አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም ያለአግባብ ከሂሳባቸው ላይ እየቆረጠባቸው መሆኑን ደንበኞች ተናገሩ

ከኢትዮ ቴሌኮም ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ በገንዘባችን ከገዛነው ላይ ያለአግባብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ደንበኞች ተናገሩ፡፡

ደንበኞቹ ብዙዎቻችን ቤት በተቀመጥንበት በዚህ ሰዓት ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ ተቋሙ ገንዘባችንን ያለአግባብ እየቆረጠብን ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ሆነዋል፡፡

በቤት በሚቆዩበት ጊዜ ደግሞ ረጅሙን ጊዜአቸውን የሚያጠፉት በስልኮቻቸው ኢንተርኔት በመጠቀም መሆኑን ነግረውናል፡፡

ነገር ግን እንዚህ ተጠቃሚዎች በተለይ ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚሞሉት ጥቅል አልበረክት እንዳላቸው እና ቴሌ ያለአግባብ ገንዘብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ገንዘብ ካለአግባብ ከመቁረጥ ባለፈም የኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቆራረጠ እና ፈጣን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው ነግረውናል፡፡

የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለደንበኞቻቸው የዋጋ ቅነሳ እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮምም እንደ ተቋም የዋጋ ቅነሳ ማድረግ ሲኖርበት ጭራሽ ያለ አግባብ ገንዘባችንን መቁረጡ አሳስዝኖናልም ብለውናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ያአግባብ ገንዘብ እየቆረጠብን ነው፣ የኢንተርኔት አገልግሎቱም ፈጣን አይደለም የሚለው ቅሬታ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ተቋሙ ምላሽ ሊሰጠን አልፈቀደም፡፡

በትዕግስት ዘላለም
ሚያዝያ 6 ቀን 2012 ዓ.ም
Via ABRHAM YOHANNES Ethiopian Legal Brief
https://telegram.me/lawsocieties
WHO officials say it’s unclear whether recovered coronavirus patients are immune to second infection
This raises concerns that patients don’t develop immunity after surviving Covid-19.

“With regards to recovery and then reinfection, I believe we do not have the answers to that. That is an unknown,” said Dr. Mike Ryan, executive director of WHO’s emergencies program.

World Health Organization officials said Monday not all people who recover from the coronavirus have the antibodies to fight a second infection, raising concern that patients may not develop immunity after surviving Covid-19.

“With regards to recovery and then reinfection, I believe we do not have the answers to that. That is an unknown,” Dr. Mike Ryan, executive director of WHO’s emergencies program, said at a press conference at the organization’s Geneva headquarters on Monday. 

A preliminary study of patients in Shanghai found that some patients had “no detectable antibody response” while others had a very high response, said Dr. Maria Van Kerkhove, WHO’s lead scientist on Covid-19. Whether the patients who had a strong antibody response were immune to a second infection is “a separate question,” she added.

More than 300,000 of the 1.87 million coronavirus cases across the world have recovered, WHO officials noted, adding that they need more data from recovered patients to understand their antibody response, whether that gives them immunity and for how long. 

“That’s something that we really need to better understand is what does that antibody response look like in terms of immunity,” Van Kerkhove said.

Ryan said there are questions about whether the virus can reactivate after a patient recovers and tests negative for Covid-19.

“There are many reasons why we might see reactivation of infection either with the same infection or another infectious agent,” he said. In general, “there are many situations in viral infection where someone doesn’t clear the virus entirely from their system.” Some patients can also clear the main infection but develop a secondary bacterial infection, he said. 

The U.S. Centers for Disease Control and Prevention has said that it is developing a test to detect the presence of coronavirus antibodies to determine if a person could be immune to the disease. While such a test can determine who has been exposed to the virus, it’s not clear if it can identify those immune to reinfection, according to the WHO.

WHO officials also warned Monday against lifting social distancing restrictions and reopening businesses, even as U.S. political leaders, from President Donald Trump to New York Gov. Andrew Cuomo, have said they hope to reopen businesses as soon as it is safe to do so. 

“While Covid-19 accelerates very fast, it decelerates much more slowly. In other words, the way down is much slower than the way up,” WHO Director-General Tedros Adhanom Ghebreyesus said at a press conference at the organization’s Geneva headquarters on Monday. “That means control measures must be lifted slowly and with control. It cannot happen all at once.”

