#ፀደቀ‼️
ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገር የሚያሰችል አዋጅ ፀደቀ‼️
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣዩ ክፍል መሸጋገር የሚያስችል የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል።
የአዋጁ መፅደቅ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያስችል ነው ተብሏል።
የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለምክርቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት፣ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን መሠረት አድርገው ከተቀረጹ መርሐግብሮችና ዕቅዶች አንጻር ትምህርትን ለመምራት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም።
ይህንን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት አዲስ አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል። አዋጁ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚደረገውን ሪፎርም ያግዛል።
በአዋጁ ከፍተኛ የትምህርት አቀባበል ያላቸው ተማሪዎች የሚገኙበትን የትምህርት ክፍል ሳያጠናቅቁ ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገር እንዲችሉ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።
አዋጁ ብቁ የትምህርት ባለሙያ፣ አመራርና አደረጃጀት ለመፍጠር ይረዳል ያሉት ሰብሳቢው፣ በመላው ሀገሪቱ ሁሉም የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት የሚከናወነው የመማር ማስተማር ሂደት የሀገሪቱን እሴት ጠብቆ እንዲካሄድ ግልጽ አቅጣጫ የሚሰጥ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
https://www.alehig.com/