አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ #ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ #ህገ- ወጥ ነው።
ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።
የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው።
አብርሀም ዮሀንስ
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የቁሙ ቀንድ ከበት ማረድ ፤ በባዶ እግር መሄድ ፤ አጭር ቁምጣ መልበስ የተከለከለ ነው!! -
የምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል ይሕውም፦

1. ያለ እድሜ ጋብቻ እና የህግ ማእቀፍ ያላቸው ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ በወጣው ህግ መሰረት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረግ፤

2. ከአለባበስ ባህላችን አኳያ በዞናችን ስር ያላችሁ ሁሉም ወረዳዎች  የምንመራው ህዝብ አንድም ሰው በባዶ እግሩ እንዳይሄድና ቁምጣ ሱሪ ለብሶ የሚሄድ ሰው እንዳይኖር በቁርጠኝነት መስራት፤

3.  ተዝካርን በተመለከተ በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም ስርአተ በቤተክስቲያን በሚያዝዘው መሰረት ስርአተ ፍትሃት ላደረጉ ካህናት አባቶች ብቻ ቤተክርስቲያን ላይ 1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲቀርብ፤

4.  ጋብቻ አንዱ ባህላዊ እሴታችን መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ እና ትውልድ መቀጠል ስላበት ጋብቻ ይቁም አይባልም ነገር ግን በጋብቻ ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስን በተመለከተ

ለአጋቢ ሽማግሌዎችና ለቤተሰብ የሚሆን1 በግ/ፍየል እና  2 ሌማት ብቻ እንዲሆን የተወሰነ ስለሆነ እና የቀንድ ከብት ማረድ ፍጹም የተከለከለ መሆኑ ታውቆ በውሳኔው መሰረት በየደረጃው ያላቹህ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ከፍትህ ተቋሙ ጋር ተቀናጅታቹህ እንድታስፈጽሙ በጥብቅ እያሳወቅን  አፈጻጸሙንም በጋራ እየገመገማቹህ የተገኘውን ውጤት እና የመጣ ለውጥ እስከ ጥር15/2015 ዓ/ም እንድታሳዉቁ እናሳዉቃለን፡፡ -
የምስ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት
https://t.me/lawsocieties
አንተን ወይም አንቺን በዚህ ቴሌግራም ላይ ያላችሁን ተሳትፎ የሚገልፀው ፎቶ
*A* ነው ወይስ *B*⁉️ የሚወክልዎትን ይምረጡ። https://t.me/lawsocieties
አንተን ወይም አንቺን በዚህ ቴሌግራም ላይ ያላችሁን ተሳትፎ የሚገልፀው ፎቶ
*A* ነው ወይስ *B*⁉️
Anonymous Poll
49%
A
36%
B
15%
none https://t.me/lawsocieties
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
https://t.me/lawsocieties
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
https://t.me/lawsocieties
209136.pdf
279.3 KB
አስገድዶ መድፈር ማስረጃ ምዘና
Abreham Yohannis
የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካከል ያለው ልዩነት!

አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካሄድ ማለት ለማከናወን ያሰቡትን የቢዝነስ አይነት (በተለይ አዲስ ቢዝነስ) ጠቅላላ ሁኔታ መዳሰስ ሲሆን ለሚሰራው ቢዝነስ በዛ ያሉ አማራጮች ስለመኖራቸው ማሳየት እና የሚታሰበው ፕሮጀክት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው የሚያጣራ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ከብት ማደለብ የሚባል ቢዝንስ ስለማዋጣቱ ቢጠና እስካልተተገበረ ድረስ ሃሳባዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጪነት ጥናት ከዳታ በመነሳት፤ የቀደሙ አቅርቦት እና ፍላጎትን በመለካት፤ የፖሊሲ አማራጮች መኖራቸውን ማጣራት፤ በመጪው ጊዜ አቅርቦት፤ ፍላጎት እና ዋጋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ትንበያ መስራት፤ ቢዝነሱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መለየት፤ የሚጠበቁ መፍትሄዎችን ማሳየት፤ የፕሮጀክቱን ማህበራዊ ቅቡልነት ማረጋገጥ፤ ቢዝነሱ በገበያ ያለውን ተፎካካሪነት መለካት፤ ወዘተ ነው፡፡

