የሥራ_ውል_ለማቋረጥ_ስለሚሰጥ_ማስጠንቀቂያ
አዋጅ 1156/2011
በ አዋጁ አንቀጽ 28 በተመለከቱት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ አሠሪው ውሉ ለሚቋረጥበት ሠራተኛ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ይገደዳል:: የማስጠንቀቂያው አስፈላጊነት ሠራተኛው የሥራ ውሉ እንደሚቋረጥ አውቆ በራሱ በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እንዲችል ነው፡፡
የማስጠንቀቂያው ጊዜ የአገልግሎት ዘመን: የሥራ ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት: እንዲሁም ውሉ የሚቆይበት ጊዜ መሰረት በማድረግ ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር ድረስ ይረዝማል፡፡ የአሰጣጥ ስርዓቱ በጽሑፍ ሆኖ አጥጋቢ ምክንያት ከሌለ በቀር ለሠራተኛው በእጁ መሰጠት አለበት፡፡ ማስጠንቀቂያ ያለመስጠት ውጤት በአንቀጽ 40 ከተመለከተው ክፍያ (ማለትም ከስንብት ከፍያ) በተጨማሪ ለሠራተኛው በማስጠንቀቂያ ጊዜ ሊከፈለው ይገባ የነበረውን ደመወዝ መክፈል እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 44 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የማስጠንቀቂያ ጊዜን በተመለከተ እንደ ሠራተኛው የአገልግሎት ዘመን የሚለያይ ሲሆን በዚሁ መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰና፡ አንድ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ አንድ ወር: ከአንድ ዓመት እስከ ዘጠኝ ዓመት ያገለገለ ሠራተኛ ሁለት ወር : ከዘጠኝ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ሦስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ የሥራ ውል በቅነሳ ምክንያት ሲቋረጥ የአገልግሎት ዘመን እና የውሉ የቆይታ ጊዜ ግምት ውስጥ ሳይገባ ለሁሉም ሠራተኛ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡ አንቀፅ 35
የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ አስፈላጊነት ሠራተኛው የሥራ ውሉ እንደሚቋረጥ አውቆ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ እንደመሆኑ የአሰጣጥ ስርዓቱ አመቺና ቀላል ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር ማስጠንቀቂያው ውሉ የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶችና ውሉ የሚቋረጥበትን ቀን በመግለጽ በጽሑፍ ተዘጋጅቶ ለሠራተኛው በእጁ መሰጠት ያለበት ሲሆን ሠራተኛው በአካል ካልተገኘ ወይም ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነ ለ10 ተከታታይ ቀናት ግልጽ በሆነ የማስታወቂያ ሰሌዳ መለጠፍ ይኖርበታል፡፡ አንቀፅ 34
#የሥራ_ውል_በማስጠንቀቂያ_የሚቋረጥባቸው_ምክንያቶች_በአንቀጽ_28_ስር_ተዘርዝረዋል፡፡
እነሱም
1) ሠራተኛው የተመደበበትን ሥራ ለማከናወን ችሎታው ቀንሶ ሲገኝ ወይም የሥራ ችሎታውን ለማሻሻል አሠሪው ያዘጋጀለትን የስልጠና ዕድል ባለመቀበሉ ምክንያት ሲሰራ የቆየውን ሥራ ለመቀጠል የሥራ ችሎታ የሌለው ሆኖ ሲገኝ ወይም ስልጠና ከተሰጠው በኋላ አስፈላጊውን አዲስ የሥራ ችሎታ ለመቅሰም የማይችል ሲሆን፤
2) ሠራተኛው በጤንነት መታወክ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት በሥራ ውሉ የተጣለበትን ግዴታ ለመፈጸም ለዘለቄታው የማይችል ሆኖ ሲገኝ
3) ድርጅቱ ወደሌላ ቦታ ሲዛወር ሠራተኛው ወደ አዲሱ ቦታ ተዛውሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፤
4) ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲሰረዝና ሠራተኛውን ወደሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ፡፡
5) ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
6) አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
7) የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸዉ።
ከህግ አገልግሎት /legal service ተገኘ
https://telegram.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/