አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አለ ሕግ ነው ያልከው⁉️⁉️
በላ አሳየን በላ...... አሳየን እስኪ ሕግህን ለዚች ምስኪን አንድፍሬ እንቦቅላ ልጅ... አሳየና አሳየን 😥😥😥😡😡😡😥😡😡😥🥺 ባደባባይ አሳዩንና እህት ወንድሞቹዋ ያለመሸማቀቅ እንዲያድጉ እንፍቀድ.... አሳዩንና ሚሊዮን ሕፃናትን አለንላችሁ አሉላችሁ እያልን እናሳድግ 👉አሳዩን ሕጋቹን አሳዩን የዝህችን ምስኪን ነብስ ለሚልዮኞች ዕረፍታቸው ለብዙዎች ነፃነታቸው እንድናደርግ አሳዩን ሕጋቹን ⁉️⁉️
Honorable member Voice of AleHig አለሕግ expresses deep sorrow and concern over the tragic crime committed against an innocent 7-year-old girl.
#Yibka_Tsegaye_Girma
Share and be voice for justice.
"የግድያ ወንጀሉ ብቻ በራሱ የእድሜ ልክ ወይም የሞት ፍርድ ሊያስቀጣው ሲገባ ስር ፍርድ ቤቱ በ25 አመት ፅኑ እስራት ብቻ  ውሳኔ ሰጥቶ ማለፉ ስህተት ነው፡፡" የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የህፃን ሄቨን ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ማኅበሩ በመግለጫው ምን አለ?

- በመጀመሪያ ተከሳሽ በምርመራ ሂደት የተገኘው መረጃ በግድያው ወንጀል ብቻ የሚያስከስስ ነው በማለት በግድያ ወንጀል ብቻ  የምርመራ ሂደቱ ቀጥሎ ነበር፤

- ከማኅበሩ የረጅም አመት በጎ ፈቃደኛ ከሆኑት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ምርመራ ክፍል ሀላፊ ጋር በመሆን ምርመራው እንደገና እንዲጣራ በማድረግ ተከሳሹ በግድያ ወንጀል ብቻ ሳይሆን በአስገድዶ መድፈርና በግድያ ወንጀል እንዲከሰስ ማድረግ ተችሏል፤

- ድርጊት ፈፃሚው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነው የባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።

- የስር ፍርድ ቤትም ወንጀለኛውን በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ብቻ መቅጣቱ  እጅግ ያነሰና  የግድያ ወንጀሉ ብቻ በራሱ የእድሜ ልክ ወይም የሞት ፍርድ ሊያስቀጣው ሲገባ ስር ፍርድ ቤቱ በ25 አመት ፅኑ እስራት ብቻ  ውሳኔ ሰጥቶ ማለፉ #ስህተት ነው፡፡

- [ይህ ውሳኔ] የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችን እና የቅጣት አወሳሰን መመሪያው ሊታይና ሊሻሻል እንደሚገባ የሚያመለክት ነው፡፡

- ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የህክምና ማስረጃ ለማጣራት በማለት ያስቀርባል የሚል ትዕዛዝ በመስጠት ለጥቃት አድራሽ የማይገባ ተስፋ መስጠቱ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጉዳዩን እየተከታተለ መቆየቱንና ህፃን ሄቨን ፍትህ እንድታገኝ ማኅበሩ የበኩሉን ጥረት እያደረገ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethmagazine
የሕጻን ሔቨን ክስ
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 620/3
የወሊድ መከላከያ ህክምና የወሰደው አባወራ ድጋሚ አባት መሆኑን ተከትሎ ክስ መሰረተ

የአራት ልጆች አባት የሆነው ሰው እርግዝና እንዳይፈጠር የሚከላከል ህክምና ቢያደርግም ሳይፈልግ አምስተኛ ልጅ አባት ለመሆን ተገዷል

የሕክምና ስህተት የሰራው ተቋም ልጄ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የማሳደጊያ ይከፈለኝ ሲል ክስ መስርቷል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3AxaCl6

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
#ጉምሩክ

" ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች

በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት የነበሩ ውስብስብ የንግድ መዛባቶችን እና ብሮክራሲዎችን እንደሚያስቀር እንተማመናል " ብለዋል።

ነገር ግን የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ነሐሴ 03/2016 እና ነሐሴ 10/2016 ያወጣቸው ሰርኩላሮች ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

" ይህም ሰርኩላር ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና ከጉምሩክ ትራንዚት እና መጋዘን አስተዳደር የሚጣረስ በመሆኑ ነው " ብለዋል።

አስመጪዎቹ " የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD/01/2024 ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን ከ22/11/2016 በፊት የተመዘገቡ እና ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች ላይ በደብዳቤ ቁጥር 4/0/04/17 ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ስርኩለት የተላከ ሲሆን ነገር ግን ሰርኩለር በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ሲያብራሩም ፦

" በጉምሩክ ደንቡ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የቀረጥ ማስከፈያ የሚወሰነው ዲ/ዬን. በተመዘገበበት እለት ያለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ተመን በመጠቀም ነው።

ይህ ማለት በዮኒሞዳል አሰራር ሕጋዊ ዶክሜንት አሟልተን ዲ/ዬን ሞልተን ክፍያ ፈፅመን ሰነዱን የተሟላ መሆኑን ለጉምሩክ ኦፊሰር ተረጋግጦ ትራንዚት ተፈቅዶልናል፡፡

ትራንዚት ካስፈቀድን በኋላ ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው በአንድ ወር የትራንዚት ጊዜ ገደብ ውስጥ ኘሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን ወደ አገር ውስጥ አስገብተናል የጉምሩክ ሪስክ የሚጣለው ደግሞ እቃዎቹ አገር ውስጥ / መድረሻው ጣቢያ / ሲደርሱ መሆኑን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ነው።

እቃዎቹ ተጓጉዘው በድሬዳዋ መስመር /ደወሌ/ ለሚገቡ በድሬዳዋ ድልድይ ተሰብሮ ከ3 ሳምንት በላይ መቆማቸው ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው " ብለዋል።


" የጉምሩክ ኮሚሽን ከላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስቸኳይ የውሳኔ ማሻሻያ እንዲደረግልን እና በአዋጁ መሰረት እንድንስተናገድ " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ፤ " ጉምሩክ  ኮሚሽን አዋጅን በሴኩላር በማሻር የማይሆን ስራ እየሰራ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አስመጪዎች አሁንም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሴኩርላር ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም።

አሁንም ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል።

ጉዳዩ  በገበያና ስራው ላይ ሚያመጣውን ከፍተኛ ተፅእኖ በመረዳት እውቀትን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በውይይት መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Customs #Ethiopia

@tikvahethiopia
#ወሳኝ_መረጃ!

ፍራንኮ ቫሉታ ተፈቀደ! ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች ውጭ ሁሉም ዕቃዎች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተፈቅዷል! (ይህ ውሳኔ በገበያ በሚወሰን የምንዛሬ ተመን ስርዓት ውስጥ ተጠባቂ ነው)::
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት እነማን ናቸው?


ሰሜን ኮሪያ በአስገድዶ  መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞችን በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላት


ስድስት ሀገራት ደግሞ ብልት እስከ ማኮላሸት ድረስ ወንጀለኞችን ይቀጣሉ

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://bit.ly/46PX9AE

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
በዓለም ላይ ከሚገኙ ሴቶች መካከል 35 በመቶው ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው።

ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም ይላል ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው በሪፖርቱ።

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመላው ዓለም ያለ ክስተት ቢሆንም የተወሰኑ ሀገራት ወንጀሉን ፈጽመዋል በተባሉ ጥፋተኞች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጅተዋል።

ሰሜን ኮሪያ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባሉ ወንጀለኞች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የሚፈቅድ ህግ አላት።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከባድ ቅጣት የሚጥሉት ሀገራት የትኞቹ ናቸው? በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3Av2AZS

#የሕግአማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
እሁድ እሁድ ስናካሂድ የነበረውን ከምሽቱ 2:30 የእሁድ ችሎት ነፃ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ ሲሆን ውይይቱን ስንጀምር የምናሳውቅ ይሆናል‼️

#የእለቱ_ችሎት

#የችሎቱ_ጭብጥ

ፕሮግራም ለአልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️

#ውሳኔ
ችሎቱ ቢያመልጥዎት በሌሉበት የሚሰማ ይሆናል።

ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ @lawsocieties የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ሆኖ ተራዝሟል።

ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይመለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ#አለ_ህግ ስም አለበት
https://t.me/lawsocieties
የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች

ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነጻ የሚሆነው፡-

1. በስራ ባህሪው ምክንያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2,200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

2. አንድ ተቀጣሪ በስራ ባህሪው ምክንያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

3. አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስርያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም ባይቀርብም ለዚህ ዓይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

4. አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራ ቦታው እንዲሁም ከስራ ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ ለነዳጅ ወጪ በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

5. አንድ ተቀጣሪ ሥራውን ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ሲንቀሳቀስ ለመጓጓዣ ወጪ የሚሰጠው ክፍያ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በስራ ላይ ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ወይም በሚያቀርበው ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከከፈለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡

6. አንድ የውጭ አገር ዜጋ ሥራን ለማከናወን ወደ የኢትዮጵያ ሲመጣ እና የውል ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል መገልገያ ዕቃዎቹ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ አይችልም፡፡

7. አንድ ግብር ከፋይ ከመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ርቀው ሥራቸውን የሚያከናወኑ ሠራተኞች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ የሚያደርጉትን ጉዞ ውጪ የሚሸፍን በሚሆንበት ጊዜ የዚህ ዓይነት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው የቅጥር ውል ውስጥ ቀጣሪው ይህ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሆኖም ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ የሚከፈለው ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረገው በአንድ የግብር ዓመት ከሁለት የደርሶ መልስ ጉዞ ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
በበኃይሉ ሺመልስ
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
ERCA
ministryofrevene
#የሕግአማካሪ #ጠበቃ
https://t.me/Ethiopialegalinfo
"ጉዳዩ ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት ተቀጥሮ አድሯል" - አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ

በሕጻን ሄቨን ጉዳይ አማራየ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱ ተከትሎ ምን ተደረገ? ጉዳዩስ ምን ላይ ነው? የሚለውን የሚዳስስ ነው።

አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ያስቀመጠው የፍርድ ሂደት፦

ድርጊቱ የተፈጸመው ከፍተኛ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት (ጦርነት) በነበረበት ወቅት መሆኑን፤ ወንጀለኛው በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላም መለቀቁንና የተጎጅ ቤተሰብን፣ የሕግ አካላትን ሳይቀር ተጽዕኖ ለማድረስ መሞከሩን ያስረዳል።

ተጠርጣሪው ዳግም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ምርመራው ተደርጎ በምርመራው እና ባሉት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች መነሻነት በተደራራቢ ወንጀል ሁለት ክስ ማቅረብ ተችሏል፡፡

ክሶቹም የግፍ ግድያ የወንጀል ሕጉ 539 እና በመድፈር መግደልን 620 (3) ያጣቀሰ ነበር። ይህም የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የሚያስቀጣ ነው ብሏል፡፡

በክርክር ሂደት ተከሳሽ ክዶ ጠበቃ አቁሞ የተከራከረ መሆኑንና ይህም ሕጋዊ አሠራር መሆኑን አንስቷል።

* የክልሉ ፍትህ ቢሮ በማብራሪያው በክርክሩ የታዩ የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ወንጀል ከተፈጸመ ተጠያቂነት ይኖራል ቢልም በሂደቱ ላይ ምርመራ ስለመጀመሩ ግን አልገለጸም።

የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ [የሥር ፍርድ ቤት] የቀረበው ማስረጃ የግፍ ግድያን ሳይኾን (539) በመደፈር መሞቷን የሚያረጋግጥ መኾኑን በማረጋገጥ ተጠርጣሪው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን አንስቷል፡፡

ፍርደኛው አሁንም ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ የጠቀሰው ማብራሪያው በአሁኑ ወቅት ፍርደኛው የፍርደኛ ይግባኝ አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል ብሏል። ይሄም ሕጋዊ እና የተለመደ አሠራር ነው ሲል ነው ያስረዳው፡፡

ጉዳዩም ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት መቀጠሩን እና አሁንም ፍትሕ ቢሮው ጉዳዩን በአግባቡ እየተከታተለው እንደሚገኝ ጠቁሟል።

"ምናልባት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ #በአሉታዊ ቢኾን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በዐቃቢ ሕግ በኩል የሚቀርብ እንደኾነም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡" ሲል ነው ቢሮው በማብራሪያው የገለጸው።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ.pdf
2.7 MB
👆👆👆
የሕፃናት ወርሃዊ የቀለብ አወሳሰን የስሌት ሰንጠረዥ
የሕፃናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ 1/2016

የፌዴራል ጠቅላይ  ፍርድ ቤት የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያን ከስር ባለው ሊንክ በመግባት ያግኙ
የፌዴራል ጠቅላይ  ፍርድ ቤት የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያን ከስር ባለው ሊንክ በመግባት ያግኙ
የፌዴራል ጠቅላይ  ፍርድ ቤት  ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties