የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች
✅ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን
✅ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣
✅የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣
✅የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣
✅ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣
✅ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣
✅ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣
✅ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣
✅ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣
✅የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣
✅የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣
✅የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣
✅ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/alehig
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.com

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/alehig
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.com
Telegram
አለሕግAleHig ️
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

👍11
❤3👍1😁1
በየመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች
👇👇👇👇👇
ንብረት ማፍራት እና መጠቀም አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም የንብረት መብት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት ጀምሮ በተለያዩ ፖሊሲዎች እና ህጎች ውስጥ ተካቶ ይገኛል። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 40/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረቱ ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ይከበርላታል። እንዲሁም በንዕስ አንቀፅ 7 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው። ቋሚ ንብረት ከሚባሉት ውስጥ ቤት አንዱ ነው። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊጠቀምበት ከሚችልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ በኪራይ ለሌላ ሰው በማስተላለፍ የቤት ኪራይ ክፍያ በመግኘት ነው። ቤቱን የሚያከራይ ሰው ለራሱ ከኪራዩ መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ ቤቱን በማከራየቱ ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የሚያደርግ ስለሆነ የቤት ኪራይ ጥቅሙ ለሁለቱም ወገን ማለት ለአከራይም ለተከራይም ይሆናል። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊያከራይ ከሚችልባቸው አገልግሎቶች ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማከራየት ይገኝበታል። በአከራይ እና በተከራይ መካከል የሚኖረው ግንኙነት በህግ የተደገፈ ሲሆን የሁለቱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ይሆናል። በመሆኑም የመኖሪያ ቤት ኪራይን የሚቆጣጠር እና የሚያስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ታውጆ በስራ ላይ እንዲውል ሆኗል።
በመሆኑም በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ትምህርታዊ ፅሁፍ ስለ አዋጁ አስፈላጊነት እና የተፈፃሚነት ወሰን፣ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን፣ ለአከራይ ስለሚሰጥ ማበረታቻ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚታደስበት ሁኔታ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች በወፍ በረር ይዳሰሳሉ።
• የቤት ኪራይ ውል ምንነት
በአዋጁ አንቀፅ 2(1) ስር እንደተደነገገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማለት ለመኖሪያነት የሚያገለግል አንድ ወይም ከአንድ በላይ ክፍሎችን የያዘ ቤትን ተከራይቶ በመጠቀም ለሚያገኘው አገልግሎት ለአከራይ ክፍያ እየፈፀመ የሚኖርበት የውል ግንኙነት ነው። ይህን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ የሚቆጣጠር አካል በክልል እንደሚሰየም አዋጁ ያስቀምጣል።
• የአዋጁ አስፈላጊነት
በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል።
• የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ተጠሪነታቸው ለክልል በሆኑ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላይ በሚፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ሲሆን ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በሌሎች ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታውን እያዩ እንደሚወስኑ አዋጁ ያስቀምጣል። በተጨማሪም አዋጁ ተፈፃሚ ከሚሆንበት ሁኔታ ውጪ ተፈፃሚ የማይሆንበት ሁኔታን የተመለከተ ሲሆን አዋጁ በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል።
• ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ
ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 4(1) የሚደነግግ ሲሆን የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። ተቆጣጣሪው አካል የማረጋገጥ እና የምዝገባ ስራውን ሲሰራ በክልሉ ሰነድን የማረጋገጥ ስልጣን ካለው አካል ጋር የሚሰራ ሲሆን ውሉ በፅሁፍ የመሆን መስፈርት፣ የማረጋገጥ እና የመመዝገብ ግዴታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳት ላይም ተፈፃሚ ይሆናል። አከራይ እና ተከራይ ውሉን በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። በአዋጁ አንቀፅ 4(5) ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል።
የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል በሚወጣ መመሪያ የሚወሰን የገንዘብ ቅጣት የሚያስከትል ሲሆን የገንዘብ ቅጣቱ በማንኛውም ሁኔታ ባልተመዘገበው ውል ላይ ካለው የሶስት ወር ኪራይ ሊበልጥ አይችልም። በተጨማሪም አዋጁ ተቆጣጣሪው አካል የቤት ኪራይ ውል ሞዴል ማዘጋጀት እና የተቋሙ ድረ-ገፅ ጨምሮ በሌላ በማናቸውም መንገድ ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋል።
ሌላው በአዋጁ የተካተተው ጉዳይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ሲሆን የተመዘገበ የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ እንደሚወሰድ ነው። ይህ እንደለ ሆኖ ተቆጣጣሪው አካል በአዋጁ መሰረት የወሰነው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማሻሻያ መነሻ በማድረግ አከራይ የጨመረው የቤት ኪራይ ዋጋ የመኖሪያ ቤቱ ኪራይ ውል ላይ የተመለከተው የኪራይ ዋጋ አካል ተደርጎ ይወሰዳል። ውሉ በሚታደስበትም ሆነ በሚፈረምበት ወቅት በነባር ተከራይም ሆነ በአዲስ ተከራይ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚቻለው ከላይ የተመለከተውን የቤቱ ኪራይ ዋጋ መነሻ አድርጎ በመውሰድ ነው።
በአዋጁ አንቀፅ 8(4) ስር እንደተደነገገው አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በአመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ነው። በዚሁ መሰረት የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የፀና ይሆናል።
አከራይ በአዋጁ መሰረት የቤት ኪራይ ውሉ የተመዘገበን የመኖሪያ ቤት ውል የውል ዘመኑ መጠናቀቅ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሳያከራየው ቆይቶ በኋላ ለኪራይ ሲያቀርበው የቤቱ የኪራይ ዋጋ የሚሆነው የቤቱ ኪራይ ሳይቋረጥ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ የሚኖረው የኪራይ ዋጋ ነው። አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ወደኋላ ሁለት ዓመት በፊት የኪራይ ውሉ የተቋረጠ የመኖሪያ ቤት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለኪራይ ከቀረበ በአዋጁ መሰረት ሊጨመር የሚችለው የኪራይ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመጨረሻ ጊዜ ሲከራይ በነበረው ዋጋ የሚከራይ ይሆናል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የዋጋ ግመታ ሥርዓት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ እስከሚወሰን ድረስ አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል።

ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍9
በሌላ በኩል አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከ 6 ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን መኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል እንደሚደረግ የአዋጁ አንቀጽ 8(10) ያስቀምጣል።
• የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን
በአዋጁ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን በስምምነት፣ በማስታወቅ ወይም በማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት አመት ሊያንስ እንደማይችል በአንቀፅ 6(1) ስር ተደንግጎ ይገኛል። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። ይህም በተለምዶ የሶስት ወር የቤት ኪራይ በቅድሚያ ተከፍሎ ለስድስት ወር የሚደረግ የቤት ኪራይ ውልን ያስቀረ፣ ለተከራይ ረዘም ያለ የኪራይ ጊዜ የሰጠ እና አነስተኛ ቅድመ ክፍያ ያስቀመጠ መሆኑን ያመለክታል።
በአዋጁ አነስተኛ የውል ዘመንን የተመለከተው እንዳለ ሆኑ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የመኖሪያ ቤት ከራይ የውል ዘመን በውሉ ላይ የተቀመጠው የውል ዘመን ይሆናል። የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በእዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው። ይሁንና ቤቱ ለሌላ ወገን የተላለፈው በስጦታ ከሆነ ተከራይ የውል ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ በተከራየው ቤት የመቆየት መብት ይኖረዋል።
የቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በእዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ሰው በመተላለፉ ውሉ የተቋረጠ እንደሆነ በአዋጁ መሰረት የሚደረግ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንደተጠበቀ ሆኖ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በተቋረጠው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ነው። በአዋጁ እንቀፅ 6(7) ስር እንደተደነገገው የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በአዋጁ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም።
• ለአከራይ ስለሚሰጥ ማበረታቻ
በአዋጁ አንቀፅ 10(1) ስር እንደተደነገገው አዲስ ቤት ሰርቶ ለኪራይ ያቀረበ አከራይ በአዋጁ ከሚወጡ የቤት ኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚቆጠር አራት አመት ነፃ ይሆናል። እንዲሁም አከራይ ነባር እና ተከራይቶ የማያውቅ የመኖሪያ ቤቱን ለኪራይ ካቀረበ በአዋጁ መሰረት ከሚወጡ የቤት ኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚቆጠር ሁለት አመት ነፃ ይሆናል። ይሁንና የኪራይ ምዝገባን የሚመለከቱ እና ሌሎች የአዋጁ ድንጋጌዎች እና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
በሌላ በኩል የመኖሪያ ቤትን ሳያከራዩ በባዶ ወይም በሌላ አግባብ ለንግድ ወይም ለመኖሪያ ወይም መሰል ተመጣጣኝ ማህበራዊ ፋይዳ ያለው አገልግሎት ሳይሰጥ ከአንድ ዓመት በላይ የሚያቆዩ የቤት ባለቤቶች የቤቱን የንብረት ግብር ተመን 25% የሚያክል ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር ከፍተኛ የቤት እጥረት ባለባቸው የከተማ አስተዳደሮች በመመሪያ ሊዘረጋ ይችላል።
• የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚታደስበት ሁኔታ
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ውል ዘመኑ ሲያበቃ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት በፅሁፍ ሊታደስ ይችላል። ውሉ ሲታደስ አከራዩ ሊያደርግ የሚችለው የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ከሚያደርገው ጭማሪ ጣርያ ሊያልፍ አይችልም።
• የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ወይም የቤት ባለቤትነት በህጋዊ መንገድ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊቋረጥ ይችላል። እነኚህ ውሉ በማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ሲሆኑ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በአንቀፅ 16 ስር እንደሚከተለው ተዘርዝረው ይገኛሉ።
• የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ፣
• የቤት ኪራዩን በውሉ ከተመለከተው ቀን ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣
• ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
• የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ፣
• በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈፅም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀምበት ከሆነ፣
• አስቦ ወይም በቸልተኝነት በቤቱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት ነው።
በተጨማሪ አዋጁ የቤት ኪራይ ውል መቋረጥ የሚያስከትለውን ውጤት በአንቀፅ 17 ስር ያስቀመጠ ሲሆን ውሉ ያለማስጠንቀቂያ ከተቋረጠ በአዋጁ መሰረት ጭማሪ ሊደረግባቸው በሚችሉ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ቤቱ ለሌላ ሰው ሲከራይ ቀድሞ ከነበረው የኪራይ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። አከራይ ይህን ክልከላ በመጣስ የዋጋ ጭማሪ ያደረገ ከሆነ ተቆጣጣሪ አካሉ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ሊጥለው ከሚችለው የገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ፣ በአዲሱ ተከራይ አመልካችነት የቤት ኪራዩ ውሉ ወደ ቀድሞ የኪራይ ዋጋ እንዲመለስ ሊያደርገው ይችላል።
በአዋጁ አንቀጽ 21(1) እና 22 ላይ እንደተደነገገው ማንኛውም በአከራይ እና ተከራይ መካከል የሚያጋጥም እና የአዋጁን አፈፃፀም የተመለከተ አለመግባባት እንዲፈታ ለተቆጣጣሪ አካሉ በአከራይም ሆነ በተከራይ በፅሁፍ የአለመግባባቱ ማመልከቻ መነሻ የሆነው ጉዳይ ባጋጠመ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ በፅሁፍ መቅረብ አለበት። ማመልከቻው የቀረበለት አካልም ቅሬታውን መርምሮ በ 30 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት።
በመጨረሻም በአዋጁ መሰረት የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና ቅጣቶች ተቆጣጣሪው አካል በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰኑ ሲሆን አዋጁም በህዝብ ተመካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ማለትም በመጋቢት 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል።
በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍11❤3
ውል ማስፈፀም እና ቀብድ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ውሎች ሁሉ ወዲያውኑ ተፈፃሚ ሊሆኑ አይችሉም። በተለያዩ ምክንያቶች ተዋዋዮች ከስምምነት ላይ ቢደርሱም የውሉን ሙሉ ክፍያ ለመክፈል ወይም በውሉ ግዴታ የገባው ወገን ግዴታውን ለመወጣት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ለማሟላት የተወሰነ ጊዜ ሊፈልግ ይችላል። በዚህ ጊዜ መሀል ተዋዋዮች ሀሳባቸውን ሳይቀይሩ ዋናውን ውል እንዲፈፅሙ ከሚያስተማምኑ መንገዶች አንዱ ቀብድ ነው።
ቀብድ ከውል አፈፃፀም ጋር ያለውን ግኙነት እና ስለ ውጤቱ ሕጉ ምን እንደሚል ለማየት፣ ውልን አለመፈፀም ማለት ምን እንደሆነ እና በሕግ የተቀመጡ የውል ማስፈፀሚያ መንገዶችን፣ እንዲሁም ቀብድ በተዋዋዮች የውል መብት እና ግዴታ ላይ የሚኖረውን ውጤት እንመልከት።
የፍትሐ ብሔር ሕጉን እየተመለከትን ቁጥር 1731(1) ላይ ስንደርስ ውል በተዋዋዮች መሀከል ሕግ ነው ይለናል። ተዋዋዮች በመሀላቸው ላለው ግንኙነት ተፈፃሚ እንዲሆን በነፃ ፍላጎታቸው የሚፈጥሩት መብት እና ግዴታ ነውና ውሉ እና ሕጉ ላይ የተቀመጡትን የተዋዋዮች መብቶች እና ግዴታዎች መፈፀም አለባቸው፡፡ ውሉ አልተፈፀመም የሚባለው ተዋዋዮቹ በውል ስምምነታቸው እና በሕጉ መሰረት ግዴታቸውን ሳይወጡ ሲቀሩ ነው፡፡
ተዋዋዮች ውል የሚገቡት በተስማሙባቸው ነገሮች ላይ የልብ ልብ ተሰምቷቸው እንዲተማመኑበት ነው፡፡ ይህን መተማመን የሚፈጥረው ደግሞ ውልን የሚያስፈፅመው ሕግ ነው። በውሉ እና በዚህ ሕግ ላይ ተመስርተው ፍ/ቤቶች በሚሰጡት ፍርድ ነው ውል የሚፈፀመው፡፡ ስለዚህ ሕጉ በምን መልኩ ውልን ያስፈፅማል ወደ ሚለው ጉዳይ እንለፍ፡፡
ውልን በግድ ማስፈፀም
የውል ግዴታውን ያልፈፀመ ተዋዋይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሰረት ለሌላው ተዋዋይ የተለየ ጥቅም የሚሰጠው እና በፈፃሚው ነፃነት ላይ ምንም መሰናክል ሳይፈጥር መፈፀም የሚችል ግዴታ ሲሆን በሕግ ተገዶ እራሱ እንዲፈፅም ይደረጋል፡፡
ለምሳሌ በአንድ የሙዚቃ አቀናባሪ እና በአንድ ድምፃዊ መሀከል ሙዚቃ ለማቀናበር የተደረገ የውል ግዴታን እንይ። አቀናባሪው እና ድምፃዊው ውሉን ከገቡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቀናባሪው ግልፅ ባልሆነ የራሱ ምክንያት ሙዚቃውን ሳያቀናብር ይቀራል።
ድምፃዊው ከሙዚቃ አቀናባሪው ጋር ውሉን የገባው የአቀናባሪውን የታወቀ ልዩ የማቀናበር ችሎታን ዓይቶ ስለሆነ ወደ እርሱ የመጣው የማቀናበሩ ሥራ በራሱ ባቀናባሪው በመሠራቱ ላይ ልዩ ጥቅም አለው ሊባል ቢችልም አቀናባሪው ግን በፖሊስ ተገዶና በፍ/ቤት ታዞ የአቀናባሪውን ፍላጎትን እና መነሳሳትን የሚጠይቀውን የሙዚቃ ቅንብር ሥራ ሊሠራ ስለማይችል ሥራው ቢባልም ነፃነቱ ስለሚጣስ በግድ ፈፅም ሊባል አይችልም።
ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=6423
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
alehig.com

ውልን አለመፈፀም

www.ebc.et

ቀብድ ከውል አፈፃፀም…

👍17🙏1
Forwarded from አለሕግAleHig ️
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቱን ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ተደራሽ ለማድረግ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በገባው ስምምነት መሰረት ቅጽ 24 እና 25 ታትመው ወጥተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ቅጽ 23 ታትሞ የወጣ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ቅጽ 26 ታትሞ ለንባብ የሚበቃ ይሆናል፡፡
መጻሐፍቱ አራት ኪሎ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፣ ፒያሳ ከቅዱስ ጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ እንዲሁም በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሚገኙት የድርጅቱ የሽያጭ መደብሮች እንዲሁም በሌሎች መጻሕፍት መደብሮች ይገኛሉ፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
መጻሐፍቱ አራት ኪሎ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፣ ፒያሳ ከቅዱስ ጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ እንዲሁም በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በሚገኙት የድርጅቱ የሽያጭ መደብሮች እንዲሁም በሌሎች መጻሕፍት መደብሮች ይገኛሉ፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍10
ለልጁ ማሳደጊያ ላለመክፈል ሞቱን ያወጀው አሜሪካዊ እስርና የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል
የ39 አመቱ አሜሪካዊ ለልጁ ማሳደጊያ እንዲከፍል የተወሰነበትን ገንዘብ ከመስጠት ሞቱን ማወጅ መርጧል።
ጄሴ ኪፕ የተባለው የኬንታኪ ነዋሪ በካሊፎርኒያ ለምትኖር የቀድሞ ባለቤቱ 100 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተወስኖበታል፤ ለልጁ ማሳደጊያ የሚሆን።
ለቀድሞ ባለቤቴ ድንቡሎ ሳንቲም ከምሰጥ ይልቅ “ሞቼ ልገላገል” በሚልም ህልፈቱን በራሱ ያውጃል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3PUktWM

👍8🤩3
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ
ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የነበረዉን ደንብ በመሻር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ለሚሰጣቸው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል ።
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አዲሱ ደንብ ከመዉጣቱ በፊት ሲሰራበት የነበረዉን የሰነዶች ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያን በመሻር ማሻሻያዉ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያ ለመወሰን ባወጣዉ በዚህ ደንብ በተቀመጠው አዲሱ የክፍያ መጠን የሰነድ አይነቶቹ ቢለያይም ለሁሉም አገልግሎቶች ከ 200 ብር ጀምሮ እስከ 500 ብር ድረስ ክፍያን ይጠይቃል ።
ካፒታል በተመለከተዉ በዚህ ደንብ ላይ ለሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ዉል ሰነድ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ሽያጭ ፣ ለመመስረቻ ፅሁፍ ሰነድ እና በስጦታ መልክ ለሚሰጡ ንብረቶች ዉል ሰነድ የክፍያ አገልግሎት ተመን ከወጣላቸው መካከል ዉስጥ ተካተዋል።
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የነበረዉን ደንብ በመሻር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ለሚሰጣቸው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል ።
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አዲሱ ደንብ ከመዉጣቱ በፊት ሲሰራበት የነበረዉን የሰነዶች ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያን በመሻር ማሻሻያዉ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያ ለመወሰን ባወጣዉ በዚህ ደንብ በተቀመጠው አዲሱ የክፍያ መጠን የሰነድ አይነቶቹ ቢለያይም ለሁሉም አገልግሎቶች ከ 200 ብር ጀምሮ እስከ 500 ብር ድረስ ክፍያን ይጠይቃል ።
ካፒታል በተመለከተዉ በዚህ ደንብ ላይ ለሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ዉል ሰነድ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ሽያጭ ፣ ለመመስረቻ ፅሁፍ ሰነድ እና በስጦታ መልክ ለሚሰጡ ንብረቶች ዉል ሰነድ የክፍያ አገልግሎት ተመን ከወጣላቸው መካከል ዉስጥ ተካተዋል።
Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
#አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍9😁1
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
Council of Ministers Regulation No.543-2024.pdf
2.8 MB
የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ።