረዳት እንደሚቻለው እንዳትከፍል ብሎ ለማዘዝ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንኳን የለም፡፡ ይህንን በማድረጉ የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይችላል ብሎ መከራከር አይቻልም፡፡ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼኩን ያሳገደው እንደሆነ ግን ቼኩ ለክፍያ በሚቀርብ ግዜ ብቻ ሳይሆን ወጪ ሲሆንም ጭምር በቂ ሂሳብ እንዲኖረው ስለሚያስፈልግ ይህ እንዳልነበረ የተረጋገጠ እንደሆነ ግን በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 693 መሠረት ተጠያቂ ሊሆን ይገባል ማለት ነው፡፡
4. ቅጣትን በተመለከተ በባንክ ሂሳቤ ውስጥ ያለኝ ገንዘብ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ገንዘብ ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ጉድለት ስለሆነ በልዩነቱ ልክ ነው መቀጣት ያለብኝ የሚል መከራከሪያ(ቅጣት ሲጣል በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሠረት የገንዘብ መጠንን ግምት ውስጥ አስገብቶ መጣል ስላለበት)፡፡ ይህንን በተመለከተ የገንዘብ መጠንን መሠረት በማድረግ ቅጣት እርከን እንደሚወሰን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ያመላክታል፡፡ ይህን ጥያቄ ለመፍታት በዋናነት መመሪያውን መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በዚህም መሠረት መመሪያው በየትኛውም ድንጋጌው ላይ በቼኩ ላይ ስለተጠቀሰው ሂሳብ እንጂ ስለልዩነቱ የሚናገረው ነገር የለም፡፡ ሕጉንና መመሪያውን መሠረት በማድረግ ስለሚሰራና በሕጉም ላይ ሆነ መመሪያው ላይ ይህን የሚፈቅድ አሰራር ስለሌለ የዚህን ዓይነት ጥያቄ የሕግ መሠረት የለውም ተብሎ ሊታለፍ ይችላል፡፡
5. አጠቃላይ ቼኩ ላይ ያለው እና የተፃፈው ነገር ከፊርማው ውጭ የእኔ ስላልሆነ ቼኩ አያስገድደኝም በወንጀልም አልጠየቅም የሚል መከራከሪያ፡፡ የንግድ ሕጉ አንቀፅ 827 ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ቼኩን ያወጣው ሰው ፊርማ ከሚለው በስተቀር ሌሎቹን አውጪው እራሱ እንዲፅፋቸው የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሌላ ሰው ሌሎቹን ነገሮች ፅፎለት ከተመለከተ በኃላ ፊርማውን ካኖረ በተፃፈው ነገር ተስማምቷል ሕጉም ሌሎቹን ፅሁፎች እራሱ እንዲፅፍ ስለማያስገድዱ በቼኩ በፍትሐብሔርም ሆነ በወንጀል ተጠያቂነት ሊኖርበት ይገባል፡፡ ነገር ግን ማስተዋል ያለብን በሌላ በኩል አውጪው በቼኩ ላይ ፊርማ ብቻ አኑሮ ለሌላ ሰው ከሰጠው ሰነድ እንጂ እንደ ቼክ እንደማይቆጠር ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ቼክ ተብሎ ለመጠየቅ ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ ፅሁፉን ማንም ይፃው ማን ዋናው ነገር አውጪው የተፃፈውን ነገር ተመልክቶ ፊርማውን
የፌስ ማስክ/ጭንብል ጉዳይ ዓለም አቀፍ እውነታዎችና የዛሬው የአዲስ አበባ ክስተት፤

የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የፊት ማስክን ማድረግ አለባቸው ብሎ የገለጸው የበሽታው ምልክት ያለባቸው ሰዎችና የጤና ባለሙያዎችን ነው። Central Disease Control (CDC) ደግሞ በተለይ ሰው የሚበዛባቸው እንደ ትራንስፖርትና ትላልቅ ገበያዎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ከቻሉ ማስክ ካልቻሉ ደግሞ እንደ ስካርፍና ሻርፕ ባሉ ነገሮች አፍና አፍንጫቸውን መሸፈን እንደሚችሉ ነው የጠቆሙት።
እንግሊዝ ደግሞ ለየት ባለ መልኩ ለጤና ባለሙያዎች የማስክ እጥረት እንዳያጋጥም ብላ ህዝቧ የማስክ ግዢና አጠቃቀሙን እንዲቀንስ አዛለች። በማስክ ኮሮናን በመከላከል ዙሪያ አሁንም የሚከራከሩ ጥናት አድራጊዎች ቢኖሩም እንደ ዋነኛ መፍትሔ የሚቀመጥ አይደለም። ዋነኛው የኮሮና መከላከያ መንገዶች አካላዊ መራራቅና የእጅ ንጽህናን መጠበቅ ናቸው። እናም ማስክ ማድረግን ግዴታ ያደረጉ እንደ ኩባና ዩጎዝላቪያ ያሉ አገራት እንኳን ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ሲሉ ህጋቸውን አላልታው ነው ያስቀመጡት። በዚህ ቦታ ማስክ ሳያረጉ የተገኙ ሰዎችም ቀላል የሚባል የገንዘብ ቅጣት እንጂ እስራት አልተፈረደባቸውም።

በአገራችን አዋጅ መሰረትም ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ብሎ በግልጽ አስቀምጧል። እነዚህም የገበያ ሞሎች፣ የህዝብ መጓጓዣዎችና ሆስፒታሎችን የሚመለከት ነው። በዚያ ላይ የማህብረሰባችንን አቅም ያማከለ የማስክ እደላና የእውቀት ማስገንዘቢያ ሥራ ሳይሰራ ሰዎችን ማስክ አላደረጋችሁም ብሎ ማሰር በግሌ ተገቢ መስሎ አይታየኝም። በዚያ ላይ ሰዎቹ በሚታሰሩበት ወቅት የሚፈጠር የሰዎች መጠጋጋት ለበሽታው መስፋፋት ይበልጥ አጋዥ እንደሚሆን ልብ ማለት ያሻል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ማህበርም ቅሬታውን አቅርቧል። የሚመለከተው አካል በቶሎ መፍትሔ ቢያበጅለት እላለሁኝ።

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)

https://telegram.me/lawsocieties
Nahom:
Hi ALE If u have land proclamations especially expropiration,urban lease holding procl no 721/2011 and rural land adminstration proclm no 456/2005 please send to me it's urgent
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
Legal Officer
#bank_of_abyssinia
#legal_services
#law
#legal_officer
Addis Ababa
LLB Degree in Law
Minimum Years Of Experience: #6_years
Deadline: May 23, 2020
How To Apply: Send your CV to HRSupport@bankofabyssina.com
Via Hahujobs
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
May 18, 2020

Legal Officer

 Bank Of Abyssinia (BOA)

 

 Addis Ababa, Ethiopia

FULL_TIME Banking Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

JOB REQUIREMENT

Education:  LLB Degree in Law

Experience: Minimum of 6 years banking experience, of which 3 years in the area of Law

Place of Work: Addis Ababa

HOW TO APPLY

Only short-listed candidates will be contacted.

Interested applicants who meet the above criteria are invited to apply within 5 working days from the date of this advertisement by sending all relevant documents only by mail to:-  HRSupport@bankofabyssinia.com

Bank of Abyssinia

Central Addis District

Addis Ababa


About Bank Of Abyssinia (BOA)

Bank Of Abyssinia (BOA)

https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
May 18, 2020

Writer for Political issues living in Ethiopia 

 Ethiopia

PART_TIME Media /Journalism Jobs in Ethiopia

Job Description

Earn money from home by paraphrasing articles. 

On-line/ part-time job. Global Media Scout Company is looking for a freelancer living in Ethiopia who is fluent in English and has or will get a bachelor's or a master's degree in Politics.

We expect you to paraphrase/write English articles about Political topics. 

Applications of people who did not study Politics or cannot write in English will not be accepted.

If you meet the requirements, then send an English version of your CV together with a copy of your diploma to the following email address "h.taboubi@globalmediascout.com".

Please state in the subject line of the email the position you are applying for.

*Salary: 3,50 $ per hour.

Exigencies: Really good English.Good knowledge about Politics.

Applications from applicants who are not studying Politics or did not study Politics will not be answered.

https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate
በክርክርና በቀጠሮ ላይ ያሉ የክስ መዛግብት ለሚቀጥለው ዓመት እንዲቀጠሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

 

ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ

በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዳይሆን ተሠግቷል

የፍትሐ ብሔር ውሳኔዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንዳይገለጹ ታገደ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ከሚታዩ የክስ መዝገቦች ውስጥ በክርክርና በቀጠሮ ላይ ያሉ መዛግብት፣ ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ባሉት ጊዜያት እንዲቀጠሩ ለየምድብ ችሎቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ተጠቆመ፡፡ ማሳሰቢያው የተሰጠው በፍርድ ቤቱ አመራሮች በመሆኑ፣ በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዳይሆን የሕግ ባለሙያዎች ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በክርክር ላይ ያሉ ወይም ክርክራቸው የተወሰነ ጊዜ የሚወስድ መዛግብት ለቀጣዩ ዓመት ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ እንዲቀጠሩ አመራሩ የገለጸ ቢሆንም፣ የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ያለው ሥርጭት ከተቃለለ፣ የቀጠሮ ጊዜ ተሰብሮ በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም. ሊሠራ እንደሚችልም አማራጭ ሐሳብ አስቀምጧል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ያስተላለፈውን ማሳሰቢያ በሚመለከት አስተያየታቸውን የሚሰጡ የሕግ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ አመራሩ የሰጠውን ማሳሰቢያ በሁለት ከፍለውታል፡፡ የመጀመርያው ከተከሳሹ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት አንፃር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሠራጭቶ ከሚገኘው ኮሮና ቫይረስ አደገኛ ሁኔታ አንፃር ነው፡፡ በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ቤተሰቦችና ሌላ የችሎት ታዳሚዎች በሌሉበት ርቀታቸውን በጠበቀ ሁኔታ ክርክር በማድረግ አንድ ደረጃ ላይ መድረስ እየቻሉ፣ ሙሉ በሙሉ መከልከል ግን የመብት ጥሰት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የፍርድ ቤቱ አመራር በወረርሽኙ ይከሰታል ብሎ የሚሠጋበትን ጉዳት የሚያሳይ በመሆኑ፣ ማሳሰቢያው ተገቢ መሆኑንም የሚደግፉ የሕግ ባለሙያዎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ዳኛ በያዘው መዝገብ ላይ የመወሰንና የማዘዝ ሥልጣኑ የዳኛው ሆኖ ሳለ፣ ‹‹ይህንን አድርግ›› ማለት በዳኝነት ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት በመሆኑ እንዳሳሰባቸውም ገልጸዋል፡፡

የሕግ ባለሙያዎቹ ከመብት ጥሰትና በዳኞች ነፃነት ላይ ጣልቃ መግባት ላይ ባነሱት ጥያቄ፣ ፍርድ ቤቱ የክርክርና የቀጠሮ መዛግብትን ከመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ለምን መቅጠር እንደፈለገ ምላሽ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ መስቀል ዋጋሪ፣ ፍርድ ቤት አልተዘጋም ብለዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ፍትሕ ማግኘት አለበት፡፡ ፍትሕ እንደ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ውኃና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች ነው፡፡ ነገር ግን ዓለም አቀፉ ኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያም በመከሰቱ፣ የሕዝብ መሰባሰብን ማለትም ችሎት ለመከታተል፣ ዋስ ለመሆን፣ ለዋስትና ያስያዙትን ገንዘብ ለመውሰድ፣ የውሳኔ ግልባጭ ለመውሰድና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣውን ማኅበረሰብ ለማስቀረት ፍርድ ቤት በከፊል እንዲዘጋ ተደርጓል፤›› ብለዋል፡፡

ለወረርሽኙ መስፋፊያ ከሆኑት ምክንያቶች አንዱ መሰባሰብ በመሆኑ፣ ያንን ለማስቀረትና የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለው አክለዋል፡፡ በጣም አስፈላጊና አስቸኳይ የሆኑ የወንጀልም ሆነ የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች እንደሚታዩ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡ የወንጀል ክስ ኖሮባቸው በማረሚያ ቤት ያሉ ተጠርጣሪ ታሳሪዎች ጉዳይ ባሉበት ቦታ በቴሌ ኮንፈረንስ ለማከራከር ዝግጅቶች እየተሟሉ መሆኑን፣ አቶ ብርሃነ መስቀል ተናግረዋል፡፡ እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ፍርድ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የሚዘጉበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ መታሰብ ያለበት ግን ሲከፈት ምን ያህል ባለጉዳይ ፍርድ ቤቶችን ሊያጥለቀልቅ እንደሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ ሳይዘጉ እንዴት መቀጠል እንዳለባቸው ከችሎት አስተባባሪ ዳኞች ጋር በተደረገ ውይይት አንድ የውሳኔ  ሐሳብ ላይ መደረሱን ጠቁመው፣ የችሎት አስተባባሪ ዳኞች ከችሎት ዳኞች ጋር በመወያየትና የዳኞቹን ውሳኔ በማወቅ፣ ችሎቶች ሳይሠሩ የሚቀጥሉበትን ማመቻቸት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የችሎት ዳኞችን ባገኙት መገናኛ ዘዴ ያነጋገሩት የችሎት አስተባባሪዎች ያገኙት ምላሽ፣ ሰኔ መጨረሻና ሐምሌ መጀመርያ አካባቢ ወረርሽኙ በስፋት ይሠራጫል የሚል ሥጋት ስላለ፣ እስከዚያው ድረስ የክርክርና የቀጠሮ መዝገቦችን ረዘም አድርጎ በመቅጠር ጊዜው በሰላም ካለፈ፣ ነሐሴ 2012 ዓ.ም. እና መስከረም ወር 2013 ዓ.ም. ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የሚያዩዋቸው ጉዳዮች ከባድና ትልልቅ በመሆናቸው፣ እንዲሁም ዳኞቹ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ያላቸው ስለሆኑ እነሱ ያልመከሩበት ውሳኔ ሊተላለፍ እንደማይችል የገለጹት አቶ ብርሃነ መስቀል፣ አንድ ዳኛን እንኳን ‹‹ይህን መዝገብ ሥራ፣ ያንን መዝገብ ተው›› ብሎ ጣልቃ በመግባትና ማዘዝ ቀርቶ ስለያዘው መዝገብ እንኳን ማንሳት እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡ ማንም አካል በዳኝነት ነፃነት ላይ ሊገባ እንደማይችልም አክለዋል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ባደረገው ውይይት የደረሰበት ስምምነት፣ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ጋር ተያይዞ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚቀርቡ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን የፍርድ ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተረኛ ችሎት ዳኞችን ቁጥር በመጨመር በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በሌሎች መዝገቦች ማለትም ለውሳኔ፣ ለብይንና ለትዕዛዝ የተቀጠሩ በርካታ የወንጀል መዛግብትና ውስን የፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን ሥራ ማቃለል እንደሆነም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

የፍርድ ቤቱ አመራር ሌላው ያስተላለፈው ሐሳብ፣ ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ ከተደረገ በኋላ የፍትሐ ብሔር የውሳኔ መዝገቦች በፍርድ ቤቱ ማኅበራዊ የትስስር ገጽ ላይ እንዲወጡ የተወሰነ ቢሆንም፣ አመራሩ እንዲቆም ወስኗል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተወሰነበት ወገን በወቅቱ ይግባኝ ማለት ስለማይችልና የፍርዱን ግልባጭ ማግኘት ስለሚቸገር፣ ሁሉም ሰው ማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ማግኘት ስለማይችል፣ የተወሰነለትም በወረርሽኙ ምክንያት ማስፈጸም ስለማይችል መታገዱን አቶ ብርሃነ መስቀል አስረድተዋል፡፡

ውሳኔ ያረፈባቸው መዛግብት በዳኞች እጅ በመሆናቸው ሰብስቦ ወደ መረጃ ቋት (ዳታ) ማስገባትም ስለማይቻል መሆኑን፣ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉም አክለዋል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የልጅ፣ የቤተሰብ ቀለብ፣ የአሠሪና የሠራተኛ ጉዳይ፣ የጉዳት ካሳ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የንግድና ኢንቨስትመንት፣ በአጠቃላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አንድምታ ያላቸው ጉዳዮችና አስቸኳይ ጉዳዮች ከሆኑ ሊታዩ እንደሚችሉ የፍርድ ቤቱ አመራር ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

በማረሚያ ቤት ሆነው የጥፋተኝነት ፍርድም ሆነ ወይም የቅጣት ውሳኔ፣ በነፃ የሚለቀቁ ወይም እንዲከላከሉ ብይን የመሥራት ሥራ በሚገባ እንዲሠራና ውጤቱ እንዲነገራቸውም አመራሩ ተስማምቷል፡፡ በክርክር ሒደት ላይ ያሉት ደግሞ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ክርክር እንዲያደርጉና ፍትሕ እንዲያገኙ ለማድረግ አመራሩ ተስማምቷል፡፡ ስምምነቱ በቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ድሬዳዋና በክልል ያሉ ተዘዋዋሪ ችሎቶችን ያካተተ ነው፡፡ ከማረሚያ ቤት ውጪ በዋስትና ያሉ መደበኛ ችሎቶች እስከሚጀምሩ ድረስ ባሉበት እንደሚቆዩም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ መዛግብት በትብብር ተሠርተው እንዲጠናቀቁ፣ ለግንቦት ወር 2012 ዓ
.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበሩ በከፊል ዝግ መሆኑን ያልሰሙ ባለጉዳዮችን፣ ዳኞች ከቻሉና ከፈለጉ ርቀታቸውን ጠብቀው ፍርዱን መንገር እንደሚችሉም ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡ የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ በሚመለከት በጣም የተቸገሩ ከሆነ እንደ ሁኔታው ዳኞች በሚሰጡት ትዕዛዝ እንዲፈጸምላቸው ተስማምተዋል፡፡ የየራሳቸውን ውዝፍ መዝገብ ሠርተው ያጠናቀቁ ዳኞች በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ፊት ዕውቅና እንደሚሰጣቸው፣ ያላጠናቀቁ ደግሞ የየራሳቸው ምክንያት ስለሚኖራቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ አመራሩ መስማማቱ ታውቋል፡፡

Ethiopian Legal Brief

A BLOG ABOUT ETHIOPIAN LAW

https://telegram.me/lawsocieties
ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች በሙሉ
________
የጥብቅና ፈቃድ በኦንላየን/online/ማደስ እንድትችሉ የኢ-አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ስራ የገባን በመሆኑ የአጠቃቀም መመሪያውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች የተመለከተውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ


shorturl.at/nJ048


https://telegram.me/lawsocieties
Never cease to do this! Your heart❤️ is the essence of your existence, listen to it, cherish it and protect It!❤️

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!!

via Christina Mishell:
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያቶች በንፋስ ስልክ ለፍቶ ምድብ ችሎት የተሰጡ ውሣኔዎች ከፊል መግለጫ

************************************************************

1. መ.ቁ 161652 ……….. ተከሳሽ ኃላፊነት የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

2. መ.ቁ 162380 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ነው፣ ተከሳሽ ለከሳሽ የ11 ቀን ደሞዝ፣

የ62 ቀን የአመት ዕረፍት ክፍያና 1500.00 ኪሳራ

ይክፈል፣ የስራ ምስክር ወረቀት ይስጥ ተብሎ ተወሰነ፡፡

3. መ.ቁ157065 ……….. በተከሣሽ የተፈፀመ ሕገወጥ ድርጊት የለም፡፡

የአገልግሎት የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ

ለከሣሾች እንዲከፈለ ተወሰነ፡፡

4. መ.ቁ149066 ……….. ስንብቱ ሕገወጥ ስለሆነ ተከሳሽ ለከሳሽ የሁለት ወር

የማስጠንቀቂያ ጊዜና የካሳ ክፍያ እንዲከፍል ተወሰነ፡፡

5. መ.ቁ163948 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ነው፣ ተከሳሽ ለከሳሽ የሁለት ወር

የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ የአገለግሎት የአመት ዕረፍት ክፍያ

እንዲከፍል ተወሰነ፡፡

6. መ.ቁ161318 ……….. ለከሳሽ የሚከፈል ክፍያ የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

7. መ.ቁ160779 ……….. የከሳሾች የዳኝነት ጥያቄ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ

ተደረገ፡፡

8. መ.ቁ163057 ……….. የከሳሽ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ የዚህ ፍ/:ት ስልጣን አይደለም፣

የቦነስ ጥያቄ በይርጋ ውድቅ ተደረገ፣ ከሳሽ 1000 ኪሳራ

ለተከሳሽ ይክፈል ተብሎ ተወሰነ፡፡

9. መ.ቁ163115 ……….. አደጋው በከሳሽ ምክንያት አልደረሰም፣ ጣልቃ ገብ ካሳ

ስለከፈለ በድጋሚ ተከሳሽ ሊከፍል አይገባም፣ ለህክምና እና

ለመድሀኒት ተከሣሽ ለከሳሽ 15000.00 ይክፈለው ተብሎ

ተወሰነ፡፡

10. መ.ቁ152984 ……….. ሕገወጥ ስንብት የለም ተብሎ ለተከሰሽ ተወሰነ፡፡

11. መ.ቁ154966 ……….. የስራ ውሉ የተቋረጠው በሕጋዊ መንገድ ነው ተብሎ ተወሰነ፡፡

12. መ.ቁ162127 ……….. የስራ ውሉ የተቋረጠው በሕገወጥ መንገድ ነው፣ የወር ደሞዝ

8500፣ የአግልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ፣ የሁለት ወር ደሞዝና የካሳ ክፍያ ለከሳሽ ይከፈለው ተብሎ ተወሰነ፡፡