Tedros outlined a checklist for countries before they should consider lifting social distancing measures:

Transmission of the virus should be controlled.

A surveillance system should be in place to detect, isolate and treat patients.

Outbreaks in hospitals and nursing homes should be minimized.

Preventive measures in essential locations such as schools and workplaces should be in place.

The risk of importing the disease from abroad should be under control.

“Control measures can only be lifted if the right public health measures are in place, including significant capacity for contact tracing,” Tedros said. 
UDHR
ለኢንተርኔት ቅርብ ለሆናችሁ የህግ ቤተሰቦች ሁሉ .....

Hello Beautiful Ethiopian Law 🏠Families (ELF),
It has been more years this channel has been created. have been sharing posting Legal Teaching Material s, Short Notes, Power points, Proclamation, Regulations, important legal news, Events, Motivation, Exit Exam Announcement, Open Vacancy, Scholarship Links, Online Course Links and more. It feels like a lot to take ...a lot of different content on one channel. Therefore, I have decided to get Volunteers who can Run this channel of

https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate

🛑This Channel will continue to share many things that will help you for your Education and work place, and I will add motivation and more of self-development contents. Scholarship, Job Vacancy and for more I need Volunteers.

Thank you for all who supported me in different ways. And thank you so much for joining this channel. ❤️
I am working in collaboration with @lawsocieties so called ALE, so please, send me your info..Via @Alemwaza

You should fill all.
Full Name:....,......
Age:
Sex:
Phone Number:
E-mail address:
Face book name:
Current living place:
Job:
Thanks👍

Let's help each other.

stay at home and be safe!

Yours
https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate
የ2ተኛ_ደረጃ_ትምህርት_በሳተላይት_ፕሮግራም.docx
25.6 KB
Educational Satellite Television Programs weekly Transmission Timetable (Week 28)- DATE 5-9/08/ 2012E.C.

ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሆኑ ለእህት ወንድሞቻችሁ አድርሱ።

stay home be safe‼️
https://telegram.me/lawsocieties
ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለሆኑ እህት ወንድሞቻችሁ አድርሱ።

🔴ከላይ ያለው ዶክመንት ይመልከቱ🛑

Educational Satellite Television Programs weekly Transmission Timetable (Week 28)- DATE 5-9/08/ 2012E.C.


https://telegram.me/lawsocieties
ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ ፖሊስ በተጠናከረ መልኩ እርምጃ እንደሚወስድ ተገለጸ፡፡
*****************************************************************************
የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ክቡር እንደሻው ጣሰው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በልጅነታችን የተከተብነው ክትባት እና አመጋገባችን ከወረርሽኙ ይከላከልልናል፣ በሽታዉ ጥቁሮችን አይዝም ወይም በሀገራችን የለም በማለት አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን የሚያዘናጉ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸው እነዚህን አሳሳች መረጃዎች የሚጽፉ፣ የሚያሰራጩ፣ የሚያትሙ እና የሚጋሩትን ለህግ በማቅረብ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ሐሰተኛ መረጃ የሚናገሩ፣ የሚያስነግሩ፣ የሚያሰራጩ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና የሚዲያ አካላት ላይም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ክቡር ኮሚሽነር ጄነራሉ ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ጥሪ ሀገር፣ ህዝብ እና ወገንን የማዳን፣ትውልድን የማስቀጠል ጉዳይ መሆኑን ሁሉም ሰው ተገንዝቦ ላቅ ባለ አስተሳሰብ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ወረርሽኙን ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሰብዓዊ መብትን የሚጥስ ሳይሆን የቫይረሱን ስርጭት የመከላከያ ዋና መሳሪያችንና በቀጣይ ሊያጋጥመን ከሚችል አጠቃላይ ቀውስ ራሳችንን የማዳኛ መንገድ በመሆኑ ይህንን ተገንዝበን መስራት አለብን ሲሉም ክቡር ኮሚሽነር ጄነራሉ ገልጸዋል፡፡
እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትም መደበኛ ህጎችን መጠቀምና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ የተደነገገውን አዋጅ እና መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መቻል አለብን ብለዋል፡፡
የፖሊስ አባላቱ ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየጠበቁ በህግ የተሰጧቸውን ስራዎች በሙሉ ልብ እና በቆራጥነት ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን ከወረርሽኙ የመከላከል ስራን በዲሲፕሊን እንደሚያከናውኑም ክቡር ኮሚሽነር ጄነራሉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ በአዋጅ፣ በደንብ እና በመመሪያ የተደነገጉ ግዴታዎች እና ክልከላዎች ላይ በቂ ጥናት በማድረግ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በመግለጽ ህጉን ለማስከበር ለሚያደርገው ጥረት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከጎኑ በመቆም አጋዥና ተባባሪ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
via Ethiopian federal police commission

https://telegram.me/lawsocieties
አለሕግAleHig ️
Photo
አንድነታችን እና አብሮነታችን የጋራ የህልውናችን መሰረት ነው፡፡
________________
አገር ማለት ሰው፣ ሰው ማለት አገር ነውና አገር እና ሰው ከሌለ ሀይማኖታዊ፣ መንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ መስራት፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ማድረግ አይታሰብም፡፡

የኮሮና ውሽንፍር ቢያስጨንቀንም እስኪያልፍ ቢያለፋንም አካላዊ ርቀታችን ከጠበቅን፣ እጃችንን በውሃና ሳሙና ደጋግመን ከታጠብን ይህም አልፎ የአብሮነት ቀን መምጣቱ አይቀርምና ቀኑ እስኪያልፍ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና ቦታዎች አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ መሰብሰብ ወይንም መገኘት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከለ ስለሆነ ለሕግ ተገዥ በመሆን ራሳችንን ከኮሮና ወረርሽኝ እንከላከል፡፡

ለሰው መዳኒቱ ሰው ነው፣ እንደሚባለው ሁሉ የአንዳችን መጠንቀቅ ለሌሎች መዳን ዋስትና በመሆኑ አንድነታችን እና አብሮነታችን የጋራ የህልውናችን መሰረት ነውና ዛሬም ሆነ ነገ እንጠንቀቅ፣ ራሳችንን እንጠብቅ!! መልዕክታችን ነው፡፡

ሰላም፣ ጤና ለህዝባችን እና ለአገራችን ይሁን!!

https://telegram.me/lawsocieties
የሥራ ውል መቋረጥ

የሥራ ውል የሚቋረጥባቸው መንገዶች

በሕግ በተደነገገው መሰረት

የሥራው ወይም የጊዜው ማለቅ

የፕሮጀክት ሥራ

የሠራተኛው ወይም አሠሪው መሞት

በጡረታ መገለል

የድርጅቱ ለዘለቄታው መዘጋት

የአካል ጉዳት

የሥራ ውልን በስምምነት ስለማቋረጥ

ሥራ መልቀቅ

ሼር

 https://telegram.me/lawsocieties

የሥራ ውል መቋረጥ

የዓለም ዓቀፉ የሥራ ድርጅት የሥራ ግንኙነት መቋረጥ ስምምነት C158 - Termination of Employment Convention, 1982 (No. 158) አንኳር ይዘትና መሪ ደንቦች ስምምነቱን ባጸደቁት ሆነ ባላጸደቁት በርካታ አገራት ዘንድ በስፋት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የስምምነቱ ወሰን በአሠሪው አነሳሽነት የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥን የሚመለከት ሲሆን ሌሎች የማቋረጫ መንገዶች አልተካተቱም፡፡ ኢትዮጵያ ይህን ስምምነት አጽድቃለች፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ. 377/96 ከስምምነቱ ጋር ሲነጻጸር አንድ እርምጃ ወደ ፊት ተራምዷል ለማለት ይቻላል፡፡

በስምምነቱ አንቀጽ 4 በአሠሪው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥባቸው ሶስት በቂና ብቸኛ ምክንያቶች ተለይተዋል፡፡ ድንጋጌው እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

The employment of a worker shall not be terminated unless there is a valid reason for such termination connected with the capacity or conduct of the worker or based on the operational requirements of the undertaking, establishment or service.

Share
https://telegram.me/lawsocieties

እነዚህ ዐበይት የሥራ ውል ማቋረጫ ግላዊና ድርጅታዊ ምክንያቶች በአዋጁ አንቀጽ 26(1) ላይ እውቅና ያገኙ ብቸኛ ምክንያቶች ሆነው ተደንግገዋል፡፡ የድንጋጌው ይዘት ከስምምነቱ ጋር ሲነጻጸር ከቋንቋ አጠቃቀም የዘለለ ልዩነት አይታይበትም፡፡

“የሥራ ውል ከሠራተኛው ጠባይ፤ ወይም የሠራተኛውን የመሥራት ችሎታ ከሚመለከቱ ግልጽ ሁኔታዎች፤ ወይም ከድርጅቱ ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ባላቸው ምክንያቶች ብቻ ሊቋረጥ ይችላል፡፡”

በስምምነቱ አንቀጽ 5 የሥራ ውልን ለማቋረጥ ተገቢ ሆነው የማይቆጠሩ አምስት ምክንያቶች የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ በአዋጁ አንቀጽ 26(2) ላይ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

ሀ) ሠራተኛው በሠራተኞች ማኅበር አባል መሆኑ ወይም በማኅበሩ ህጋዊ ተግባሮች ተካፋይ መሆኑ

ለ) ሠራተኛው የሠራተኞች ተጠሪ ሆኖ ለመሥራት መፈለጉ ወይም መሥራቱ

ሐ) ሠራተኛው በአሠሪው ላይ ቅሬታ ማቅረቡ ወይም በፍርድ ቤት በቀረበ ክስ ወይም በሌላ ክስ ተካፋይ መሆኑ

መ) የሠራተኛው ብሔረሰብ፤ ጾታ ኃይማኖት፤ የፖለቲካ አመለካከት፤ የጋብቻ ሁኔታ፤ ዘር፤ ቀለም፤ የቤተሰብ ኃላፊነት፤ የዘር ሐረግ፤ እርግዝና ወይም ማኅበራዊ አቋም

‘እርግዝና’ በሚል በጥቅል አነጋገር በአንቀጽ 26(2) መ የተጠቀሰው ምክንያት በስምምነቱ አንቀጽ 5 ‘በእርግዝና ፈቃድ ምክንያት ከሥራ መቅረት’ በሚል አምስተኛ ምክንያት ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ይህም የአንቀጽ 26(2) ድንጋጌ ከስምምነቱ ይልቅ ለእርጉዝ ሠራተኞች የበለጠ ጥበቃ እንዳደረገ ያሳያል፡፡ በአዋጁ ድንጋጌ ላይ ከፈቃድ በተጨማሪ እርግዝናን መነሻ ያደረጉ ሁሉም ምክንያቶች የሥራ ውልን ለማቋረጥ ብቁና በቂ ምክንያት ሆነው አይቆጠሩም፡፡ ይኸው የህጉ አቋም በአንቀጽ 87 ንዑስ አንቀጽ 5 እና 6 ላይ ተብራርቶ ተደንግጓል፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በስምምነት፤ በጥፋት ወይም በቅነሳ ካልሆነ በቀር ሴት ሠራተኛን ነፍሰ ጡር በሆነችበት ጊዜና ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በአራት ወራት ውስጥ ማሰናበት አይቻልም፡፡ በሌላ አነጋገር በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በአንቀጽ 28(1) በተዘረዘሩት የውል ማቋረጫ ምክንያቶች እርጉዝ ሠራተኛን ከሥራ ማሰናበት የተከለከለ ነው፡፡

አሠሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውል የሚያቋርጥበት መንገድ እንዲሁ ከስምምነቱ በተሻለ በአዋጁ ጥበቃ አግኝቷል፡፡ የስምምነቱ አንቀጽ 11 ከባድ ጥፋት ያልፈጸመ ሠራተኛ የሥራ ውሉ ከመቋረጡ በፊት አሠሪው ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው እንደሚገባ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣል፡፡ በአገራችን አሠሪና ሠራተኛ ህግ መሰረት ማስጠንቀቂያ መስጠት ብቻውን የሥራ ውልን በህጋዊ መንገድ አያቋርጥም፡፡ ከማስጠንቀቂያው በተጨማሪ በአንቀጽ 28 የተመለከቱት በቂ ምክንያቶች ሊኖሩ ይገባል፡፡
በአብርሃም ዮሐንስ
https://telegram.me/lawsocieties
🛑በጡረታ መገለል🛑
👆👆👆👆👆👆👆👆

ዋቢ ህጎች

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 715/2003

የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 243/ በሕግ በተደነገገው መሠረት የሥራ ውልን ስለማቋረጥ ብሎ በጡረታ መገለልን እንደ አንድ ውል የሚቋረጥበት መንገድ ያስቀምጠዋል፡፡ 24(3) ሠራተኛው አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በጡረታ ሲገለል፤

በጡረታ መገለል
👇👇👇👇
የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 18(1) /ሐ መሰረት የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት ነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ መውጫ ዕድሜ (በእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ retirement age) ስድሳ ዓመት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ጡረታ መውጣት ማለት በህጉ የተወሰነው የስድሳ ዓመት እድሜ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡

በህግ የተቀመጠው የጡረታ ዕድሜ 60 ዓመት ሲሆን የሚሰላውም ሠራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበውን የልደት ዘመን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሠራተኛው በህግ የተወሰነው የ60 ዓመት የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ሲደርስ የሥራ ውሉን ያቋረጠው ህግ እንጂ አሠሪው ባለመሆኑ የሥራ ውሌ ከህግ ውጪ ተቋርጧል በሚል የሚያነሳው ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
“ሠራተኛው አግባብ ባለው ህግ መሠረት በጡረታ ሲገለል” የሥራ ውሉ በሕግ በተደነገገው መሰረት ይቋረጣል፡፡
ሠራተኛው የጡረታ እድሜ ላይ ደርሶ ከተቀጣሪነት ወደ ተጧሪነት ሲሸጋገር የሥራ ውሉም ያለ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ ያበቃለታል፡፡ ያ ማለት ግን ከጡረታ በኋላ እንደገና በአዲስ መልክ ተቀጣሪ ለመሆን አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ጡረተኛው ካካበተው የረጅም ጊዜ የሥራ ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር በተለይ በአንዳንድ የሥራ መስኮች ላይ ተፈላጊነቱ ይጨምራል፡፡ ሆኖም በቋሚነት (ላልተወሰነ) ጊዜ የመቀጠር እድል የለውም፡፡
በአዲሱ አዋጅ ቁ.714/2003 ብሎም በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ 715/2003 አንድ ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ከመድረሱ በፊት ጡረታ የሚወጣበት ወይም በጡረታ የሚገለልበት ስርዓት የለም፡፡ ሆኖም ዕድሜው ለጡረታ ሳይደርስ የጡረታ አበል ባለመብትና ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ በአዋጅ ቁ. 345/1995 አንቀጽ 12(2) እንደተደነገገው ቢያንስ 20 ዓመት አገልግሎት ያለው የመንግስት ሠራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡ ድንጋጌው ሠራተኛውን የጡረታ አበል ተጠቃሚ ወይም ተከፋይ ሳይሆን የጡረታ ባለመብት ያደርገዋል፡ በዚህ መልኩ የሚገኝ የጡረታ ባለመብትነት በአዋጅ ቁ 714/2003 እና በአዋጅ 715/2003 ላይም በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም የሥራ ውሉ የተቋረጠው ሃያ አምስት ዓመት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከሆነ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ሲቀረው የጡረታ አበል ተጠቃሚነት ወይም ተከፋይነት መብት ይኖረዋል፡፡

https://telegram.me/lawsocieties
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Programme Assistant
#international_organization_for_migration_iom
#social_science
#social_development
#program_assistant
Addis Ababa
Bachelor’s Degree, or equivalent preferably in Social Sciences, Social Work, Law or international relations
Minimum Years Of Experience: #4_years
Deadline: May 2, 2020
How To Apply: Send your CV to RECADDIS@IOM.INT
Write position title and Vacancy number in the subject line of your email
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Protection Officer
#the_norwegian_refugee_council_nrc
#legal_services
#law
#protection_officer
Benishangul Gumuz
degree in law, sociology, social work, international development from a recognized institution.
Minimum Years Of Experience: #4_years
Deadline: April 30, 2020
How To Apply: by clicking the source below
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Baraki Belay)
Notice that the above decision is not enable to regulate the employee of public enterprise.
https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate