አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ ፀድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚያሻሽል ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

አዋጁ የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

አዋጁ የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል “ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ “ ያስገድዳል።

ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለ ነው።
#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም። ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በመ/ቁጥር 130/16 የሰጠው ውሳኔ ነው።
#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
የፌዴራል ህጎች በክልል ደረጃ የተቀራረበ አተረጓጎም እንዲኖራቸው በትኩረት መስራት ይገባል’’ ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ተናገሩ።

አቶ ቴዎድሮስ እንዳሉት ህጎቹ በክልል ደረጃ በተቀራረበ ደረጃ እየተተረጎሙ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ በየጊዜው መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና ውጤቱን መሰረት በማድረግ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ።

አተረጓገሞቹ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በዚህ መንገድ ማረም ችግሮችን ከምንጫቸው ለመፍታት ያስችላል ነው ያሉት።

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ የሁሉም ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች ያሉበት ነው።

በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኘ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክርም አቶ ቴዎድሮስ በመድረኩ ላይ ሲናገሩ ሠምተናል።
ንጋቱ ረጋሣ ፣ የሸገርን ወሬዎች፣ መጋቢት 27 2017
#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጋበዝ፤
የፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1249/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በፌደራል ጠበቆች እና የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅቶች ስለሚሰጥ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሥርዓት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም  ረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የረቂቁን ቅጂ ከዚህ በታች የተመለከተውን ሊንክ  በመጫን ማግኘት የሚችል ሲሆን  እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በኢ-ሜይል አድራሻ info@moj.gov.et መላክ ወይም በዋና መ/ቤት የጥብቅና ፍቃድ አስተዳደርና ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጽሁፍ መስጠት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ 

በፌደራል ጠበቆች እና የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ድርጅቶች ስለሚሰጥ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሥርዓት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ መመሪያ https://shorturl.at/etru2

ፍትህ ሚኒስቴር


#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
As lawyers, we stand in solidarity with Ethiopia’s #health_professionals. They are our #doctors and #lifesavers—second only to our Creator. Their voices must be heard, and their struggles acknowledged, especially as they face challenges that threaten their very survival.
#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
#አማራጭ_የሕግ_እውቀትና_አገልግሎት
#Alternative_legal_enlightenment_Service
Website 📱 alehig.com #+251920666595 #Mikias_Melak #Doctor #Health #Life_Savior #My_Doctor
ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የመንደር ውል ህጋዊ የሚሆንባቸው 5/አምስት/ ሁኔታዎች

የማንይቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በ ፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካልተደረገ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ከተወሰኑ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በመነሳት የመንደር ውል ህጋዊ ተብለው የሚቆጠሩበት ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ 5 ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

🥇ኛ የሽያጭ ውል መኖሩ ከታመነ ወይም ካልተካደ

🥈 ገዢ ውል እንዲፈፀምለት ክስ አቅርቦ ከሳሽ መከላከያ መልሱ ላይ በመካከላቸው ውል መኖሩን ካመነ ወይም ካልካደና በሌሎች ነጥቦች ላይ መልስ ከሰጠ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት አልተደረገም ብሎ ውድቅ ሊያደርገው አይችልም።

🥉ኛ በማህበር በመደራጀት የተሰራ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (ሰ/መ/ቁጥር 36294 ቅፅ 8)

✏️ በማህበር በመደራጀት እየተሰራ ያለ ቤት ቤቱ ተጠናቆ ካርታ እስኪወጣለት ድረስ የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ይህን ቤት ቢያስተላልፍ ቤት የመስራት መብቱን ወይም እጣውን እንዳስተላለፈ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረትን እንዳስተላለፈ አይቆጠርም። የማህበሩ አባል በስሙ ካርታና የባለቤትነት ማስረጃ እስካልተሰጠው ድረስ ቤቱ ወይም እየተሰራ ያለው ቤት በማህበሩ አጠቃላይ ይዞታ ስር የሚገኝ በመሆኑ የማህበሩ አባል ለ 3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ የሚችለው እጣውን ወይም ጥቅሙን እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት አይደለም። እንዲህ አይነት ውሎች የግድ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሊረጋገጡ አይገባም።

🔴ኛ ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (ሰ/መ/ቁጥር 32222 ቅፅ 7)

✏️ ብዙን ግዜ እንዲህ አይነት ውል ከ Real Estate ቤቶች ግንባታ ጋር የተያያ ነው። ምንም እንኳን ውላቸው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ቢሉም ዉሉ በሚደረግበት ግዜ ቤቱ ያልነበረ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከአንዱ ወደ ሌላው ተላልፏል ሊባል አይችልም። ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል የግንባታ ውል እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሊባል የሚችል ባለመሆኑ ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ አይኖርበትም።

4⃣ኛ አዋዋይ ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ለተወሰነ ግዜ ሳይፈፀምበት የቆየ የመንደር ውል (የሰ/መ/ቁጥር 36740 ቅጽ 8)

✏️ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ መሠረት በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው የመንደር ውል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች የተሟሉት የተወሰነ ግዜ ከቆየ በኋላ ቢሆንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰው አካል ፊት ያልተደረገ ነው በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም የሚል ነው።

✏️ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ እንዳለው ቤቱን የሚመለከቱ እዳና እገዳ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውል ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የፕሮቶኮል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ቢሆንም እነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውል ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የፕሮቶኮል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውል እንዳልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም፡፡

5⃣ኛ የሊዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (የሰ/መ/ቁጥር 191095 & 225796)

#በአለሕግ_ጠበቃና_ሕግ_አማካሪ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM