አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
🐪የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፥ አዋጁ የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባን በዘመናዊ መረጃ አያያዝ ሥርአት ማስደገፍን ያካተተ ነው።

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ሥርዓቱን ወጥ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ ከግቦቹ መካከል መሆኑንም ነው ምክትል ሰብሳቢው የጠቆሙት።

አዋጁ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን በመከላከል፣ ብልሹ አሰራርና ኢ-ፍትሃዊነትን በማስቀረት በኩል ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን የገለጹት እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር)፤ ዜጎች ለሚያፈሩት ቋሚ ንብረት የተጎናጸፉት የባለቤትነት እና በመሬት የመጠቀም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተግባራዊ ለማድረግ አዎንታዊ ሚና አለው ብለዋል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለ ይዞታ የሚሆኑበት ለመደንገግ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያም ተወያይቷል።

ምክር ቤቱ አዋጁን በዋናነት ለከተማ፣መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤በተባባሪነት ደግሞ ለሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቷል።
#Ethiopia@lawethiopiacomment
ፍትህ ለድሬድዋ ሴት የህግ ተማሪዎች
👇👇👇

#ፍትህለድሬድዋሴትየህግተማሪዎች
#አለሕግ #mootcourt
ፍትህ ለድሬድዋ ሴት የህግ ተማሪዎች
👇👇👇 #ፍትህ #justice #Alehig #ጾታ_እኩልነት #Ethiopia #አለሕግ
#AffirmativeAction #ladiesfirst
210987.pdf
819.7 KB
ኑዛዜ በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ቢሆንም ኑዛዜው ላይ " ኑዛዜው እንደተነበበ" ካልገለፀ ፈራሽ ነው

"ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰው ፊት ቢደረግም ስለ መነበቡ በኑዛዜው ላይ ካልተገለጸ ወይም ስለ መነበቡ አመላካች ቃል ወይም ሐረግ ከሌለ ህጋዊ ውጤት የለውም።
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰዉ ሥራዉን በሚያካሄድበት ክፍል ዉስጥ መደረጉ ኑዛዜዉ በተናዛዡና በምስክሮች ፊት መነበብና ይህም ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ላይ መገለጽ እንዳለበት በአስገዳጅነት የተደነገገዉን ሊሟላ እንደሚገባዉ እንጂ የኑዛዜዉ መነበብ ጉዳይ ቀሪ የሚያደርገዉ አይሆንም፡፡ሲል  የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ. 210987 መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ነው።
እንዲሁም በሰ/መ/ቁ. 70057 (ቅጽ 13) ላይ ባሳለፈዉ አስገዳጅ ዉሳኔ ኑዛዜዉ ላይ እንደተነበበ ካልገለጸ አልያም ኑዛዜዉ እንደተነበበ አመላካች ቃል ካልተቀመጠ ኑዛዜዉ ፈራሽ መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል።
አለሕግAleHig ️
Photo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለስንት ሰው ዋስ ለመሆን ይችላል ??
በዝምድና ወይም በመቀራረብ ቤቱን እንዲኖሩበት የሰጠ ባለቤት ቢካድ እና የሚኖርበት ሰው የእኔ ቤት ነው አልወጣም ቢል ባለቤቱ ክሱን መክሰስ ያለበት በመፋለም ነው ወይስ በህውከት ይወገድልኝ....ሌላ ??
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"የሰበር መፈለጊያ" (Cassation Finder) አሁን በ Google Drive ላይ’🎉
"የሰበር መፈለጊያ" (Cassation Finder) አሁን በ Google Drive ላይ በቀላሉና ምቹ በሆነ መንገድ ይገኛል! የ Update ችግር ከእንግዲህ አያሳስብዎ! አዲስ የሚለቀቁ የሰበር ውሳኔዎች ወዲያውኑ በእጅዎ ይደርሳሉ!
"የሰበር መፈለጊያ" የተበታተኑ መረጃዎችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ፣ የተደራጀ መረጃን በማቅረብ፣ና የቴክኖሎጂን አጠቃቀም በማሳደግ የፍትህ ስርዓቱን ውጤታማነት ያረጋግጣል።
እንዴት መጠቀም ይቻላል? እጅግ ቀላል ነው!
1. በሞባይል ስልክዎ Google Drive ይክፈቱ (ካልተጫነ ከ Play Store ላይ ያውርዱ)።
2. ከታች ያለውን "Shared Folder" የሚለውን ይንኩ።
3. "የሰበር መፈለጊያ" ከገዙ "Abrham Cassation Finder" የሚል ፎልደር ያገኛሉ።
4. ፎልደሩን ከፍተው በሚመጣው የፍለጋ ሳጥን ላይ የሚፈልጉትን ቃል፣ አንቀጽ ወይም የሰበር መዝገብ ቁጥር ያስገቡ!
5. ውጤቱን ወዲያውኑ ያገኛሉ!
በየትኛውም ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን የሰበር ውሳኔ በቀላሉ ለማግኘት ይህንን ምቹና ፍቱን መፍትሔ ይጠቀሙ!
#የሰበርመፈለጊያ #CassationFinder #GoogleDrive #የኢትዮጵያሕግ #የሕግውሳኔ #ጠበቃ #የሕግባለሙያ #ቀላልአጠቃቀም #አዲስቴክኖሎጂ #ፍትህ
https://youtu.be/g5uYE4DWcsw?si=XN8pYaUt5MAWVyZF
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሞት ፍርዱ የፍርድ ቤት ሂደት

የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እናት እና እንጀራ አባት እኚ ናቸው።

እናቷም የእንጀራ አባቷም በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ።

#FastMereja I ወላጅ እናት ወ/ሮ ሀና በየነ ትባላለች የድሬዳዋ ከተማ ገንደቆሬ ሰፈር ነዋሪ ስትሆን ከቀድሞ ባሏ ጋር የተፈታችው ይህቺ ሴት ከእሷ ጋር እየኖረ ባለው ሌላ ወንድ ከአብራኳ የወጣችውን የገዛ ሴት ልጅዋ ተገዳ መደፈሯን ስታውቅ እጮኛዋን በወንጀል እንዲቀጣ ማድረግ ሲገባት የ11 ዓመት ልጇ ላይ ፈርዳ መረጃ ለማድበስበስ በማሰብ ልጇን ላይ ጫና በመፍጠር በድብደባ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ ከ5ተኛ ክፍል የትምህርት ገበታ እና ከጎረቤቶቿ በመነጠል ከማንም ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንዳታረግ በማድረግ ለብዙ ጊዜ ቤት ተዘግቶባት እና ስራ ቦታ ድረስ ከስሯ ሳትነጥላት ብትንቀሳቀስም መረጃ ለመደበቅ በቂ ሆኖ ስላላገኘችው በመጨረሻ በአብራኳ በወጣችው የገዛ ልጇ ላይ የሰራችው ተደጋጋሚ የአረመኔ ሥራ ሳያንሳት እጮኛዋን ከወንጀል ለማትረፍ መረጃ ለማጥፋት ህዳር 1 ቀን 2015 ዓም ከእጮኛዋ ጋር በመተባበር ቀጥቅጠው ህፃን በአምላክ ግርማን ገደሏት።

***

በወላጅ እናቷ እና እንጀራ አባቷ ሕይወቷ ያለፈው ሕፃን በአምላክ ግርማ አበጋዝ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሣኔ ሰጥቷል።

ተከሳሾቹም

እናቷ ሀና በየነ በሞት እንድትቀጣ ተወስኗል::
እንጀራ አባቷ ብሩክ በሞት እንዲቀጣ ተወስኗል::
#ችሎት
https://youtu.be/3e0GwLXjodA?si=AWBOJPhIDQ3u7grE