13. መ.ቁ163046 ……….. ስንብቱ ሕጋዊ ስለTነ የሚከፈል ክፍያ የለም ተብሎ ተወሰነ፡፡

14. መ.ቁ163286 ……….. ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም ተብሎ ተዘጋ፡፡

15. መ.ቁ163781 ……….. የሚፈፀም ፍርድ የለም ተብሎ ተዘጋ፡፡ስንብቱ ሕጋዊ ስለሆነ

የሚከፈል ክፍያ የለም፡፡

16. መ.ቁ160838 ……….. ሕገ ወጥ የስራ ውል መቋረጥ አልተደረገም፣ የከሳሾች የአመት

ዕረፍት በገንዘብ ተለውጦ እንዲከፈላቸው ተወሰነ፡፡

17. መ.ቁ100885 ……….. 245870.00 ተከሳሽ ለከሳሽ ከ9% ወለድ ጋር እንዲከፍል

ተወሰነ፡፡

18. መ.ቁ130629 ……….. ወጪና ኪሳራ ለከሳሽ ተወሰነ፡፡

19. መ.ቁ149428 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

20. መ.ቁ160338 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

21. መ.ቁ108882 ……….. አመልካች የቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል፡፡

22. መ.ቁ164086 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

23. መ.ቁ47163 ……….. ለከሳሽ በከፊል ተወስኗል፡፡

24. መ.ቁ163771 ……….. አመልካቾች በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

25. መ.ቁ163356 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

26. መ.ቁ115972 ……….. ተከሳሽ የቀረቡት የዳግም ዳኝነት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

27. መ.ቁ157525 ……….. የከሳሽ የሞግዚትነት ማስረጃ በፍ/:ት የታገደ ስለሆነ መዝገቡ

ተዘጋ፡፡

28. መ.ቁ158450 ……….. በድጋሚ የቀረበ ክስ ስለሆነ በብይን ተዘጋ፡፡

29. መ.ቁ153958 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

30. መ.ቁ157995 ……….. ፍርድ :ቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም ተብሎ ተዘጋ፡፡

31. መ.ቁ163133 ……….. ክሱ በይርጋ ታግዷል ተብሎ ተዘጋ፡፡

32. መ.ቁ162014 ……….. የአመልካቾች የክልከላ ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡

33. መ.ቁ157809 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

34. መ.ቁ156037 ……….. ከሳሽ በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ተወስኗል፡፡

