አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
1. Register on Wabi as a Lawyer
እንደ ጠበቃ ይመዝገቡ
ዋቢ ላይ መመዝገብ ለህግ ባለሙያዎች የሚያስገኛቸው ጥቅሞች:
ዋቢ የጠበቆችን ሙያ ለማዘመን የሚረዳ መድረክ ሲሆን ጠበቆች ዋቢ ላይ በነፃ በመመዝገብ የተለያዩ የህግ ሰነዶችን ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መልኩ ተሰናድተዉ ያገኛሉ እንዲሁም የህግ ብሎጎች ላይ ይሳተፋሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ በዋቢ የጠበቆች ዝርዝር ዉስጥ በመካተት ለህግ አገልግሎት ፈላጊዉ ህብረተሰብ በይበልጥ ተደራሽ ይሆናሉ።

2. Register on Wabi as a Client
እንደ ተጠቃሚ ይመዝገቡ
ዋቢ ላይ መመዝገብ ለተጠቃሚዎች የሚያስገኛቸው ጥቅሞች:
ተጠቃሚዎች በዋቢ ላይ በመመዝገብ ስለ ህግ ያላቸዉን ግንዛቤ ማስፋት፣ የትኛዉንም ከህግ ጋር የተገናኘ ጥያቄ ማቅረብ ፣ በዘርፋ የታወቁ ጠበቆችን ዝርዝር በነፃ እና በቀላሉ ማግኘት እንዲሁም ወቅታዊ ህግ ነክ መረጃዎችን መከታተል ይችላሉ ።

ዋቢ ላይ ዛሬዉኑ በነፃ ይመዝገቡ!
https://wabilaws.com/am/users/sign_up

ዋቢን ይጎብኙ!
Wabilaws.com

የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ይከታተሉ!
Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=61562959684020
Instagram:
https://www.instagram.com/wabi_laws?igsh=aWR0M3ZqMWZnemcx&utm_source=qr
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/wabilaws/
Telegram:
https://t.me/WABI_laws

ማሳሰቢያ:
ይሄ ድህረ-ገፅ የአዋጅ 1249/2021 መሠረት በማድረግ የተቋቋመ ሲሆን በአዋጁ የተከለከለውን በአገናኝ የሚደረግ የጥብቅና አገልግሎት በማይፃር መልኩ ይሰራል። ዋቢ ከጠበቃውም ሆነ ከደንበኛው እንደ አገናኝ ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም ።
Quick Guide to Ethiopian Labour Proclamation 1156/2019
https://www.alehig.com/quick-guide-to-ethiopian-labour-proclamation-1156-2019/
This guide is designed to simplify the understanding of the new Labour Proclamation, providing general knowledge and assisting our clients in enhancing their human resource management practices.
Prepared by:
Mikias Melak
Legal Consultant and Attorney
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
ሚኪያስ መላክ +251920666595
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group

👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/

New official website
https://www.alehig.com
ክፍት የስራ ማስታወቂያ👇👇👇
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባለው ክፍት የስራ ቦታ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸውን በዜሮ አመት የስራ ልምድ እና ከአምስት አመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸውን ሙያተኞች አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
መመዝገቢያ መስፈርቶች
1ኛ ኢትዮጵያዊ የሆነች/የሆነ በኢትዮጵያ የሚኖር
2ኛ ለህገመንግስቱና ለህግ የበላይነት ተገዥ  የሆነ
3ኛ የየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች  እና ወንጀል ቅጣት የሌለበት፡፡
4ኛ በታታሪነቱ/ቷ/ በስነምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች/ ማስረጃ  ማቅረብ  የሚችል/የምትችል/
5ኛ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የተመረቀ/ች
6ኛ የስራ ልምድ ዜሮ አመት በ2015 እና በ2016 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ሆነው የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ለወንዶች የመመረቂያ ነጥባቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች 3.25 እና ከዚያ በላይ
7ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት /15/ አስራ አምስት
8ኛ ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ ላላቸው በአቃቢ ህግነት፣ በዳኝነት ፣ በህግ ምርምር ፣ በመምህርነት እና በተመራማሪነት ያገለገለ/ች/ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
9ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት ከአምስት ዓመት በላይ ላገለገሉ 10/አስር
10ኛ ደመወዝ በተቋሙ ስኬል መሰረት
11ኛ የስራ ቦታ ቢሮው በሚሰጠው ምደባ ቦታ፣
ተመዝጋቢዎች /ተወዳዳሪዎች/ ለምዝገባ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች   ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ፓስፖርት የትምህርት ማስረጃቸውን ዋና ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ከምትኖሩበት አካባቢ አግባብነት ካለው አካላት የተፃፈ የስነምግባር ማስረጃ፣
የምዝገባ ቦታ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ መስከረም 12ቀን 2017ዓ.ም በሚለው እትም ወጥቷል።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0115159550 /  0115159548
        የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ለማግኘት በአዋጅ ቁጥር 1249/2ዐ13 የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ/የምታሟላ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ/ት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
ሚኪያስ መላክ +251920666595
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group

👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/

New official website
https://www.alehig.com
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ለመረጃ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከሚሰጡ አገልግሎቶች የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ የተደረገባቸው ጠቅላላ ዝርዝር።

https://www.alehig.com

https://t.me/AleHig
ለተሽከርካሪ ቦሎ፣ ስም ዝውውር እና ለጠፋ መንጃ ፈቃድ እስከ 150 ፐርሰንት የክፍያ ጭማሪ ተደረገ

ለተሽከርካሪ ቦሎ፣ ስም ዝውውር እና የጠፋ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት እስከ 150 ፐርሰንት የሚደርስ የክፍያ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ያወጣው ይህ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ በተቋሙ ታሪክ ከፍተኛው ነው።

የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በአራት ቀን በፊት በቂርቆስ ክፍል ከተማ እንደ ሞዴል ተደርጎ የታሪፍ ክፍያውን ማስከፈል ያስጀመረ ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

በዚህም መሰረት
ለቦሎ የነበረ ክፍያ ከ650 ብር ወደ 1,850 ብር ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን፣

ለስም ዝውውር ከ5,600 ብር የነበረው ወደ 10,000 ብር፣

ለለተሽከርካሪ የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ 17ሺህ 100 ብር የነበረው ወደ 30 ሺህ ፣

የጠፋ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት 750 ብር የነበረው ወደ 5 ሺህ ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አዲስ ማለዳ አሰምታለች።
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
ሚኪያስ መላክ +251920666595
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group

👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/

New official website
https://www.alehig.com
ከግብር/ታክስ ጋር በተያያዘ በወንጀል የሚያስጠይቁ ጥፋቶች

በግብር ወይም ታክስ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉን በመተላለፍ የሚፈፀሙ በመሆኑ ክሱ የሚመሰረተው የሚታየው እና ይግባኝ የሚቀርበው በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ነው፡፡ በወንጀል ከሚያስጠይቁ የጥፋት ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላይ የሚፈፀም ጥፋት፣
2. ህግን በመጣስ ግብር/ታክስ ባለመክፈል፣
3. የሀሰት ወይም አሳሳች መረጃ ማቅረብ፣
4. የግብር/ታክስ ሚኒስቴሩ ስራ ማሰናከል፣
5. ያለ ደረሰኝ ግብይት መፈፀም፣
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/vktow0
ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት የጎደለው የቤት ጥያቄ ...
ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም ፤ ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጥ መቅረቱ አሳዝኖናል " - ቅሬታ አቅራቢዎች

ለ21 ዓመታት ኮንዶሚኒየም ይደርሰናል ብለው ሲቆጥቡ የቆዩ የኮንዶሚኒየም ነባር ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሳይወጣላቸው፣ ቤቶቹ ለልማት ተነሽዎች በመሰጠታቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በዕጣ ለማግኘት ሲጠባበቁ የቆዩ በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ፣ ለልማት ተነሽዎች ቤቶች መሰጠታቸው ኢፍትሐዊ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡

ይህን ቅሬታ ያቀረቡት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።

" ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጠን መቅረቱ አሳዝኖናል " ብለዋል።

ለልማት ተብሎ ቤታቸው የፈረሰባው ዜጎች ቤት ሲሰጣቸው የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝጋቢዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ለምን በመንግሥት የተሠሩ ቤቶች አይሰጡንም ? ያሉት ተመዝጋቢዎቹ፣ ለሁለት አሠርት ዓመታት ቤት ለማግኘት በመጠበቃቸው በተለየ ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይና የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎች ጣራ በመንካታቸው፣ ለችግር ተዳርገናል ያሉት ተመዝጋቢዎች፣ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለንም ወይ ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ለዓመታት ምላሽ በተነፈገው ጥያቄያቸው ምክንያት በመንግሥት ላይ ያላቸው እምነት መሟጠጡን ገልጸዋል፡፡

ተመዝጋቢዎቹ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ቅሬታቸውን ቢያሰሙም እስካሁን መፍትሔ እንዳላገኙ አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ምን ምላሽ ሰጡ ?

- አጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ከሁለትና ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የብድር አቅርቦት ችግር ተጨማሪ ግንባታ ማድረግ አላስቻለም፡፡

- ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ግንባታ አይካሄድም ፤ ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስኪከፈል ድረስም ሲያገኝ የነበረው ብድር ተከልክሏል።

- ኮርፖሬሽኑ ካለበት ዕዳ ውስጥ 36 ቢሊዮን ብር ተመላሽ አድርጓል ፤ ቀሪ 37.7 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ አለበት ፤ ለመክፈልም የተለያዩ አማራጮችን እያጤንን ነው።

- በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የሚሰጠው ለማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ ነው። ለሰፊ የቤት ግንባታ ግን ተጨማሪ ብድር አይሰጥም።

- ለልማት ተነሽዎች ቅድሚያ መስጠትን መመርያው የሚያዝና የሚደግፈው ነው። ነገር ግን የኮንዶሚኒየም ዕጣ ጠባቂዎችን ወደ ጎን ከመግፋት ጋር መገናኘት የለበትም።

- የቤት አቅርቦት ጉዳይ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በቤት አቅርቦቱ በአማራጭ የቤት ልማት ላይ እየተሠሩ ነው።

- ከተለመዱት 40/60 እና 20/80 ቤቶች በተጨማሪ በ70/30 ፕሮግራምና በማኅበር ቤቶች አቅም ያላቸው እንዲገነቡ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል።

- ኮርፖሬሽኑ እስካሁን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሲገነባ የነበረው በቦንድ ግዥ ነበር፤ አሁን ግን የከተማ አስተዳደሩ ካለው በጀት ላይ እየመደበ ብድሩን እየከፈለና ለኪራይ የሚሆኑ ቤቶች እየገነባ ነው።

- ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትና ባለሀብቶች ተቀናጅተው የሚገነቧቸው ቤቶች አሉ ፤ ለዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሰጡ ነው።

- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ቁጠባ ያቋረጡ አሉ። ነገር ግን አሁንም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሉም ወይም ጨርሰን ሰጥተናል አላልንም።

- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቅሬታ ትክክል ነው። ነገር ግን ከተማው ያለበትን የቤት አቅርቦት ችግር ሲፈታ የተመዝጋቢዎቹን ችግርም በዚያው ይፈታል።

- የነባሩ የዕጣ አወጣጥ ሒደት ቆሟል ወይም አልቆመም ብለን መናገር አንችልም፤ ምናልባት የባንክ ብድር ከተመለሰ እንደገና በሌላ ብድር ቤቶች ተገንብተው ለዕጣ ጠባቂዎች ለመስጠት ጥረት ይደረጋል።

- የተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሒደት ይቀጥላል ወይም አይቀጥልም የሚለው በቤት አቅርቦት ሁኔታው ይወሰናል።

- ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች በአንድም በሌላም መንገድ ቢጣራ ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ለኮሪደር ልማት ተነሽዎች የ40/60 እና የ20/80 ቤቶች ተሰጥተው አልቀው ወደ ኪራይ ቤት እየተገባ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና የአስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና በበኩላቸው፣ በ1997 ዓ.ም. ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው ዕጣ ያልወጣላቸውን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ አለመገኘቱን አቶ መንግሥቱ ገልጸው፣ እንደገና በደብዳቤ ተጠይቆም ምላሽ ካልተገኘ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማምራት መታቀዱን ተናግረዋል።
#ሪፖርተርጋዜጣ
#ቤት ፈላጊዎች ሼር አድርጉ ፣ ፍትህን የምትደግፉ #Share
ቅንነት አያስከፍልም ሼር።
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group

👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/

New official website
https://www.alehig.com