አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
From tomorrow onwards there are new communication regulations.

All calls are recorded

All phone call recordings saved

WhatsApp is monitored

Twitter is monitored

Facebook is monitored

All social media and forums are monitored

Inform those who do not know.

Your devices are connected to ministry systems.

Take care not to send unnecessary messages

Inform your children, Relatives and friends about this to take care

​​Don't forward any posts or videos etc., you receive regarding politics/present situation about Government/PM etc.​​

Police have put out a notification termed ..Cyber Crime ... and action will be taken...just don't delete ...

Inform your friends & others too.

Writing or forwarding any msg on any political & religious debate is an offence now....arrest without warrant...

This is very serious, plz let it be known to all our groups and individual members as group admin can b in deep trouble.

Take care not to send unnecessary messages.
Inform everyone about this to take care.

Please share it; it's very much true. Groups please be careful.
👍1
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ማለት ነው? 🇪🇹

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት መንግስት በ መደበኛው ስርአት ለማከናወን የማይችላቸውን ነገሮች እንዲያከናውን ጉልበት የሚሰጠው ህገመንግስታዊ መሳሪያ ነው ፡፡ በአሁኑ ሰአት በርካታ ሀገራት በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ነዉ ያሉት : ለምሳሌ ዩናይትድ ስቴትስ : ጃፖን : ሀንጋሪ : ቡልጋሪያ : ስሎቫኪያን መመልከት ይቻላል ::

በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 93 መሰረት ፡የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የሕግ ማስከበር ሥርአት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን ፡ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት ፡ የፌደራሉ መንግስት ፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነግግ ይሆናል ፡፡ ስለሆነም አሁን በተከሰተው ወረርሽኝ የተነሳ ዛሬ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፡ በዚህ ሰአት ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን ስልጣኑም በህገ መንግስቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን ፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘ ደረጃ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው ፡፡ ቢሆን ግን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ የማይገድባቸው መብቶች ተብለው በህገ መንግስቱ የተቀመጡት 1) የኢትዮጵያ መንግስት ስያሜ ፡ ማለትም ኢፌዴሪ የሚለውን 2) ኢሰብአዊ አያያዝ መከልከሉን 3) የእኩልነት መብትን እና 4) የብሄሮች ፡ ብሄረሰቦች ፡ ህዝቦች መብት ነው ፡፡ እነዚህ ከላይ ያሉት አራቱ መብቶች መቼም ቢሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት እርምጃ የማይገደቡ መብቶች ሲሆኑ ቀጥሎ ሊገደቡ የሚችሉ መብቶችን እናያለን ፡፡

በቀጣይ ጊዜያት መንግስት የሚያወጣቸዉ ዝርዝር መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ : በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩትን ሊገደቡ የሚችሉ የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን ለመጥቀስ ያህል 1) የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃነት የመያዝና የመግለፅ መብት፡ 2) የመሰብሰብ ፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነት 3) የመደራጀት መብት 4) የመዘዋወር ነፃነት 5) የመምረጥ እና የመመረጥ መብቶች ፡ እያለ ይቀጥላል ፡፡ ባጭሩ አሁን የተከሰተውን ወረርሺኝ ለመግታት፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ታውጃል ፡ ይህ ማለት ደግሞ ፡ በህገ መንግስቱ የተረጋገጡት የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶች ለጊዜው ወረርሽኙን ለመግታት ሲባል እንደ አስፈላጊነቱ ሊገደቡ ይችላሉ ማለት ነው ፡፡

ስለሆነም በዚህ ሰአት መንግስት በቀጣይ የሚያወጣቸዉን መመሪያዎች ማክበር እና ከፀጥታ አካላት ጋር ተናቦ በቅንጅት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል እንጂ መብቴ ነዉ ብሎ መድረቅ አያስፈልግም ምክንያቱም መብቶች ሊገደቡ ስለሚችሉ ::

በተረፈ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን ::

ምንጭ;
ከህግ አገልግሎት /legal service ተገኘ
https://telegram.me/lawsocieties
ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፅሁፍ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከለው ቀርቧል፦

1) የአዋጁ አስፈላጊነት እና አላማ
🔴🔴🔴የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 🔴🔴

የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፅሁፍ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከለው ቀርቧል፦

1) የአዋጁ አስፈላጊነት እና አላማ

#Ethiopia : የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት ለሃገር እና ለህዝብ አደጋ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የሚተዳደርበትን ሥርዓት በአንቀጽ 93 ላይ አስቀምጧል። በአንቀጽ 93 (1) (ሀ) መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ መነሻ ከሚሆኑ ሁኔታዎች አንዱ “የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት” የሚል ነው።የኮቪድ-19 የሕዝብን ጤንነት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ እንደሆነ ዕሙን ነው።

ይህን ወረርሽኝ ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ውጤታማ ለማድረግ ደግሞ ከተለመደው አሠራር እና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ወጥቶ በልዩ ሁኔታ መንቀሳቀስ ይጠይቃል። አዋጁ መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን በሚወስድበት ጊዜ የተሻለ ነጻነት እና አቅም እንዲኖረው፣ የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት እንዲቻል በማሰብ ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ከሕግ አንጻር አስቻይ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ፤ የዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላማ፣ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተጓዳኝ ተግዳሮቶችን በተመለከተ አስፈላጊውን እርምጃዎች የመደንገግ ስልጣን ለስራ አስፈጻሚው የመንግስት አካል መስጠት ነው። እነዚህ አላማዎች ያሉት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዛሬው እለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆዋል።

2) የአዋጁይዘት

የአዋጁ አንኳር ይዘት በአዋጁ አንቀጽ 4(1) የተለፀው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወረርሽኙ ሥርጭት እያስከተለ ያለውንና ሊያስከትል የሚችለውን ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳቶች ለመቀነስ እና ለመከላከል ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚያወጣቸው ደንቦች የመብት እገዳዎችንና፣ እርምጃዎችን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 (4) (ሀ)እና (ለ) መሰረት ለመደንገግ የተሰጠው ስልጣን ነው። ይህም ማለት የወረርሽኙ ሥርጭት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ወይም ለመከላከል እንደሁኔታው እና እንደአስፈላጊነቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማወጣት የመብት እገዳዎችን ማድረግ እና እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።

እነዚህን የመብት ገደቦች እና እርምጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወስጥ ዘርዝሮ ማስቀመጥ ያልተቻለው አስፈላጊ የሚሆኑት ገደቦች እና እርምጃዎች ከጊዜ ጊዜ እና በሃገሪቱ ውስጥ ከቦታ ቦታም ሊለያዩ ስለሚችሉ ነው። እንደወረርሽኙ ስርጭት የስፋት አድማስ፣ እንደሚያስከትለው ጉዳት አስፈላጊ የሆኑት ገደቦች እና እርምጃዎች ሊለዋወጡ ይችላሉ።

አዋጁ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ ውስጥ ሁሉ የሚያስፈልጉት ክልከላዎች እና መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ተለዋዋጭነት ሊኖራቸው ስለሚችል፣ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት፣ በየጊዜው ያለውን ሁኔታ በመገምገም እና ስለቫይረሱ ስርጭትም ሆነ ባህሪ የሚገኙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን፣ የህዝብ ጤና ባለሞያዎችን ምክር ከግምት በማስገባት የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ያስልፈጋል። ይህን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ዝርዝር እና ቋሚ የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን ከመዘርዘር ይልቅ እንዳስፈላጊነቱ ተለዋዋጭ (flexible) በሆነ ሁኔታ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማውጣት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን እንዲደነግግ አዋጁ ስልጣን ይሰጠዋል። አዋጁ በዚህ መልክ የተቀረፀው አስፈላጊ የሆኑ የመብት እገዳዎች እና እርምጃዎች ዝርዝር ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ፣ ከቦታ ቦታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ፣ ተጨባጭ ሁኔታውን ከግምት በማስገባት፣ አስፈላጊ እና ተመጣጣኝ የሆነ እገዳ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ነው። ይህ አይነት አካሄድ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በሕገ-መንግሥታዊ መብቶችም ላይ ሊደርስ የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አስፈላጊ ከሆነው መጠን ያላለፈ እንዲሆን ለማድረግ ይረዳል። በደፈናው ከሚጣሉ ገደቦች ይልቅ፣ በየጊዜው ያለውን ሁኔታ እና ስጋት ከግምት በማስገባት፣ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲህ ያለ ማዕቀፍ ተመራጭ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ደንቦችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማንኛውም ሁኔታ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 (4) (ሐ) ልዩ ጥበቃ የተደረገላቸውን ድንጋጌዎች የሚገድቡ ሊሆኑ አይችሉም። ከዚህ በተጨማሪ በአለም አቀፍ ህግ እና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ በተለመደው አሰራር መሰረት ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው የ “አስፈላጊነት” እና “ተመጣጣኝነት” መርሆዎችም የሚንስትሮች ምክር ቤትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስልጣን የሚገድቡ አጠቅላይ መርህዎች ተደርገው በታሳቢነት የሚወሰዱ ናቸው።

• አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስፈጸም ኃላፊነትን በተመለከት የመብት እገዳዎቹና እርምጃዎቹ ዝርዝር ሁኔታ በየጊዜው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚሁ ዓላማ በሚያቋቁመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እየተወሰነ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግያመላክታል።

• አዋጁ ማንኛውም ሰው በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በሕግ አስከባሪ አካላት ወይም ሌላ በሕግ ሥልጣን ባለው አካል የሚሠጥ ሕጋዊ ትዕዛዝ እና መመሪያን የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል። እንዲሁም የፌደራል፣ የክልል የሕግ አስከባሪ ተቋማት እና ሌሎች በሕግ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት ተመጣጣኝ ኃይል በመጠቀም በአዋጁ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ይፋ የተደረጉ የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን የማስፈጸም ስልጣን እንደሚኖራቸው ይደነግጋል።

• አንቀጽ 6 በወንጀል ሕግ የተካተቱ አግባብነት ያላቸው የወንጀል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣ እርምጃዎችን፣ የተሰጠ መመሪያ ወይም ትዕዛዝን ሆን ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሶስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር እስከ ሁለት መቶ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል ያስቀምጣል።

• አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አንቀጽ 7 በአቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የሚደነገጉ የመብት እገዳዎችና እርምጃዎች ዝርዝር ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እና ሕግ የማስረፅ ሃላፊነት በተጣለበት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በስፋት ለሕዝብ ተደራሽ በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን መገለጽ እንዳለባቸው ይደነግጋል። የፌደራልም ሆነ የክልል፣ እንዲሁም የግል ሚድያዎች ከዚህ ጋር የሚሰጡ ማብራሪያ እና ገለጻዎችን በተለያዩ ቁንቋዎች ለህዝብ የማድረስ ሃላፊነት እና ግዴታ አለባቸው።

• አዋጁ በመላው ሃገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ለአምስት ወራት ተፈጻሚ ይሆናል።
https://telegram.me/lawsocieties
Gone Wiz z. Wind:
hey selam nw, exitn betemelekete mn adis nger ale?
የሥራ_ውል_ለማቋረጥ_ስለሚሰጥ_ማስጠንቀቂያ

አዋጅ 1156/2011

በ አዋጁ አንቀጽ 28 በተመለከቱት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ አሠሪው ውሉ ለሚቋረጥበት ሠራተኛ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ይገደዳል:: የማስጠንቀቂያው አስፈላጊነት ሠራተኛው የሥራ ውሉ እንደሚቋረጥ አውቆ በራሱ በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እንዲችል ነው፡፡

የማስጠንቀቂያው ጊዜ የአገልግሎት ዘመን: የሥራ ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት: እንዲሁም ውሉ የሚቆይበት ጊዜ መሰረት በማድረግ ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ድረስ ይረዝማል፡፡ የአሰጣጥ ስርዓቱ በጽሑፍ ሆኖ አጥጋቢ ምክንያት ከሌለ በቀር ለሠራተኛው በእጁ መሰጠት አለበት፡፡ ማስጠንቀቂያ ያለመስጠት ውጤት በአንቀጽ 40 ከተመለከተው ክፍያ (ማለትም ከስንብት ከፍያ) በተጨማሪ ለሠራተኛው በማስጠንቀቂያ ጊዜ ሊከፈለው ይገባ የነበረውን ደመወዝ መክፈል እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 44 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

የማስጠንቀቂያ ጊዜን በተመለከተ እንደ ሠራተኛው የአገልግሎት ዘመን የሚለያይ ሲሆን በዚሁ መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰና፡ አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ አንድ ወር: ከአንድ ዓመት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ ሁለት ወር : ከዘጠኝ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ሦስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ የሥራ ውል በቅነሳ ምክንያት ሲቋረጥ የአገልግሎት ዘመን እና የውሉ የቆይታ ጊዜ ግምት ውስጥ ሳይገባ ለሁሉም ሠራተኛ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ አንቀፅ 35

የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ አስፈላጊነት ሠራተኛው የሥራ ውሉ እንደሚቋረጥ አውቆ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ እንደመሆኑ የአሰጣጥ ስርዓቱ አመቺና ቀላል ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር ማስጠንቀቂያው ውሉ የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶችና ውሉ የሚቋረጥበትን ቀን በመግለጽ በጽሑፍ ተዘጋጅቶ ለሠራተኛው በእጁ መሰጠት ያለበት ሲሆን ሠራተኛው በአካል ካልተገኘ ወይም ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነ ለ10 ተከታታይ ቀናት ግልጽ በሆነ የማስታወቂያ ሰሌዳ መለጠፍ ይኖርበታል፡፡ አንቀፅ 34

#የሥራ_ውል_በማስጠንቀቂያ_የሚቋረጥባቸው_ምክንያቶች_በአንቀጽ_28_ስር_ተዘርዝረዋል፡፡

እነሱም
1) ሠራተኛው የተመደበበትን ሥራ ለማከናወን ችሎታው ቀንሶ ሲገኝ ወይም የሥራ ችሎታውን ለማሻሻል አሠሪው ያዘጋጀለትን የስልጠና ዕድል ባለመቀበሉ ምክንያት ሲሰራ የቆየውን ሥራ ለመቀጠል የሥራ ችሎታ የሌለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ስልጠና ከተሰጠው በኋላ አስፈላጊውን አዲስ የሥራ ችሎታ ለመቅሰም የማይችል ሲሆን፤
2) ሠራተኛው በጤንነት መታወክ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት በሥራ ውሉ የተጣለበትን ግዴታ ለመፈጸም ለዘለቄታው የማይችል ሆኖ ሲገኝ
3) ድርጅቱ ወደሌላ ቦታ ሲዛወር ሠራተኛው ወደ አዲሱ ቦታ ተዛውሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፤
4) ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲሰረዝና ሠራተኛውን ወደሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ፡፡
5) ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
6) አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
7) የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸዉ።

ከህግ አገልግሎት /legal service ተገኘ
https://telegram.me/lawsocieties
👍1
ስለ ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ትንሽ ነጥብ ለማንሳት ያክል፡

የስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ብዙ ዓይነት ነው። ኣንዱ ከሰላም ና መረጋጋት የሚያውክ ብጥብጥ ጦርነት ወዘተ ሲኖር የሚታወጅ public orderን ለማስጠበቅ የሚታወጅ ሲሆን። በFDRE ህገመንግስት መሰረት ለ Federal መንግስት የተሰጠ ስልጣን ነው።ሌላው ground ደግሞ የ ህዝቡ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ደህንነት በተፈጥሮ ኣደጋ ወይም በወረርሽኝ በሽታዎች ወዘተ ምክንያት ኣደጋ ላይ ሲወድቅ ። ይህ ለፌደራል መንግስት ና ለክልሎች በጋራ የተሰጠ ስልጣን ነው። እዚ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ሁለቱም መንግስታት (የ ፌደራል ና የክልል ) በጉዳዩ ላይ ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ያወጡ እንደሆኑ የህገቹ ተፈፃሚነት እንዴት ይሆናል የሚል ነው።ኣንዳንድ ሀገሮች ጉዳዩን ለመፍታት በሕገመንግስታቸው ያስቀመጡት conflict of law rule ኣላቸው።ለምሳሌ Federal supermacy clause ኣንዱ ነው።የሁለቱም መንግስታት ህግ የተጋጩ እንደሆነ ወይም በክልሎች ወጥቶ የነበሩ ህጎች በ ፌደረሉ ህግ ከተሸፈኑ የፌደራል መንግስት ሕግ የክልሎቹ ተክቶ ተፈፃሚ ይሆናል። ይህ እንዲሆን ግን የፌደራል ኣዋጁ ራሱ ሕገመንግስታዊ መሆን ኣለበት። በሌሎች ሕገመንግስቶች የምናገኘው ሌላው መንገድ ደግሞ ጉዳዩ በፖለቲካ ውይይት ና ሂደት በስምምነት እንዲፈታ ክፍት ኣድርጎ መተው ነው። የእኛ ህገመንግስት የተከተለው approach ሁለተኛው ነው። ህገመንግስቱ የ constitutional supermacy እንጂ የ Federal supermacy ኣላስቀመጠም። የክልል ና የ ፌደራል መንግስታት በተሰጣቸው ስልጣን ልክ ተከባብሮ ና ተባብሮ የመስራት ሕገመንግስታዊ ግዴታ ኣለባቸው።የፌደራል መንግስት የክልሎች ስልጣን ማክበር ኣለበት።የክልል መንግስታትም የፌደራል መንግስት ስልጣን ማክበር ኣለባቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሁለቱም መንግስታት በጋራ የሚሰሩት ስራ ከሆነ ወይም ሁለቱን ሚና ለመጫወት ስልጣኑ ና ፍላጉት ያላቸው ከሆነ፣ የጋራ ፎሮም ወይም ሌላ የሚይስማማ መንገድ በመፍጠር እየተስማሙ ና እየተናበቡ በትብብር ና በመከባበር መንፈስ ስራቸው መስራት ይችላሉ።ኣንዱ የሚችለው ሰርቶ ስራው ከኣቅሙ በላይ ሲሆን ሌላው እንዲያግዘው ሊጠይቅ ይችላል። የህዝቡ ችግር ከመቅረፍ ኣንፃር የተሸላው የትኛው ነው? ለህዝቡ ቅርብ ና ተደራሽ የሆነውስ የትኛው ነው ወዘተ በሚል የስራ ክፍፍል ለማድረግ ሊስማሙ ይችላሉ። ወይ ደግሞ ሁለቱም በሚያወጥዋቸው ህጎች የእርሰበርስ መናበብ ሊፈጥሩ ይችላሉ። በቀጥታ የሚነጋገሩበት የጋራ ፎሮም ባይፈጥሩም በሚያወጥዋቸው ህጎች tacitly ሊስማሙ ይችላሉ።ይህ ሲሆን በስምምነት የሚፈፀም ነው የሚሆነው። ከዚ ኣንፃር ከነገው የ HPR ምን ይጠበቃል። እንደኔ፣
ከነገው ኣስቾኳይ ግዜ ኣዋጅ የሚጠበቀው፡
1. ከክልሎች በጋራ ና በትብብር የሚሰራ የኮሮና ቫይረስ የመከለከል ና መቆጠጠር ኣስተባባሩ ኮሚቴ ማቋቋም። ኮሚቴው ከክክሎች ጋር የ መረጃ ልውውጥ የሚያካይድ ና ክልሎች በሚጠይቁት ጥያቄ መሰርርት የ ሎጂስቲክስ supply የሚያቀርብ ና የሚያስተባብር ይሆናል።
2. በሁሉም ክልሎች ተግባረራዊ እንዲደረጉ የሚፈለጉ ጥቅል የ ኮሮና መከላከል ስታንዳርዶች ማስቀመመጥ። በሌላ ኣባባል፣ ሁሉም የሚያስማሙ የ WHO guidelineዎች ወደ ጥቅል የህግ ማእቀፍ መቀየር።
3. የተቀመጡ ስታንዳርዶች ክልሎች የself determination መብታቸው ና ነፃነታቸው በጠበቀ መልኩ በራሳቸው ኣኳሃን የመወሰን ና የማስፈፀም ህገመንግስታዊ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በግልፅ ቛንቃ መግለፅ። Anti commandering clause.
3. ቫይሮሱን ለመከላከል ና ለመቆጣጠር የሚያስችል በቅድምያ ለክልሎች የሚሰጥ በጀት መመደብ
4. ቫይረሱን መከለከል ና መቆጣጠር የቻለ ክልል የሚሰጠው positive incentive ማስቀመጥ። በፌደራል መንግስት የሚሰጥ Award grant or performance grant ማስቀመጥ።
5.ቫይሮስን መከለከል ያልቻለ ና የህዝቡን ጤንነት ኣደጋ ላይ የጣለ ክልል ከፌደራል መንግስት የሚያጣው ነገር -negative incentive ማስቀመጥ።

ባለፈው ሳምንት ጓደኛየ Endalk G. Negash ለ VOA የሰጠው ቃለመጠይቅ ኣዳምጬዋለህ።በጣም ኣሪፍ ቃለመጠይቅ ነበር። ያነሰሀቸው ብዙ ነጥቦች ተስማምቶኛል። ከconcurrent power የሚመነጭ ግጭት ለመፍታት ኣስመልክቶ በሰጠሀው የመፍትሄ ሓሳብ ላይ ግን ኣልስማማም። Federal supermacy ውጤታማ የሚሆነው የፖለቲካ climateቱ ጤናማ ቢሆን ነበር። የክልል ና የፌደራል መንግታት የፖለቲካ ልዪነት ና ውጥረት ባይኖራቸው ጉዳዩ ትዝ የሚለው ስለማይኖር ችግር ኣይፈጥርም ነበር።ኣሁን ግን የፌደራል መንግስት ና የክልል መንግስት በዓይነቁራኛ የሚጠባበቁበት ግዜ ነው። በዚ ግዜ ሊሰራ የሚችለው በሕገመንግስቱ የተቀመጠው mutual respect clause መሰረት በማድረግ በመከባበር ና በትብብር መስራት ነው። With regards!
via gebreabzgi / w
lecturer at Mekele University
https://telegram.me/lawsocieties
Meaza Ashenafi
Meaza Ashenafi
New Doc 2020-04-10 17.16.35.My Docs.pdf
194.4 KB
ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ በPDF

https://telegram.me/lawsocieties
🔴በኮሮና እዳንያዝ የሚከላከል ባህላዊ መዳኒት🔴

2ፍንካች ነጭ ሽንኩርት 2ዝንጅብል
1/4 ቀይ ሽንኩርት መውቀጥ
8ፍሬ ጥቁር አዝሙድ ሳይፈጭ
8ፍሬ ድንብላል ሳይፈጭ
1የሾርባ ማንኪያ ነጭ አዝሙድ ሳይፈጭ
1ሎሚ ጭማቂ በማደባለቅ በ አንድ ሊትር ውሃ መበጥበጥ እና 🔴ለ1ቀን ማሣደር ከዚያም አንድ ሊትሩን በአንድ ቀን መጠጣት
ለሚቀጥለውም ቀን በዚሁ መልክ ማዘጋጀት 🔴ለ3ቀን መጠጣት ህመሙ እንዳይዘን ይከላከላል።

ብለው በውስጥ መስመር ላኩልን ያገሬ ሰዎች እባካችሁ እንሞክረው እና እራሳችንን እንከላከል።🔴

@lawsocieties

https://telegram.me/lawsocieties
የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

* ማሳሰቢያ: ይህ ፅሁፍ ከሳምንት በፊት የተፃፈ ነው። ለመስተዳድሩ Benefit of doubt ለመስጠት 15 ቀኗ ትለፍ በሚል ሳይለጠፍ ቆይቷል።

መሪ ድርጅቱ እንደሆነ ሁሌም ፖሊስ ስቴት (police-state) ለመፍጠር የተቀባበለ ይመስለኛል። በተለይ ግራ የተጋባ ሰሞን፣ የግለሰብ ፖለቲካ የነገሰ ሰሞን እና የሐሳብ ድርቅ ሲመታው አይጣል ነው። ሁሌም የታየ ነው። ፍርሃት እና ሥጋት ያፋፋዋል፣ መዳኛውም ነው። ስለዚህ እሷን መጀን ብሎ ያለችዋን ፍርሃት ማጉላት እና ማለብ አቋራጩ መንገድ ይመስለዋል። ልንወረር ነው ከሰመች እና ኮሮና መጣልን። የሚያሳዝነው አሁን አሁን መድህን ከርዕዮተ–አለም ይልቅ ከስቴድየም ማግኘት ጀምሯል።

የሚገርመኝ አክቲቭ/ንቁ ነኝ የሚለው ልሂቅ ነው፤ ለመጠየቅ ሳይሆን ለማመን የተቀባበለው ማለቴ ነው። የማይናቅ ቁጥር ያለው ዝም ያለ ልሂቅ እንዳለ ሳይረሳ። ሶሻል ሚዲያም ከድሮው የስብሰባ አገዛዝ የተለየ አይደለም። በሆነ አክቲቪስት/ምሁር በኩል ሃሳቡን ያሰርጋል ድርጅቱ፣ ልሂቁ የራሱ ሃሳብ እንዲመስለው ይደረጋል፣ ከዛ ደግፎ ይከራከራል። በዛ ላይ ቀድሞ በደንብ የተሰራው የፌደራል V. ትግራይ "ግብግብ" ለአስቸኳይ አዋጅ ተቀባይነት ጠቅሟል። ፌደራሉ የማይረባ እና ሃላፊነት የጎደለው ነው የሚለውን (አይሆንም ማለቴ አይደለም) ለማስረገጥ ትግራይ ቀድማ እርምጃ መውሰድ አለባት ይልሃል። በዛ ላይ ኮሮና ነው፣ አስበው። (አለምን ያንቀጠቀጠ፣ ያውም ጂ7ቶችን፣ ስለዚህ እኛን ካገኘንማ ይጨርሰናል 😊 አዎን አውስትራሊያ እሳት ቃጠሎ ጎድቷታል፣ ውይ እኛ ጋር ቢመጣ ደግሞ አለቀልን፣ የእሳት አደጋ መኪና አለን? 😃 ) ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ ...

እስኪ ጉዳዩ የአመፅና ብጥብጥ ነው እንበል። መቼ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው? ሶስት፣ አራት አመት በፊት ስንሰልቀው ስንወቅጠው ነበር እና አላሰለችህም። ብጥብጡ ከተለመደው የፖሊስ እና ፀጥታ ኃይል እና አሰራር በላይ ሲሆን ነው። አለቀ። ታድያ ኮሮና በአገራችን ብሎም በትግራይ እንደዛ አይነት ደረጃ ላይ ደርሷል ወይ ብለን መጠየቅ ነው። ስንት ቆሰለ፣ ሞተ፣ ፖሊስን ጨምሮ ትላለህ ለብጥብጥ። ኮሮናም የራሱ አውድ/ኮንቴክስት አለው። መንግስት ቴስት አድርጎ ያመጣው ማስረጃ አለ? እሱን የምታረጋግጥበት ገለልተኛ መንገድ መፈለጉን እንርሳው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ካለበት ደግሞ ከላይ በጠየቅነው ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ምን ምን ስልጣንን ያካተተ ይሁን? በአገርም በክልልም ስርጭቱ ምን ያህል ነው? በእግዜር በአገር 29 ሆኖ 2 ተርፈዋል። (አንተ ዱቅ ብለህ በኮሮና ቻናል፣ ማለትም ሲኤንኤን ኒውዮርክ የአስቸኳይ ጊዜ ይታወጅ አይታወጅ የሚል ክርክር ታያለህ፣ የኛ ሚዲያም ራሱ ሲኤንኤን ሆኗል) የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ የሞቱ ሰዎች ቁጥር፣ መተላለፊያ መንገድ ወዘተ ታይቶ መንግሥት ለዛ ሲባል ይሄ ይሄ ስልጣን ይኑረው ይባላል። ይሄ ይሄ አያስፈልግም ምክንያቱም ከመረጃው ጋር ወይ ከቁጥሮች ጋር አይሄድም ይባላል። ለምሳሌ አንድም የተያዘ ሰው መኖሩን አልሰማንም አላየንም። ምርመራ ትናንት ተጀመረ ተባለ፣ ለምን ከዚያ በኋላ ስለ አዋጅ አንነጋገርም ነበር? ራንደም ምርመራ ማድረግ ይቻላልኮ፣ ሳምፕል ፖፑሌሽን ሳይዝ ወስደህ። ከዛ ባለው ስጋት መሰረት አስቸኳይ ጊዜ ይወራል፣ ከተስማማህበት ደግሞ ስለሚገባው ስልጣን ይወራል። ስልጣኑም በዛው በስጋቱ መሰረት ይወሰናል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የክልሉ ድንበር (entry point) ላይ ብቻ ሊያተኩር ይችላል፣ በኔ እምነት ከዛ ማለፍ የለበትም ነበር። ወይ "እንደ አሁኑ" ከተማ ገጠር ሊሆን ይችላል፣ ክላስተር ለይተን ማድረግም ይቻላል፣ ሙሉ በሙሉ ቤት ቅር ሊሆንም ይችላል (አሁን እራሱ እየፎከረ ነው ሊቀመንበሩ)። የትኛው ደረጃ እንደ ታወጀ እየው እስኪ በትግራይ? ሱቅህ ውስጥ ገብቶ ፍሪጅ ያሽግልሃል። በየቀኑም ስልጣኑም እየጨመረ ነው። እንዴት? በምን መሰረት? እንደ ህፃን ሓንጉጉ ስለተባለ ፈርተን እናውጃለን? እርምጃችን ከቻይና ጋር ተመሳስሎ፣ በበሽታ የተያዘ ሰው እንኳን የለንም።

እንበልና የአብይ መንግስት ሲዳማ ላይ ወይ ሶማሌ ላይ አስቸኳይ ጊዜ ቢያውጅ እንዴት ነበር የምትከራከረው? የኢፌዴሪ ህገመንግስት ምነው ተረሳ፣ ከአድማስ ባሻገር ብቻ ነው የሚታየን? አሁን ደሞ ሌሎች ክልሎች (ማለቴ ገዥ ፓርቲዎች) የትግራይን ፈለግ እየተከተሉ ነው 😔 በነበረው ትርክት ከሄድን ይሄን እድል ተጠቅሞ አስቸኳይ ጊዜ ያውጃል ብለን ምንጠብቀው ዶር አብይ ነበር እኮ 😃

ወደ መሬት ስንወርድ ደሞ እዚ ሰፈር ይታወጅ የሚለው፣ የሚያውጀው፣ የሚፈፅመው ሁሉም ደሞዝተኛ ነው። እሱ ምን አለበት? ቤት ተዘግቶብህ፣ ቢዝነስ ቆሞብህ፣ መኪና ቆሞብህ፣ ሥራ ከነደሞዙ ቆሞብህ አላየህም። ያውም የኪራይ ስራ። በዛ ኪራይ–ቤት ሰርቶ ባገኘው የመኖርያ ቤቱን ኪራይ ከፍሎ ስንት ቤተሰብ የሚያስተዳድረው ስንት ነው? አውቶቡስ፣ ሚኒባስ ስንት ነው? ደግሞ ያንን የደደቢት ብድር የሚከፍለውስ? የባንክ ብድር ያለበት? የንግድ ፈቃድ ልዩነት (ቁርስ ቤት ብሎ ቡና አብሮ የሚሸጡ፣ ቁርስና ኮፊ ሐውስ የሚል፣ ኮፊ ሐውስ ብሎ ቁርስም ሲሸጡ የነበሩ) አስገራሚ የኑሮ ደረጃ ልዩነት ፈጥሯል። የገጠሩን ህዝብ ተወው፣ ድሮስ ሁሉም ለራሱ ፖለቲካ ሲል ያነሳዋል እንጂ ማን ትዝ ብሎት? ህዝብ እዬዬ እያለ ነው። ከማማህ ላይ ውረድ እና እየው፣ ስማው። ተከራከርለት። ልክ የፌዴራሉን መንግስት እና ፓርቲ እንደምትጠይቀው እና እንደምትሞግተው የራስህንም ክልል መንግስት እና ፓርቲ ጠይቅ። ሞግት።

* ይህ ፅሁፍ ኮሮናን "ዝም ብሎ በሽታ ነው፣ አያሰጋም እያለ ነው" ብለህ አትውሰደው። አታምታታ። ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጉዳይ ነው።

* ኮሮናን ለመከላከል እጃችንን ቶሎ ቶሎ እንታጠብ፣ ንክኪ እናስወግድ። ሰው በዛ ባለበት ቦታ አፍና አፍንጫችን ላይ መሸፈኛ እናድርግ።
via ሀሰን ሙሀመድ
https://telegram.me/lawsocieties
Mathias:
Hyyy ale.. do u have info about exit exam of zis year.. pleas share if any
FSC decided files.pdf
5 MB
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በከፊል ዝግ ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከመጋቢት 11- 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ችሎቶች በቀረቡ መዝገቦች ላይ የተሰጡ ውሳኔዎች የሚገልጽ መረጃ እንዲህ ቀርቧል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
በችሎቶች የተሰጡ ውሳኔዎች Table.pdf
160.7 KB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽንን ለመከላከል በከፊል ዝግ ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመጋቢት 11 - 28/2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ችሎቶች በቀረቡ መዝገቦች ላይ የተሰጡ ውሳኔዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