35. መ.ቁ134072 ……….. የንብረት ክፍፍል ውሣኔ ተሰጠ፡፡

36. መ.ቁ150205 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

37. መ.ቁ162732 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

38. መ.ቁ163737 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

39. መ.ቁ163080 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

40. መ.ቁ159116 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

41. መ.ቁ157951 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

42. መ.ቁ163011 ……….. ፍቺና የልጅ ቀለብ ውሳኔ ተሰጠ፡፡

43. መ.ቁ166929 ……….. የቀለብ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

44. መ.ቁ163359 ……….. የልጅነት ውሣኔ ተሰጠ፡፡

45. መ.ቁ158817 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

46. መ.ቁ163410 ……….. የፍቺ ውሣኔ ተሰጠ፡፡

47. መ.ቁ162108 ……….. የከሳሽ ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡

48. መ.ቁ151719 ……….. የአመልካች አ:ቱታ ላይ በከፊል ተወሰነ፡፡

49. መ.ቁ153968 ……….. ስምምነት ተሻሽሎ ፀደቀ፡፡

50. መ.ቁ155813 ……….. አመልካች ድርቸው እንዲሰጣቸው ተወሰነ፡፡
በአሰራር ሂደት የሚከሰቱ ስህተቶች ለዳኝነት ነጻነት አለመኖር ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ እንደማይገባ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡
ሰሞኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር አጣሪ ችሎት በቀረበ አንድ የፍትሐ-ብሔር ጉዳይ ላይ በአመራሩ ጣልቃ ገብነት ሁለት ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንደተሰጠ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ በፍርድ ቤቱ ዳታ ቤዝ ባለሙያዎች በተፈጠረ የአሰራር ስህተት ምክንያት መሆኑን ጉዳዩን ያጣራው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
በፍርድ ቤቱ አመራር ጣልቃ ገብነት የዳኝነት ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ጥቆማ የደረሰው የጠቅላይ ፍ/ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ጉዳዩን ለማጣራት ባካሄደው ምርመራ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች የሰበር አጣሪው ችሎት በአምስት ዳኞች ውሳኔ የሰጠበትን ጉዳይ ቀደም ሲል “አያስቀርብም” ለማለት በመዝገቡ ውስጥ ተያይዞ የቀረበን ቅጽ በመመልከት ውሳኔ እንደሰጠ የሚገልጽ የተሳሳተ መረጃ በመረጃ ቋት (Database) ውስጥ በማስገባታቸው ምክንያት የተፈጠረ ችግርን መነሻ በማድረግ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
የፍርድ ቤቱ የፍርድ ስራ ምርመራና የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ችግሩን የፈጠሩት ባለሙያዎችንና የችግሩን ስረ ነገር ለመለየት የማጣራት ስራውን የቀጠለ ሲሆን በዚህ ያልተገባና ሃላፊነት በጎደለው ተግባር ላይ ድርሻ ያላቸው ባለሙያዎች ለተፈጠረው ስህተት በዲሲፕሊን እንዲጠየቁና በፍርድ ቤቱ በተዘረጋው የተጠያቂነት ስርዓት ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡም የዳኝነት ነጻነት የለም፤ የዳኝነት አካሉ አሁንም ከጣልቃ ገብነት ነጻ አልወጣም እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚተላለፈው መረጃ ከእውነት የራቀና መሰረት የሌለው መሆኑን ተረድቶ በዳኝነት አካሉ ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም አስተያየቶችና የሚቀርቡ ትችቶችን በጥንቃቄ እንዲመዝናቸው ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቶች ዜጎች ፍትህ ለማግኘት ጠንካራ ተስፋ የሚጥሉባቸው ተቋማት ናቸው ያለው ዳይሬክቶሬቱ የፍ/ቤቶች መልካም ገጽታን የማጠልሸትና የህዝቡን አመኔታ በመሸርሸር አሉታዊ ውጤት ያላቸው መረጃዎችን በማንጨት የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ቆም ብለው ጥቅምና ጉዳቱን እንዲያመዛዝኑም መክሯል፡፡ የምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የደረሰበትን የምርመራ ውጤትም እንዲህ አብራርቷል፡፡
ጉዳዩ በጀ ፎር ኮንስትራክሽን እና አስማማው ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ የውል ክርክር ሲደረግበት የቆየ ነው፡፡ አመልካች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባቀረበው አቤቱታ የፍርድ ቤቱ ይግባኝ ችሎት ዳኝነት በጠየቁበት ጉዳያቸው ላይ የሰጠው ውሳኔ የህግ ትርጉም ስህተት ያለው መሆኑን ጠቅሰው የሰበር ችሎቱ ጉዳዩን አይቶ እንዲያርምላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የአቤቱታውን ተገቢነት እንዲያጣራ በመዝገብ ቁጥር 185837 ጉዳዩ የቀረበለት 1ኛ ሰበር አጣሪ ችሎት ጥር 8 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን ሰምቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በጉዳዩ ላይ የችሎቱ ሁለቱ ደኞች የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡበት እና አንድ ዳኛ ግን በጉዳዩ ላይ እንነጋገርበት ማለታቸውን የሚያሳይ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የተሞላ የውሳኔ ቅጽ ተያይዟል፡፡ በዚህም ምክንያት ችሎቱ ውሳኔ ያልሰጠ መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል፡፡
አቤቱታ አቅራቢው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጉዳያቸው ውሳኔ ሳይሰጠው ረጅም ጊዜ መውሰዱን፤ መዝገባቸውም ቀጠሮ ሳያገኝ መቆየቱንና በዚሀም ምክንያት ጉዳያቸው በምን ደረጃ ላይ እንደለ መረጃ ማግኘት ያልቻሉ መሆኑን ጠቅሰው መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንትም ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፡፡ ከችሎቱ ዳኞች ጋርም ባካሄዱት ውይይት ክብርት ፕሬዝደንቷ በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 21 (1) በተሰጣቸው ስልጣንና በችሎቱ ዳኞች ስምምነት ጉዳዩ በሶስት ዳኞች ከሚታይ ይልቅ በአምስት ዳኞች እንዲታይ የስራ መመሪያ ይሰጣሉ፡፡
አምስቱ ዳኞችም መዝገቡን መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም አስቀርበው ጉዳዩን መርምረዋል፡፡ በመጨረሻም ሰበር ችሎቱ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ላይ ሊያያቸው የሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮች ያሉበት ነው በማለት “ያስቀርባል” የሚል ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ያሳልፋል፡፡
በዚህ ሂደት መዝገቡ ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ዳታ ቤት በመሄዱ የዳታ ቤዝ ባለሙያዎች መጀመሪያ የውሳኔ ሃሳብ የቀረበበትን ነገር ግን ውሳኔ ያላረፈበትን ቅጽ በመመልከት ጉዳዩ “አያስቀርብም” ተብሎ መወሰኑን የሚገልጽ መረጃ መረጃ ቋት (Database) ውስጥ በስህተት ያስገባሉ፡፡ ይህም መረጃ ለባለጉዳዮች በ992 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይደርሳቸዋል፡፡ ባለጉዳዮቹም ውሳኔውን ተቀብለው በዝምታ ያልፋሉ፡፡ በሌላ በኩል በበችሎቱ ውሳኔ መሰረት በሪጂስትራር በኩል የአመልካች የሰበር አቤቱታ ከፍርድ ቤቱ መጥሪያ ጋር ለተጠሪ እንዲደርስ በታዘዘው መሰረት መጥሪያው እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
የተፈጠረውን ስህተት ለማረም በመረጃ ቋት (Database) በገባው ትክክለኛ መረጃ መሰረት ለባለጉዳዮቹ መዝገቡ ያስቀርባል ተብሎ መወሰኑን እንዲሁም ለምርመራ እና የመልስ መቀባበያ ቀጠሮ መሰጡተን የሚገልጽ መረጃ በ992 አጭር የጽሁፍ መልእክት በድጋሚ ይደርሳቸዋል፡፡
በአንድ ጉዳይ ላይ አንድ ችሎት በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ እንዴት ሊሰጥ ይችላል የሚል ተገቢነት ያለው ጥያቄ ምናልባትም ከግራና ቀኝ ተከራካሪ ባለጉዳዮች መካከል አንዱ ያነሳሉ፡፡ ለዚህም ጥያቄ አሁን ላይ ማንነታቸው ተለይቶ ያልታወቁ አካላት ያልተገባና እውነታነት የሌለው ምክንያት በመስጠት የዳኝነት ነጻነት በአመራሩ ጣልቃ ገብነት መጣሱንና የውሳኔ ለውጥ መደረጉን የሚገልጽ መረጃ መሰራጨት መጀመሩን የምርመራ ክፍሉ አመልክቷል፡፡ ነገር ግን አቤቱታ አቅራቢው ባለጉዳይ ከላይ እንደተገለጸው ለፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ውሳኔ ዘገየብኝ፤ መዝገቡም ቀጠሮ ባለመያዙ ጉዳያቸው ያለበትን ደረጃ ማወቅ አለመቻላቸውን የሚገልጽ መሆኑን ከመዝገቡ ጋር የተያያዘው ማስረጃ ያሳያል፡፡
ይህን አይነት የተለመደ አቤቱታ የመቀበልና አስተዳደራዊ መፍትሄ የመስጠት አሰራር በተሳሳተ ግንዛቤ ዓላማውን እንዲስት በማድረግ አቤቱታው ውሳኔ እንዲሻሻል የቀረበ በማስመሰልና ከእውነት የራቀ መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን የምርመራ ክፍሉ ጠቁሟል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በዲሲፕሊን የሚጠየቁ አካላትን ለይቶ ተገቢው አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን በማረጋገጥ ጉዳዩን ለማጣራት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም የመዝገቡን ሙሉ ግልባጭ በማግኘት ማጣራት እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሰበር መረጃ

#Ethiopia : ግብፅ ከኢትዮጵያና ሱዳን ተቋርጦ የነበረውን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሚደረገውን ድርድር ለመቀጠል የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏን የሀገሪቱን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ Daily News Egypt ዘግቧል።

via Natnael Mekonnen: