አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
7👍3
።።። የዋስ መብት (Bail) ።።።።             
ወንጀል የማህበረሰብን አጠቃላይ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ከመሆኑ አንፃር ማህበረሰቡ ወንጀል ፈጻሚዎች እንዲለዩ እና የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይፈልጋል፡፡ በአንፃሩ በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ እስካልተባሉ ድረስ ነፃ ሆነው የመገመት መብት ያላቸው በመሆኑ የማህበረሰቡን ፍላጎት እና የተጠረጠሩ ሰዎችን መብት በአማከለ መልኩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የዋስ መብት የህግ ጥበቃ ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የዋስ መብትን ምንነት፣ የዋስ መብትን በተመለከተ በሀገራችን ያለውን የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የዋስ መብትን የሚያስነፍጉ ልዩ ሁኔታዎችን በዝርዝር የምንመለከት ይሆናል፡፡
የዋስ መብት ምንነት......👇👇👇👇👇
https://wp.me/pfoz3m-85
https://wp.me/pfoz3m-85
👍206
ተቀጥሮ መስራትን የማያበረታታው ነጩ ካፒታሊዝም /Pure Capitalism/ በኢትዮጵያ፣

በሚኪያስ መላክ ብርሀኔ
          እና
አቤል ወንድሙ ኃይሌ

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 12 (3) መሠረት ማንኛውም ተቀጥሮ የሚሰራ ሠራተኛ መክፈል የሚኖርበትን ግብር አሠሪው ከሠራተኛው ገቢ ላይ ሳይቀንስ የሠራተኛውን ግብር ራሱ አሰሪው በሙሉ ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ ፣ በአሰሪ የተከፈለው የግብር መጠን ሠራተኛው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡ 
እንዲሁም፤
በገቢ ግብር አዋጅ አንቀፅ 10 (3) መሠረት ተቀጣሪው በመቀጠር የሚገኘውን ገቢ ለማግኘት የሚያወጣውን ማንኛውም ወጪ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም፡፡ 
ነገር ግን  
በዚሁ በገቢ ግብር አዋጁ አንቀፅ 15 (1) ፣ (5) እና (7) መሠረት ግብር የሚሰላበት የኪራይ ገቢ ነው የሚባለው ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ውስጥ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ነው፡፡
በተጨማሪም፤
በገቢ ግብር አዋጁ አንቀፅ 20 ፤ 22 እና ሌሎችም ተያያዥ ድንጋጌዎች መሠረት አንድ ነጋዴ ገቢ ለማግኘት የሚያወጣው ወጪ ተቀናሽ እንዲደረግላቸው ሕጉ በግልጽ አስቀምጧል። 

በመሆኑም፤
የኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ እና ሌሎችም ሕጎች ተቀጥሮ መስራትን የማያበረታቱ የነጩ ካፒታሊዝም /Pure Capitalism/ ርዕዮተ ዓለም መገለጫዎች ይመስላሉ። 

ከኢኮኖሚ አቅም አንፃር ስናየው ነጋዴ እና አከራይ የተሻለ ገቢ የሚያገኙ እና በአንፃራዊ የተሻሉ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ሆነው እያለ ግብር የሚሠላበትን ገቢ ለማግኘት ያወጡት ወጪ ተቀናሽ ተጠቃሚ ሲሆኑ ፤ ይህ ተጠቃሚነታቸው በኢኮኖሚው ውስጥ ነጋዴውና የኪራይ ንብረት ባለሀብቶች የሚያደርጉትን የነቃ ተሳትፎ ለማበረታታት አስፈላጊነቱ የሚታመንበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በተቃርኖ ግን ድሀው እና ለፍቶ አደሩ አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ገቢው እዚህ ግባ የማይባል የወር እና ቀን ገቢ አነስተኛው ተከፋይ ሠራተኛ ገቢውን ለማግኘት የሚያወጣው ወጪ ተቀናሽ የማይደረግለት ሲሆን ይባስ ብሎ አሰሪ ግብሩን ቢከፍልለት እንኳ እንደ ተጨማሪ ገቢ ተቆጥሮበት ግብር እንዲከፍልበት ሕጉ ያስገድዳል። 
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Alternative legal enlightenment
(ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
#አለሕግ #Alehig
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
ሚኪያስ መላክ
#ጠበቃ እና #የሕግአማካሪ
#ሚኪያስ #መላክ 👈👈👈

+251920666595
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
#Legal Information🔵

👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉Telegram_Group👈
https://t.me/AleHig_Group

👉Instagram👈
https://www.instagram.com/alehigofficial

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/alehig/

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com

New official website
https://www.alehig.com
👍28🥰1
ሶስት አሜሪካውያን በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሞት ቅጣት ተላለፈባቸው

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢምባሲ ሰራተኞች የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉት ነበር ብሏል
https://bit.ly/4emBdQq
👍3
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው።


ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።

የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው።

ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420
በአብርሀም ዮሀንስ
👍9😁1
145_2015_የአዲስ_አበባ_ከተማ_ነዋሪነት_ምዝገባ_እና_የነዋሪነት_አገልግሎት_አሰጣጥ_መመሪያ.pdf
942.5 KB
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁ. 145-2015
👍4
የ2017 የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ማስታወቂ.pdf
540.5 KB
የ2017 የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የፍትህ አካላት የህግ ምርምርና ስልጠና ማዕከል የ2017 በጀት ዓመት የቅድመ ስራ ስልጠና የሰልጣኞች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ስለዚህ ከነገ ዓርብ 03/01/2017 ጀምሮ ማስታወቂያ በመለጠፍ እስከ 07/01/2017 ዓ.ም እያንዳንዱ መዋቅር 2 ሰልጣኝ በመመልመል  አወዳድራችሁ እንድትልኩ እንገልፃለን።

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ
መስከረም 02/2017
https://t.me/AleHig
👍22
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲዯር የሲቪሌ ምዝገባ እናየነዋሪነት አገሌግልት ኤጀንሲበአዱስ አበባ ከተማ አስተዲዯር የሲቪሌ ምዝገባ እናየነዋሪነት አገሌግልት ኤጀንሲ መመሪያ ቁጥር 145/2015
https://www.alehig.com/2010-2/
👍2
ውድ #የአለሕግ ቤተሰቦች ስለ አዲሱ የአለሕግ ዌብሳይት ገብታችሁ እዩትና አስተያየት እና ጥቆማችሁን አድረሱን እናመሰግናለን::
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.alehig.com/
https://www.alehig.com/
https://www.alehig.com
👍7
በሰባት ዳኞች የተለወጡ የሰበር ውሳኔዎች
≈≈≈
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 ስር እንደተደነገገው አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠን ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ እንደሚደረግ እና በዚህ መልኩ የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ለሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት አስገዳጅ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

በዚህ መሰረት ባሳለፍነው በጀት አመት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት ውሳኔ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች አጭር መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ የውሳኔዎቹን ሙሉ ግልባጭ በፍርድ ቤቱ ዌብሳይት https://www.fsc.gov.et/ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

መልካም ንባብ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
https://www.alehig.com
👍127