አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ መደብ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በ2013 እና 2014 የትምህርት ዘመን ከከፍተኛ የትምሀርት ተቋማት በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቁ ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ በእጩ ዐቃቤ ሕግ ደረጃ መደብ የቅድመ ስራ ስልጠና በመስጠት አወዳድሮ ለመቅጠር መስከረም 06 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት በተወዳዳሪነት የተመዘገባችሁ እና በማስታወቂያው የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች (ለፈተና የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ከሚፈተኑበት አዳራሽ አድራሻ ጋር ከዚህ ማስታወቂያ ስር ተያይዟል) የመጀመሪያ ዙር የፅሁፍ ፈተና ኅዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር አዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና የፍትሕ ሚኒስቴር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የመሚሰጥ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰአቱ ቦታው እንድትገኙ እያሳውቅን ወደ ፈተና አዳራሹ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ፣ ማጣቀሻም ሆነ ሕግጋትን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
November 24, 2022
👆👆👆👆👆👆👆👆

ማስታወሻ፡-
1.  በኦንላን የተመዘገባችሁ ተወዳዳሪዎች ፡-
•  የትምህርት ማስረጃችሁን ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር፤
•  መልካም ስነምግባር ያላችሁ ስለመሆኑ ከምትኖሩበት አካባቢ የተፃፈ ማስረጃ እንዲሁም
•  በዐቃቤ ሕግነት ለማገልገል የፈለጉበትን/የተነሳሱበትን ምክንያት የሚገልፅ በአማርኛ ቋንቋ የተፃፈ (አንድ ገጽ) እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፈ (አንድ ገጽ) ፅሁፍ ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት ፤ አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፣ ወረዳ 08 ፣ ጆሞ ኬንያታ ጎዳና ፤ ከባንቢስ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
2.  በተጨማሪም የመወዳዳሪያ መስፈርቱን አሟልታችሁ ለፈተና በተጠሩት ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ ያልተካተተ ተመዝጋቢዎች ካላችሁ ቅሬታችሁን ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ ከላይ በተገለፀው የጉባኤው ጽ/ቤት አድራሻ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የዐቃብየነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት
#Share
https://t.me/lawsocieties
November 24, 2022
በፍትሕ ሚኒስቴር ስር ባሉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከሚሰጡ የፍትሕ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ለሚገጥሞት ቅሬታ አቤቱታዎትን የት ማቅረብ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እየተከናወነ ካለውና እየጨመረ ከመጣው የሥራ ፍሰት አንጻር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ተግባራት አቀናጅቶ እንዲመራ እና ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግ እና የቅርብ አመራር በመስጠት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከስር ከስር እየቀረፉ ውጤታማ ተግባር እንዲያከናውን ለማስቻልም በማሰብ የ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ ከተገልጋይ አንጻር ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል አንዱ የሚቀርቡ አቤቱታና እና ቅሬታዎችን ሰንሰለቱን ጠብቀው መቅረባቸውን የማረጋገጥ፣ የማስተናገድ፣ ዉሳኔ የመስጠት እና አፈፃፀሙን የመከታተል ኃላፊነት ይገኝበታል፡፡

በመሆኑም በድሬዳዋ እና ሃዋሳ የሚገኙትን ጨምሮ በአስራ ሁለቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር አቤቱታ ወይም ቅሬታ ለማቅረብ ሲፈልጉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡን አለፍ ብሎ ቫርኔሮ አደባባይ አጠገብ የፍትህ ሚኒስቴር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚገኝበት ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ቀርበው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር
ለሕግ ፣ ለፍትሕ ፣ ለርትዕ
በጎግል ማፕ (Google Map) ለመመራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://goo.gl/maps/TZjJNGSkz7GM4M6L6

https://t.me/lawsocieties
November 25, 2022
የወንድሙን ልጆች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ ጋዶላ ጎዱማ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አሳሼ አታረ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ረቡዕ ዕለት በግምት ከቀኑ 11 ሰዓት አከባቢ በእርሻ ማሳዬ የሚገኘውን አትክልት በበግ አስበልተዋል በሚል የወንድሙን ልጆች ገድሏል።

የክስ መዝገቡ ተከሳሽ የስድስትና የስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት የወንድሙን ልጆች አባብሎ ወደ ቤቱ ካስገባ በኋላ በስለት ወግቶና ቆራርጦ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎና በማዳበሪያ ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ መጣሉን ያስረዳል።

ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የጎፋ ዞን አቃቤ ህግም የወንጀል ህግ አንቀፅ 539(1)ሀ/ድንጋጌን በመጥቀስ ክስ መስርቶበት በማስረጃ በመረጋገጡ ግለሰቡ ላይ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ መተላለፉን ከደቡብ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#tikvahethmagazine
November 25, 2022
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
.......👇👇👇👇👇👇👇
በፍትህ ስርዓቱ ስላጋጠመው አደጋ የመፍትሄ አቅጣጫ እና
ለዳኞች እና አቃቤ ህጎች ፍልሰት  ምክንያቶቹ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች‼️

👆👆👆👆👆👆👆👆👆

እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
🔘 Live on Telegram 👈👈

#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
👇👇👇👇👇👇👇👇
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ.......

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig

Watch "Ale_Hig🔴አለ_ህግ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
November 25, 2022
175155.pdf
537.6 KB
November 25, 2022
የፌድራል_ጠቅላይ_ዐቃቢ_ህግ_ማቋቋማያ_አዋጅ.pdf
550.9 KB
... የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ…
Proclamation No. 943/2016Federal Attorney General Establishment Proclamation
November 25, 2022