አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Emanuel T Future Lawyer:
Hello Ale Family
I am Eskendir From Gambela University School of Law.
I am in need of Sound Lecture on Law of Person, Family law and on Succession. Please send me.
Stay Home Stay Safe!
Thank You!

Please if u have ,dont post it , just send me through my chat.. because time is not for seeking such kinda help.
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብ ይፋ ሆነ
https://telegram.me/lawsocieties
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው አዋጅ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅጽደቁ ይታወቃል።
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ይዘት በሚመለከት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በህገ መንግስቱ አንቀፅ 93 ንኡስ ቁጥር 4 መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ማውጣት እንዳለበት ይደነግጋል።

በዚህም መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣውን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ዝርዝር በሚመለከት ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

ማስፈፀሚያ ደንቡ አጠቃላይ አራት ዋና ዋና ከፍሎች ያሉት ሲሆን ይሄውም ክልከላን የሚያስቀምጥ፣ ግደታዎችን የሚጥል፣ የአስፈፃሚ አካላትን ክንውን እንዲሁም ልዩ ለዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

ክልከላን በሚመለከት ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።

ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።

በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።

በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡
https://telegram.me/lawsocieties
#DrAbiyAhemed

April 11, 2020

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት የተጣሉ ግዴታዎች ይፋ ሆነዋል!

የኮሮናቫይረስ ቨወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ ደንብ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጽድቋል። በዚሁ ደንብ መሰረትም የተጣሉ ግዴታዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።


1. ማንኛውም ኮቪድ-19 እንዳለበት የተጠረጠረ ሰው ወይም ወደ ሀገር የሚገባ አለማቀፍ መንገደኛ ኳራንታይን የመደረግና የኮቪድ-19 ምርመራ የማድረግ ግዴታ አለበት፤

2. ወደ ሀገር የገባ አለማቀፍ መንገደኛ ኳራንታይን በሚደረግበት ጊዜ የራሱን ወጪ የመሸፈን ሀላፊነት ያለበት ሲሆን፣ መንገደኛው የመክፈል አቅም የሌለው ከሆነ መንግስት ለዚሁ አላማ ባዘጋጀው ቦታ እንዲቆይ ይደረጋል፣

3. በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ማንኛውም ሰው መንግስት በሚያዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ክፍል የመቆየት ግዴታ አለበት፤

4. በጉዞ ወቅት ኮቪድ-19 አለበት ተብሎ የሚጠረጠር መንገደኛ ሲኖር የማጓጓዣ አንቀሳቃሹ በአቅራቢያው ላለው ወይም ለሚያርፍበት የመግቢያና መውጫ ኬላ ሀላፊ ወይም የኮቪድ19 ምርመራ ለሚያደርግ ቡድን የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፤

5. የኮቪድ-19 ያለበት ወይም አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣

6. የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ አለበት፤

7 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 6 የተመለከተው የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል፡፡

8. ማንኛውም አገልግሎት የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ማዘጋጀትና ተገልጋዮች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፣

9. ማናቸውም አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማቱ የሚሄዱ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፤

10.የመንግስት የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የግል የሚዲያ ተቋማት ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች፣ የዜና ትንተናዎች ወይም ፕሮግራሞች ሳይጋነኑ ወይም ሳይቃለሉ ተገቢው መረጃ ወደ ሕዝቡ የማድረስ እና አላግባብ የሆነ ድንጋጤና ሽብርን የማይፈጥሩ መሆን አለባቸው፣

11.ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር ለሚገኙ ሰራተኞች ስለቫይረሱ አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች ላይ ቢያንስ እጅ ለመታጠብ የሚያስችል ውሃና ሳሙና ማዘጋጀት ፣ በተቻለ መጠን ሌሎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

12.ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በአንድ ክፍል ውስጥ፣ በአንድ መስሪያ ቦታ ወይም በአንድ ትራንስፖርት ውስጥ ተጨናንቀውና አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በማያስችል መልኩ እንዳይሰሩ ለማድረግ አስፈላጊውን ፈረቃ ማመቻቸት፤ ሰራተኞቹ ቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን ሁኔታ ወይም እረፍት በመውሰድ ስራ ቦታ እንዳይመጡ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤

13.ማንኘውም የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግስት ተቋምና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚስተዳድር የግል ድርጅት ሰራተኞቹ ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ ትራንስፖርት መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ በስራ ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤

14.ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ማረሚያ ቤት ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤

15 ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፤

16.ማንኛውም አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፣ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ አግለግሎት እንዲሰጥ፣ አገልግሎቱን እንዲያሰፋ፣ ምርት እንዲያመርት፣ የሚያመርተውን ምርት መጠን እንዲጨምር፣ አዲስ ምርት አይነት እንዲያመርት ወይም ምርቱን መንግስት በሚወስነው ተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግስት፣ ለሾማቾች ወይም ለህብረት ስራ ማህበራት እንዲሸጥ በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ማድረግ አለበት።

17.ሆቴሎች ለደንበኞቻቸው አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የእጅ መታጠቢያ ውሀና ሳሙና የማቅረብ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ የሆቴሉ ተጠቃሚዎችም እጃቸውን መታጠባቸውንና አስፈላጊውን ንፅህና አጠባበቅ ስርአት ተግባራዊ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ እንዲሁም ደንበኞች ከተጠቀሙ በኋላ የተገለገሉባቸውን ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮችና ሌሎች እቃዎች የማከም ግዴታ አለባቸው፣

18.ማንኛውም በስራ ላይ ያለ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

https://telegram.me/lawsocieties
This is valid all year round but, especially in times of crisis like #Covid19 one, we need to rely only on accurate, up-to-date information. Avoid spreading rumors and when in doubt, check the source you are getting the information from.

Follow accurate public health advice from the World Health Organization (WHO) or your local health authority.

https://telegram.me/TransparencyEthiopia
YES I CAN:
ሰላም ውድ የ ኣለ ቤተሰቦች ከ ጉንበት 3-6 እንዲሰጥ ተይዞለት የነበረው ሃገር ኣቀፍ የ ሕግ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከ ከፍተኛ ኣመራር አንዳ ኣረጋገጥኩት ላልተወሰነ ግዜ ተራዝማል በምሆንም ኣሁንም ማለትም ቡሃላ ሚሰጠን ግዜ ስለ ማይታወቅ አንደ ለመድነው ግዜ ሰጠን አንድናነብ ያው ለ ፊልም ግዜ ካለን ለ ሶሻል ሚድያ ግዜ ካለን ለ ማንበብም ግዜ አንስጠው ዝም ከማለት ይሻላል ስለዚ አንደ ወትሮ በደንብ እናንብብ #ኣሁን ነው ቤታችን ቁጭብለን የ ሰው ልጅ ምናተርፈው በታችን እንቀመጥ #ፈጣሪ የ ኣለም ህዝብ ማርልን # via ክብሮም ስዩም ባህርዳር ዪንቨርስቲ
COVID 19.docx
67 KB
የኮቪድ 19 የሥራ ቦታ ምላሽ (workplace Response) የሶስትዮሽ ፕሮቶኮል
Yeasirateya kenesa.docx
5.3 MB
የሠራተኛ ቅነሳ ስለሚፈፀምበት ሥነ ስርዓት
የወጣ መመሪያ
#Ethiopia : በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ ያለፈን ሰው እንዴትና የት እንደሚቀበር እንዲሁም በቀብሩ ላይ የሚገኙትን ዘመዶች ብዛት የሚወስነው መንግስት ነው::
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
Information from patients recovering from the Hospital ...

@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties

Every day we are there:

1. Take Vit C-1000
2. Vitamin E
3. 10:00 - 11:00 sunlight for 15-20 minutes.
4. Egg one item
5. Take a rest / get a 7-8 hour min
6. Drink 1.5 L of water daily and every meal should be warm (not cold).
That's what we do at the hospital.

This is to tell all of us that the pH for the coronary virus varies from 5.5 to 8.5

What we need to do, to defeat the coronary virus, is to consume more alkaline foods above the virus's pH level.

Some of them are:
* Lemon - 9.9 pH
* Lime - 8.2 pH
* Avocados - 15.6 pH
* Garlic - 13.2 pH *
* Mango - 8.7pH
* Tangerine - 8.5pH
* Pineapple - 12.7 pH
* Dandelion - 22.7 pH
* Orange - 9.2 pH

How did you know you had a coronavirus?

1. Itching in the throat
2. Dry throat
3. Dry cough
4. High temperature
5. Shortness of breath
6. Loss of smell and taste

So when you pay attention to these things quickly take warm water with lemon and drink.

Do not keep this information to yourself. Give to all your family and friends. Be careful
https://telegram.me/lawsocieties
ከሆስፒታል፤


 1. ቫይታሚን ሲ-1000 ውሰዱ
 2. ቫይታሚን ኢ
 3.የፀሐይ ብርሃን ለ 15-20 ደቂቃዎች ፡፡
 4. እንቁላል አንድ
 5. እረፍት ይውሰዱ / 7-8 ሰዓት ያግኙ
 6. በየቀኑ 1.5 ሊትር ውሃ ይጠጡ እና እያንዳንዱ ምግብ ሞቅ (ቀዝቃዛ መሆን የለበትም)።
 በሆስፒታል ውስጥ የምናደርገው ይህን ነው ፡፡

 ይህ ለከባድ የደም ቫይረስ ፒኤች ከ 5.5 እስከ 8.5 እንደሚለያይ ለሁላችን ለመንገር ነው

 የደም ቧንቧ በሽታን ለማሸነፍ ምን ማድረግ አለብን ከቫይረሱ ፒኤች ደረጃ በላይ ብዙ የአልካላይን ምግቦችን መመገብ ነው ፡፡

 ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ
 * ሎሚ - 9.9 ፒኤች
 * ፟ ኖራ ሎሚ - 8.2 ፒኤች
 * አቮካዶ - 15.6 ፒኤች
 * ነጭ ሽንኩርት - 13.2 ፒኤች *
 * ማንጎ - 8.7 ፒኤች
 * መንደሪን - 8.5 ፒኤች
 * አናናስ - 12.7 ፒኤች
 * ዳንድልዮን - 22.7 ፒኤች
 * ብርቱካን - 9.2 ፒኤች

 ኮሮናቫይረስ እንዳለብዎ እንዴት ያውቃሉ?

 1. በጉሮሮ ውስጥ ማሳከክ
 2. ደረቅ ጉሮሮ
 3. ደረቅ ሳል
 4. ከፍተኛ ሙቀት
 5. የትንፋሽ እጥረት
 6. ማሽተት እና ጣዕም ማጣት

 ስለዚህ ለእነዚህ ነገሮች ትኩረት በሚሰጡበት ጊዜ በፍጥነት በሞቀ ውሀ ሎሚ ይጠጡ።

 ይህንን መረጃ ለራስዎ አያስቀምጡ ፡፡ ለሁሉም ቤተሰብዎ እና ጓደኞችዎ ይስጡ ፡፡ ተጥንቀቅ
https://telegram.me/lawsocieties
#Ethiopia : ሜሴንጀር ላይ የሆነ በንግድ ባንክ ስም የተከፈተ የሚመስል የቴሌግራም ቻነል ጆይን ካደረጋችሁና ለ50 ሰው ሼር ካደረጋችሁ 10 ሺህ ብር ሽልማት አለው የሚል ነገር እየተሰራጨ ነው። ለእኔም ብዙ 10 ሺህ ሽልማት ፈላጊወች ልከውልኛል። ለማንኛውም የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በስሜ የሚነግዱ አጭበርባሪወች ስለሆኑ እንዳትሰሟቸው፣ ጆይንም አታድርጓቸው፣ ለሌላ ሰውም አታሰራጩላቸው የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል። አጭበርባሪወቹን ግን ብዙ የቴሌግራም ተከታይ ለማግኘት የሄዱበት የብልጠትና የማጭበርበር የሀሳብ ፈጠራ ሌላ ልማታዊ ቦታ ላይም ቢያውሉት ለአገራችን ትራንስፎርሜሽን ትልቅ ድርሻ ይኖረው ነበር።

Via Nathnael