አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ድጋፍ ፍጪ ሰራተኞች የምሳ እቃ
በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሚሰራ አንድ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ በየጊዜው የምሳ ሰዓት ሲደርስ ስራውን አጠናቆ ለምሳ ሲወጣ እጁን በኪሱ ውስጥ ከቶ ከጊቢው ወጥቶ ሲሄድ እመለከታለው።

አንድ ቀን በተመሳሳይ ከጊቢ ወጥቶ የስራ ሰዓት ሲደርስ ሲመለስ አገኘሁትና ጠጋ ብዬ ጠየኩት።

ሁል ጊዜ ስመለከትህ ምሳ ሰዓት ከጊቢ ትወጣለህ ውጪ ነው ወይስ ቤትህ ሄደህ ነው ምሳ የምትበላው? በማለት ጠየኩት

''አይ አንቺ ''ብሎ ፈገግ አለ

የምሬን እኮ ነው አልኩት መልስ እየጠበኩ

''ዝም ብዬ ዞር ዞር ብዬ ነው የምመለሰው ያው ለሰዓት ማዳረሻ '' አለኝ

አልገባኝም አልኩት በድጋሚ

''አይ ታሪክዬ'' አለ በሀዘን ስሜት እየተዋጠ

ቀጠል አደረገና ''1700 ብር ነው የወር ደሞዜ ከዝች ደሞዜ ላይ የቆርቆሮ ቤት 1400 ብር ተከራይቼ ነው የምኖረው ታድያ በምሳ እቃ ምኑን ልቋጥር ፣ ከየትስ አምጥቼ ምግብ ቤት እገባለሁ ብለሽ ነው ያው ሰዓት እስኪደርስ ልደታ ቤተክርስቲያንን ተሳልሜ ትንሽ ቁጭ ብዬ ምሳ ተመግቦ እንደመጣ ሰው ዞር ዞር ብዬ ነው የምመለሰው'' አለኝ

'',በቀን አንዴ ማታ ላይ ትንሽ ከተመገብን አይበዛብንም ብለሽ ነው ''

አለ በቀልድ መልክ እንዳልከፋው ለማስመሰል ፈገግ እያለ

ወዲያው ውስጤ በሀዘን ተሞላ ምነው ባልጠየኩት ብዬ እራሴን ወቀስኩኝ

በዚህ መልኩ በተመሳሳይ ህይወት ውስጥ በፍርድ ቤቱ በድጋፍ ሰጪ ዘርፍ ላይ በሚከፈላቸው አነስተኛ ደሞዝ ህይወታቸውን እየገፉ ያሉ በርካቶች ናቸው።

በዚህ ኑሮና በዚህ ደሞዝ ቤተሰብ የሚመሩ ህጻናት ልጆች ያሏቸውም ይገኛሉ።

የጠ /ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በኃላፊነት ተሹመው የነበሩት የቀድሞ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊና ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ችግር ተረድተው '' የደሞዛችንን ያስተካክሉልን ይሆናል ''ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰራተኞች በርካቶች ነበር።

ይሁንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ደሞዝ በሚመለከት ምንም ማስተካከያ ሳይደረግ ሁለቱም ፕሬዝዳንቶች በገዛ ፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ተሰማ።

ከዛ በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር ነበሩ የተባሉት የቀድሞ ጠበቃ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ፣በዳኝነት ዘርፍ ላይ ለበርካታ ጊዜያት አገልግለዋል የተባሉት ወይዘሮ አበባ እምቢ አለ እንደ ቅደም ተከተላቸው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ።

በጥር 15 ቀን 2015 ከቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች የስራ ኃላፊነት ርክክብ አድርገው ስራቸውን ጀመሩ ከዚህ በኋላ ደግሞ በድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ዘንድ ሌላ ተስፋ ተጫረ

ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ/ ም ደግሞ ሌላኛው የፍርድቤቶች ሰራተኞችን ተስፋ የሰነቀ ፌሽታን የፈጠረ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሰራተኞች አስተዳደር ደንብ መፅደቁ ተሰማ ፣

ይህ ከተሰማ አሁን አምስት ወራት ተቆጠረ

ይሁንና ደንቡ ተግባራዊ ሆኖ ጠብ የሚል ነገር ይኖራል በሚል ተስፋ በተለመደው በኑሮ ጫና ውስጥ ሆነው የህይወታቸውን ውጣ ውረድ የሚገፉት ሰራተኞች ተግባራዊነቱን በተመናመነ ተስፋ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ተስፋ የቆረጡት ደግሞ ስራቸውን እየለቀቁ የተሻለ እንጀራ ፍለጋ ላይ ተሰማርተዋል።

''ያም መጣ ይህ ለራሱ እንጂ ለኔ የሚያስብ የሚጠቅም የለም '' በማለት ፊታቸውን ወደ ፈጣሪ ያዞሩና ከነገ ዛሬ ይሻል ይሆን ብለው ፈጣሪያቸውን ተስፋ ያደረጉም አሉ።

ለማንኛውም የተቋማት መሪዎች በቤታችሁ ወይም በሆቴል ስትመገቡ፣ስትዝናኑ፣ውስኪም ስታፈሱ ፣በዝቅተኛ ደሞዝ የሚሰቃዩ ሰራተኞችን አስታውሱ እላለሁ።

በኔ በኩል አበቃሁ
Via #TarikAdugna
Tarik Adugna
በታረክ አዱኛ ፌስቡክ ገፅ ላይ ተገኘ
ሰላም ለሀገራችን ህዝብ ይሁን
ይድረስ #አለ_ህግ #Ale_Hig አባላት እና ደጋፊዎች ፣
ሼር በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩ።
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👆👆👆👆🙏🙏🙏🙏🙏

@Lawsocieties #አለ_ህግ
#Lawsocieties @Alehig

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

Telegram Channel
https://t.me/lawsocieties

👇👇👇👇👇👇👇
👉Facebook Page 👈
👆👆👆👆👆👆👆


👇👇👇👇👇👇👇👇
👉Telegram Channel 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