አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የትዳር አጋሩን የተለያየ የሰውነት ክፍል በቢላዋ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ አስራት ተቀጣ

ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት የትዳር አጋሩን በቢላዋ ጭቅላቷን፣ አንገቷን፣ ፊቷን፣ የግራ ክንዷንና ጣቷን፣ ደረቷንና ጀርባዋን በመውጋት የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስሜነህ ግርማ በለጠ የተባለው ተከሳሽ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡20 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስኮ ሰፈረ ወርቅ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የትዳር አጋሩ የሆነችው ሟች ማህሌት ፍቃዱ ላይ ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።

ግልሰቡ ይህንን በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ የቆየ ሲሆን ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ባለማቅረቡና የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።
#TikvahethMagazine
#አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍141
የህዝብ ሮሮ አሁንም የሚሰማበት ተቋም
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ፓስፖርት ፈልገው ወይም በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል።
ወጣት፣ ሴት፣ ወንድ፣ ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም «ፓስፖርት ፈልገው ነው?» እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱን ለመመልከት በመሥሪያ ቤቱ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎችም ይህንን መመልከት ችለዋል፣ ሆኖም በወቅቱ መረጃ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ በፖሊሶች ክልከላ ምክንያት አልተሳካም።
አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ አሠራር ዘርግቻለሁ ቢልም አሁንም በርካታ ተገልጋዮችን አገልግሎቱ ደጃፍ ላይ መመልከት አልቀረም።
ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት እና ፎቶ ለመነሳት በመሥሪያ ቤቱ መገኘት ግዴታቸው በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121413
👍152😭1
ሳይናዘዝ የሞተ ሰዉ ወራሾች ተዋረድ(hierarchy of intestate succession)

በ/ፍ/ሕ/ቁ አንቀፅ 842 መሰረት ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሾች ናቸው። ወራሾቹም የሟችን ድርሻ እኩል እንደሚካፈሉ ይሄ ድንጋጌ ያሳያል።  ከልጆቹ አንዱ ሞተዉ እንደሆነና ልጆች አፍርተው እንደሆነ ልጆቻቸውን በሟች እግር ተተክተዉ እንደሚወርሱ የዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 3 ያመለክታል።

ሟች ምንም አይነት ወደታች የሚቆጠር ተወላጆች ከሌሉት አባት እና እናቱ በሁለተኛ ደረጃ ወራሽነት ይጠራሉ። እናትና አባትም የሟችን ንብረት እኩል እንደሚካፈሉ ከፍ/ሕ/ቁ 843 እና 844(1) መገንዘብ ይቻላል። ከሟች ወላጆች አንዱ ቀድመዉ የሞቱ እንደሆነ ልጆቻቸው ወይም የነርሱ ተወካዮች በእነርሱ እግር ተተክተው ይወርሳሉ።

በሦስተኛ ደረጃ ወራሽነት አያቶች የሚጠሩ ሲሆን ይህም የሚሆነው ሟች ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም አባትና እናት ወይም የነርሱ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ከሌለዉ እንደሆነ ከ/ፍ/ሕ/ቁ 845(1) መገንዘብ ይቻላል።

ከላይ የተጠቀሱት ወላጆችም ሆነ ተወላጆች በማይኖሩበት ጊዜ ቅድመ-አያቶች በአራተኛ ደረጃነት ለዉርስ እንደሚጠሩ ከፍ/ሕ/ቁ 847 እንገነዘባለን።

በመጨረሻም ምንም  አይነት ዘመዶች የሌሉ እንደሆነ የሟችን ሀብት የወራሽነት መብት ለመንግስት/ሐገር ይተላለፋል።

በሕሊና ጌታቸው የሕግ ቢሮ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍161
Forwarded from ሕግ ቤት
ውጤትዎን ይመልከቱ!

