አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#Ethiopia

ግምሩክ ኮሚሽን አምራቾች ወደ አገር ዉስጥ እቃዎችን ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ ብቻ እንዲስተናገዱ ፈቅዷል።

ኮሚሽኑ በአምራቾች ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ ዕቃዎች የዋጋ አተማመን ስርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

158/2011 የተደነገገውን በጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ዋጋ አተማመን መመሪያ እንዲከለስ ማድረጉን ነዉ የተገለጸው።

ይህ መመሪያ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ በሚወስንበት ወቅት የሚወስደው ጊዜ ከአምራቾች ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ይገኛል።

ይሄን ተከትሎ በአምራቾች ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ አተማመን ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን ተነግሯል።

መመሪያ ቁጥር 158/2011 እስኪሻሻል ድረስ በክሊራንስ ጊዜ የዋጋ ማጣራት ሃደቱ የሚወስደውን ጊዜ ለማስቀረት በሚል አምራቾች እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ በሚያቀርቡት ህጋዊ የግብይት ዋጋ እንዲስተናገዱ ኮሚሽኑ በላከው ሰርኩላር ፈቅዷል።

ይህ ሰርኩላር ፦
- አምራቾች
- ልዩ መብት የተሰጣቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ፕሮግራም ተጠቃሚ ድርጅቶች፥
- ለኢንቨስትመንት ሥራ ዕቃዎችን በቀረጥ ነፃ የሚያስገቡ ድርጅቶች፤
- የመንግስት ፕሮጀክትን ለመስራት በግል ድርጅቶች የሚገቡ ዕቃዎች፣
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተቋማትን ይመለከታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካቲፓል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
ትራምፕ በአሜሪካ የሚወለዱ ህጻናት በቀጥታ ዜግነት እንዳያገኙ ያሳለፉት ውሳኔ በፌደራል ዳኛ ታገደ

22 ግዛቶች ህጻናትን "ሀገር አልባ" ያደርጋል ያሉት የፕሬዝዳንቱ የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ እንዲታገድ ክስ መስርተዋል።

https://bit.ly/3E9XGmO
የተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች
1. በማናቸውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ግዥ አፈፃፀም የሚከተሉት የግዥ ዘዴዎች ሥራ ላይ ይውላሉ፡-
ሀ) ግልፅ ጨረታ፣
ለ) በማጣሪያ የሚከናወን ጨረታ፣
ሐ) ውስን ጨረታ፣
መ) በቀጥታ የሚፈፀም ግዥ፡፡ የፌደራል የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016 https://www.alehig.com/proclamation-no-1333-2024-the-federal-public-procurement-and-property-administration-proclamation/
ጀርመን የቤት ውስጥ ጥቃት ለሚፈጽምባቸው ወንዶች መጠለያ ማዘጋጀት ጀመረች

በ"ወንዶች መጠለያዎቹ" በሴቶች አካላዊ፣ ወሲባዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶች ብሶታቸውን የሚተነፍሱበት እድል ተመቻችቶላቸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hAb8Pc
#ፀደቀ‼️
ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገር የሚያሰችል አዋጅ ፀደቀ‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገር የሚያስችል የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል።

የአዋጁ መፅደቅ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያስችል ነው ተብሏል።

የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለምክርቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት፣ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን መሠረት አድርገው ከተቀረጹ መርሐግብሮችና ዕቅዶች አንጻር ትምህርትን ለመምራት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም።

ይህንን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት አዲስ አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል። አዋጁ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚደረገውን ሪፎርም ያግዛል።

በአዋጁ ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገር እንዲችሉ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

አዋጁ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር ይረዳል ያሉት ሰብሳቢው፣ በመላው ሀገሪቱ ሁሉም የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት የሚከናወነው የመማር ማስተማር ሂደት የሀገሪቱን እሴት ጠብቆ እንዲካሄድ ግልጽ አቅጣጫ የሚሰጥ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
https://www.alehig.com/
206006.pdf
826.1 KB
ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን አቅርቦ ክሱ ሊሰማ በተቀጠረበት ዕለት ባለመቅረቡ በፍ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) መሰረት ክርክሩ በሌለበት እንዲታይ ብይን ከተሰጠ የመከላከያ ክርክር የማቅረብ መብቱን ከማሳጣት አልፎ በቀሪዎቹ የክርክር ሂደቶች ከመሳተፍ አያግደውም።
559_የኢሚግሬሽን_የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት_ደንብ.pdf
823.9 KB
የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 559/2017
Council of Ministers Immigration Amendment Regulation No 559/202
560_የኢሚግሬሽንና_ዜግነት_አገልግሎት_ሠራተኞች.pdf
1.2 MB
ደንብ ቁጥር 560/2017
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሠራተኞች መተዳደሪያ ደንብ
Regulation No. 560/2024
Immigration and Citizenship Service Employees Administration Regulatio
ካርታ ማምከን ማለት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ /ደብተር ወይም ካርታ/ በመሰረዝ ዋጋ የማሳጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ነው።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp📱 #+251920666595
Telegram📱 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት 📣❗️🆕

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ ሊሟሉ እሚገባቸው ጉዳዮች ብሎ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጧል።

በዚህም በሽያጭ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ለማድረግ፦

1. በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈ ማንኛውም ዓይነት እዳ እና እገዳ እንዲሁም ቀረጥ ያለበት ከሆነ የስምምነት ደብዳቤ መኖሩን ማረጋገጥ፣

2. ኮድ 01 እና ኮድ 03 ከሆነ ከገቢዎች የግብር ክሊራንስ መቅረቡን

3. የዘመኑን ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ/ቦሎ፤ ያደረገ መሆኑን፤

4. የጸደቀ የውልና ማስረጃ ሰነድና የስም ዝውውር 2% የከፈለበት ማስረጃ መኖሩን፣

5. የንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ አንዱ የግምት ውጤት ለሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ይላካል፤ ሁለተኛውን የግምት ውጤት ሁለቱ ተዋዋዮች ውል መፈፀም የሚችሉ ለመሆኑ በሸኚ ደብዳቤ ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተላከበት ሰነድ፤

6. የቤት ተሸከርካሪ ከሆነ የግምት ውጤቱን በቀጥታ ሰሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተላከበት ሰነድ፤

7 . የገዢ ሁለት ፎቶ ግራፍ

8. የስም ዝውውርና የአገልግሎት ለውጥ የሚያደርግ ከሆነ ተሸከርካሪው በድጋሚ ለቴክኒክ ምርመራ ብቃት ማረጋገጫ ሲቀርብ እገልግሎቱ ይሰጣል ሲል አስቀምጧል።

በተጨማሪም ቢሮው በዚሁ መረጃው ላይ በሰጠው ማሳሰቢያ፦

1. የሚገዙት ተሽከርካሪ የሻንሲና ምተር ቁጥር ትክክለኛነት የማረጋገጥ፣

2. የተሚገዙት ተሽከርካሪ ሊብሬና ተሽከርካሪ ስለያዙ እና ዉክልና ስለተሰጦት ብቻ ሀጋዊ ተሽከርካሪ ማለት ስላልሆነ የሚገዙት ተሽከርካሪ በተመዘገበበት ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛነቱ መረጋገጥ አለበት ሲል ገልጿል።
#tikvahethmagazine
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp📱 #+251920666595
Telegram📱 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
capital market amharic.pdf
268.2 KB
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መግለጫ ለባለ አክስዮን ማህበሮች

ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሞት የተለዩ ተጠርጣሪዎችን ንብረት እንዲወረስ የሚያደርገው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው‼️
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ተጠርጣሪው በሞት ቢለይ ወይም ከሀገር የሸሸ ቢሆንም ንብረቱ  እንዲታገድና ጉዳዩ ተጣርቶ ግለሰቡ በሌለበት እንዲወረስ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡

በአዲሱ የንብረት ማስመለስ አዋጅ  በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሰረተ የንብረት ማስመለስ አዋጁ እንደሚያካትት ሲገለፅ  ይህም ተጠርጣሪው በሞት ቢለይ ወይም ከሀገር የሸሸ ቢሆን ንብረቱ እንዲሁ የሚቀር ሳይሆን እንዲታገድና ጉዳዩ ተጣርቶ ግለሰቡ በሌለበት እንዲወረስ ይደረጋል ሲል ፍትህ ሚኒስትር አስታውቋል።

የጸደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ተፈጻሚ ሲሆንም  ምክንያታዊ ያልሆኑ ክሶች እንዳይመጡ ተጠርጣሪው ግለሰብ ስለ ጉዳዩ ቀርቦ እንዲያስረዳ ዕድል የሚሰጥና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ ተፈጻሚ የሚሆን ነውም ብሏል።

አዋጁ በህገ-ወጥ መንገድ በወንጀል የተገኘ ንብረትን በአግባቡ በማስመለስ የሀገርንና የህዝብን ሀብት ከወንጀል ለመጠበቅ የሚሰራበት ነው ተብሏል።

የማይመለስ ጉዳት ማለትም ንብረቱ ከሃገር ሊሸሽና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶ ከሆነ ጊዜያዊ እግድ በራሱ በፍትህ ሚኒስቴር ያለፍርድቤት ትዕዛዝ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

አዋጁ አንድ ግለሰብ በቅን ልቦና ባለማወቅ ንብረቱ ህገ-ወጥ መሆኑን ሳያውቅ የገዛ ቢሆን ንብረቱ እንዳይወረስ ተገቢውን ጥበቃ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

በአዋጁ ላይ በተደነገገው መሰረትም ህገ-ወጥ ንብረት በማፍራት የተጠረጠረ ሰው ያለደረሰኝ በሰውም ሆነ ሌሎች ያስረዱልኛል ባላቸው ማስረጃዎች ጥፋተኛ አለመሆኑን ማስረዳት የሚያስችል መመሪያ እንዳለውም ተነስቷል።

አዋጁን ለማስፈጸም ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር የሚሰራ ሲሆን  ንብረቱ ኢትዮጵያ ቢሆንም በውጭ ሀገራት በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ ለማስመለስ የሚሰራበት ነው ተብሏል።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM