አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
November 18, 2021
November 20, 2021
Screenshot_20211119-145340.jpg
269.3 KB
November 20, 2021
November 21, 2021
November 21, 2021
November 22, 2021
November 22, 2021
November 23, 2021
November 23, 2021
November 23, 2021
November 23, 2021
November 24, 2021
November 24, 2021
ያለውን እርምጃ እስከመውሰድ የሚደርስ ነው፡፡
በተጨማሪም የጥብቅና አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ጥቅም መጠበቁን ማረጋገጥ እንዲሁም የደንበኞችን ጥቅም ለማስጠበቅ ጠቀሜታ ያላቸው የጠበቆች መብቶችም መከበራቸውን የመከታተል ሀላፊነት አለበት፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በጠበቃ ወይም በጠበቃ ድርጅት ዘንድ የሚቀመጥን የደንበኛ የአደራ ሂሳብ አያያዝ አመራርን እንዲሁም ከአደራ ሂሳቡ የሚገኝ ወለድን አጠቃቀምን በተመለከተ መመሪያ የማዘጋጀት፣ የሂሳቡ በአግባቡ ስለመያዙም መቆጣጠርና ኦዲት ማድረግ፣ ከአደራ ሂሳብ አያያዝን በተመለከተ ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን መቀበልና ምርመራ ማድረግ ግድፈት ተፈፅሞ ሲገኝም በዲሲፕሊን ጉባኤ እንዲታይ መምራት፣ የአደራ ሂሳብ በአግባቡ ይያዝ ዘንድ ስልጠናዎችን መስጠት ወይም የማሰጠት ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

ማህበሩ በህግ ትምህርት ጥራት ላይ የራሱን አበርክቶ የማድረግ እንዲሁም ለህግ የበላይነት መከበር፣ ሰብአዊ መብቶች መከበር እና ለሀገራችን የህግ ስርአት ማደግ አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት ሀላፊነት ተጥሎበታል፡፡

በአጠቃላይ የፌደራል የጠበቆች ማህበር ከህግ ትምህርት ጥራት ጀምሮ በጥብቅና አስተዳደር ዙሪያ ሰፋ ያለ ተሳትፎ ያለው ማህበር ሆኖ በአዋጁ የተቋቋመ ሲሆን ይህም ጠበቆች በማህበራቸው አማካኝነት ለሀገራችን የህግ ሥርአት እና ለጥብቅና ሙያ ማደግ የራሱን ሚና እንዲጫወት እንዲሁም ጠበቆች በተደራጀ መልኩ ሙያቸውን እንዲመሩና መብታቸውንም እንዲያስከብሩ የሚረዳ በመሆኑ ጠበቆች ይህንን ተረድተው በሙሉ ፈቃደንነት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ማህበረሰቡም ይህንን አውቆ ለሚያገኘው የጥብቅና አገልግሎት ጥራት ከማህበሩ ጋር በመተባበር እንዲሰራ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
https://t.me/lawsocieties
November 24, 2021
November 24, 2021
November 24, 2021
እንደሚታወቀው ኃላፊነታቸው የተወሰኑ ኩባንያዎች ዋነኛ ባህርይ ዕዳቸው በኩባንያው ሀብት ላይ የተወሰነና ወደ አባላቱ ሀብት የማይሸጋገር መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የቁጥጥር ሥርዓቱ ደካማ ከሆነ የኩባንያው ብቸኛ ባለሀብት መሆኑን በመጠቀም በዕዳ ከመጠየቅ ለመሸሽ ሲባል የኩባንያውን ሀብት ወደ ግል ሀብት የማሸሽ አጋጣሚን ሊያሰፋ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የኩባንያ መረጃዎች በአንድ ሰው ቁጥጥር ሥር ያሉ በመሆኑ በሦስተኛ ወገኖች ሊተላለፉና ሊታወቁ የሚገቡ መረጃዎች እንዳይታወቁ ሊደረግ የሚችልበት ዕድል ሊኖር ይችላል የሚል ሥጋት ያለ በመሆኑ ነው እንዲህ አይነት የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ያስፈለገው፡፡

4. የማህበሩ አመሰራረት
እንደሌሎች ማህበሮች ሁሉ ባለ አንድ አባል ኃለፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር የሚቋቋመው በመመስረቻ ጽሑፍ ሲሆን በንግድ መዝገብ ውስጥ እንደተመገዘበ የህግ ሰውነት የሚያገኝ ሲሆን ፣ ማህበሩን ለመመስረት ዝቅተኛ ዋና ገንዘቡ ከብር 15,000 (አሥራ አምስት ሺ) ማነስ የለበትም ፡፡ ከላይ እንደተመለከተው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሚመሰረተው አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት ሲሆን አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግና መግልጫውም በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት ያለበት ሲሆን መግለጫው የሚከተሉትን ነገሮች ማሳየት አለበት ማኅበሩ አንድ አባል ብቻ ያለው መሆኑን፤ የአባሉን ስም፤ዜግነትና አድራሻ፤ አባሉ የሞተ፣ የጠፋ ወይም በፍርድ የተከለከለ እንደሆነ ስለ ወራሾቹ ወይም ስለ አባሉ ሆኖ ሕጋዊ ተግባራትን እንዲፈጽም የታጨው የንብረት ጠባቂ ሰው ስም፤ ዕጩ ንብረት ጠባቂው ፍቃደኛ ሆኖ ኃላፊነቱን የተቀበለ መሆኑን፤ የማኅበሩን ስም፤ዋና መሥሪያ ቤት፤ ካሉትም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶቹን፤ የማኅበሩን የንግድ ዓላማ፤ የማኅበሩ ዋና ገንዘብ መጠንና፤ይኼው በሙሉ የተከፈለ መሆኑን የሚያሳይ መግለጫ፤ በዓይነት የተከፈለ መዋጮ ካለ ግምቱን፤ የሥራ አስኪያጁን ስምና ሥልጣን፤ ካለ ኦዲተሩን፤ ማኅበሩ የሚቆይበትን ጊዜ፤ ማኅበሩ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያስታውቅበተን መንገድና ጊዜ እና ሌሎች በሕግ ወይም በአባሉ እንዲካተቱ የተወሰኑ ጉዳዮችን ፡፡

ሌላው የምስረታው አካል የሆነው ጉዳይ እጩ ንብረት ጠባቂን በተመለከተ ነው፡፡ የማህበሩ አባል ወይም መስራች አንድ ሰው በመሆኑ ግለሰቡ በተለያዩ ምክንያቶች ስራውን መስራት ባይችል በህግ በግልፅ የተመለከተ አባሉን ተtክቶ የሚሰራ ሰው ከሌለ የንብረት ብክነትና መሰል ችግሮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ በሶስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር በአንድ ሰው የሚመሰረት በመሆኑ አመራሩን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ከላይ ተመልክተናል፡፡ ስለሆነም አባሉ በሌለ ጊዜ፣ ቢሞት፣ ቢጠፋ ወዘተ ለማህበሩ ሀላፊነት የሚወስድ ወይም የማህበሩን ንብረት የሚጠብቅ አካል ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በህጉ ዕጩ ንብረት ጠባቂ የሚባል አካል ወይም ሰው እንዲኖር አስገዳጅ ድንጋጌ የገባ ሲሆን ዕጩ ንብረት ጠባቂው ዕጩነቱን የተቀበለ መሆኑን ሰነዶችን ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካላረጋገጠ በስተቀር፤ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሊመሠረት አይችልም እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለተለያዩ ባለ አንድ አባል ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማኅበራት የንብረት ጠባቂ ሆኖ መመረጥ አይችልም ፡፡
የንግድ ስራዎች በግለሰብ ነጋዴነት ከሚሰሩ ይልቅ በማህበርነት መሰራታቸው ለነጋዴውም ለሶስተኛ ወገኖችም የተሻለ ጥበቃ ስለሚሰጥ ግለሰብ ነጋዴዎች ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር መለወጥ ስለሚችሉበት ሁኔታም በህጉ ተመልክቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ግለሰብ ነጋዴ የንግድ ሥራውን ወደ ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርነት መለወጥ ይችላል፤ ሆኖም ግን ግለሰብ ነጋዴው ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከመመሥረቱ በፊት ለገባበት ዕዳ ሁሉ ከማኅበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ኃላፊ ይሆናል ፡፡
5. የማህበሩ አመራር (Governance)
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲኖረው ሕጉ የሚያስገድድ ሲሆን አባሉ ራሱ ወይም ሌላ ሰው የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊሆን ይችላል ፤ ዋናው ሥራ አስኪያጁም አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ያለው ሥልጣን እና ተጠያቂነት ይኖረዋል ፡፡ እንዲሁም ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የሚኖረው ሲሆን፣ የማኅበሩ አባል የአንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያለውን ሥልጣን ይኖረዋል፤ አባሉ በጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣኑ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ቃለ-ጉባዔ ስብሰባው በተደረገ ከሦስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በጽሑፍ ተዘጋጅተው የማህበሩ ማህደር ውስጥ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፤ በማኅበሩ ምሥረታ ጊዜ በተሰጠ መግለጫ ውስጥ የተካተቱትን ነገሮች የሚለውጥ ማንኛውም ውሳኔ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በንግድ መዝገብ ውስጥ መግባት አለበት እንዲሁም የአባሉ ውሳኔዎች የዚህን አንቀጽ ድንጋጌዎች ያላሟሉ ቢሆኑ እንኳን በሕግ ፊት የጸኑ ናቸው፤ ሆኖም ጉድለቱ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አባሉና ማኅበሩ በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናሉ ፡፡

6. የማህበሩ መፍረስ
ማህበሩ እንደአግባብነታቸው በንግድ ሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተመለከቱት ለማህበራት መፍረሻ ምክንያቶች በሚያገጥሙበት ጊዜ ሊፈርስ የሚችል ሲሆን የፈረሰው ማህበር አባል ያለበትን ዕዳ በሙሉ የከፈለ ከሆነ የማኅበሩ ሀብት ሳይጣራና ባለበት ሁኔታ በጠቅላላው ለአባሉ ይተላለፋል ፤ ምክንያቱም ማህበራት ሲፈርሱ ኦዲት የሚደረጉት በሁለት ምክንያች ሲሆን አንደኛው የማህበራትን አባላት መበት ለመጠበቀ ነው፣ ሁለተኛው ደግሞ የሶስተኛ ወገኖችን መብት ለመጠበቅ ነው፡፡ በባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ግን አባሉ አንድ ስለሆነ የአባላጥ ጥቅም የሚባለ ነገር የማይነሳ ሲሆን፣ ሶስተኛ ወገኖችን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚለው ነጥብ ደግሞ እዳ እንደሌለበት መረጋገጥ እንዳለበት ህጉ ያስቀምጣል፣ ሆኖም በማናቸውም ምክንያት ማኅበሩ ከፈረሰ በኋላ ገንዘብ ጠያቂዎች የቀረቡ እንደሆነ አባሉ በግሉ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ አባሉን ተጠያቂ ለማድረግ የሚቀርብ ክስ ገንዘብ ጠያቂው የማኅበሩን መፍረስ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በአምስት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፤ የማኅበሩ ሀብት ለአባሉ ከተላለፈ ከአሥር ዓመት በኋላ ምንም ዓይነት ክስ ሊቀርብ አይችልም ፡፡ ማህበሩ በሚፈርስበት ጊዜ አባሉ አባሉ በራሱ ምርጫ መደበኛውን የሒሳብ ማጣራት ሂደት ለመከተል ይችላል ፡፡
🟢 @lawsocieties
🟡 @lawsocieties
🔴 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
November 24, 2021
November 25, 2021
November 25, 2021