ነገር ግን ፕሮጀክቶች (Business Plan) ገንዘቡ ከየት ተገኝቶ፤ ምን ያህል ሰዎች ተቀጥሮ፤ የት አካባቢ አምርቶ፤ ምን አምርቶ፤ እንዴት ሸጦ፤ እንዴት ማስታወቂያ አሰርቶ፤ እንዴት ምርቱን አከፋፍሎ፤ ስንት ሸጦ፤ በስንት ሸጦ፤ ወዘተ የሚሉ የታክቲክ እና የስትራቴጂ ስልቶችን በመንደፍ ከኢኮኖሚ አንጻር አትራፊ/አዋጪ ማድረግ እንደሚቻል የሚሰራ ሰነድ ነው፡፡

ከብት ማድለብ አዋጪ መሆኑ ሳይጣራ ከብት ለማድለቢያ መኖ የሚገዛበት ቦታ ሊመረጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) የሚሰራው የቢዝነሱ አዋጪነት (Feasibility Study) ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ኢንቨስትመንት ፍቃድ፤ የቦታ ጥያቄ ወይም ብድር ለመጠየቅ የሚሰራው ጥናት የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ፕሮጀክት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንዲሁም በፖሊሲ የሚደገፍ መሆኑን በማጣራት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቢዝነስ ፕላን ቢዝነሱን ላሰበው ሰው ብቻ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ዋና አላማው ኢኮኖሚያዊ አዋጪ (ትርፋማ) መሆኑ ብቻ ነው፡፡
The Ethiopian economist views
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የዓለማችን የመጀመሪያው “ሮቦት ጠበቃ” ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው

DoNotPay በተባለ የአሜሪካ ኩባንያ የበለፀገው "ሮቦት ጠበቃ" ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት በመቅረብ ነው ስራውን የሚጀምረው።

ይህ የሮቦት ሥርዓት ከፍጥነት ገደብ በላይ በማሽከርከር የተከሰሰ ደንበኛውን ነጻ ለማውጣት የሕግ ምክር ሊለግስ በቀጣዩ የካቲት ወር ፍርድ ቤት እንደሚቆም ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።

ሮቦቱ ይህን ማድረግ የሚያስችለውን አቅም ያገኘው ተጨባጭ የሕግ እውነታዎችን መሠረት አድርጎ በመሠልጠኑ እንደሆነ ተመላክቷል።
ዝርዝሩን ከተከታዩ ሊንክ ያነብቡ https://am.al-ain.com/article/robot-lawyer-takes-first-case
#ውክልና
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳዮቻቸውን ራሳቸው መፈፀም የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ሊገጥሟቸው ይችላል፡፡ ለዚህ መፍትሄ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው ውክልና ነው፡፡ ሆኖም ውክልና በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን በህግ በተቀመጠው ሥርአት መሰረት የሚፈፀም ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ስለ ውክልና ምንነት፣ ስለውክልና አይነቶች፣ ስለውክልና ጠቀሜታ እና ውክልና ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

የውክልና ምንነት

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2199 መሰረት ውክልና ማለት ተወካይ የተባለው ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደርሱ በመሆን አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎችን በወካዩ ስም ለማከናወን ግዴታ ሚገባበት ውል ነው፡፡ በዚህም ተወካዩ ልክ እንደወካዩ በመሆን የወካዩን ሥራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚደረግ ውል ነው፡፡
ውክልና ከልዩ የውል ህጎች ውስጥ አንዱ እንደ መሆኑ መጠን አንድ ህጋዊ ውል ሊያሟላቸው ያሚገባውን በፍትሐብሔር ህጉ በአንቀፅ 1678 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል፡፡ ይኸውም፡-

👉ውል ለመዋዋል ችሎታ ያለው ሰው መሆን
👉ጉድለት የሌለው ፈቃድ ወይም ስምምነት መኖር
👉በቂ የሆነ እርግጠኝነት ያለው የሚቻል እና ህጋዊ የሆነ ጉዳይ መሆን
👉የውል አፈፃፀም ፎርም በህግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዛዙ ባይፈፀም ፈራሽነት የሚያስከትል ሲሆን ህግ በሚያዘው ልዩ ፎርም መሆን ናቸው፡፡

