አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጋብቻ በንብረት በኩል ስለሚኖረው ውጤት

አንድ ሰው ወደ ጋብቻ ከመግባቱ በፊት በላቡና በወዙ ሰርቶ ያገኘው ወይም በስጦታ ወይም በውርስ ያገኘው ሀብትና ንብረት ሊኖረው ይችላል፡፡ይህን ከትዳሩ በፊት ያገኘውን ሀብትና ንብረት ወደ ትዳር ሲገባ የግል ንብረቱ ሆነው ይቀጥላል፡፡በትዳሩ ውስጥ ከገባ በኋላም ለግሉ በስጦታም ወይም በውርስ ያገኘው ንብረት የግል ንብረት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ነገር ግን ተጋቢዎች የግል ንብረታቸው የሆነውን የጋራ ንብረት ነው በማለት ሊስማሙ ይችላሉ፡፡

ተጋቢዎች ትዳር የሚፈጽሙ እስከ መጨረሻው አብሮ ለመኖር መሆኑ እሙን ነው፡፡ በዚህ በትዳር ባሉበት ጊዚያት በግል ንብረትነት ይዘዋቸው ያሉ ንብረቶችን መሸጥ መለወጥ አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ የግል ንብረቶችና ሀብቶችን በመሸጥ ወይም በመለወጥ የሚገኘው አዲስ ንብረትና ሀብት የግል ንብረት ይሆናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ በግል ሀብት የተገዙ ወይም የተለወጡ ንብረቶች የግል ሀብትና ንብርት እንደሆኑ የግል ንብረቱ ባለቤት ለፍ/ቤት የግል ይባልልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረብ እና ማፅደቅ አለበት፡፡ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 58(1)ና(2) ይህን ይገልፃሉ፡፡

ይህ ካልሆነ ግን በአንቀጽ 62/2/ መሠረት የጋራ ንብረት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37275 ላይ በነበረው ክርክር የአመልካች የግል ንብረት የነበረ ቤት በትዳር ባሉበት ጊዜ ሽጠው በተሸጠው ገንዘብ ሌላ አዲስ ቤት ገዝተዋል ነገር ግን አመልካች አዲስ የገዙትን ቤት የግል ይባልልኝ በማለት ጥያቄ ለፍርድ ቤት ያላቀረቡ እና ያላጸደቁ በመሆነ የጋራ ንብረት ነው በማለት ወስኖል፡፡

ኑሮ በትዳር ውሰጥ የጋራ ቢሆንም ከላይ በተገለጸው መልኩ ተገቢያዎቹ የግል ንብረቶቻቸውን ይዘው በትዳር በመቀጠል ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እነዚህ ንብረቶችም የሚተዳደሩት በግል የንብረቱ ባለቤት በሆነው ሰው ነው፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 59 ላይ እያንዳንዱ ተገቢ የግል ሀብቱን እራሱን ለማስተዳደርና ገቢውንም ለመቀበል ይችላል፡፡ እንዲሁም የግል ሀብቱን ራሱ ሊያዝበት ነፃነት አለው በማለት ይገልፃል፡፡ ነገር ግን የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው አንደኛው ተገቢ የግል ንብረቱን በሙሉ ወይም በከፊል ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድርለት እና እንዲያዝበት በጋብቻ ውላቸው ሊወሰን ይችላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው ተጋቢ ሌላኛውን ተጋቢ ስለንብረቱ አስተዳደር ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህ ሲሆን ሌላኛው ተጋቢ ሲጠይቅ የይህንኑ የመስጠት ግዴታ አለበት (የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 60(2) )፡፡ እንዲሁም ከተጋቢዎቹ አንዱ የግል ንብረቱንና ሀብቱን በሙሉ ወይም በከፊል እንዲያስተዳድርለት ለሌላኛው ተጋቢ ውክልና መስጠት እንደሚችል በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 61 ላይ ተቀምጧል፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በጋብቻ ውስጥ ተጋቢዎች የግል ንብረት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ይህን ንብረት በዋንኛነት የንብረቱ ባለቤት የሚያዝበትና የሚስተዳድረው መሆኑን እንዲሁም የግል ንብረቱ ባለቤት የሆነው አንደኛው ተጋቢ ሌላኛው ተጋቢ እንዲያስተዳድርለት በጋብቻ ውል ወይም በውክልና መስጠት እንደሚችል ተረድተናል፡፡(በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ57-61)

ተጋቢዎች በትዳር ከተሳሰሩበት እለት ጀምሮ ህይወታቸውን በጋራ ሲመሩ የጋራ ንብረት ማፍራታቸው አይቀሬ ነው፡፡በጋብቻ ውላቸው ተጋቢዎች ከትዳር በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ንብረት ማድረግም ይችላሉ፡፡በጥቅሉ በትዳር ዘመናቸው ተጋቢዎች የግል ንብረትና ሀብት እንደሚኖራቸው ሁሉ የጋራ ንብረትና ሀብት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ከተሻሻለው የቤተሰብ ህጋችን አንቀጽ 57 እና 58 ለመገንዘብ የምንችለው ነገር በትዳር ውስጥ የተፈሩ ሀብቶችና ንብረቶች ፣ ለተጋቢዎቹ በጥቅሉ በውርስ ወይም በስጦታ የተሰጡአቸው ሀብትና ንብረቶች በተጨማሪም የግል ሀብትና ንብረት ተሸጦ ወይም ተለውጦ የተገኘ ንብረት ሆኖ የግል ንብረቱ ባለቤት በፍርድ ቤት ቀርቦ የግል ንብረት መሆኑን ያላጸደቃቸው ንብረቶችና ሀብቶች ሁሉ የጋራ ንብረት እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአንቀጽ 62(1) ላይ ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸውና ከግል ወይም ከጋራ ንብረታቸው የሚያገኟቸው ገቢዎች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻቸው እንደሚሆኑ ይገልፃል፡፡የግል ንብረት የግል ቢሆንም ከንብረቱ የሚገኝ ገቢ ግን የጋራ ነው፡፡

በጋብቻ ውስጥ የተጋቢዎች የጋራ ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ ተመዝግቦ ሊገኝ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ማንኛውም ንብረት በአንደኛው ተጋቢ ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን የጋራ ሀብት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡(የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 63(1) )https://t.me/lawsocieties
🇦 🇧 🇩 🇺 🇱 🇱 🇦 🇭 🇮:
Hello ale do u have info regarding z date of exit exam (Abdullahi K. Dire Dawa University)
No.he is not subjected to sentence.b/c article 23 of the fdre constitution
  I am doing my LLB thesis now,  titled with .  Setting Precedent under Article 6(1) of the CPC: Analysis of the Decision of the Cassation Division of the Federal Supreme Court-Focus on the Element of “Appeal”
.... the decree or the order from which appeal lies but from which no appeal is preferred...."( Art. 6(1) of CPC.  this is the phrase i am doing my research now.

  on this point the cassation overruled its previous decision( File NO 16624)  with new one( File NO 43821).   therefore, i  beg you to help me to share Federal  higher or lower courts decision with regard Article 6(1) of the civil procedure code(review of judgement)  which contradicts or re affirms the  current position of the cassation on the point at hand   which will help me to examine the current application of the cassation division decision by federal  higher and lower courts.
if  you have file No only tell me which court entertained it to get it the hard copy.
thank you!
alesocieties2011@gmail.com
M Boss:
If you have the new administrative proclamation draft.please send me now

Mohammed N. From AMU
Forwarded from ሕግ ቤት
እስኪ ወደ ዝርዝር እንግባ እና እንደኔ በፍጥነት ለመጀመር ያክል የሚከተሉት ስራዎች ብንሰራ፦

1. ስለ exit exam ቀን የሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ በኛ በህግ ተማሪዎች በኩል Reasonable Time fix አድርገን በቅርቡ ለሚካሄደው የኮንሰርትየም ስብሰባ ማቅረብ።

2. ባለፈው ኮንፈረንስ ላይ ከቀረቡ ጥሩ ጥሩ ልምዶች ወደየ ዩኒቨርስቲው association/ union ወስዶ ወደ ተግባር መግባት።

3. Advisory Committee የራሱ የሆነ group ፈጥሮ ከዚህ group የሚነሱ ሀሳቦች ያካተተ የማማከር ስራ ቢጀምር።

ሓበን ጠ.
ከመቀለ ዩ.
ሰላም በያላችሁበት......
ሃበን....ከመቀሌ. ዩ.
ልክ ነህ ግን፡፡ በዚህ አሁን ባለን አቋም ምንም አይነት ስራ መስራት አንችልም ብዬ አምናለሁ፡፡ከላይ ካስቀመጥካቸው ነጥቦች ውስጥ በዋናነት ባለፈው በነበርን ውይይት የልምድ ልውውጦቾን በመውሰድ የሌሉንን እንዲኖሩን ለማድረግ እንችል ይሆናል፡፡በሌሎቹ ነጥቦች ዙሪያ ግን መቅደም ያለበዥ ጉዳይ አለ ፡፡የህብረቱ የስራ እ/ሴና ይዘት በግልፅ ሊታወቅ ይገባል ለዚህም የረቂቅ ዝግጅትና መመሪያውን በመተርጎም ህጋዊ ሰውነት ሊያገኝ የሚችልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ፡፡ከመግቢያና አላማ እስከ ተፈፃሚነት ወሰን ለሚመለከተው አካል በቅድሚያ ሊደርሰውና ሊያውቀው ይገባል ፡፡የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚም የራሱ የሃላፊነት መጠንና ይዘት ሊገለፅለት ይገባል ፡፡አለበለዚያ እየገባን ምን እንስራ አይነት ልመና እንጀምራለን እንደፈለግን ያሻንን ሃሳብ እየመረጥን ቢሆንስ እያልን ለመቀጠል እንገደዳለን፡፡መመሪያና ደንብም ያስፈለገው ይህ አይነት ክፍተት እንዳይፈጠር ከተፈጠረም ለመሙላት ነው፡፡ምን እንስራ ለማለት ቅድሚያ የመዋቅራዊ አሰራሩ ከመመሪያና ደንቡጋ ተዋህዷል ወይ የሚለው መረጋገጥ አለበት፡፡ከዛም በወሰደው ሃላፊነት ልክ እንዲሰራ ይገደዳል ለተጠያቂነትም ለጠያቂነትም ምቾትን ይፈጥራል፡፡
.
.
በተደጋጋሚ እንደገለፅኩት የadvisor ኮሚቴዎችም የሰራቸው ሁኔታ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል፡፡የተሻሉ ሃሳቦችን ለማምጣት ሊታይ የሚችል ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልት ሲዘረጋ ብቻ ነው የሚሰራው፡፡ከዛ ውጪ በሃሳብ ልውውጥ ብቻ ይቀራል፡፡
.
.
በሌላ መልኩ የexit exam ጉዳይን በተመለከተ አሳሳቢ ቢሆንም መሰረታዊ መዋቅራችን ተስተካክሎ "እኛ"ብለን ለመናገር የሚያስችል አቅም ከሌለን ተፅእኖ መፍጠር አንችልም፡፡የመናገር እድሉን ስላገኘነው ብቻ ተናግረን ለማለፍ ካልሆነ በስተቀር እንጅ፡፡

ይሄ እንዳለ ሆኖ በቅድሚያ፡-

1ኛ፡የህብረቱ መመሪያና ደንብ ተተርጉሞ ግልፅ ሊሆን ቢችል፡- ጥቅሙ...የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚ የሃላፊነት ወሰኑን አውቆ ባለበትና በቻለው መጠን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ስለሚያደርገው

2ኛ፡የተዋቀረው ስራ አስፈፃሚ የህብረቱን ህጋዊ ሰውነት ዳር ማድረስ ቢችል ማለትም አንድ ወጥ የሆነ አቋም እንዲኖረውና ለተቋቋመበት አላማ ለስራው እ/ሴ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር......ከተጠሪቱ እስከ አጋራ አካላቶቹ ከግንኙነት ወሰኑ እስከ ጠቅላላ የስራ እ/ሴዎቹና ተያያዥ ጉዳዮች መቋጫ ስለሚያስገኝ

3ኛ፡የአጭር ጊዜ የስራ እቅድ ማዘጋጀት.....ይህም ማንኛችንም እንደፈለግን እንዳንሄድና በተመረጡና በተመጠኑ እቅዶች እንድንቀሳቀስ ስለሚያስገድደን ወዳውም ለምንሰራው ስራ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ግልፀኝነትን የሚያመጣና የሚታይ ስራ ለመስራት ስለሚያግዝ በሌላ መልኩ ደግሞ ሁሌም የጠባቂነት መንፈስ ይዞን በቸልተኝነት እንዳንተኛ ሲያደርገንና ስራዎቻችነን የበለጠ ቀና እና ውጤታማ ስለሚያደርገን፡፡አለበለዚያ አድስ ሃሳብ ሲመጣልን ለምን ይሄን አንሰራም እያልን የቅንጅት ስራ ሳይሆን የፍላጎት ብቻ ይሆናል፡፡

4ኛ፡ የህብረቱን የበጀት አቅም ግንባታ ለማሳደግ የሚረዳ የፋይናንስ ስትራቴጂ መንደፍ.....መቼም ቢሆን ይህን የሚያክል አገራዊ ህብረት ፈጥረን በይሁንታና በልመና በየቢሮው እየዞርን ለዝግጅት ስንፈልግ ልንሰቃይ አይገባም፡፡አንድም በጀት ከሌለው ንቀትን ያመጣል ሁለትም በተሳታፊዎች ዘንድ የሞራል ውድቀትን ያስከትላል በሌላ መልኩ ህብረቱ ህልውናውን ያጣል፡፡በመሆኑም ከአጋራ አካላት ጀምሮ እስከ መደበኛ አባላት ድረስ የሚያስተዳድርና የሚመራ ብሎም የበጀት አቅምን ሊያሳድግ የሚያስችል ረቂቅ ቢዘጋጅ፡፡ይህ መሆን ካልቻለ ግን መዳረሻችን ግልፅ ነው ተስፋ ካልቆረጥን በየቢሮው በመዞን ደጅ መጥናት ካልሆነ ደግሞ ህብረቱ ይፈርሳል፡፡የምናስባቸው ትልልቅ ሃሳቦች የሚራመዱት በፋይናንስ ነው የ፡ስራ አስፈፃሚው እንደ ልቡ ሮጦ ጉዳዮችን የሚያስፈፅመው በዚሁ ፋይናንስ ነው ተገናኝቶ ለማውራትም ብቻ አጠቃላይ እ/ሴያችን ካለን እውቀት ባለፈ እንደውም ከዛም በላይ የፋይናንስ አቅም ሲኖረን ነውና ቢታሰብበት፡፡

5ኛ፡የመወያያ አጀንዳዎችን በመምረጥና በማዘጋጀት መወያየት ቢቻል....ገንቢና አዳድስ ሃሳቦችን ለመሰብሰብ ስለሚያግዝ ወዳውም አንድነታችንን ስለሚያጠናክር......


መልካም ጊዜ

#አህመድ.M.
ከአርባ ምንጭ
አዣድቶኤል:
ሰላም አለ ?በአፈፃፀም ጊዜ ስለሚቀርብ የቀደምትነት መብት በተመለከተ መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ኮሜንታሪ ወይም የግል ሃሳብ ካለህ ? አመሰግንሃለሁ
አመልካች በተጠሪ ላይ ጋብቻ ሳንፈፅም እንደ ባልና ሚስት በመኖር የተፈራ የጋራ ንብረት ልካፈል ሲሉ ላቀረቡት አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 መሰረት ተሟልቶ የቀረበ መልስ፤
የአመልካች አቤቱታ በአጭሩ
አመልካችና ተጠሪ ከሚያዚያ 4 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 8 ቀን 2006 ዓ.ም ጋብቻ ሳንፈፅም እንደ ባልና ሚት ስንኖር በጋራ ያፈራናቸውን ንብረት አሁን ግንኙነታችንን መቀጠል ባለመቻላችን የተዘረዘሩትን ንብረቶች ግማሽ እንድካፈል ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
እኔ እና አመልካቸ ስንኖር የነበረው አመልካች እንደሚሉት ጋብቻ ሳንፈፅም እንደ ባልና ሚስት ሳይሆን በወንድና በሴት ጓደኝነት ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም አመልካች ለአቤቱታው መነሻ በሆነው ነገር ላይ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን ስላላሳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ መሰረት መዝገቡ እንዲዘጋልኝ በማክበር አመለክታሁ፡፡
መልስ
ከላይ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ፍ/ቤቱ የማይቀበለው ከሆነ የሚከተለውን መልስ አቀርባለሁ፡፡ አመልካችና ተጠሪ እንደ ባልና ሚስት ኖራችኋል ቢባል እንኳን ግንኙነታችን የተቋረጠው ሐምሌ 08 ቀን 2004 ዓ.ም ነው፡፡ በመሆኑም ግንኙነቱ 3 ዓመ፣ት ያልሞላው በመሆኑ ያፈራነው የጋራ ንብረት የለም የተዘረዘሩት ንብረቶችም የግል ንብረቶቼ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በአቤቱታው ላይ ያስቀመጧቸው የንብረት ዝርዝሮች በሙሉ በግል ጥረቴ ያለ አመልካች ድጋፍ ያፈራኋቸው በመሆኑ የገራ ሊባሉ አይችሉም በዚህ ረገድ አመልካች የሚካፈሉት ንብረትም የለም፡፡
አመልካች ክቡር ፍ/ቤቱን የምጠይቀው ዳኝነት
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የሌለ በመሆኑ ተጠሪ ለአመልካች የሚያካፍሉት ንብረት የለም ተብሎ እንዲወሰንልኝ፣ በክሱ ምክንያት ለደረሰብኝ መጉላላት ተገቢው ወጪና ኪሳራ እንዲቆረጥልኝ በማክበር አመለክታለሁ፡፡
አንተ/አንቺ በዚህ ችሎት ዳኛ ብትሆን/ብትሆኚ ፍርድህ/ ፍርድሽ ምን ልሆን ይችላል ? ፍርዳችሁን በኢትዮጵያ ህግ አግባብነት ያለው መሆን አለበት ።
አለሕግAleHig ️
EDITED PART I FINAL.doc
ለመጀመሪያው ጥያቄ የአለም አቀፍ ህጎች የህግ ምንጫቸው ብዙ ነው፡፡ለምሳሌ፡ስምምነት በዋዋነት የሚጠቀስ ነው( convention/treaty)....በሌላ መልኩ general principle,intr'n customry laws,judicial decission...ተጠቃሽ ናቸው እነዚህ ህጎች አንዱ ለአንዳቸው ቀዳሚ አይደሉም(there is no heirarchy)....