የተከበረው ፍርድ ቤት በሚል በዳኞች ፊት የሚቆመው ሕዝብ እርሱም የተከበረ ነው።
ዳኝነት ሕዝብን ለመዳኘት የተሰጠ በትረ-ስልጣን ነው፡፡ የተከበረው ፍርድ ቤት፤ ክቡር ዳኛ፤ ክብርት ዳኛ በማለት በችሎቶች እና በዳኞች ፊት የሚቆመው ተከራካሪ ወገን በትረ-ስልጣኑን ያስጨበጠ እና እርሱም የተከበረ በመሆኑ ተገቢው ክብር ተሰጥቶት ሊስተናገድ ይገባል፡፡
ዳኞች ሰዎች በመሆናቸው የተለያዩ ስሜቶች ሊንጸባረቁባቸው እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ በዳኝነት ወንበር ላይሲቀመጡ ግን የዳኝነት ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ሊያደርጓቸው የሚችሉትን ስሜቶች ለመቆጣጠር የሚያስችላቸው ክህሎት /emotional intelligence / ሊኖራቸው ይገባል፡፡
ዳኞች በየዕለቱ የሚሰጡት ትዕዛዝ፤ ብይን፤ ፍርድ በትውልድ ላይ ይወስናል፡፡ ዳኞች የሚሰጡት ውሳኔ በሕዝብ፤ በሐገር ኢኮኖሚ፤ ፖለቲካ እና ሰላም ላይትልቅ እንድምታ አለው፡፡ ሕዝቦች በሰላም ወጥተው እንዲንቀሳቀሱ፤ ተማሪው እንዲማር፤ ገበሬው እንዲያዘምር፤ ሠራተኛው እንዲሰራ፤ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፤ የሐይማኖት አባቶች እንዲጸልዩ እንዲሰብኩ፤ ጋብቻ እንዲኖር፤ ትውልድ እንዲቀጥል፤ ማሕበራዊ እሴቶቻችን ወጎቻችን እንዲጠበቁ ዳኞች ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡
አመቺ ያልሆኑ እና አስቻይ ያልሆኑ ሁኔታዎች ቢፈጠሩ እንኳን ሚዛን ጠብቀው ተከራካሪ ወገኖችን አክብረው የመፍረድ ሕገመንግስታዊ እና ሞራላዊ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስችልም አንድ ሀይል አለ፡-ብእር! ወርቃማ ቀለም! ወርቃማ የዳኛ ማንነት!
እትመት አሰፋ
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#የዳኞችስነምግባር #አለሕግ #ህግ
❤26👍18