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2200 ወካይ ለተወካይ የውከልና ስልጣኑን በቃል ወይም በዝምታ ሊሰጥ የሚችል ሲሆን ህጉ የውከልና ስልጣኑ በተለያየ ፎርም መሰጠት አለበት በማለት የሚያዝ ከሆነ ግን ይህ መሟላት ይኖርበታል፡፡

የውክልና አይነቶች

በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::
#የውክልና #አይነቶች

በአጠቃላይ ሁለት አይነት የውክልና ስልጣን ሲኖር ይህም ጠቅላላ እና ልዩ ውክልና በመባል ይታወቃሉ::

1ኛ.ጠቅላላ ውከልና

ይህ ውክልና በጠቅላላ አነጋገር የሚደረግ የውክልና አይነት ነው፡፡ ጠቅላላ ውክልና ተወካይ የአስተዳደር ስራዎችን ብቻ ለመስራት የሚያስችለው የውክልና አይነት ነው፡፡ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 2204 የአስተዳደር ስራዎች የሚባሉት ምን ምን አይነት ስራዎች እንደ ሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም፡-

• የወካዩን ሀብት ማስቀመጥ፣ መጠበቅ
• ከ3 አመት ለማያልፍ ዘመን ማከራየት
• በብድር የተሰጠውን ሀብት መሰብሰብ
• ከሀብቱ የሚገኘውን ገቢ ተቀብሎ ማስቀመጥ
• ለተከፈለ እዳ ደረሰኝ መስጠት
• ሰብሎችን መሸጥ
• ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ እቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን መሽጥ የአስተዳደር ስራዎች ናቸው፡፡

2ኛ ልዩ ውክልና

ይህ ውክልና ወካይ ለተወካይ ከአስተዳደር ስራዎች ውጪ ተወካይ የተለየ ተግባር እንዲፈፅምለት በመግለፅ የሚሰጠው የውክልና አይነት ሲሆን ይህም ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው፡-

• የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ
• አስይዞ መበደር
• ካፒታሎችን ኢንቬስት የማድረግ አክሲዮኖችን የመግዛት የመሸጥ በማሕበር የመግባት
• ስጦታን ማድረግ
• በአንዳንድ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ መከራከር የመሳሰሉ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችለው የውከልና አይነት ነው፡፡

የወካይ እና የተወካይ ግዴታዎች

የፍትሐብሔር ህጉ በቁጥር 2208 እና ተከታዮቹ መሰረት ተወካይ በርካታ ግዴታዎች አሉበት፡፡ በዋናነት ተወካይ ለወካይ በሚሰራበት ወቅት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እና በውክልና በተሰጠው አደራ ላይ ልክ አንድ የቤተሰብ አባት እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መከወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ተወካዩ በሚሰራበት ወቅት ለወካዩ ጥቅም ማሰብ እና ወካይ በሰጠው የስልጣን ወሰን ውስጥ ብቻ ተግባሩን ማከናወን የሚጠበቅበት ሲሆን ወካዩ ሳያውቅ በወኪልነቱ ምክንያት ከሚሰራው ስራ አንዳችም ጥቅም መውሰድ የለበትም፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ ሁሉ የስራውን አካሄድ፣ መግለጫ እና ሂሳብ በየጊዜው ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በውክልናው ምክንያት የሚያገኛቸውን መረጃዎችም የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡

በሌላ በኩል ወካዩም ግዴታዎች እንዳሉበት ከፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2219 እና ተከታዮቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዋናነትም ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ ለመክፈል ውል ገብቶ ከሆነ ወይም ተወካዩ በውክልና የፈፀመው በሙያ ውስጥ በተመለከተ የግል ሥራው ከሆነ ወካዩ ለተወካዩ የድካም ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ተወካዩ የውክልናው ሥራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈን የሚጠበቅበት ሲሆን ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልና ስራው መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከሚገባው የውል ግዴታ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡

የውክልና ጥቅም

ውክልና ለወካይ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጥ ነው፡፡ ከነዚህ ጥቅሞች መካከል ወካይ በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የእውቀት እና ልምድ ማነስ ሳያግደው የተለየ እውቀት እና ልምድ የሚያስፈልገው ስራ በወኪሉ በኩል ማከናወን መቻል፣ በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት ያገኙ ተቋማት ምንም እንኳን የህጋዊ ሰውነት ቢኖራቸውም እንደ ተፈጥሯዊ ሰው የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የማይችሉ በመሆናቸው በውክልና ስልጣን በተሰጠው ተፈጥሮዊ ሰው ምክንያት ተግባራቸውን በውክልና ማከናወን እንዲችሉ ማድረጉ ይጠቀሳሉ፡፡ በተጨማሪም እድሜቸው ለአካለመጠን ያልደረሱ እና ችሎታ ያጡ ሰዎች ህግ የሚስጣቸው ተወካዮች ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ውክልና ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ስለውክልና መቅረት

ውክልና ከተሰጠ በኋላ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል ማለት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቀሪ ሊሆንባቸው የሚያስችሉ ሁኔታዎች በህጉ ላይ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ሁኔታዎች መካከል ውክልናን መሻር፣ የውክልና ስልጣንን መተው፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ መሞት፣ የወካዩ ወይም የተወካዩ ለመስራት ችሎታ ማጣት ስልጣንን ቀሪ ከሚያረጉ ሁኔታዎች መካካል ናቸው፡፡

ውክልናን መሻር

ወካይ አስፈላጊ መስሎ ሲታየው የሰጠውን የውክልና ስልጣን መሻር እና ለተወካይ የሰጠውን የውክልና ውል እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ወካይ ተወካይ በእርሱ እና በ3ኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሰጠውን ውክልና በማንሳት ለሚመለከታቸው አካለት እና በውክልናው ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖችን ስለውክልናው መሻር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ የተሰጠው የውክልና ጊዜ ከማለቁ በፊት የውክልናው መሻር በተወካይ ላይ ኪሳራ አድርሶበት እንደሆነ ወካይ ተወካይ ላይ በውሉ መሻር ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ ካሳ የመክፈል አላፊነት አለበት፡፡ ብዙ ወካዮች ለጋራ ጉዳያቸው የወከሉትን ተወካይ በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላ ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን ሊሽረው አይችልም፡፡

የወኪል የውክልና ስልጣኑን መተው

ተወካዩ የውክልናውን ሥራ እንደሚተው ለወካዩ አስታውቆ ወክልናውን ለመተው የሚችል ሲሆን የውክልና ሥራውን መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ተወካይ ለደረሰው ኪሳራ ካሳ የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡ ሆኖም ተወካይ የውክልና ስራውን መቀጠሉ በእርሱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ኪሳራ የሚያስከትልበት መሆኑ ከታወቀ እና ሥራውንም ለመቀጠል በፍፁም የማያስችል ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሳራ እንዲከፍል አይገደድም፡፡ በሌላ በኩል ብዙ ተወካዮች አንድ አይነት ጉዳይ እንዲያከናውኑ ተወክለው እንደሆነ እና ከመካከላቸው አንድኛው የውክልና ስራውን ለመቀጠል በአንድ ምክንያት ያልቻለ እንደሆነና የውክልና ስራውን ካቋረጠ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአንዱ መቋረጥ የሌሎቹንም ተወካዮች የውክልና ስልጣን የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ

በአጠቃልይ ውክልና ጊዜን፣ ገንዘብን እና አቅምን በመቆጣብ በዋናነት ወካዩን የሚጠቅም በመሆኑ የታለመለትን አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ወገኖች የውክልና ስምምነት በህጉ ላይ የተቀመጡለትን መስፈርቶች እና ሁኔታዎችን ማወቅ እና ማሟላት አለባቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
chat ersha mahber.pdf
2.8 MB
የፌደሬሽን ምክር ቤት ለረጅም ጊዜ በመንግስት እጅ ሆነው ጥያቄ ሳይቀርብባቸው የቆዩ ቤቶች የመንግስት እንደሆኑ ይቆጠራሉ በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ
#danielfikadu
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Mikias Melak)
#አለ_ህግ🔵Ale_Hig ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች https://www.youtube.com/@Lawsocieties ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ🔴 All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው @LawsocietiesBot / lawsocieties@gmail.com
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties