አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Opportunity to study in the USA for free!

🇺🇸Boston University Presidential in the USA 2024 | Fully Funded

University: Boston University
Eligible nationality: All Nationalities
Award country: United States
Last Date: 1 December 2023

Benefits:

1) Scholarship coverage: $25,000
2) International students will get a full tuition fee waiver for their undergraduate degree.
3) This is a renewable scholarship, so every year scholarship will be renewed for those students who will meet the criteria.
4) International students will also get additional undergraduate fee coverage.
5) Students will get an opportunity to become a part of Boston University.

👉👉 Apply Link:
https://bit.ly/3rsXubW
👆👆👆👆
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/


Telegram Channel

https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
የቀጠለ......👇👇👇👇 https://youtu.be/90IUZnJOMDg?si=etsMGJhfIzx7Shpw
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ድጋፍ ፍጪ ሰራተኞች የምሳ እቃ
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሚሰራ አንድ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ በየጊዜው የምሳ ሰዓት ሲደርስ ስራውን አጠናቆ ለምሳ ሲወጣ እጁን በኪሱ ውስጥ ከቶ ከጊቢው ወጥቶ ሲሄድ እመለከታለው።

አንድ ቀን በተመሳሳይ ከጊቢ ወጥቶ የስራ ሰዓት ሲደርስ ሲመለስ አገኘሁትና ጠጋ ብዬ ጠየኩት።

ሁል ጊዜ ስመለከትህ ምሳ ሰዓት ከጊቢ ትወጣለህ ውጪ ነው ወይስ ቤትህ ሄደህ ነው ምሳ የምትበላው? በማለት ጠየኩት

''አይ አንቺ ''ብሎ ፈገግ አለ

የምሬን እኮ ነው አልኩት መልስ እየጠበኩ

''ዝም ብዬ ዞር ዞር ብዬ ነው የምመለሰው ያው ለሰዓት ማዳረሻ '' አለኝ

አልገባኝም አልኩት በድጋሚ

''አይ ታሪክዬ'' አለ በሀዘን ስሜት እየተዋጠ

ቀጠል አደረገና ''1700 ብር ነው የወር ደሞዜ ከዝች ደሞዜ ላይ የቆርቆሮ ቤት 1400 ብር ተከራይቼ ነው የምኖረው ታድያ በምሳ እቃ ምኑን ልቋጥር ፣ ከየትስ አምጥቼ ምግብ ቤት እገባለሁ ብለሽ ነው ያው ሰዓት እስኪደርስ ልደታ ቤተክርስቲያንን ተሳልሜ ትንሽ ቁጭ ብዬ ምሳ ተመግቦ እንደመጣ ሰው ዞር ዞር ብዬ ነው የምመለሰው'' አለኝ

'',በቀን አንዴ ማታ ላይ ትንሽ ከተመገብን አይበዛብንም ብለሽ ነው ''

አለ በቀልድ መልክ እንዳልከፋው ለማስመሰል ፈገግ እያለ

ወዲያው ውስጤ በሀዘን ተሞላ ምነው ባልጠየኩት ብዬ እራሴን ወቀስኩኝ

በዚህ መልኩ በተመሳሳይ ህይወት ውስጥ በፍርድ ቤቱ በድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ላይ በሚከፈላቸው አነስተኛ ደሞዝ ህይወታቸውን እየገፉ ያሉ በርካቶች ናቸው።

በዚህ ኑሮና በዚህ ደሞዝ ቤተሰብ የሚመሩ ህጻናት ልጆች ያሏቸውም ይገኛሉ።

የጠ /ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በኃላፊነት ተሹመው የነበሩት የቀድሞ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊና ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ችግር ተረድተው '' የደሞዛችንን ያስተካክሉልን ይሆናል ''ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰራተኞች በርካቶች ነበር።

ይሁንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ደሞዝ በሚመለከት ምንም ማስተካከያ ሳይደረግ ሁለቱም ፕሬዝዳንቶች በገዛ ፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ተሰማ።

ከዛ በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር ነበሩ የተባሉት የቀድሞ ጠበቃ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ፣በዳኝነት ዘርፍ ላይ ለበርካታ ጊዜያት አገልግለዋል የተባሉት ወይዘሮ አበባ እምቢ አለ እንደ ቅደም ተከተላቸው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

በጥር 15 ቀን 2015 ከቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች የስራ ኃላፊነት ርክክብ አድርገው ስራቸውን ጀመሩ ከዚህ በኋላ ደግሞ በድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ዘንድ ሌላ ተስፋ ተጫረ

ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ/ ም ደግሞ ሌላኛው የፍርድቤቶች ሰራተኞችን ተስፋ የሰነቀ ፌሽታን የፈጠረ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ መፅደቁ ተሰማ ፣

ይህ ከተሰማ አሁን አምስት ወራት ተቆጠረ

ይሁንና ደንቡ ተግባራዊ ሆኖ ጠብ የሚል ነገር ይኖራል በሚል ተስፋ በተለመደው በኑሮ ጫና ውስጥ ሆነው የህይወታቸውን ውጣ ውረድ የሚገፉት ሰራተኞች ተግባራዊነቱን በተመናመነ ተስፋ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ተስፋ የቆረጡት ደግሞ ስራቸውን እየለቀቁ የተሻለ እንጀራ ፍለጋ ላይ ተሰማርተዋል።

''ያም መጣ ይህ ለራሱ እንጂ ለኔ የሚያስብ የሚጠቅም የለም '' በማለት ፊታቸውን ወደ ፈጣሪ ያዞሩና ከነገ ዛሬ ይሻል ይሆን ብለው ፈጣሪያቸውን ተስፋ ያደረጉም አሉ።

ለማንኛውም የተቋማት መሪዎች በቤታችሁ ወይም በሆቴል ስትመገቡ፣ስትዝናኑ፣ውስኪም ስታፈሱ ፣በዝቅተኛ ደሞዝ የሚሰቃዩ ሰራተኞችን አስታውሱ እላለሁ።

በኔ በኩል አበቃሁ
Via #TarikAdugna
Tarik Adugna
በታረክ አዱኛ ፌስቡክ ገፅ ላይ ተገኘ
ሰላም ለሀገራችን ህዝብ ይሁን
ይድረስ #አለ_ህግ #Ale_Hig አባላት እና ደጋፊዎች ፣
ሼር በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩ።
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏

@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
የማስረጃ ዓይነቶች እና ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸው ፍሬ ነገሮች👇

የአንድን ፍሬ-ነገር መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ የሚቻለው ማስረጃ በማቅረብ ነው፡፡ ማስረጃ በሰው ምስክሮች፣ በዘገባ፣ በሰነድ፣ ተጨባጭነት ባላቸዉ ሊታዩና ሊዳሰሱ በሚችሉ ነገሮች እና በኤግዚቢት መልክ ሊቀርብ ይቻላል፡፡ አቀራረቡም በሕግ በተደነገገው መሰረት ነው፡፡ በክርክር ሂደት ማስረጃ የማያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍሬ ነገሩ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች ስላሉ ነዉ፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ ስለ ማስረጃ ዓይነቶችና ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንመለከታለን፡፡

1. የማስረጃ ዓይነቶች
ማስረጃ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል ከሚቻልባቸው ዘዴዎች እና ማስረዳት ከሚፈለገው ፍሬ ነገር ወይም መደምደሚያ ጋር ማስረጃው የሚኖረውን ግንኙነትን መሠረት በማድረግ በተለያዩ መንገዶች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

 ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከምንጠቀምበት ዘዴ አንጻር

ሀ. የሰው ማስረጃ
ሰዎች በአካል ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለችሎት መረጃ የሚሰጡበት መንገድ ሲሆን ፍሬ ነገሩን ለፍርድ ቤቱ የሚገልፁት በንግግር ወይም በምልክት ነው፡፡ ይህም የምስክርነት ቃል ይባላል፡፡ የሰው ማስረጃዎች ቀጥተኛ ምስክር፣ የአከባቢ ምስክርና የባለሞያ ምስክር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ለ. የሰነድ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት በላዩ ላይ የተፃፈበት፣ የተሳለበት ወይም ማናቸዉም ዓይነት ምልክት የተደረገበት ሲሆን ለምሳሌ ውሎች፣ ቼኮች፣ ለፖሊስ ወይም ለፍርድ ቤት የተሰጠ የዕምነት ቃል የተመዘገበበት፣ በጽሁፍ የተገለፀ የላብራቶሪ ወይም የህክምና ምርመራ ውጤት የሰነድ ማስረጃዎች ናቸው፡፡
ሐ. ገላጭ ማስረጃ
ይህ የማስረጃ ዓይነት ፍርድ ቤት እንዲያየውና ግንዘቤ እንዲወስድበት የሚቀርብ ማስረጃ ነው፡ ለምሳሌ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ወንጀል ለመፈፀም አገልግሎት ላይ የዋለ መሣሪያ በማስረጃነት ሲቀርብ ገላጭ ማስረጃ ይባላል፡፡
 ማስረዳት ከተፈለገው ፍሬ ነገር አንጻር፤

 ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ

ማስረጃ ቀጥተኛ ነዉ የሚባለው አንድን በጭብጥነት የተያዘ ፍሬ ነገር ወይም የተወሰደን መደምደሚያ ትክክለኛነት በቀጥታ ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል የሚቀርብ ሲሆን ነዉ፡፡ ከዚህ አንፃር ምስክር ቀርቦ በጭብጥ የተያዘው ፍሬነገር መኖሩን ወይም አለመኖሩን ራሱ በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት በማየት፣ በማሽተት፣ በመቅመስ፣ በመስማት ወይም በመዳሰስ ያወቀ መሆኑን የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ በሰነድ ማስረጃ በኩልም በማስረጃነት የቀረበው ሰነድ በጭብጥ የተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖርን ወይም የተደረሰበት መደምደሚያ ትክክለኛ መሆኑን ሰነዱ ራሱ በቀጥታ ያረጋግጣል ወይም ያስተባብላል በሚል የቀረበ ከሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡ ለምሳሌ በቂ ስንቅ ሳይኖረው ቼክ ፈርሞ ሰጥቷል በሚል ገንዘብ እንዲከፍል በተከሳሽ ላይ ለቀረበ ክስ ከሳሽ ቼኩን በማስረጃነት ያቀረበ ቢሆን ተከሳሹ ስለመፈረም አለመፈረሙ እና ስለ ገንዘቡ ልክ ቼኩ በቀጥታ የሚናገር ስለሆነ ቀጥተኛ ማስረጃ ይባላል፡፡

 ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ
ማስረጃ ቀጥተኛ ያልሆነ ነዉ የሚባለው ከሁለት ሁኔታዎች አንፃር ነዉ፡- አንደኛዉ ማስረጃ ያስረዳል የተባለዉን ፍሬ ነገር ምንጭ ማስረጃዉ ራሱ በቀጥታ ያወቀዉ ሳይሆን ከሌላ ያገኘዉ ወይም የተረዳዉ ሲሆን ነዉ፡፡ ምስክር ሌላ ሰዉ የገለፀለት መሆኑን ጠቅሶ የሚመሰክር ሲሆን ቀጥተኛ ሳይሆን የስሚ ስሚ ማስረጃ (Hearsay Evidence) ይባላል፡፡ የስሚስሚ ማስረጃን ቀጥተኛ ያልሆነ የሚያሰኘዉ ማስረጃዉ ፍሬ ነገሩን የሚገልፀዉ ራሱ በቀጥታ እንዳወቀ ሳይሆን ከሌላ ሰዉ የሰማዉ ወይም ከሰነድ ያነበበዉ በመሆኑ ነዉ፡፡ በሰነድ ማስረጃም በኩል የስሚ ስሚ የሚያሰኘዉ ማስረጃ ሆኖ የቀረበዉ ሰነድ ላይ የተገለፀዉ ፍሬ ነገር አዉቃለሁ በሚል በሌላ ሰዉ የተዘጋጀ ሲሆን ነዉ፡፡

ሁለተኛዉ ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ ነዉ የሚባልበት ሁኔታ የሚያጋጥመዉ አካባቢያዊ ማስረጃ (Circumstantial Evidence) የቀረበ እንደሆነ ነዉ፡፡ አካባቢያዊ ማስረጃ በጭብጥ ስለተያዘዉ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር በቀጥታ አይነግረንም፡፡ ይልቁንም የተወሰኑ ፍሬ ነገሮችን መኖር ወይም አለመኖር በማረጋገጥ ከዚህ ተነስተን በጭብጥ የተያዘዉን ፍሬ ነገር በተመለከተ አንድ ዓይነት መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ የሚያደርግ ነዉ፡፡
የማስረጃዉ ቀጥተኛ ወይም አካባቢያዊ መሆን አለመሆኑን መለየት በማስረጃ ምዘና ጊዜ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡
1. ማስረጃ ስለማያስፈልጋቸዉ ፍሬ ነገሮች
ከፍሬ ነገሮቹ የተለየ ባህሪ ወይም የሚያከራክር ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ የማይሆንባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነሱም፡-
ሀ. ፍርድ ቤት ግንዛቤ ሊወስድባቸዉ የሚችሉ ወይም የሚገቡ ፍሬ ነገሮች፣ ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 3/1987 መሠረት በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የወጡ ነገሮችን ፍርድ ቤቶች ሊቀበሏቸዉ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡ በነጋሪት ጋዜጣ ላይ የተገለፀ ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ሌላ ማስረጃ መቀበል አያስፈልግም፡፡ ጋዜጣዉን በመመልከት ብቻ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል፡፡
ለ. በፍርድ ቤት በሚደረግ የክርክር ሂደት በተከራካሪ ወገን የታመኑ ፍሬ ነገሮች፣
ሐ. ጠቅላላ እዉነታዎች (Universal Truth)፣
መ. የሕግ ግምቶች (Presumptions) ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ (የተወለደ) ልጅ አባቱ ባልየው እንደሆነ ህጉ ግምት ይወስዳል፡፡

በአጠቃላይ ግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች ያስረዱልናል የሚሏቸዉን ማስረጃዎች ወይም ማስረጃ ባይቀርብባቸዉም በሕግ መሠረት የሚወሰኑትን ለይቶ ለማቅረብ የማስረጃ ዓይነቶችን እና ማሰረጃ የማያስፈለጋቸዉን ፍሬነገሮች ማወቁ ተገቢ ነዉ፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/


Telegram Channel

https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
የሽያጭ ውል👇👇👇👇👇👇
የሰዉ ልጆች በዚች ምድር ላይ ሲኖሩ የተለያዩ ህጋዊ ውጤት ያላቸውን ተግባራት ያከናዉናሉ፡፡ ከእነዚህ ህጋዊ ዉጤት ከሚያስከትሉ ተግባራት አንዱ የሽያጭ ዉል ነዉ፡፡ የሽያጭ ዉል ሰዎች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የሕይወት መስተጋብራቸው ዉስጥ ከሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት አንዱ ሲሆን የጠቅላላው የውል ግዴታ አንዱ ዘርፍ ነዉ፡፡
በዚህ አጭር ፅሁፍ የሽያጭ ዉልን ምንነትና አፈፃፀም፣ የሻጭና የገዥ ግዴታዎች እንዲሁም የውል አለመፈፀም የሚያስከትለውን ሕጋዊ ውጤቶች እንመለከታለን፡፡

የሽያጭ ውል ምንነት

በፍትሐብሔር ህጋችን ቁጥር 2266 መሰረት ሽያጭ ማለት ሻጭ የሆነው አንዱ ወገን ገዥ ለሆነው ሌላ ወገን ዋጋው በገንዘብ የተወሰነውን አንድ ነገር ገዢው ሊከፍለው ግዴታ በገባበት መሰረት ሊያስረክብና ሀብትነቱን ሊያስተላልፍ የሚገደድበት ውል ነው፡፡ በህጉ ድንጋጌ መሰረት ሽያጭን ለማከናወን መሟላት ያለባቸው ፍሬ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡-

ውል መሆኑ፡- ሽያጭ በሻጭና በገዢው መካከል የሚደረግ ውል እንደመሆኑ መጠን የውልን መሰረተ ሀሳቦችና መመዘኛዎች ተከትሎ መፈፀም የሚገባው መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ ይህም ማለት ውልን ለመመስረት አስፈላጊ የሆኑትን እንደ የተዋዋዮች ነፃ ፈቃድ፣ የተዋዋዮች ችሎታ መኖር፣ የውሉ ፍሬ ነገር በእርግጠኝነት የሚቻል፣ ህጋዊና ሞራላዊ መሆን እና የውሉ ፎርም ወይም ቅርፅን በሚመለከት የውልን አካሄድ ተከትሎ መከናወን አለበት፡፡

በሁለት አካላት መካከል ስለመከናወኑ፡- የሽያጭ ውል የሚከናወነው በሁለት ወገኖች ማለትም በሻጭ ወገን እና በገዢ ወገን መካከል ነው፡፡

ንብረቱን የማስረከብና ስመሀብቱን የማስተላለፍ ግዴታ፡- የንብረቱ ባለቤት ንብረቱን ለማስረከብ ብቻ ሳይሆን ስመሀብቱንም ለማስተላለፍ ከገዥው ጋር መስማማት ይጠበቅበታል፡፡ ይህም የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

በንብረት ላይ የሚደርግ መሆኑ፡- በትርጉሙ ክፍል የሽያጭ ውል በንብረት ላይ የሚደረግ መሆኑን እንደመስፈርትነት አካቶት እናገኘዋለን፡፡ ይህም ማለት የሽያጭ ውል ፍሬ ነገር ንብረት መሆን አለበት ለማለት ነው፡፡

ዋጋው በገንዘብ የተወሰነ መሆኑ፡- አንድ ውል የሽያጭ ውል ለመባል የሸያጩ ፍሬ ነገር የሆነው ንብረት ዋጋው በገንዘብ የተተመነ መሆን ይገባዋል፡፡ በገንዘብ ያልተተመነ ዋጋ ከሆነ የዕቃ ለውጥ ከመሆን አልፎ የሽያጭ ውል መስፈርትን ማሟላት አይችልምና ነው፡፡

እንደማንኛውም የውል ዓይነቶች የሽያጭ ውልም ተዋዋይ ወገኖች (ገዥና ሻጭ) በዕቃው ምንነትና ዋጋ ላይ ተነጋግረው ስምምነት ላይ ሲደርሱ የሽያጭ ውሉ ይመሰረታል፡፡ ይህም ማለት ገዥና ሻጭ በውሉ ፍሬ ነገሮች ላይ ስምምነታቸውን ሲገልፁ ውሉ እንደተፈፀመ ይቆጠራል ማለት ነው፡፡

የሻጭ ግዴታዎች

ዕቃ የማስረከብ ግዴታ፡-

የሽያጭ ውል ከተከናወነ በኋላ ሻጭ የግብይት ምክንያት የሆንውን ዕቃ/ንብረት ለገዥ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ዕቃውን ሲያስረክብም መጠኑንና ዓይነቱን በሚመለከት በውላቸው መሰረት መሆን ይገባዋል፡፡ ሻጩ በመጠን ያነሰ ንብረት ወይም የተለየ ዓይነት ዕቃ ካስረከበ ግዴታውን እንዳልፈፀመ ይቆጠራል፡፡ ዕቃውን የሚያስረክብበት ቦታና ጊዜም ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ ተዋዋይ ወገኖች ዕቃውን የሚረካከቡበትን ጊዜና ቦታ ከወሰኑ በውላቸው መሰረት መሆን የሚገባው ሲሆን ጊዜና ቦታውን ካልወሰኑ ደግሞ ጊዜውን በተመለከተ በመርህ ደረጃ የዕቃው ዋጋ ክፍያ ሲፈፀም ዕቃ የማስረከብ ግዴታውም ወዲያዉኑ መከናወን ያለበት መሆኑን በፍ/ብሔር ሕጉ በቁጥር 2278 ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን በሆነ ምክንያት ይህ ሳይደረግ ቢቀር ገዢው አስረክበኝ ብሎ ሲጠይቅ ሻጩ ወዲያውኑ ማስረከብ የሚገባው ሲሆን የማስረከቢያ ቦታውን በሚመለከት ግን ሽያጩ በተደረገበት ወቅት በነበረው መስሪያ ቤት ወይም መስሪያ ቤት ባይኖረው እንኳን ሻጩ አዘውትሮ በሚጠቀምበት ቤቱ መሆን እንደሚገባው የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2276 እና 2279 በቅደም ተከተል ይደነግጋሉ፡፡

ስመ-ሀብት የማስተላለፍ ግዴታ፡-

የሽያጭ ውል ልዩ መገልጫ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ሻጩ የሽጭ ምክንያት የሆነውን ንብረት ስመ-ሀብትን የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ ይህም ሲባል የባለቤትነትን መብት ያለተጨማሪ ሕጋዊ ሂደት ይዞታን በማስተላፍ ብቻ የሚያሰጡ ንብረቶች እንደ ተራ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የመሳሰሉት ንብረቶቹን በትክክለኛው ጊዜና ቦታ በማስረከብ፣ ልዩ ተንቀሳቃሽ የሆኑትን እንደ ተሽከርካሪ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ደግሞ ለገዥው ከማስረከብም በተጨማሪ የሚመለከተው አካል ጋር አስፈላጊ ሰነዶችን አሟልቶ በማቅረብ ስመ-ሀብትነቱን የማዛወር ሂደት የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡

ዋስትና የመስጠት ግዴታ፡-

ሌላኛው የሻጭ ግዴታ ከተሸጠው ዕቃ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠሩ ችግሮች ለገዥው ዋስትና የመስጠት ግዴታ ነው፡፡ ይህ የግዴታ ዓይነት የሚፈለገው ከዕቃው የባለቤትነት መብት ጋር ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ ከዕቃው ጥራት እና ተስማሚነት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሻጩ ለገዢው ዋስትና የመስጠት ግዴታ ያለበት መሆኑን በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 2282፣ 2287 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እና በየንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/06 አንቀፅ 14(5) ንባብ መረዳት እንችላለን፡፡

የገዥ ግዴታዎች

ገዥም በበኩሉ የራሱ የሆኑ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት የገዥ ግዴታዎች ተብለው የሚታወቁት የዕቃውን ዋጋ የመክፈልና የገዛውን ዕቃ በተገቢው ጊዜ የመውሰድ ግዴታዎች መሆናቸው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2303 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ የዕቃውን ዋጋ የመክፈል ግዴታ ሲባል የገዥው ገንዘብ የመክፈል አቅም ያለው መሆንና የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን ማዘጋጀቱን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን እንደየውሉ ዝርዝርና በአካባቢው ባህል በተለመደው መልኩ መክፍል ግዴታንም ያካትታል፡፡

ልክ እንደ የማስረከብያ ቦታና ጊዜ ክፍያ የሚፈፀምበት ቦታና ጊዜም ወሳኝ በመሆኑ በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ክፍያው የሚፈፀምበት ቦታ በውላቸው ላይ የተገለፀ ከሆነ በዛው ቦታ መፈፀም የሚገባው ይሆናል፡፡ በውላቸው ላይ ከፍያ የሚፈፀመው ሻጭ ዕቃውን ለገዥው በሚያስረክብበት ወቅት ነው የሚል ሀሳብ ካለበት ደግሞ ክፍያው የሚፈፀምት ቦታ ዕቃው የሚረከብበት ቦታ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በውላቸው ውስጥ እነዚህ ዝርዝሮች ከሌሉበት ግን ክፍያው የሚፈፀምበት ቦታ በሻጩ ቤት እንደሆነ ሕጉ ይደነግጋል፡፡ (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2309)
ክፍያ የሚፈፀምበትን ጊዜ በሚመለከት የእጅ በእጅ ሽያጭ በሚሆንበት ወቅት ገዥው ዋጋውን መክፈል ያለበት የገዛውን ዕቃ ሲረከብ ሲሆን ሽያጩ የዱቤ በሆነ ወቅት ደግሞ ዋጋው መከፈል ያለበት በውሉ ተገልፆ ከሆነ በውሉ መሰረት ካልተገለፀ ግን ሻጩ እንደጠየቀ ወዲያዉኑ መሆን ይገባዋል፡፡ (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2311)

የውል አለመፈፀምና ውጤቶቹ

በተዋዋይ ወገኖች የውል አለመፈፀም በሚያጋጥም ጊዜ ሕጉ የውል ግዴታውን ባልተወጣው አካል ላይ ቅጣትና ኪሳራን የሚያስከትል ሲሆን የውል ግዴታውን ለፈፀመው ደግሞ ውሉ እንዲፈፀምለት ወይም ለጉዳቱ ተመጣጣኝ ካሳ የሚያገኝባቸው የተለያዩ መፍትሔዎችን /Remedies/ ያስቀምጣል፡፡
በመሆኑም እንደውሉ ያልተፈፀመለት ተዋዋይ ወገን የሚከተሉት ሦስት መፍትሔዎች ይኖሩታል፡፡ እነዚህም፡- ውልን በግድ ማስፈፀም፣ ውልን ማፍረስ እና የጉዳት ካሳ መጠየቅ ናቸው፡፡ እንደወሉ ያለተፈፀመለት ወገን ወደመፍትሔዎች ከመሄዱ በፊት ውሉን ያልፈፀመውን ሰው ሕጉ በሚፈቅደው አኳኋን የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን በውላቸው ውስጥ ማስጠንቀቅያ መሰጣጣት አስፈላጊ አይደለም ተባብለው ከተስማሙ ማስታወቅያ መስጠት ሳያስፈልግ በቀጥታ ወደ መፍትሔዎቹ መግባት ይቻላል፡፡

ውልን አስገድዶ ማስፈፀም ማለት እንደውሉ ያልፈፀመውን ሰው ከፍላጎቱ ውጪ ማድረግ የሚገባውን እንዲያደርግ ማድረግ ነው፡፡ ሻጩ ዕቃውን የማስረከብ ግዴታውን ካልተወጣና ገዥው የውሉ መፈፀም ልዩ ጥቅም የሚያስገኝለት ከሆነ ገዥውን በህግ አስገድዶ የማስፈፀም መብት እንዳለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2329 ስር ተደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል ገዥው ክፍያውን ሳይከፍል ቢቀርና በንግድ ልማድ መሰረት ሁለቱን ተዋዋዮች በሚያቻችል ሽያጭ ለመሆን የሚችል ካልሆነ በስተቀር ሻጩ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2333 መሰረት ገዥውን እንዲከፍለው በህግ ማስገደድ ይችላል፡፡ ሌላው የውል አለመፈፀም መፍትሄ ውልን ማፍረስ ሲሆን በፍርድ ቤት ወይም በተዋዋይ ወገኖች በራሳቸው መደረግ ይችላል፡፡ ውልን በግድ ከማስፈፀምና ውልን ከማፍረስ በተጨማሪ ለደረሰ ጉዳት ካሳ ማስከፈልም ሌላኛው የውል አለመፈፀም መፍትሔ ነው፡፡ የጉዳት ካሳ የሚከፈለው በውል አለመፈፀም ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ወገን ውሉ ቢፈፀም ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ጥቅም እንዲያገኝ ለማስቻል በማሰብ ነው፡፡

በአጠቃላይ የሽያጭ ውል የጠቅላላ የውል ግዴታ አንድ አካል እንደመሆኑ በመሰረታዊው የውል ሕግ መርሆዎች የሚገዛ ስለሆነ ሰዎች ዕቃ ሲገዙም ሆነ ሲሸጡ ጠቅላላ የውል ሕግ መርሆዎችን እንዲሁም የሽያጭ ውልን የተመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎችን ተከትለው ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ገዢና ሻጭ የገቡትን ግዴታ እንደውሉ መፈፀም ያለባቸው ሲሆን ግዴታው ሳይፈፀም ቢቀር ውል ያልተፈፀመለት ወገን በህጉ የተመለከቱ መፍትሄዎችን መጠቀም ይችላል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/


Telegram Channel

https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