አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Industrial Parks Development Corporation በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position: 8 postions
Senior Auditor and Senior Lawyer

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ:
BA/MA/LLB

🇪🇹 የስራ ቦታ:Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ሀምሌ
11/2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/industrial-parks-development-corporationq/
ማስታወቂያ
የኢፌዴሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ መንገድ ገብተው የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገር ዜጎችን የመመዝገብና የመቆጣጠር ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 354/1995 እና ደንብ ቁጥር 114/1997 የተሰጠው ተቋም ነው።

ስለሆነም፣
• በተለያዩ የቪዛ ዓይነት ወደ ኢትዮጵያ የገባችሁና ቪዛችሁ የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤
• የመኖሪያ ፈቃዳችሁ የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤
• ምንም አይነት ቪዛም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላችሁ፣
• በኢ.ፌ.ዴ. ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት ወይም የጥገኝነት ጠያቂ ዕውቅና አግኝታችሁ በከተማ ስደተኝነት በፈቃድም ይሁን ያለፈቃድ በአዲስ አበባ እና በዙሪያው በሚገኙ ከተሞች የምትኖሩ የውጭ አገር ዜጎች በሙሉ፡-
አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከሐምሌ 11 እስከ 25/2014 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ የሚያካሂድ ስለሆነ፤ ዘውትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በሁሉም ስራ ቀናት ማንነታችሁን የሚገልፅ ሕጋዊ ሠነድ /ፓስፖርት፣ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የስደተኛ መታወቂያ ወይም የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ ፣ የጉዞ እና/ወይም ሌሎች ተያያዥ ሠነዶችን/ ይዛችሁ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
• በአዲስ አበባ ከተማ፡- በሁሉም የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ/ቤቶች እና ፒያሳ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣
• በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች፡- ገላን፣ ዱከም፣ ለገጣፎ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ እና ሰበታ
እንዲሁም ቢሾፍቱ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤቶች ናቸው፣
ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባልተመዘገቡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
ማሳሰቢያ፡- የውጭ ዜጐችን በመቅጠር የምታሰሩ፣ በቤታችሁ ተከራይቶ ወይም በጥገኝነት የምታኖሩ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ መመዝገባቸውን እና የምዝገባ ማረጋገጫ መውስዳቸውን እንድታረጋግጡ እናሳስባለን።

ለበለጠ መረጃ ድረገፃችንን ይጎብኙ፡- www.invea.gov.et.
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Notice
The Immigration and Citizenship Service of the Federal Democratic Republic of Ethiopia is mandated to register and administer legal permits for foreign nationals living in Ethiopia according to Proclamation No. 354/2003 and Regulation No. 114/2004. As a result, to make legal processes the Immigration and Citizenship Service announces this registration.
Therefore, all foreigners with:
• Expired visas;
• Expired Residence permits; and
• Those without any visa or residence permit;
• As well as refugees or asylum seekers requesting status and residing in Addis Ababa and its vicinities with or without an urban refugee permit;
Should register in person between July 18 to August 01, 2022 in all days at work hours including Saturday and Sunday by bringing legal documents that testify your personality (Such as - passport, resident ID, Refugee ID, Proof of Registration, and/or any travel documents).
Place of Registration: -
• Addis Ababa: Vital Events Registration Offices of all Woredas and Immigration and Citizenship Service, Piazza Office;
• Oromia Special Zone within the vicinity of Addis Ababa: Vital Events Registration Offices at Gelan, Dukem, Lege Tafo, Sululta, Burayu, Holeta, Sebeta, and Bishoftu town.
The Immigration and Citizenship Service would like to notify you that it will take legal measures against those who fail to register on the dates mentioned in this notice.
Remark: - Those who hire and give shelter or rent a house to foreign Citizens should follow up their registry and make sure whether they take proof of registration.

For further inquiries, please visit our website: - www.invea.gov.et.
Immigration and Citizenship Service
Addis Ababa, Ethiopia.
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ
#Alehig
@lawsocieties
@AleHig
https://t.me/lawsocieties
Audio
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎችን በድምፅ እንሆ
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች ለሁሉም በተለይም ለአይነ ስዉራን ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ ሰለሞን ማስታዎቂያ እና ህትመት ከፍትህ ፕሮግራም ጋር በመተባበር እንደሚከተለዉ አቅርበዉላችኋል፡፡ ከዚህ ቀደም ቀርበዉ የነበሩትን ማለትም ከቅፅ 22 እስከ 24 ድረስ ካሉ የሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዎች መካከል 25 የጠተመረጡ ዉሳኔዎች ጨምሮ ሌሎች 25 ዉሳኔዎችን በማካተት እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡
የተፈታኝ_ስም_ዝርዝር_እና_የፈተና_ቦታ_1.pdf
3.5 MB
ለአዲስ አበባ ከተማ ዓቃቤ ህግ ተፈታኞች
👆👆👆👆👆👆👆👆
#Clickethiopian laws
#ፍቺ
የሁለት ተጋቢዎችን የትዳር ግንኙት በሕግ መሠረት ማቋረጥ

ጋብቻ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው የፍቺ ውሣኔ ሲሰጥ መሆኑ የቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 75/ሐ/ ያመለክታል፡፡

ጋብቻ አንድ እንደሆነ ሁሉ ጋብቻው በፍቺ ሊፈርስ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሁለት የጋብቻ ስርአቶች መከናወናቸውም ሁለት ጊዜ የፍቺ ውሣኔ እንዲሰጥ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡

ተጋቢዎቹ ግንኙታቸውን ማቋረጥ ከፈለጉ ጋብቻው በሁለት አይነት ስርአት ስለተፈፀመ ግንኙቱን ለማቋረጥ እያንዳንዱን ጋብቻ አስመልክቶ የፍቺ ውሣኔ ሊሰጥ የሚገባው አይሆንም፡፡ የሕጉም አላማ ይህ አይደለም፡፡

አንድ ወንድ እና ሴት ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጋቡ በኋላ በድጋሚ በውጭ አገር ጋብቻ መስርተው በዛው አገር በፍርድ ቤት ፍቺ ከፈጸሙ በግራ ቀኙ መሐከል የነበረው ጋብቻ አንድ ብቻ በመሆኑ በውጭ አገር የተሰጠው የፍቺ ውሣኔ ይህን በመካከላቸው የነበረውን አንድ ጋብቻ እንዳፈረሰ ተደርጎ ሊቆጠር ይገባል፡፡
ግራ ቀኙ ውጭ አገር ከሄዱ በኋላ ሌላ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት መፈፀማቸው ሁለት ትይዩ /Parallel/ ትዳር ውስጥ ነበሩ ሊያሰኛቸው አይችልም፡፡ በመሆኑም በመካከላቸው የነበረው የጋብቻ ግንኙነት አንድ የመሆኑን ያሕል የሚፈርሰውም በአንድ የፍቺ ውሣኔ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 40781 ቅጽ 8
Via Ts Md
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ
#Alehig
@lawsocieties
@AleHig
https://t.me/lawsocieties
የሥራ ስንብት ክፍያ ስሌት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በአዋጅ 156/201 አንቀጽ 40 መሰረት ስሌቱን ለመስራት መጀመሪያ የሠራተኛው አማካይ የቀን ደመወዝ መታወቅ አለበት፡፡ የሥራ ሰዓቱ በሳምንት 48 ሰዓት የሆነ ሠራተኛ ወርሃዊ የሥራ ሰዓቱ 208 ሰዓት ነው፡፡
በወር የሚያገኘው ደመወዝ 208 ሰዓት ለሰራበት የሚከፈለው ክፍያ ነው፡፡

ወርሃዊ ደመወዙ ለ 208 ሰዓት ሲካፈል የአንድ ሰዓት ደመወዙን ይሰጠናል፡፡

በወር 9,000 ብር የሚከፈለው ሠራተኛ የአንድ ሰዓት ደመወዙ ብር 9000/208 ብር 43.269.23 ነው፡፡

የአንድ ሰዓት ደመወዝ በስምንት የሥራ ሰዓት ሲባዛ አማካይ የቀን ደመወዝ ይሰጠናል፡፡ ስለሆነም ብር 43.269.23 ሲባዛ በ 8 የሚሰጠን ውጤት ብር 346.15 ይሆናል፡፡

የሠራተኛው የቀን ደመወዝ ብር 346.15 መሆኑን ከለየን ቀጣዩ ስራ የስንብት ክፍያውን በአንቀጽ 40 መሰረት ማስላት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ፡- አምስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው ሠራተኛ የስንብት ክፍያ እንደሚከተለው ይሰላል ፡

ሀ. ለመጀመሪያው ዓመት አገልግሎት ብር 346.15 (የሠራተኛ አማካይ የቀን ደመወዝ) ሲባዛ በ 30 ብር 10,384.5

ለ. የብር 10,384.5 አንድ ሶስተኛ ብር 3,461.5 ሲሆን ይህም በቀሪዎቹ የአገልግሎት ዓመታት ላይ ይባዛል ፡፡ (ብር

3,461.5 ሲባዛ በ 4) እኩል ይሆናል ብር 13,846 :: የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ 09 11 19 02 99

ሒ ከላይ በ ሀ እና ለ የተገኘው ውጤት ሲደመር (0,384.5 ብር + 3,846 ብር) ጠቅላላውን የስንብት ክፍያ መጠን ይሰጠናል፡፡
ስለሆነም አምስት አመት የሰራ ሠራተኛ የሚያገኘው የስራ ስንብት ክፍያ 24,230.5 ብር ነው ፡፡
በሳሙኤል ግርማ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ
#Alehig
@lawsocieties
@AleHig
https://t.me/lawsocieties
The U.S. Agency for International Development is seeking offers for the provision of legal advice
https://g.co/kgs/EdTzNb

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ
#Alehig
@lawsocieties
@AleHig
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
🅰🅰Pacta Sunt Servanda🅰🅰
🅰 Be Trustworthy 🅰
The more people trust you, the happier you’re going to be. If people don’t trust you, you’re going to live a pretty miserable life.

If you want to be happy, you’ve got to become somebody that people trust.

Any time you go to a bank for a loan, they’re going to do a credit check. They want to know if you’re worthy of being trusted with credit. Do you pay your bills on time? Do you have a track record of keeping your word? Can you be depended on to pay this money back? Are you creditable?

The thing is, everybody around you is doing a credit check on your life every moment of your life. They want to know if you are what you say you are. Are you the real deal? Are you showing your true colors? Can you be trusted?

If you’re going to be happy in your relationships and in life, you have to learn to be a trustworthy and reliable person.

How do you develop a reputation of reliability?

First, you live with integrity. Integrity doesn’t mean you’re perfect. It means what you see is what you get. You are the real deal, because your actions match your words.


Second, you keep your promises.
🅰🅰Pacta Sunt Servanda 🅰🅰

This means you keep a promise, even when you find out it’s going to cost you more than you thought.

Learning to live with integrity and keep your promises will show others that you can be trusted and will in turn make you a much happier person.
🅰🅰Pacta Sunt Servanda 🅰

law is your day to day life.....real life experience🅰
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የውጪ ንግድ ምርት ናሙናዎች አቀባበል አና አላላክ መመሪያ ቁጥር 72/2014ዓ.ም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 768/2004 አንቀጽ 32(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወጪ ንግድ ምርት ናሙናዎች አላላክ እና አቀባበል መመሪያ ያዘጋጀ መሆኑን እና መመሪያው በፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 16 መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል እንዲመዘገብ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ መመሪያው በስራ ላይ እንዲውል የመመሪያውን ቅጅ ልከዋል፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር #አለ_ህግ #Alehig @lawsocieties @AleHig
4-0013-15 8-11-14.pdf
8.7 MB
የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የውጪ ንግድ ምርት ናሙናዎች አቀባበል አና አላላክ መመሪያ ቁጥር 72/2014ዓ.ም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 768/2004 አንቀጽ 32(2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወጪ ንግድ ምርት ናሙናዎች አላላክ እና አቀባበል መመሪያ ያዘጋጀ መሆኑን እና መመሪያው በፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 16 መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል እንዲመዘገብ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ መመሪያው በስራ ላይ እንዲውል የመመሪያውን ቅጅ ልከዋል፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties