አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation)

ታዋቂው የስኬትና የመልካም ስብእና አስተማሪ ብራያን ትሬሲ ስለ አንድ የማይለወጥ ሕግ ይነግረናል፡፡ ይህንን ሕግ፣ የማከማቸት ሕግ (the law of accumulation) በማለት ይጠራዋል፡፡ ሕጉ እንደዚህ ይላል፡-

“ማንኛውም የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ ወደ ክሬዲት ወይም ደግሞ ወደ ዴቢት በመግባት ይቆጠራል“።

ከዚህ ውጪ ምንም ስሌት የለም፡፡ ከራስ በራስ ጋር ባለን ግንኙነት እሳቤም ሆነ አንዳንድ ልማዶች አንጻር ስንመለከተው የምናደርገው ነገር ሁሉ ወይ እንድናከማች ወይም እንድናባክን ያደርገናል፡፡

ዛሬ በግዢ፣ በሽያጭ፣ በመስጠት፣ በመቀበልና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ከገንዘብ ጋር የነበራችሁ ንክኪ አስቡት ይህ ሂደት ወይ ክሬዲት ተጨምሮላችኋል ወይም ዴቢት ሆኖ ተቀናሽ አድርጋችኋል፡፡

ከሰዎች ጋር ባለንም ግንኙነት ስሌቱ ይኸው ነው፡፡ የምደርጋቸው ነገሮች፣ ከማድረግ የምንከለከላቸው ነገሮች፣ የምንናገራቸው ነገሮች . . . በሙሉ ወይ ጨምረውልናል ወይም ቀንሰውብናል፡፡

ሁኔታዎችን በዚህ መልኩ ማየት ስንጀምር ለምናደርጋቸውም ሆነ ለማናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እንድንንቀሳቀስ ያግዘናል፡፡

ካደረግን ወይም ካላደረግን፣ ከተናገርን ወይም ዝም ካልን በኋላ ስለወጤቱ ከማሰብና ከመጨነቅ ቀድ ሞውኑ ይህ ነገር የሚታሰብልኝ ወደ ክሬዲት ነው ወይስ ወደ ዴቢት ብለን እናሰብ፡፡
via #Dreyob በዶ/ር እዮብ
#Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
https://t.me/Ethiopialegalinfo
ማንኛውም #የመንግሥት ሠራተኛ ለጋብቻ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ሰባትም(7) የሥራ ቀናት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ 1064/2010 አንቀፅ 45

ማንኛውም #የግል ድርጅት ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም ከክፍያ ጋር ለ ሶስት(3)የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 81 (1)(U)(ለ)
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
#NegereFej #ነገረፈጅ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሠራተኛ እና አሠሪዎች ማኅበራትን በተመለከተ በስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ለተደረገ ጥናት መረጃ የሰጡ ባለሙያዎች በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈፀም አስረድተዋል።ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ አነስተኛ ደመወዝ ክፍያ፣ ያለምንም ክፍያ ትርፍ ሰዓት ማሠራት እና ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ የደኅንነት እና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ሳይሟሉ እንዲሠሩ መገደደ ከመብት ጥሰቶቹ መካከል ተጠቀሱ ናቸው።

ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት እንዳላቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 43 ስር ተደንግጓል።
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
“400 የኢቢሲ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳላቸው” ያጋለጠው ግለስብ ከሥራ “ተባረረ”

ዓርብ የካቲት 8 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) ለዘጠኝ ዓመታት ያገለገለው ወገን አበበ የተባለ ግልሰብ በኢቢሲ የተለያየ የሥራ ዘርፍ ላይ ያሉ “400 የሚሆኑ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ” እንዳላቸው አጋልጠሃል በሚል ከስራ መባረሩን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በወገን አበበ ላይ “ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት” ወንጀል ክስ የመሰረተበት ሲሆን፤ ወገን አበበ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው ሠዎችን ሥም ዝርዝር በማቅረብ ተከራክሮ ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 7 ቀን 2016 በዋለ ችሎት ወገን አበበ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል።

“በተቋሙ ውስጥም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የሚያነሳና ቅሬታ የሚያቀርብ ካለ ከስራhttps://addismaleda.com/archives/36171
———
986_ስለ_ውጭ_ድርጅቶች_ምዝገባና_አስተዳደር_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር_986_2016_.pdf
1.4 MB
ስለ ውጭ ድርጅቶች ምዝገባና አስተዳደር የወጣ መመሪያ
ቁጥር 986/2016
A DIRECTIVE ON THE REGISTRATION AND
ADMINISTRATION OF FOREIGN ORGANIZATIONS
NO . 986 /2024
https://t.me/Ethiopialegalinfo
#Ethiopialegalinfo
በ24 አመት ውስጥ 17 ጊዜ የወሊድ ፈቃድ የወሰደችው ጣሊያናዊት ተከሰስች

ትራስ በሆዷ ይዛ አረማመዷንም የነፍሰጡር በማስመሰል ለአመታት ቀጣሪዎቿን ስታጭበረብር የቆየችው የ50 አመቷ ጎልማሳ አንድም ልጅ አልወለደችም።

https://bit.ly/3SGyU1q
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Women have the fundamental right to move freely and safely from one place to another, including in their use of public transportation services.

ሴቶች የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን መጠቀምን ጨምሮ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በነፃነት እንዲሁም ደህንነታቸው ተጠብቆ የመንቀሳቀስ መሰረታዊ መብት አላቸው።
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
ለ:- ሁሉም መገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሙሉ
አዲስ አበባ

ጉዳዩ:- የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጠን ስለመጠየቅ
ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ተቋማችን የፌዴራል የፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ባለ ድርሻ ካላት ጋር በመሆን ʺበኢትዮጵያ እና ሶማሌ ላንድ መካከል የባሕር ዳርቻ በሊዝ ለመጠቀም የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት አለም አቀፍ ሕጋዊ ተቀባይነት እና አንደምታˮ በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ጥናት ጽሑፍ የሚቀርብበትና ውይይት የሚደረግበት መድረክ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና የሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል የሚያካሄድ ይሆናል፡፡
በመሆኑም የተለያዩ የፍትሕ ዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንስቲትዩታችን ባልደረቦች፣ ዳኞች፣ አቃቤ-ህጎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሕግ ባለሙያዎች የሚገኙበትን መርሃ ግብር ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ቸርቸር ጎዳና በሚገኘው ግራንድ ኤሊያና ሆቴል በመገኘትና ሪፖርተሮችን ወደ ስፍራው በመላክ እንዲዘግቡልንና እና በሚዲያችሁ እንድታሰራጩልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ይግባኝ ማስፈቀጃ/ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
#በሕጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326
የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ድምጽ ገጽ ተገኘ
#የሕግመረጃ #አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
የትዳር አጋሩን የተለያየ የሰውነት ክፍል በቢላዋ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ አስራት ተቀጣ

ከሌላ ወንድ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለሽ በሚል ምክንያት የትዳር አጋሩን በቢላዋ ጭቅላቷን፣ አንገቷን፣ ፊቷን፣ የግራ ክንዷንና ጣቷን፣ ደረቷንና ጀርባዋን በመውጋት የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስሜነህ ግርማ በለጠ የተባለው ተከሳሽ ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡20 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስኮ ሰፈረ ወርቅ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የትዳር አጋሩ የሆነችው ሟች ማህሌት ፍቃዱ ላይ ወንጀሉን የፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።

ግልሰቡ ይህንን በማድረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ የቆየ ሲሆን ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ባለማቅረቡና የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሽ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።
#TikvahethMagazine
#አለሕግ #Alehig
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
የህዝብ ሮሮ አሁንም የሚሰማበት ተቋም
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ፓስፖርት ፈልገው ወይም በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል።
ወጣት፣ ሴት፣ ወንድ፣ ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም «ፓስፖርት ፈልገው ነው?» እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱን ለመመልከት በመሥሪያ ቤቱ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎችም ይህንን መመልከት ችለዋል፣ ሆኖም በወቅቱ መረጃ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ በፖሊሶች ክልከላ ምክንያት አልተሳካም።
አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ አሠራር ዘርግቻለሁ ቢልም አሁንም በርካታ ተገልጋዮችን አገልግሎቱ ደጃፍ ላይ መመልከት አልቀረም።
ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት እና ፎቶ ለመነሳት በመሥሪያ ቤቱ መገኘት ግዴታቸው በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=121413
ሳይናዘዝ የሞተ ሰዉ ወራሾች ተዋረድ(hierarchy of intestate succession)

በ/ፍ/ሕ/ቁ አንቀፅ 842 መሰረት ልጆች የመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሾች ናቸው። ወራሾቹም የሟችን ድርሻ እኩል እንደሚካፈሉ ይሄ ድንጋጌ ያሳያል።  ከልጆቹ አንዱ ሞተዉ እንደሆነና ልጆች አፍርተው እንደሆነ ልጆቻቸውን በሟች እግር ተተክተዉ እንደሚወርሱ የዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ 3 ያመለክታል።

ሟች ምንም አይነት ወደታች የሚቆጠር ተወላጆች ከሌሉት አባት እና እናቱ በሁለተኛ ደረጃ ወራሽነት ይጠራሉ። እናትና አባትም የሟችን ንብረት እኩል እንደሚካፈሉ ከፍ/ሕ/ቁ 843 እና 844(1) መገንዘብ ይቻላል። ከሟች ወላጆች አንዱ ቀድመዉ የሞቱ እንደሆነ ልጆቻቸው ወይም የነርሱ ተወካዮች በእነርሱ እግር ተተክተው ይወርሳሉ።

በሦስተኛ ደረጃ ወራሽነት አያቶች የሚጠሩ ሲሆን ይህም የሚሆነው ሟች ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም አባትና እናት ወይም የነርሱ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ከሌለዉ እንደሆነ ከ/ፍ/ሕ/ቁ 845(1) መገንዘብ ይቻላል።

ከላይ የተጠቀሱት ወላጆችም ሆነ ተወላጆች በማይኖሩበት ጊዜ ቅድመ-አያቶች በአራተኛ ደረጃነት ለዉርስ እንደሚጠሩ ከፍ/ሕ/ቁ 847 እንገነዘባለን።

በመጨረሻም ምንም  አይነት ዘመዶች የሌሉ እንደሆነ የሟችን ሀብት የወራሽነት መብት ለመንግስት/ሐገር ይተላለፋል።

በሕሊና ጌታቸው የሕግ ቢሮ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
Forwarded from ሕግ ቤት
ውጤትዎን ይመልከቱ!

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ውጤትዎን ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/

#tikvahuniversity