አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
https://www.youtube.com/@Lawsocieties

https://www.youtube.com/@Lawsocieties

Subscribe እያደረጋችሁ

Subscribe እያስደረጋችሁ 🔴
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በምርመራ ወቅት በፖሊስ ጣቢያ የተሰጠ የምስክሮች ቃል በፍ/ቤት ያለው ተቀባይነት፤ ሕጉ፣ ትግበራው እና የሰበር ችሎት
======================================

አንድ ወንጀል ስለመፈጸሙ እና ድርጊቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጣሪው ሰው የድርጊቱ ፈጻሚ ስለመሆኑ ፖሊስ ምርመራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ከሚያጣራባቸውና ከሚያረጋግጥባቸው የማስረጃ ዓይነቶች መካከል አንዱ የሰው ምስክሮች ናቸው፡፡ ይህን መሰረት በማድረግ የዚህ ጹሁፍ ዓላማ የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145ን ህጉን ፣በፍ/ቤት ትግበራ ያለውን የህጉን ትርጉም እና የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም አቋምን ከተከሳሽ መብት አኳያ በማመዛዘን ያስዳስሳል፡፡

የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145

በፖሊስ ምርመራ የተሰጠ ቃል በማስረጃነት ሊቀርብ ስለመቻሉ

(1) ዐቃቤ-ህጉ ወይም ተከሳሹ ሲያመለክት በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው ይችላል፡፡

(2) ከዚህ በኃላ ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ የሚጠቅም መስሎ ከታየው የዚህ ቃል ግልባጭ ለተከሳሹ እንዲደርሰው አድርጎ በዚህ መሰረት ምስክሩ የሰጠውን ቃል ለማስተባበል ይቻላል፡፡

የአንቀጹ ርእስ እንደሚያስረዳው በፖሊስ ምርመራ የተሰጠ የምስክርነት ቃል በፍ/ቤት እንደ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ የሚቻል ስለመሆኑ በግልጽ ያስቀመጠና ጥያቄ የማያስነሳ ጉዳይ ቢሆንም መቼና በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ይህ በምርመራ ወቅት የተሰጠ የምስክርነት ቃል በፍ/ቤት ተቀባይነት የሚኖረው የሚለውን በተመለከተ ግን ህጉ የገለጸው ነገር ባለመኖሩ ይህ አንቀጽ ለትርጉም ክፍትና እስካሁን ድረስ ገዢ የሆነ ትርጉም ያላገኘ አከራካሪ ጉዳይ ስለመሆኑ እንደሚከተለው አስረዳለሁ፡፡

የሕጉ ትርጉም

በፖሊስ ምርመራ ወቅት የተሰጠ የምስክሮች ቃልን እንደ ማስረጃ ፍ/ቤት ሊቀበለው የሚችልበት ሁኔታዎችን በምንፈትሽበት ጊዜ ሁኔታዎቹ በተለይ የተከሳሹን መብት ከመጠበቅ አኳያ ያሉትን መሰረታዊ መብቶች በጠበቀና ባከበረ መንገድ ሊተረጎሙ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ እነዚህም ሊከበሩ የሚገባቸው የተከሳሹ መሰረታዊ መብቶች፡-

አንደኛ ህገ-መንግስታዊ ነው፡፡ ይህም ስለመሆኑ ማንኛዉም በወንጀል የተከሰሰ ሰው ያሉትን መብቶች አስመልክቶ በህገ-መንግስቱ አ.ቁ 20 ላይ የተዘረዘረ ሲሆን ከያዝነው ጉዳይ አኳያ ጠቃሚ የሚሆነው ንዑስ ቀ. 4 “የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ…”መብት ያለው ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህንን የህገ-መንግስት ድንጋጌ በተመለከተ ብዙ ጊዜ በፍ/ቤት ክርክር የተነሳበት በመሆኑ ( በእርግጥ ክርክር የተነሳው በሽብር እና በሙስና በተጠረጠሩ ተከሳሾች ላይ ሲሆን ምክንያቱም ዐቃቤ-ህግ ያቀረበውን ክስ ላይ አለኝ ያላቸውን ምስክሮች ለደህንነታቸው ሲባል በሚል ምክንያት ስም ዝርዝር ባለማስፈሩ የተነሳ ነው) ህገ-መንግስት ጉዳይ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን የማየትና ትርጉም የመስጠት ብቸኛው ባለስልጣን የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተረጎመው ይህ አንቀጽ ተከሳሾች የቀረቡባቸውን ምስክሮች አስመልክቶ ያላቸው ህገ-መንግስታዊ መብት የመጠየቅ (cross-examine) ማድረግ ብቻ ስለመሆኑ አስረድቷል፡፡ የተከሳሾች ይህ የመጠየቅ መብት የሚከበረው ደግሞ ምስክሮቹ ቃላቸውን የሰጡት ተከሳሾች የመጠየቅ መብታቸው በሚከበርላቸው ፍርድ ለመስጠት በተቋቋሙ ተቋም ውስጥ የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በፖሊስ በምርመራ ወቅት ምስክሮች ቃላቸውን ሲሰጡ ተጠርጣሪዎቹ የመገኘትም ሆነ የመጠየቅ መብት የላቸውም ስለዚህ የወ/ስ/ስ/ህ/ቁ 145 ልዩ ሁኔታዎች ሲተረጎሙ ይህን የተከሳሽ ህገ-መንግስታዊ የመጠየቅ መብት ያከበረ መሆን አለበት።
https://t.me/lawsocieties
የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር
ዜጎች ሠላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ መብትና ነጻነታቸው ተከብሮ የመኖር መብት አላቸው፡፡ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን መብትና ደህንነት ማስከበር የመንግስት ዋነኛ ሃላፊነት ነው፡፡ ከሰላምና ደህንነት ጋር በተያያዘ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም የሚነሳ እንደመሆኑ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎች መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በሀገራችን የጦር መሳሪያ አያያዝ የሚመራበትን የህግ አግባብ እንዲሁም በአጥፊዎች ላይ ያለውን የህግ ተጠያቂነት እንዳስሳለን፡፡

የጦር መሳሪያ ምንነት

የጦር መሳሪያ ማለት በአስነሺ ኃይል የሚፈነዳ ወይም በፍንዳታ ኃይል ጥይትን፣ አረርን፣ ቦምብን፣ ፈንጂን፣ ሚሳይልን፣ ሮኬትን እና ማናቸውም ተተኳሽ ነገር በማስፈንጠር በሕይወት፣ በአካል ወይም በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መሳሪያ ሲሆን ጥይትን እና ተያያዥነት ያላቸውን አባሪዎችን የሚጨመር መሆኑን አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 2(2) ሥር ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ አባሪዎችን የተባሉት የመሳሪያ መያዣን፣ ማንገቻን፣ መለዋወጫ፣ ማፅጃ፣ መጠገኛ እንዲሁም የጥይት መያዣ መጋዘን ወዘተ የሚጨምር ነው፡፡ በሌላ በኩል አዋጁ በአንቀፅ 2(13) ስር ከጦር መሳሪያ ውጪ ላሉ ጉዳት አድራሽ ዕቃዎች ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን ይህም በስለታማነታቸው ምክንያት ወይም የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም ወይም መርዛማ በመሆናቸው በሰው አካልና ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ እንደ ሳንጃ፣ ገጀራ፣ሜንጫ፣ ጦር፣ ቀስት ጎራዴ፣ ሴንጢ እና መሰል መሳሪያዎችን የሚያጠቃልል እንደሆነ ከአዋጁ መረዳት ይቻላል፡፡

የጦር መሳሪያ የሚሰጥበት አግባብና ይዘቱ
👆👆👆
በግለሰብ ደረጃ የሚያዙ የጦር መሳሪያዎች ለመያዘ የፀና ፍቃድ ያስፈልጋል፡፡ ዜጎች የጦር መሳሪያ ፍቃድ ከማግኘታቸዉ በፊት የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለዉ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር ፍቃድ ያለው መሆን፣ የአደገኛ ዕፅ ወይም የመጠጥ ሱስ የሌለበት መሆን፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በህግ ችሎታውን ያላጣ ሰው መሆን፣ የተስተካከለ አእምሮ ያለው ወይም የሐይል አጠቃቀም ባህሪ የሌለው መሆኑ በተቆጣጣሪ ተቋም የታመነበት መሆን፣ የመሳሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና እንዲወስድ ሲጠየቅ ፍቃደኛ መሆን፣ ለጦር መሳሪያ ፍቃድና እድሳት አስፈላጊውን ክፍያ መክፈል፣ መልካም ሥነ ምግባር ያለው ለመሆኑ ከሚኖርበት አካባቢ አስተዳደር የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ መቻል ወዘተ በአዋጁ የተጠቀሱ መስፈርቶች ናቸው፡፡

የተጠቀሱትን መስፈርቶች ለሚያሟላ ሰው የሚሰጠው የጦር መሳሪያ ፍቃድ የባለፈቃዱን ሰው ሙሉ ስም፣ ፎቶ፣ የትውልድ ቀን፣ አሻራ፣ አድራሻ፣ የጦር መሳሪያውን አይነት፣ የውግ ቁጥር፣ የጥይት ብዛት፣ ተዛማጅ እቃ፣ ፍቃዱን የሰጠው ባለስልጣን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም፣ ፍቃደ የተሰጠበት ቀን እና ፍቃድ የሚያበቃበት ቀን እንዲሁም ሌሎች ተቆጣጣሪው ተቋም በመመሪያ የሚያወጣቸውን መስፈርቶችን የሚያካትት መሆን አለበት፡፡ ይህም ያስፈለገበት መሰረታዊ ዓላማ በፍቃድ ተቀባዩም ሆነ ሰጪዉ ላይ የህግ ተጣያቂነት ለማስፈን እንዲሁም የተደራጀ መረጃ መያዝ ወንጀልን በመከላልም ረገድ ጠቃሚ በመሆኑ ነው፡፡

የጦር መሳሪያ አጠቃቀምንና አያያዝን አስመልክቶ የተከለከሉ ተግባራት

ማንኛውም ሰው የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ፣ አባሪ እቃዎችን እና ለልማት ሥራ የሚውሉትን ሳይጨምር የጉዳት አድራሽ እቃዎችን ወደ ሀገር ማስገባት፣ ከሀገር ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ ማሳየት፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር፣ ማጓጓዝና ማምረት የተከለከሉ ተግባራት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በአምራቹ ወይም በተቆጣጣሪ ተቋም የተሰጠ የጦር መሳሪያ የውግ ቁጥርን በሙሉ ወይም በከፊል መቀየር፣ ማጥፋት ወይም በማናቸውም አይነት ሁኔታ ተለይተው እንዳይታወቁ ማድረግ እንዲሁም የጦር መሳሪያን ወይም የጦር መሳሪያን የተመለከተ አገልግሎት ማስተዋወቅ የተከለከለ ነው፡፡

በሌላ በኩል አያያዝን በተመለከተ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም አድማ በሚደረግባቸው ስፍራዎች፣ የምርጫ ሥራዎች የሚከናወኑበት ቦታዎች፣ በሆቴሎች፣ በሲኒማና ትያትር ቤቶች፣ በሙዚየሞችና ተመሳሳይ በሆኑ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ በትምህርት፣ በሀይማኖትና እምነት ተቋማት ግቢ ውስጥ፣ በሆስፒታሎችና ክልኒኮች፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የህዝብ አገልግልት በሚሰጥባቸው ስፍራዎች፣ ፓርኮች ወይም በዱር እንስሳት መጠለያዎች ወዘተ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ተግባር ነው፡፡

በተያያዘም የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ሰዉ ፈቃድ ከተሰጠው ክልል ውጪ ባሉ የክልልና ትላልቅ ከተሞች ለሕዝብ በሚታይ መልኩ ታጥቆ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ ሆኖም በሥራ ላይ ላሉ የህግ አስከባሪዎች ለስራቸዉ አላማ የጦር መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈቃድ ተሰጠው ሰው በአዋጁ አንቀፅ 18 ሥር የተመለከቱት ግዴታዎች ያሉበት ሲሆን ለአብነትም የጦር መሳሪያውን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው የፍቃድ ወረቀቱን አብሮ መያዝ የሚጠበቅበት ከመሆኑም በተጨማሪ መሳሪያው ሲበላሽ፣ ሲጠፋ፣ ሲሰረቅ፣ ሲቀማ ወይም በማንኛውም ምክንያት ከቁጥጥሩ ውጪ ሲሆን በ15 ቀናት ውስጥ ለተቆጣጣሪው ተቋም ማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለሚታደስበት፣ ስለሚታገድበት፣ ስለሚሰረዝበት እና ስለሚወረስበት አግባብ

በአዋጅ አንቀጽ 13፣ 14 እና 15 መሰረት የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የፍቃድ አገልግሎት ጊዜው ከማብቃቱ ከ60 ቀናት በፊት የእድሳት ጥያቄውን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና ለተሰሠጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሸን ተቋም ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ቀርቦ ተቆጣጣሪው ተቋም የእድሳት ጥያቄው ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የቀድሞው ፍቃድ እንደፀና ይቆያል፡፡ ፍቃድ የተሰጠው ሰው ያቀረባቸው ማስረጃዎች አጠራጣሪ ሆነው ሲገኙና ጉዳዩን ማጣራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ከተሰጠው ፍቃድ ውጭ መሳሪያውን ለሌላ ተግባር ያዋለው ስለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ሲኖር እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ያበቃና ያልታደሰ ከሆነ ፈቃዱ ይታገዳል፡፡ ነገር ግን ባለፈቃዱ በ60 ቀናት ውስጥ በቂ ምክንያት አቅርቦ ማስታካከል ከቻለ እግዱ ይነሳለታል፡፡ ነገር ግን ማስታካከል ካልቻለ የጦር መሳሪያው በተቆጣጣሪ ተቋሙ ይወረሳል፡፡

በተጨማሪም መሣሪያው ወንጀል የተፈጸመበት ስለመሆኑ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ፣ ባለፍቃዱ ሲሞት፣ ያለበት አድራሻ ሳይታወቅ ሲቀር ወይም በፍርድ ወይም በህግ ችልታውን ሲያጣ፣ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ ከፈረሰ ወይም ከተዘጋ፣ በራሱ ፍላጎት ፍቃዱን ሲመለስ፣ ፍቃዱን ለማግኘት ከሚያስፈለጉ መስፈርቶች አንዱ የተጓደለ ከሆነ፣ ሀሰተኛ ማስረጃ ያቀረበ መሆኑ ሲታወቅ እንዲሁም መሳሪያ ከተበላሸና ሊጠገን የማይቻል ከሆነ ፈቃዱ ተሰርዞ ይወረሳል፡፡

የወንጀል ተጠያቂነት

 በጦር መሳሪያ መነገድ ወንጀል በሚመለከት የወንጀል ህግ አንቀፅ 481 ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

 ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ ከላይ የተመለከተውን ክልከላ እና ግዴታ በመተላለፍ የፀና ፈቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ካስገባ፣ ከሀገር ካስወጣ፣ ካስቀመጠ፣ ከተገለገለ፣ ከደለለ፣ ከገዛ፣ ከሸጠ፣ ካጓጓዘ፣ ካመረተ…ወዘተ ከ1 እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና ከ5,000 እስከ 10,000 በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
👉 በህጋዊ መንገድ የታጠቀውን የጦር መሳሪያ ተቆጣጣሪው ተቋም ሳይፈቅድ የሸጠ ሰው ከ1አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡

 የተሸጠው ለአሸባሪ ወይም ለህገ-ወጥ ቡድን ከሆነ ቅጣቱ 1 አመት እስከ 3 አመት ወይም እንደነገሩ ሁኔታ እስከ 5 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ይሆናል፡፡

 በህጋዊ መንገድ የታጠቀውን የጦር መሳሪያ በማስያዣነት የተጠቀመ ወይም በትውስት ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ ከ1 ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡

 የመሳሪውያን የውግ ቁጥር በሙሉ ወይም በከፊል የቀየረ፣ ያጠፋ ወይም በማናቸውም አይነት ሁኔታ ተለይተው እንዳይታወቁ ያደረገ ማንኛውም ሰው ከ6 ወር እስከ 2 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት የሚቀጣ ሲሆን ሌሎች ጥፋቶችም አንደጥፋቱ አይነት የቅጣት መጠን ተቀምጦላቸዋል፡፡

ማጠቃለያ

ዜጎች ሰላምና ደህንነታቸው ተከብሮ የመኖር መብት እንዳላቸው ሁሉ በህግ የተጣሉባቸውን ግዴታዎች ማክበር አለባቸው፡፡ የጦር መሳሪያ በግለሰብ ደረጃ የሚፈቀደው ዜጎች ለሰላማቸው አስጊ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው ራስን መካላክል እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡

ሆኖም የጦር መሳሪያ ለጥፋት አላማ ሊውል ስለሚችልና ገዳይ መሳሪያ ስለሆነ ጥንቃቄ እና ቁጥጥር ሊደረግለት ይገባል፡፡ በመሆኑም የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚስፈልገው በመሆኑ ፍቃድ የተሰጠው አካል በህጉ ላይ የተቀመጡትን የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ግዴታዎችን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
#ኢትዮጵያ #ኤክሳይዝ_ታክስ

ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማሻሻይ ተደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎች ላይም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲቀንስ ያደርጋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተሰምቷል።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

- በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤

- ከ3000 ሲሲ ባላይ  ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤

- ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ ወልዱ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ " አሁን በጣም ትኩረት የምናደርገው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ነው። ነዳጅን ለማበረታታ አይደለም (የኤክሳይዝ ታክሱ መቀነሱን ማለታቸው ነው) ግን በጣም ከፍ ያለ ከሚሆን ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ስላሉት ሲወጣ ይታያል አሁን ያለውን ከፍተኛ ሁለት መቶ አርባ አካባቢ ያለው ወደ መቶ ሃያ አካባቢ ዝቅ እንዲል ፤ በየደረጃው እንደዛ እንዲስተካከል ነው። " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ አዋጁን ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ከፍተኛ የሆነውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በመቀነስ #የኤሌክትሪክ_ተሽከርካሪዎች እና የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ መሳይ ወልዱ ፤ " ታክሱን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በተለይ የሀገር ውስጥ ገጣጣሚዎችን በማበረታታት አቅርቦትን ስለሚጨምር ፍላጎትም ይመጣል። አቅርቦትም ስለሚመጣ ዋጋ ተመጣጣኝ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ፤ ይሄ ወደ ቀረጥና ታክስ ነፃ የሚደረጉ ሩጫ ሁሉ ይቀንሰዋል፤ ይሄ ከፍተኛ መሆኑ ለዛ አንዱ ማበረታቻ ስለሚሰጥ ፤ ዋጋውን ይቀንሰዋል  በተለይ የኦውቶሞቲቭ ኢንድስትሪው የሀገር ውስጡ የራሱን ሚና ይጫወታል በማሳደግ እየተረጋጋ ይሄዳል የሚል ሃስብ ነው ያለው። " ሲሉ ገልፀዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተካተተው ሌላው ፤ 10 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸው የነበሩት የቪድዮ ካሜራ እና ቴሌቪዥን ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ተደርጓል።

አቶ መሳይ " በመጀመሪያው ማሻሻያ እራሱ ቴሌቪዥን ወደ 40 % ነበር የነበረው በጣም ተቀንሶ 10% ነው የተደረገው። የቪድዮ ካሜራም እንደዛው ፤ በጣም አስተያየት ተደርጓል የመጀመሪያው ላይ ግን የገቢ ክፍተት እንዳይፈጠር ቀስ በቀስ መውጣት ስላለብን ከ40 % ወደ 10 % ተደርጓል በተለይ ከስነ ጥበብ ከማሳደግ እና ከመደገፍ አንፃር ታይቶ ፣ ቴሌቪዥንም ህብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝበት የመንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የሚሰማበት ስለሆነ እሱ ላይም ቅናሽ ተደርጓል። በሂደት ስናየው አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ ያስፈልጋል የሚል ነው #ቴሌቪዥንና #ቪድዮ_ካሜራ በተለይ በዛ ውስጥ ባይካተቱ የሚል ሀሳብ ነው የቀረበው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ2012 ነበር ለ30 ዓመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ ያሻሻለችው ፤ አሁን ከ3 ዓመት በኃላ የሚደረገው ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር  እኩል እንድትራመድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተወሰደ ነው።
#Ethiopianbusinessdaily
https://t.me/lawsocieties
ፍቅረኛሞች ከነበሩት ከዳኛ ትንሳዔና ከገቢዎች ሠራተኛዋ ዙፋን ህይወት ህልፈት ምን እንማራለን
~~~................
ይሄ እኮ ከዓለም ዋንጫ ጨዋታ በላይ ትንታኔ የሚሻና ለብዙዎች መማሪያና ማስተማሪያ ሊሆን የሚገባው ጉዳይ ነው።

ትንሳዔ ህግ የተማረ ዳኛ ነው። ፍሬሽ ተመራቂ አይደለም። የረጅም ጊዜ ልምድ ያለውና የተረጋጋም ነው ይባልለታል። ታድያ እንዴት እንዲህ ያለ አጥፍቶ የመጥፋት ውሳኔ ላይ ደረሰ?

ዙፋን በገቢዎች መሥሪያ ቤት የምትሠራ፣ የትንሳዔ የሀገሩ ልጅና ፍቅረኛው ናት። እሷስ ትንሳዔን እልህ ለማስያዝና "አሳብድሃለሁ" እያለች ለመቅበጥና ለመወስለትን ምን አደፋፈራት? "እልህ ምላጭ ያስውጣል" ተረትን ማሰብ እንዴት አቃታት?

የማወራው ከእዚህ መንደር በቃረምኩት መረጃ ነው።

ልጄ እንደ ዙፋን እንድትሆን አልፈልግም። ልጄ እንደ ትንሳዔ እንዲሆን አልፈልግም። ክስተቱ ለጥናትና መፍትሔ ፍለጋ መነሻ እንዲሆን ያስፈልጋል።

"የሰው ሆዱን የወፍ ወንዱን ማወቅ አይቻልም" ይሉት አባባል አለ። ሰው ተማርሮ ሲጨክን እንዲህ በራሱም በሚወደውም ሊጨክን እንደሚችል ገምቶ ፍቺንና መለያየትን በእርጋታና በመስማማት መፈጸም ተገቢ ነው።

ህግን ተማምኖ "ልክ አስገባዋለሁ" የሚለው ድፍረት ብዙ እንደማያዋጣ ከበቂ በላይ ክስተቶች አይተናል።

"ፍቅር እውር ነው" ይል ነበር;ቀዳሚው ትውልድ። ያ ትውልድ የሰው ባህሪይ ገብቶታል!

ያሁኑ ትውልድ ትምክህቱን በህግ ላይ ብቻ አድርጎ ብዙ ሰው ጠፋ። የሰው ልጅ ስነ-ልቦናን እስክንረዳ ስንት ሰው አሲድ ይደፋበት? ስንት ሰው ጥይት ይርከፍከፍበት? ስንት ሰው መርዝ ይጋት? ስንት ሰው ይሙት? ስንት ሰው ተያይዞ ይለቅ?

ወንዱ ገዳይ ባይሞት ኖሮ ይሄኔ ሰልፍ እንውጣ ባዮች ሺ ነበሩ። አሁን ግን ዝም ዝም ዝም ብቻ። ለምን? እነርሱ መፍትሔያቸው ከቅጣት ያለፈ አይደለማ! ተቀጪ ካጡ መፍትሔ የላቸውም።

መፍትሔው ሰልፍ አይደለም። መፍትሔው ፍርድ አይደለም። መፍትሔው ህግ አይደለም። መፍትሔው ቅጣት አይደለም።

መፍትሔው የወንድ ልጅ ሳይኮሎጂን መረዳት ነው። መፍትሔው የሴትን ልጅ ባህሪይ መረዳት ነው። መፍትሔው የማህበሩን ሳይኮሎጂ መረዳት ነው። መፍትሔው አሰቃቂ ርምጃዎች ለምን በዙ ብሎ ምክንያቱን መፈለግ ነው። መፍትሔው ህጉን ከሰው ባህሪ ጋር አጣጥሞ ማስተካከል ነው።

ትንሳዔ ህግ ያውቃል። የደረሰበትን የስነ-ልቦና ጉዳት ህግ እንደማይፈታለት ገብቶታል። እናም ህጉን ተሻግሮ ውሳኔውን በእጁ ወሰነ።

የሀገራችን ህግ የሰው ሳይኮሎጂን ሊያጤን ይገባል። ህግ የሰው ሳይኮሎጂን፣ ባህልን፣ ሃይማኖትን፣ የማህበረሰቡን የጋራ እሴት ከግምት ሊያስገባ ያስፈልጋል። ያለዚያ ብዙ ሰው ሊያልቅ ነው። ህግ ይቀጣል እንጂ ህግ ነፍስ አያድንም፣ ነፍስ አይመልስም።

ልጄ ሆይ! እህቴ ሆይ! "ሰው በህግ ብቻ አይኖርም" የሚለውን ቃል አስተውዪ።

ግዴለም ከመሞት መሰንበት ይሻላል። እልህን ወደጎን አድርጎ በጥበብና በፍቅር መኖር ይሻላል። አብሮ መሆን ካልተቻለም በጥበብና በመከባበርና በፍቅር መለያየት ይሻላል።

ከእንግዲህ የሞቱትን "ነፍስ ይማር" ማለት እንጂ ሌላ ምን ማለት ይቻላል?

መፍትሔው ልብ መግዛት ነው። ሁልሽም ከዚህ ትምህርት ውሰጂ! ያልተነገሩ ብዙ እንዲህ ያሉ ክስተቶች አሉ።

ወንዱ በፊት ለፊት በጉልበት የገደላት ሴት፣ ሴቷም በጓዳ እንደ አይጥ በመርዝ ጭጭ ያደረገችው ወንድ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ምንሊክ ሆስፒታል ያላወቀው የሰፈር ሀሜታ የሆነ ሞት ብዙ ነው።

የዛሬው ህግ ከትናንት በምን ተሻለ? ምንስ አጎደለ? ወፍ እንዳገሯ ትጮሃለችና የተውሶ ህግን ትቶ የአገሩን ስነ-ልቦና የተከተለ ህግ ማውጣት ይበጃል።

ግዴለም መከባበር ይበጃል። ግዴለም ህጉን ማረቅ ይበጃል። ግዴለም ፍቅር ይበልጣል።

ቀጣዩ ትውልድ ይንቃ! ያሁኑ እንኳ ተወዛግቧል፤ ገና እስኪነቃ ብዙ ማገዶ ይፈጃል፣ ብዙ ነፍስ ያስጨርሳል፣ ብዙ ሰልፍ ያሳየናል።

የነገው ትውልድ ግን ንቃ!
@Get Toughe
Via voice of justice
https://t.me/lawsocieties
#ተቋሙ_ሐሰተኛ_የትምህርት_ማስረጃን_ለማጥራት_ከባለድርሻ_አካላት_ጋር_በቅንጅት_እየሠራ_ነው
====== ====== ====
አዲስ አበባ፡- በፌዴራልና በክልል የመንግሥት ተቋማት በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው የሚሠሩ ግለሰቦችን ለማጥራት በትብብር እየተሠራ መሆኑን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ማርታ አድማስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት በሚሠራው መጠነ ሰፊ ሥራ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠሩ ነው።

የፌዴራልና የክልል ተቋማት አዲስ የሰው ኃይል ቅጥር ሲፈፅሙ እና የደረጃ ዕድገት ሲሠጡ የሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ መሆንና አለመሆኑ እንዲጣራላቸው ወደ ተቋሙ መላካቸው አብረው የመሥራት ቁርጠኝነታቸውን ያሳያል ብለዋል።

እንደማሳያም የደበብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከክልል እስከ ወረዳ ያለው የመንግሥት መዋቅር ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማጋለጥና በማጥራት ሂደት ቀዳሚ እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ተቋማት ከትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን ጋር በቅርበት እየሠሩ መሆኑን ወይዘሪት ማርታ ተናግረዋል።

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለማጥራት ተማሪዎች አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ማምጣታቸውንና መረጃ ተቀብሎ የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
ምክር ቤቱ ሁለት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓትን እና የመንግስትና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የአዋጆቹን አስፈላጊነት አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ እንዳሉት፤ የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓቱን ደህንነት ለማስጠበቅና በፋይናስ ዘርፉ አስተማማኝና ቀልጣፋ ሥርዓት በመዘርጋት፤ ለውጦችን እና እድገት ታሳቢ ባደረገ መልኩ የክፍያ ስርአቱን ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
 
የተከበሩ አቶ ደሳለኝ አያይዘውም፤ የመንግስት እና የግል አጋርነት ረቂቅ አዋጅን በሚመለከት የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ለማገዝ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመው፤ በመንግስትና በግል ባለሀብቶች በጋራ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ምቹ ምህዳር በመፍጠር፤ ለግል ሴክተሩ የእውቀትና ክህሎት ሽግግር በመፍጠር የፋይናንስ ሴክተሩን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው፤ የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓት የሀገራችንን የፋይናስ ዘርፍ በማገዝ እድገት እና ብልጽግና ለማምጣት እንዲሁም የግል ዘርፉን በማሳተፍ ለኢኮኖሚው እድገት መነቃቀትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል የተከበሩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለመግስት እንደ ሀገር ተግዳሮት የሆነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በጨረታና በድርድር የሚለው ለኪራይ ሰብሳቢነት በር ስለሚከፍት በረቂቅ አዋጁ ላይ በጨረታ ብቻ በሚል ቢቀመጥ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የተከበሩ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የክፍያ ሥርዓት አዋጁ ሙሉ በሙሉ የባንክ ስራን ተክቶ የማይሰራ በመሆኑ ከባንክ በመለስ ያሉ የክፍያ ስርአቶችን የውጭ ባለሃብቶችና ዜጎች እንዲሳተፉ ለማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
የባንክ ገዥው የተከበሩ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) አክለውም የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት አዋጁ ስያሜን በተመለከተ፤ በብዙ የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ልምድ በመውሰድ ተሞክሮዎቹ ብሔራዊ የሚለው ስያሜ የጋራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው፤ የመንግስት እና የግል አጋርነት ያደጉ ሀገራት የተጠቀሙበት ሀገራቸውን ለማሳደግ ውጤታማ ስራ የሰሩበት በመሆኑ መንግስትና የግል ሴተክተሩ ተቀራርበው በመስራት ለፕሮጀክቶች ተፈጻሚንት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ ክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1282/2015 ሆኖ በሶስት ድምጸ ተአቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ምክር ቤቱ በውሎው፤ የመንግስትና የግል አጋርነትን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1283/2015 ሆኖ በአንድ ተቃውሞ እና በአንድ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቀዋል፡፡

በ መኩሪያ ፈንታ
(ዜና ፓርላማ)፣ ታህሳስ 13፣ 2015 ዓ.ም፤
ParlamaNews
www.hopr.gov.et
https://t.me/lawsocieties
ከዛሬ ጀምሮ ሲሚንቶ በነጻ ገበያ እንዲ ተወሰነ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ከዚህ በፊት የነበረው የሲሚንቶ ሽያጭ መመሪያ መቀየሩን ገልጸዋል።

መመሪያው የሲሚንቶ ዋጋ በመንግሥት ተወስኖ እንዲሸጥ መደረጉ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሳበት እንደነበር የጠቀሱት አቶ ተሻለ በዚህም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች፥ ሲሚንቶን በቀላሉ እንዳያገኙ አድርጓቸው እንደነበር ተናግረዋል ።

በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም አከፋፋዮችን እና ቸርቻሪዎችን መምረጥ የፋብሪካዎቹ እድል ነው ብለዋል።

የፋብሪካዎቹ የመሸጫ ዋጋ ለጊዜው ምርታማነት እስከሚጨምር ድረስ የፋብሪካ ዋጋ በስድስት ወር አንድ ጊዜ በሚኒስቴሩ እንደሚወሰን ነው የተናገሩት።

መንግስት ከግብይቱ የወጣ ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረትም መንግስት ሽያጩ ያለ ደረሰኝ እንዳይካሄድ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስረድተዋል። በግብይቱ ውስጥም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ግዴታ መሆናቸውን ጠቁመዋል። እያንዳንዱ ፋብሪካ የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም አከፋፋዩን የመምረጥ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ በየትኛውም ቦታ ቁጥጥር እና ክትትል ሳይደረግበት በነጻ ገበያ ይካሄዳል ነው ያለው ሚኒስቴሩ። ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚወጣ ማንኛውም ተሽከርካሪ የመዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደሚኖርበትም ነው የተናገሩት።(ሼር)
 https://t.me/lawsocieties
የፉብሪካ የመሸጫ ዋጋ
220830.pdf
825.3 KB
ከባንክ ሂሳቤ ላይ ገንዘብ አላአግባብ ወጪ በመደረጉ ባንኩ ገንዘቡን እንዲመልስ የሚል ክስ ሲቀርብ የፎረንሲክ ምረመራውን ውጤት ብቻ መሠረት በማድረግ ባንኩን ለክሱ ኃላፊ ማድረግ መሰረታዊ ስህተት ነው።
ሰ/መ/ቁ. 220830 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
በወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ መረጋገጥ ይኖርበታል።
በመሆኑም ክስ ከቀረበበት ባንክ ዉጪ በሌሎች ባንኮች ከወጪ ማዛዣ ክፍያ ጋር በተያያዘ ልምድ ባላቸዉ የባንክ ባለሙያዎች እንዲታይ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ግዴታዉን የተወጣ መሆን አለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የባለሂሳቡ ባንክ ደብተር ቀርቦ ሂሳቡ ተቀንሶ የተጻፈ መሆን አለመሆኑ ሆነ የባለሂሳቡ መታወቂያ በማየት ባንኩ ያረጋገጠ መሆን አለመሆኑ ደግሞ በሰው ማስረጃ ሆኖ የባንክ ሂሳብ ደብተሩ ካለ በማስቀረብ መረጋገጥ ይኖርበታል።

https://t.me/lawsocieties
ታስረው እንዲቀርቡ ታዘዘ።

የፍርድ ቤት መጥሪያ ፈርመው ወስደው ሳይቀርቡ የቀሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ።

የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ ተጭበርብሯል ተብሎ የከባድ ሙስና ወንጀል በቀረበባቸው ተከሳሾች ላይ የዓቃቢህግ 2ኛ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት መጥሪያ ፈርመው ተቀብለው ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ታስረው እንዲቀርቡ ዛሬ ትዕዛዝ የተሰጠው።

  ትዕዛዙን የሰጠው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

በአ/አ ከተማ በሀምሌ 1ቀን 2014 ዓ/ም ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር ተያይዞ  ዕጣው ተጭበርብሯል ተብሎ የአ/አ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት  ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን እና  ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑትን አቶ አብርሀም ሰርሞሌን ጨምሮ በአጠቃላይ በ 11 ተከሳሾች ላይ በየደረጃው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

ተከሳሾቹ  ወንጀሉን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ምስክር  እንዲሰሙለት ጠይቆ ነበር።

በዚህ መሰረት ዓቃቢህግ በሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም በአ/አ ከተማ ወጥቶ ከነበረው የ14ኛ ዙር 20/80  እና የ3ኛ ዙር የ40/60  ከኮንዶሚኒዬም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ  ስርዓት ጋር ተያይዞ እንዲሁም  ለምቷል የተባለው ሶፍትዌርን የሚመለከት እና የተደረገ የኦዲት ስርዓትን ላይ ያተኮረ ምስክርነት እንዲሰማለት  የምስክር ጭብጥ  ካስመዘገበ በኋላ በህዳር 22 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ፍርድ ቤቱ የዓቃቢህግ ምስክር ቃል መሰማት ጀምሮ ነበር።

ፍርድ ቤቱ  እስካሁን የ 8 የዓቃቢህግ ምስክሮችን ቃል ያዳመጠ ሲሆን በ2ኛ የዓቃቢህግ ምስክር ሆነው የተቆጠሩት የአ/አ ቤቶች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ግን  መጥሪያ ደርሷቸው ፈርመው የወሰዱ ቢሆንም በችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።ፍርድ ቤቱም ግለሰቡ በፖሊስ ታስረው በይደር እንዲቀርቡ ትዕዛዝ  ሰጥቷል።

Via:- Tarik Adugna
https://t.me/lawsocieties