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ውጤትዎን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/

#tikvahuniversity
👍9
#ይህ ሕግ ለሁሉም የሚሰራ ሕግ ነው። የግል ሆነ የመንግሥት ሠራተኛ ተግባራዊ የሚሆን መብት ነው።
#የማንኛውም ሠራተኛ ደመወዙ
1. በሠራተኛው ስምምነት ወይም
2. በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም
3. በሕግ በተደነገገው መሠረት ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም።
#ይግባኝምክረሕግ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍16🤮2👏1
አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻው የዕገታ ወንጀል
***************
(ኢ ፕ ድ)
... ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ወንጀል እየጨመረ መጥቷል።

የሰዎች በታጣቂዎች የመታገት ዜና እንግዳ መሆኑ ከቀረ ሰነባብቷል። ክስተቱም በተወሰኑ መጥፎ ዕጣ በገጠማቸው ሰዎች ላይ የሚከሰት ሳይሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እና በብዛት የሚያጋጥም ስጋት ሆኗል።

እንደ ሀገር ዕገታ ተፈጸመ ሲባል መስማት የተለመደ ወደ መሆን ተሻግሯል፡፡ የጭነትም ሆነ የሰው መጓጓዣዎች የዕገታ ሰለባ ስለመሆናቸው በሰፊው ይሰማል፡፡ ከኢንዱስትሪዎች እስከ ቤተ እምነቶች የዕገታ ወንጀል ተቃጣባቸው መባሉ ተለ ምዷል ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121860
👍14
 
National Bank of Ethiopia (NBE) amends the limit of Birr and foreign currency holdings within the territory of the country.

The Limits on Birr and Foreign Currency Holding in the Territory of Ethiopia (as Amended) Directive No. FXD/87/2024, “hereinafter the New Directive,” replaces the previous FXD/81/2022 Directive coming into effect on February 22, 2024.  A significant change introduced by the new Directive is the exemption for transit passengers from declaring their foreign currency holdings. This applies to individuals who stay for a maximum of 24 hours in Ethiopia and continue their journey on the same or different aircraft.
Other than the particular change regarding transit passengers, the new Directive maintains the limits on Birr and foreign currency holding in Ethiopia set by the previous directives. Accordingly, residents entering or leaving Ethiopia may hold up to a maximum of 3000 ETB per trip. However, individuals traveling to Djibouti are allowed a higher limit of 10,000 ETB.
Likewise, the new Directive, just like the previous ones, requires Ethiopian residents to convert any foreign currency brought into the country at authorized forex bureaus within 30 days. If the amount exceeds 4000 USD, a customs declaration is mandatory. However, foreign nationals of Ethiopian origin or Ethiopian Nationals residing abroad and entering the territory of Ethiopia with the aim of staying for more than 90 days are permitted to hold foreign currency with a maximum limit of 10,000 USD provided that a customs declaration can be provided. If the amount exceeds or is equivalent to 10,000 USD, the person is required to deposit the foreign currency into his/her Non-Resident Foreign Currency Account or Foreign Exchange savings account within 90 days from the date of entry. The new Directive also maintains the previous provisions of the amended Directive that allows Ethiopian residents to travel abroad with foreign currency, provided they present bank advice for its purchase within 30 days from the date of the bank advice.  @NegereFej
https://t.me/NegereFej
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ያለውን የብር እና የውጭ ምንዛሪ ይዞታ ገደብ አሻሽሏል።

በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የብር እና የውጭ ምንዛሪ አያያዝ ገደብ (በተሻሻለው) መመሪያ ቁጥር FXD/87/2024 "ከዚህ በኋላ አዲሱ መመሪያ" ከየካቲት 22 ቀን 2024 ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውን የFXD/81/2022 መመሪያ ይተካል። በአዲሱ መመሪያ የወጣው ጉልህ ለውጥ ተሳፋሪዎች የውጭ ምንዛሪ ይዞታቸውን ከማወጅ ነፃ መሆናቸው ነው። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ቢበዛ ለ24 ሰአታት የሚቆዩ እና በተመሳሳይ ወይም በተለያየ አውሮፕላን ጉዟቸውን የሚቀጥሉ ግለሰቦችን ይመለከታል። ትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተ ከመጣው ለውጥ በተጨማሪ አዲሱ መመሪያ በኢትዮጵያ በቀድሞው መመሪያ የተቀመጠውን የብር እና የውጭ ምንዛሪ ይዞታ ላይ ገደብ አስቀምጧል። በዚህ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ወይም የሚወጡ ነዋሪዎች በአንድ ጉዞ እስከ 3000 ETB ሊይዙ ይችላሉ። ነገር ግን ወደ ጅቡቲ የሚጓዙ ግለሰቦች ከፍ ያለ ገደብ 10,000 ETB ተፈቅዶላቸዋል። እንደዚሁም አዲሱ መመርያ ልክ እንደቀደሙት ኢትዮጵያውያን ነዋሪ የሆኑ የውጭ ምንዛሪ በተፈቀደላቸው ፎሮክስ ቢሮዎች በ30 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲቀይሩ ያስገድዳል። መጠኑ ከ4000 ዶላር በላይ ከሆነ፣ የጉምሩክ ማስታወቂያ ግዴታ ነው። ነገር ግን የውጭ ሀገር ዜጎች ወይም ኢትዮጵያውያን ከ90 ቀናት በላይ ለመቆየት በማለም በውጭ ሀገር የሚኖሩ እና ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የጉምሩክ ማስታወቂያ እስካልተፈቀደ ድረስ ከፍተኛው 10,000 ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንዲይዙ ተፈቅዶላቸዋል። ገንዘቡ ከ10,000 ዶላር በላይ ከሆነ ወይም ከ10,000 ዶላር በላይ ከሆነ ግለሰቡ የውጭ ገንዘቡን ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 90 ቀናት ውስጥ ነዋሪ ያልሆነው የውጭ ምንዛሪ አካውንት ወይም የውጭ ምንዛሪ ቁጠባ ሂሳብ ማስገባት ይጠበቅበታል። አዲሱ መመርያ ባንኩ ምክር ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለግዢው የባንክ ምክሮችን ካቀረቡ በተሻሻለው መመሪያ ቀደም ሲል የወጣውን የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በውጭ ምንዛሪ እንዲጓዙ የሚያስችላቸውን ድንጋጌዎች አጽንቷል። #Google translation
https://t.me/NegereFej
#ነገረፈጅ #Negerfej
👍5
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም። ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።

ሰ/መ/ቁጥር 215444 | ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም


👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍10🥰3
Forwarded from ሕግ ቤት
ሰ/መ/ቁጥር 220553 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም
ከተሽከርካሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ ስላስረከበኝ በተሽከርካሪው ሰርቼ ማግኘት ያለብኝን ገቢ እንዲከፍለኝና ውሉ እንዲሰረዝ በሚል በከሳሽ የተጠየቀ ዳኝነት እንደውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ካሳ እንዲከፈልና እና ውሉ እንዲሰረዝ (actions for cancellation of a contract and damage) የቀረበ ክስ በመሆኑ በክሱ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ 10 ዓመት የይርጋ ጊዜ እንጂ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2298 ስር የተደነገገዉ አይደለም።
👍19
ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው ሞግዚትና አስተዳዳሪ የመሆን መብታቸው ሊከበር የሚችለው ለህፃናቱ ጥቅምና ደህንነት እስከሰሩ ወይም ሊሰሩ የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ ነው ።

አባት ከመወለዱ በቀር አይቶት የማያውቅ ልጅ እናቱ በምትሞትበት ጊዜ ለልጅ ጥቅም ሳይሆን በንብረቱ ለመገልገል በማሰብ ሞግዚት እና አስተዳደሪ እንዲሆን ቢጠይቅ ከህገመንግስቱ አንቀፅ 36 አንፃር የህፃናትን ጥቅም ለማስጠበቅ ተብሎ ተከልክሎ ሌላ ሰው ሊሾም ይገባል።
የሰ/መ/ቁ23632 ቅፅ 5
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍3
የትምህርት_ማስረጃ_ማረጋገጫ_እና_የአቻ_ግመታ_መመሪያ_990.pdf
5.5 MB
Educational Credentials Authentication and Equivalency Directive No 990/2024
ትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ
👍14🤬1
 ክርክሩ የስራ ክርክር ሲሆን የምድብ ችሎትን ስልጣን በተመለከተ ያቀረበው መቃወሚያ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 222 መሰረት አንድ ከሳሽ በክስ አቤቱታው ላይ የተከራካሪ ወገኖች ሙሉ አድራሻ መገለፅ አለበት፡፡
ይህ የሚሆንበት ዋናው ጉዳይ የሚታይበትን ምድብ ችሎት ለመለየት እና ባለጉዳዮች በፍርድ ቤት አሰራር በሚደረግ ምደባ እንጂ በግል ዳኛና ምድብ ችሎቶችን እንዳይመረጡ ለማስቻል ነው፡፡ በዚህም መሰረት የአመልካች አድራሻ የካ ክፍለ ከተማ ሲሆን የተጠሪ አድራሻ ደግሞ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነው ሆኖ እያለ ጉዳዩ በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለዉና ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠዉ አሰራር መሰረት መዝገቡ ለየካ ምድብ ችሎት እንዲተላለፍ በማለት ነው።
ችሎቱ ይህን አስመልክቶ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚከተለው ነው።
አሁን ባለዉ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በፌዴራል ደረጃ ያለዉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንድ ፍርድ ቤት ብቻ እንደሆነና የሚያስችለዉም በአዲስ አበባ እና በድሬ ዳዋ ከተሞች እንደሆነ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/3 ፣ ከአንቀጽ 14-16 እና 30/2 ስር ከተደነገጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በየክፍለ ከተማዉ ያሉት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች በሕግ የአካባቢ(የግዛት ክልል)ሥልጣናቸዉ ተወስኖ የተደረጁ ሳይሆኑ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ተደራሽ ለመሆን በአስተዳደራዊ ዉሳኔ የተዋቀሩ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም በሬጅስትራር በኩል መዛግብቶች ሲከፈቱ ምድብ ችሎቶቹ የተዋቀሩበትን ዓላማ በሚያሳካ መልኩ እየታየ መዝገቦች እንዲከፈቱ መደረግ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የአንድ ክስ መዝገብ የተከሳሹ አድራሻ ከሚገኝበት ክፍለ ከተማ ዉጭ በሆነ ምድብ ችሎት ዘንድ ከተከፈተ ምድብ ችሎቱ በአንድ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ማዕቀፍ ዉስጥ ሆኖ ጉዳዩን የሚዳኝ በመሆኑና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአካባቢ(የግዛት ሥልጣን)በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በመላዉ የከተማ አስተዳደሩ ግዛት ክልል ዉስጥ በመሆኑ ክሱ የቀረበለት ምድብ ችሎት ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን የለዉም ተብሎ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም፡፡

አመልካች ምድብ ችሎትን መምረጥ ዳኛን እንደመምረጥ የሚቆጠር ነዉ በማለት ያነሳዉን ክርክር በተመለከተም አንድ ዳኛ ከባለጉዳዩ ወይም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ስላለዉ ጉዳዩን የገለልተኛነት እና የዳኝነት ነጻነት መርህ ጠብቆ ለመዳኘት አይችልም የሚባል ከሆነ ዳኛ ከችሎት እንዲነሳ የሚጠየቅበት ሥነ ሥርዓት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 33 እና 34 ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡በመሆኑም አመልካች ጉዳዩን ከዳኘዉ ምድብ ችሎት ተገቢነት ጋር በተያያዘ ያቀረበዉን ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ባለመቀበሉ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡
የሠ/መ/ቁጥር 205068 ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም የምድብ ችሎት ስልጣን
በአብርሃም ዮሀንስ ሎው ኮርነር ቴሌግራም ገጽ ተገኘ
ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ።

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


👉የቴሌግራም ቻናል 👈

👉Facebook Page 👈

👉YouTube 👈

0920666595
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👍132