አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ስለባልና ሚስት የጋራ እና የግል ንብረቶች በተመለከተ የፌዴራሉን የቤተሰብ ሕግና የተመረጡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን መሰረት በማድረግ የቀረበ

በ፡ ሙሉቀን ሰይድ ሐሰን

በዚህ ጽሑፍ ጋብቻ በተጋቢዎቹ የግልና የጋራ ንብረት ላይ ስለሚኖረው ውጤት እንዲሁም በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የግል ወይም የጋራ ሊባል ሲለሚችልበት የሕግ አግባብ፤ በተጋቢዎቹ መካከል የሚደረግ የስጦታ ውል ሕጋዊ ውጤቱና የአደራረግ ስነ ስርዓቱ፣ በትዳር ውስጥ የወጣ ወጪ ለትዳር ጥቅም ዋለ ሊባል ስለሚችልባቸውና የማይቻልባቸው ሁኔታዎች ከፌዴራሉ የቤተሰብ ሕግ እንዲሁም ከሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር በተመረጡ የንብረት አይነቶች በመከፋፈል ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ በጽሑፉ፦

- የግል ወይም የጋራ ንብረት ለማለት መሰረቱ
- የግል ንብረት
- ቤትና ይዞታን በተመለከተ
- ይዞታው ከጋብቻ በፊት በምሪት የተገኘ ሆኖ ቤቱ ግን በጋብቻ ውስጥ በጋራ የተሰራ በሆነ ጊዜ
- የአንደኛው ተጋቢ የግል የሆነ ቤትን በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስቱ እድሳት ካከናወኑ
- ከጋብቻ በፊት አንደኛው ተጋቢ ተበድሮ ቤት ቢሰራ እና ብድሩ በጋብቻ ጊዜ ከጋራ ሀብት ( ደመወዝ) ቢከፈል ቤቱ የጋራ? ወይስ የግል ሊባል ይገባል?
- በውርስ በተገኘ ንብረት ምትክ በካሳ መልክ ከመንግስት በተሰጠ ገንዘብ የተሰራ ቤትን በተመለከተ
- የስጦታ ውል በባልና ሚስት መሀከል የሚደረግበት የሕግ አግባብ
- ለትዳር ጥቅም የዋለ ገንዘብ
- የኮንዶሚኒየም ቤት
- የንግድ ፈቃድ

የሚሉ ነጥቦችን ይዟል።

መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/joint-and-personal-property-of-spouses-under-ethiopian-law
የመረጃ ነፃነት ህግ ተግባራዊነት - ለመልካም አስተዳደር መስፈን
\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\
የሀገራችን ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰላቸውን አመለካከት የመያዝና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዳላቸው ያብራራል። ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች መካከል መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሽ ናቸው።በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል ጥራቱ የተጠበቀ፤ ወቅታዊ፤ ትክክለኛ፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ የሆነ ለፖለቲካዊ፤ ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጾ የሚያደርግ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ይታመናል።
አለሕግAleHig ️
የመረጃ ነፃነት ህግ ተግባራዊነት - ለመልካም አስተዳደር መስፈን \\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\ የሀገራችን ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰላቸውን አመለካከት የመያዝና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዳላቸው ያብራራል። ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች መካከል መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሽ ናቸው።በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን…
የመረጃ ነፃነት ህግ ተግባራዊነት - ለመልካም አስተዳደር መስፈን
\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\

ይህንኑ ሀገራዊ ሃላፊነት ለማስፈፀም እንዲቻል በአገሪቱ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጋር በሚጣጣም መልኩ የተቀረፀው የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 ወጥቶ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ይታወቃል።በተለይ የመረጃ ነፃነት ህጉ ከህዳር 25/2004 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ይፋ ሆኗል።አዋጁ ህገ መንግስታዊ መሰረት ያለውን ሃሳብን በፃነት የመግለጽ መብት የበለጠ የሚያጠናክርና ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን፤ በዜጎች መካከል የሚደረገውን የሃሳብና የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን የአሰራር ነፃነት ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ተቋማዊና መዋቅራዊ ችግሮችን ያስወግዳል።
ከዚህም በተጨማሪ በነፃና በህጉ መሰረት ሃሳብን የመግለጽና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን አስመልክቶ ያዳበርናቸውን አዎንታዊና ገንቢ ልምዶች የመጠበቅና ይበልጥ የማጠናከርን አስፈላጊነት በመረዳት ተግባራዊ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።ሌላው አዋጁ በመንግስት እጅ ያሉ መረጃዎችን የማግኘት መብት ለዴሞክራሲያዊ ህብረተሰብ የሚኖረውን ፋይዳ በአግባቡ የሚፈፀምበት ሁኔታ እውን ለማድረግ ድርሻው የጎላ ነው።
በዚህም መሰረት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ግልጽ የመንግስት የተጠያቂነት እሴትን ለማዳበርና ለማጠናከር እንዲሁም የህዝብን ጠቅምን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይፋ ወጥተው ህዝብ እንዲወያይባቸው ለማድረግ የመንግስት ተቋማት ለማንኛውም መረጃ ፈላጊ መረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።ይህንን ግዴታ በማስፈፀምና መረጃ የማግኘት መብትን በማስተግበር ረገድ አዋጁ ስልጣን ከሰጣቸው ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው።
መረጃ ጠይቆ የማግኘት መብትን ከማረጋገጥ ጋር የተቆራኘው ይህ ሃላፊነት ተነፃፃሪ የህዝብንና የግለሰብ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የወጡ ተገቢ ገደቦች እንደተጠበቁ ሆኖ ከማንኛውም መንግስታዊ አካላት ዜጎች መረጃ ለመጠየቅ፤ ለማግኘትና ለማስተላለፍ ያላቸውን መብት ተፈፃሚ የማድረግ ዓላማን ተግባራዊ ለማድረግ ያገለግላል። ይህ ደግሞ የስልጣን ባለቤት የሆነውን የህዝብ ነፃ ተሳትፎ የሚያረጋግጥና ከሁሉም በላይ የአሰራር ግልጽነት፤ ተጠያቂነትና ውጤታማት የሰፈነበት መንግስታዊ ሥርዓትንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን መሳኝ ነው።
መረጃ ማግኘት ዜጎች ሊነፈጉት የማይገባ መብት ነው።ስለሆነም ተቋሙ በመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ መረጃ ለመስጠትና ለማመቻቸት የተደራጁ የህዝብ ግንኙነት ክፍሎች ለሚቀርብላቸው የመረጃ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዲችሉ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በመረጃ ነፃነት ህጉ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እያደረገ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማቱ ደግሞ ህጉን እንዴት ተግባራዊ እያደረጉ እንደሆነ የቁጥጥር ስራዎችን አከናውኗል።ከዚህ በተጨማሪም የመረጃ ጥያቄዎች የሚቀርቡበትንና የሚስተናገዱበትን ፎርማቶችን በማዘጋጀትና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም የማብራሪያ ሰነዶችን በማሰራጨት የህዝብ ግንኙነት አካላት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።
ተቋሙ በመረጃ ነጻነት ዳይሬክቶሬት ዘርፉ በሚያከናውናቸው ተግባራት ህጉን ለመተግበር የሚያግዙ የተለያዩ የህግ ማእቀፎች እንዲዘጋጁ ሃሳብ በማቅረብ ድጋፍ ያደርጋል።መረጃዎችን አትሞ በማዘጋጀት ረገድም ግልጽ የአሰራር መመሪያ አዘጋጅቶ በመንግስት ተቋማት እንዲተገበር ያመቻቻል፡፡
በዘርፉ ከሚከናወኑ አበይት ተግባራት መካከልም መረጃ ከማግኘት መብት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የመፍታት መፍትሄ አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።በዘርፉ የስራ እንቅስቃሴም ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል ሥርዓት እንዲዘረጋ የማድረግ ሃላፊነት ተጥሎበታል ፡፡
የመረጃ ነጻነት ዳይሬክቶሬት ዘርፍ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ስለ ህጉ አፈጻጸም ዓመታዊ ሪፖርት በመሰብሰብ ፣የተጠቃለለ ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያቀርባል።አዋጁን በመተግበር ሂደት ከተገኙ በጎ ተሞክሮዎችና ካጋጠመ ችግሮች በመነሳትም ለተሻለ አፈጻጸም የሚያበቃ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል።በስራ ላይም ያውላል።
ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችና አግባብነት ላላቸው አካላት ስለ ህጉ ይዘት ስልጠና የመስጠት ድርሻውን የሚወጣው ይህ ዘርፍ ከዋና እንባ ጠባቂ የሚሰጡ ሌሎች ጨማሪ ተግባራትን የመከወን ሃላፊነት አለበት፡፡
ዘርፉ መረጃ ከማግኘት መብት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች በአስተዳደራዊ የይግባኝ ሂደት ተመልክቶ ውሳኔ ይሰጣል።የሰነዶችን አጠባበቅ አስተዳደርና አወጋገድን አስመልክቶም የሚመለከታቸውን ወገኖች በማማከር የተግባር መመሪያን ያዘጋጃል፡፡
በአጠቃላይ ተቋሙ የህዝብ የመረጃ የማግኘት መብትን ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን አውን ለማድረግ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ባለድርሻ አካላት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በማስራት በመረጃ ነፃነት ህጉ የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት ከማናቸውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እየሰራ ይገኛል።የመረጃ ነፃነት ህግ ተግባራዊ መሆን የግልጽነትንና የተጠያቂነትን አሰራር በማስፈን ለመልካም አስተዳደር መስፈን የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል።
አዲስ ዘመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ጋር በመተባበር ቅዳሜ ነሐሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም
224876.pdf
1 MB
የውርስ ሀብት በእጁ አድርጎ ያልያዘ ወራሽ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት አይችልም።
የፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) ከሳሹ መብቱንና የውርሱ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሶስት አመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ለማግኘት እንደማይችል ደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ በይዘቱ የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት የሚችለው የውርስ ንብረቶቹን በእጁ የያዘው ሰው ብቻ ስለመሆኑ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ሰ-መ-ቁ 224876 ቀን ጥቅምት 2 2015 ዓ.ም
#Click Ethiopian Laws
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
የንግድ_ምዝገባ_ፈቃድ_እና_ድኅረ_ፈቃድ_ኢንስፔክሽን_መመሪያ_ቁጥር_935.pdf
946.7 KB
አዲስ መመሪያ❗️❗️❗️❗️

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የፀደቀ አዲስ “የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 935/2015 🕹🕹🕹
አሐዱ ባንክ በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position: -
1:Attorney

2:Senior Attorney

📚ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:-
LLM, LLB

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ አዲስ አበባ

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ታህሳስ
29 /2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://tikusjobs.com/job/ahadu-bank-job-vacancy-13/
224876.pdf
1 MB
የውርስ ሀብት በእጁ አድርጎ ያልያዘ ወራሽ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት አይችልም።
የፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) ከሳሹ መብቱንና የውርሱ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሶስት አመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ለማግኘት እንደማይችል ደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ በይዘቱ የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት የሚችለው የውርስ ንብረቶቹን በእጁ የያዘው ሰው ብቻ ስለመሆኑ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ሰ-መ-ቁ 224876 ቀን ጥቅምት 2 2015 ዓ.ም
https://t.me/lawsocieties
የኑዛዜ አይነቶችና የኑዛዜ ማረጋገጫ
በኢትዮጵያ የውርስ ህግ ሰው ህይወቱ ካለፈ በኋላ በህይወት ዘመኑ ያፈራቸው ንብረቶቹን ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲከፋፈል የሚያደርግበት ሁለት አይነት መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም ያለኑዛዜ የሚደረግ ውርስ እና በኑዛዜ የሚደረግ ውርስ ናቸው፡፡ በሁለቱም ዘዴዎች የሚደረግ የንብረት ማስተላለፍ ሂደት በፍትሐ ብሔር ህግ የሚገዛ ሲሆን ለውርሱ ተፈፃሚነት ህጉ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የኑዛዜ አይነቶች እና የኑዛዜ ማረጋገጫ በዝርዝር ይዳሰሳሉ፡፡

የኑዛዜ አይነቶች

በኢትዮጵያ ህግ 3 የኑዛዜ ዓይነቶች አሉ፡፡ ሁሉም የኑዛዜ አይነቶች መከትል ያለባቸው ፎርማሊቲዎች ወይም ቅድመ ሁኔታዎች በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐ ብሔር ህጋችን ውስጥ በዝርዝር የተቀመጡ ሲሆን መስፈርቶቹ ያልተሟሉ እንደሆነ ኑዛዜው በህግ ፊት ውድቅ (ፈራሽ) ይሆናል፡፡ ህጉ የመስፈርቶቹን መሟላት በተመለከተ ጥብቅ (strict) ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት የኑዛዜ ቃል በሚፈፀምበት ወቅት ተናዛዡ በህይወት ስለማይኖር ትክክለኛ ሀሳቡን ማወቅ የሚቻለው ትቶት ከሄደው የኑዛዜ ሰነድ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ሰነድ ደግሞ ለአፈፃፀም እንዲያመች መስፈርቶቹን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ መከተል አለበት፡፡ በፍ/ህ/አ 880 ስር እንደተደነገገው 3ቱ የኑዛዜ አይነቶች

1. በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ (public will)
2. በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ (holographic will)
3. በቃል የሚደረግ ኑዛዜ (oral will) ናቸው

• በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ( የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 881-883)

በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ሌላ ሰው የሚፅፈው ወይም ተናዛዡ ራሱ የሚፅፈው የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህ ኑዛዜ በተናዛዡ ወይም በሌላ ሰው ከተፃፈ በኃላ ተናዛዡ እና ምስክሮች ባሉበት መነበብ አለበት፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተቀባይነት እንዲኖረው ተናዛዡና ምስክሮች ባሉበት መነበቡ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ይህ መስፈርት (formality) መሟላቱ በኑዛዜው ላይ መስፈር አለበት፡፡ ይኸውም በኑዛዜው ላይ "ይህ ኑዛዜ ተናዛዡ እና ምስከሮች ባሉበት ተነቧል" ተብሎ መገለጽ አለበት፡፡ በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ ላይ የምስክሮች ብዛት 4(አራት) መሆን ሲኖርበት አራቱም ምስክሮች ኑዛዜው ተነቦላቸው በኑዛዜው ላይ ፊርማቸውን ወዲያውኑ ማስፈር አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜው ላይ ኑዛዜው የተደረገበት ቀን ማለትም ቀን፣ ወር፣ ዓመተ ምህረት መፃፍ አለበት፡፡

የምስክሮችን ብዛት በተመለከተ በግልፅ ለሚደረግ ኑዛዜ ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዳኛ ወይም ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ሥራቸውን በሚያካሄዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ማግኘት ሁለት ምስክሮች ብቻ በቂ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ የሚከተሉትን ፎርማሊቲዎች መከተል አለበት፡፡

 በተናዛዡ በራሱ ወይም እሱ እየተናገረ በሌላ ሰው ሊፃፍ ይችላል
 ተናዘዡና አራት ምስክሮች ባሉበት መነበብ አለበት
 በኑዛዜው ላይ ተናዛዡና ምስክሮቹ ባሉበት መነበቡ በግልፅ መፃፍ አለበት
 ኑዛዜው የተደረገበት ቀን፣ ወር እና ዓ.ም መፃፍ አለበት
 አራት ምስክሮች መኖር አለባቸው፣
 ተናዛዡና ምስክሮች ኑዛዜው እንደ ተነበበላቸው ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም የጣት አሻራቸውን ማሳረፍ አለባቸው
 በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ምስክሮች አካለመጠንን የደረሱ (18 ዓመት የሞላቸው) ወይም በህግ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው
 ምስክሮች ኑዛዜው የተፃፈበትን ቋንቋ ለማወቅና የተፃፈውን ለመስማት ወይም ለማንበብ ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

እነዚህ ከላይ የተመለከቱት መስፈርቶች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቶችም የኑዛዜ ቃልን ለማስፈፀም መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችን በጥብቅ የሚቆጣጠሩ ሲሆን መስፈርቶቹ ካልተሟሉ ኑዛዜውን ውድቅ ያደርጉታል፡፡

• በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 883-891)

በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደርግ ኑዛዜ ሙሉ በሙሉ በተናዛዡ የሚፃፍ የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ይህን የኑዛዜ አይነት የሚያደርገው የተማረ ወይም ኑዛዜው የሚፃፍበትን ቋንቋ መፃፍና ማንበብ በሚችል ሰው ሲሆን የምስክሮችን መኖር የሚፈልግ አይደለም፡፡ በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ በተናዛዡ የእጅ ፅሁፍ ወይም በማሽን (በኮምፒዩተር) ሊፃፍ ይችላል፡፡ ተናዛዡ ኑዛዜውን በኮምፒዩተር የሚፅፈው ከሆነ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ እራሱ ስለመፃፉ በእጅ ፅሁፉ ማመልከት አለበት፡፡ ይህም ኑዛዜውን ያደረገው ተናዛዡ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ኑዛዜው በማሽንም ሆነ በእጅ ቢፃፍ ተናዛዡ በእንዳንዱ ገፅ ላይ ቀን ፅፎ ፊርማውን ማስፈር ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በኑዛዜ ሰነድ ላይ ተናዛዡ ይህ ሰነድ "ኑዛዜ" ነው በማለት በግልፅ መግለፅ አለበት፡፡ እነዚህ መስፈርቶች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡ በተጨማሪ በተናዛዡ ፅህፈት የሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው በተደረገ በሰባት(7) ዓመት ውስጥ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት መቀመጥ አለበት፡፡

በአጠቃላይ በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ በህግ ፊት ተቀባይነት እንዲያገኝ እና ተፈፃሚነት እንዲኖረው የሚከተሉት መስፈርቶች በሙሉ መሟላት አለባቸው፡፡

 ሙሉ ለሙሉ በተናዛዡ መፃፍ አለበት
 በኑዛዜው ላይ በግልፅ "ይህ ሰነድ የኑዛዜ ሰነድ ነው "ተብሎ መገለፅ አለበት
 በተናዛዡ በአያንዳንዱ ገፅ ላይ ቀን እና ፊርማ መስፈር አለበት
 ኑዛዜው በተደረገ በሰባት አመት ውስጥ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ መቀመጥ አለበት፣( የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 903)
 ተናዛዡ ግልፅ በሆነ ፊርማው ካላፀደቃቸው በስተቀር የተናዛዡን ፈቃድ ለመለወጥ የሚችል ፍቀት፣ ስርዝ ወይም ድልዝ ያለባቸው ኑዛዜዎች ፈራሽ ናቸው፡፡

ከእነዚህ ከላይ ከተገለፁት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ወይም ከአንድ በላይ ካልተሟላ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል ወይም ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ ነገር ግን ኑዛዜ ፈራሽ ሆነ ማለት ወራሾች ንብረት አያገኙም ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ውርሱ በቁጥር 842 እና ተከታዮቹ መሰረተ ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ውርስ በሚተላለፍበት ሂደት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡


የቃል ኑዛዜ (የፍ/ብ/ህገ/ቁጥር 892-894)

የቃል ኑዛዜ ማለት አንድ ሰው የሞቱ መቃረብ ተሰምቶት የመጨረሻ የፍቃድ ቃሎቹን ለሁለት ምስክሮች የሚሰጥበት የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ ከፍ/ህ/ ቁጥር 892 እንደምንረዳው የቃል ኑዛዜ በመደበኛ ሁኔታ (under normal circumstances) የሚደረግ አይደለም፡፡ ተናዛዡ ይህን የኑዛዜ አይነት የሚያደርገው በቅርብ ጊዜ እሞታለው ብሎ ሲያስብ ለምሳሌ አደጋ ደርሶበት ፅኑ ህመም ውስጥ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ባለጊዜ ሌሎቹን የኑዛዜ አይነቶች ማለትም በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ ሁኔታዎች አይፈቅዱለትም ማለት ነው፡፡ በመሆኑም በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ላይ ተናዛዡ የሚናዘዘው በተገደበ ሁኔታ (restricted testamentary disposition) ይሆናል፡፡ በዚህ የኑዛዜ አይነት ተናዛዡ ሙሉ ፍላጎቱን ለማንፀባረቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ህጉ ገደቦችን አስቀምጧል፡፡

በፍ/ሕ/ቁጥር 893 መሰረት አንድ ሰው የቃል ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በተለይ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
 የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱትን ትዕዛዞች ለመስጠት
 እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ የኑዛዜ ስጦታ ለማድረግ፣
 አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆቹ አስተዳዳሪን ወይም ሞግዚትን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ለመስጠት ነው፡፡

በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ውስጥ ከብር አምስት መቶ በላይ ኑዛዜ ተደርጎ ከሆነ ከአምስት መቶ ብር በላይ ያለው ተቀናሽ ይሆናል፡፡ በቃል የተደረገ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሶስት ወር በኋላ ተናዛዡ በህይወት የቆየ እንደሆነ ኑዛዜው ተፈፃሚ አይሆንም ወይም ፈራሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ተናዛዡ ያንያህል ጊዜ ሳይሞት ከቆየ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ እድል አለው ተብሎ ይገመታል፡፡

በሌላ በኩል ብዙ ኑዛዜዎች ካሉ አብሮ ተፈፃሚ ሊሆኑ በሚችሉበት መጠን ልዩ ልዩ ኑዛዜዎች አብረው ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሁለት ኑዛዜዎች ቃላት ሁለቱም ሊፈፀሙ ያልቻሉ ወይም የተቃረኑ እንደሆነ በኋላ የተደረገው ኑዛዜ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ንብረቱን በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚፈልግ ሰው ሶስቱን የኑዛዜ አይነቶች ፎርማሊቲያቸውን በሟሟላት እንደየሁኔታው ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ኑዛዜ አድራጊው የኑዛዜ ቃላት ተፈፃሚነት እንዲያገኙ በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች በጥንቃቄ መከተል አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኑዛዜው ውድቅ ስለሚሆን የተናዛዡ ፍላጎት ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

 የኑዛዜ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ

በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዳት ያለበት በዚህ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው ነው፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የተደረገ ኑዛዜ መኖር የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ፅሁፍ ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋውል ስልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት ሹም ተክክለኛ ሆኖ የተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው፡፡ ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ መንገድ ለማስረዳት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በጥፋት ወይም በቸልተኝነት ኑዛዜው እንዲጠፋ ካደረገ ሰው የጉዳት ኪሳራ ለማግኘት ከሆነ በማናቸውም አይነት መንገድ ኑዛዜዎችን ማስረዳት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው ሁለት ነገሮችን በመሰረታዊነት ማስረዳት ያለበት ሲሆን እነሱም በተናዛዡ የተደረገውን ኑዛዜ በማቅረብ የኑዛዜን መኖር እና የኑዛዜውን ይዘት በማስረዳት ማለትም እሱ የኑዛዜው ተጠቃሚ (beneficiary) መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልተጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

https://t.me/lawsocieties
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳን በተመለከተ እስር ከተፈፀመባቸው ግዜ ጀምሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል::
-----------------------------------
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ጉዳዩ አሁንም በፍርድ (በይግባኝ ሂደት) ላይ ያለ እንደመሆኑ መጠን ማህበሩ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቷል::

በዚህም በታሰሩበት ኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ላይ ፍቃድ ያላቸውን ሁለት ጠበቆች ማህበሩ በመመደብ ተገቢው የህግ ሂደት እየተፈፀመ ይገኛል:: ከዚህ በተጨማሪ ማህበሩ የጉዳዩን ትክክለኛ ምክንያት ከተለያዩ አካላት ለማጥራትና ለማረጋገጥ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል::

የይግባኝ ክርክሩም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመጪው እሮብ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ይሰማል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁ. 1249/2013 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ዋነኛው የህግ የበላይነት መከበር ጋር የተያያዙ ተግባራት መሆናቸው እንዳሉ ሆኖ ጠበቆች በሀገራችን የህግ ስርአት ላይ የሚኖራቸውን የጎላ ሚና መወጣት እንዲችሉ እና ለደንበኞቻቸው ጥራት ያለው የህግ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሏቸው መብቶች መከበራቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት::

በጉዳዩ ላይ ማህበሩ ተገቢውን ክትትል እያደረገ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ ተቋሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በተገቢው የሚሄድበት መሆኑንና የሚደረስባቸው ሂደቶች በይፋ እንደሚገልፅ ያሳውቃል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ታህሳስ 23 2015ዓ.ም
https://t.me/lawsocieties
ሰ-መ-ቁ 231739 ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 በመተላለፍ የሚቀርቡ የወንጀል ክሶች በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች መታየት ያለባቸው በሶስት ዳኞች ነው።

ምንም እንኳን ይህ አዋጁ በሶስት ዳኞች የሚታዩ በማለት የለየው በአንቀጽ 4(2) እና አንቀጽ 8(3) የተመለከቱ ጉዳዮችን ቢሆንም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት በማድረግ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሶስት ዳኞች ስለሚታዩ ጉዳዮች ለመደንገግ የወጣው መመሪያ ቁጥር 009/2013 ዓ.ም የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር እና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ጉዳዮች በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሶስት ዳኞች የሚታዩ መሆኑ በግልጽ የደነገገ በመሆኑ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 በመተላለፍ የሚቀርቡ ሁሉም የወንጀል ክሶች መታየት ያለባቸው ያለ ልዩነት በሶስት ዳኞች ነው።
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ፊት የቤት ሽያጭ ውል ተደርጎ እንደገና በዚያው ቤት ላይ በሌላ ቀን የመንደር ውል የሽያጭ ስምምነት ተደርጎ በፍርድ ቤት ክስ ሲቀርብ የመንደር የሽያጩ ውሉ በግልጽ ካልተካደ ህጋዊ ውጤት አለው።

በዚህ መዝገብ ተጠሪዎች (ሻጭ) እና አመልካች (ገዢ) በቀን 23/04/2010 ዓ/ም የመኖሪያ ቤት በብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺ ብር) ለመሸጥ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ፊት የሽያጭ ውል አድርገዋል። እንደገና ይህንኑ ቤት በብር 1,300,000,00 (አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለመሸጥ በቀን 01/05/2010 ዓ/ም የመንደር ውል አድርገዋል።

ሻጭ ያልተከፈለ ቀሪ ብር 860,000.00(ስምንት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) እንዲከፈላቸው ክስ ሲያቀርቡ ገዥ የሽያጭ ውል ስምምነት ሻጭ እንደሚሉት በቀን 01/05/2010 ዓ/ም የተደረገ ሳይሆን በቀን 23/04/2010 ዓ/ም ተደርጎ በውልና ሰነዶች ማረጋገጫ የፀደቀ ነው፡፡ በቀን 01/05/2010 ዓ/ም የተደረገ የቤት ሽያጭ ዉል ነዉ በማለት ተጠሪዎች ያቀረቡት ውል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720 እና 1721 መሰረት ረቂቅ ሰነድ ነዉ፡፡ በመሆኑም ተጠሪዎች ብር 860,000.00 ይከፈለን በማለት ያቀረቡት ክስ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

አቤቱታው የቀረበው ገዥ የመንደር ውሉን አልካዱም በሚል ቀሪ ገንዘቡን እንዲከፍሉ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የፌዴራሉ የሰበር ችሎትም ገዥ ውሉን አልካዱም በሚል በክልሉ ሰበር ችሎት የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የለበትም በማለት አጽንቶታል።
የሰ/መ/ቁጥር 216608 ጥቅምት 03 ቀን 2015 ዓ/ም
https://t.me/lawsocieties
እንደ አማርኛ #ሀ እና እነደ እንግሊዝኛዋ #r አሽቃባጭ አላየሁም!
ተመልከቱልኝ ለሃብታሞች በየት ለድሃዎች በየት እንደሚገቡ

https://t.me/lawsocieties
*1. ለወታደር:(ለሰላም(ለሉአላዊነት)
2. ለመምህር:(ለእውቀት)
3. ለዶክተር:(ለጤና)
4.
ለዳኛ:(ለፍትህ ስርዓት ቤተሰብ) ለህግ
ዋጋ ያልሰጠች እና ክብር የሌላት አገር መጨረሻዋ ምንም ነው‼️
#አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
*1. ለወታደር:(ለሰላም(ለሉአላዊነት)
2.  ለመምህር:(ለእውቀት)
3. ለዶክተር:(ለጤና)
4.
ለዳኛ:(ለፍትህ ስርዓት ቤተሰብ) ለህግ
ዋጋ ያልሰጠች እና ክብር የሌላት አገር መጨረሻዋ ምንም ነው‼️
#አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties