አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
SER'ATA MANGEST.pdf
1.2 MB
SER'ATA MANGEST: An early Ethiopian Constitution
Author(s): Bairu Tafla and Heinrich Scholler
Law and Politics in Africa, Asia and Latin America, Vol. 9, No. 4 (1976), pp. 487-499
ከአስተዳደራዊ ውሳኔ ቅሬታ ማቅረቢያ የአስራ አምስት ቀን የጊዜ ገደቦች
በተለያዩ ህጎች ላይ አቤቱታ ለማቅረብ ወይም ሌላ ህጋዊ ተግባር ለመፈጸም የተለያዩ የጊዜ ገደቦች ተቀምጠዋል። ከእነዚህ ውስጥ በአምስራ አምስት ቀን የተወሰኑ የጊዜ ገደቦች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
የኅብረ ት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁ. 985-2009
1. አንቀጽ 12/3/
የማንኛውም ኅብረት ሥራ ማህበር የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሻሻል በጠቅላላ ጉባዔው ሲወሰን የተደረገው ማሻሻያ እና በዚህ አዋጅ መሠረት የተላለፈ የኅብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ በሦስት ቅጅ ተደርጎ ውሳኔ በተላላፈ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አግባብ ላለው ባለሥልጣን መቅረብ አለበት፡፡
2. አንቀጽ 33/2/
የኅብረት ሥራ ማህበር የሥራ አመራር ኮሚቴ በድምጽ ብልጫ ሲወስን ወይም ከጠቅላላ አባላቱ መካከል አንድ ሶስተኛው ስብሰባ እንዲጠራ ሲጠይቁ የ15 ቀን ቅድሚያ ማስታወቂያ በማውጣት አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1048-2009ዓ.ም
3. አንቀጽ 37/2/
በኦዲትና ኢንስፔክሽን መኮንን ወይም በሌላ የባቡር ትራንስፖርትን እንዲያስተዳድር በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የሥራ ኃላፊ በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ቅሬታ የሚቀርብበት ጊዜ
ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ውሳኔው በተሰጠ ወይም አቤቱታ አቅራቢው ውሳኔ መሰጠቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
4. አንቀጽ 37/3/
የባቡር ትራንስፖርትን እንዲያስተዳድር በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የበላይ ኃላፊ ቅሬታ ሲቀርብለት በቅሬታው ላይ ውሳኔ ለመስጠት በህግ የተቀመጠለት ጊዜ
የጂኦተርማል ሀብት ልማት አዋጅ ቁጥር 981-2008
5. አንቀጽ 10/2/
የጂኦተርማል ጉድጓድ መስክ የማልማትና የመጠቀም ፈቃድ እንዳይሠጥ ተቃውሞ የሚያቀርብ ሰው በአንቀጽ 10/1/ መሰረት ጥያቄ የቀረበበት ቦታ በመገናኛ ብዙሃን እንዲታወቅ በተደረገ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ያቀረበ እንደሆነ ፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን በጉዳዩ ላይ በሚመለከታቸው ወገኖች መካከል ድርድር እንዲጀመር ያደርጋል።
የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923-2008
6. አንቀጽ 38/2/
ወደ ውጭ አገር ለሥራ የላከውን ሠራተኛ በሚሄድበት አገር ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በ፲፭ ቀናት ውስጥ አሳውቆ የማስመዝገብ፣ የሥራ ፈቃድና የመኖሪያ ፈቃድ ስለማግኘቱ የማረጋገጥና ይህንኑ መረጃ አሟልቶ ለሚኒስቴሩ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. አንቀጽ 50/2/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን በአንቀጽ 50 አንቀጽ 1 መሠረት የሰጠውን ትዕዛዝ /አስተዳደራዊ ጥፋት በፈጸመ ኤጀንሲ ላይ የሚወስደው እርምጃ/ አቤቱታ የቀረበበት ኤጀንሲ በ፲፭ ቀናት ውስጥ የመፈፀም ግዴታ አለበት፣፡
8. አንቀጽ 59/1/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን የዚህን አዋጅ ድንጋጌ ወይም በአዋጁ መሠረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ በሚፈፀመው ጥፋት ላይ በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በደረሰው በ፲፭ ቀናት ውስጥ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወይም በክልል ሥልጣን ለተሰጠው ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
9. አንቀጽ 69/1/ ለ የኤጀንሲ ግዴታ
ሠራተኛው ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስበት ወይም ሲሞት ጉዳት የደረሰበትን ሠራተኛ ወይም አስከሬን የሚቆይበት በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ከግል ንብረቶቹ ጋር የአየር ትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን ሠራተኛው ስለደረሰበት ጉዳት ወይም ሞት ከሚገልጽ ሕጋዊ የህክምና ማስረጃ ጋር በማያያዝ በ፲፭ ቀናት ውስጥ ወደ አገሩ የመመለስ እና ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ወጪዎችን የመሸፈን፤
10. አንቀጽ 67/1/
ሚኒስቴሩ ወይም አግባብነት ያለው ባለሥልጣን አቤቱታን በተቀበለ በሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ለቀረበበት አካል በማሳወቅ ሁለቱ ወገኖች ቀርበው ጉዳዩን በ፲፭ የሥራ ቀናት ውስጥ በስምምነት እንዲጨርሱ ጥረት ያደርጋል፡፡
የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 922-2008
11. አንቀጽ 33/1/
ሰነድ አረጋጋጭ በዚህ አዋጅ መሠረት መስጠት ያለበትን አገልግሎት ቢከለክል ወይም አዋጁን በመተላለፍ አገልግሎት ቢሰጥ ማንኛውም ቅሬታ ያለው ሰው ለሰነድ አረጋጋጩ የበላይ ኃላፊ በ፲፭ የሥራ ቀን ውስጥ አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859-2006
12. አንቀጽ 154/1/
ለጉምሩክ ኮሚሽን የአቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍል የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ይግባኝ ቅሬታውን ያስከተለው ውሳኔ በፅሑፍ በተሰጠ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በፅሑፍ መቅረብ አለበት፡፡
የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 840-2006
13. አንቀጽ 15/6/
ወንጀል ሰርቶ ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ሰው ይቅርታ እንዲደረግለት ሲጠየቅለት ይቅርታውን ለመቀበል የማይፈልግ መሆኑን የይቅርታ መጠየቅያ ደብዳቤ ቅጅ በደረሰው በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ለቦርዱ ካላስታወቀ በይቅርታ ጥያቄው እንደተስማመ ይቆጠራል፡፡
14. አንቀጽ 23/7/
በሀሰተኛ ወይም በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ይቅርታ እንዲሁም በሁኔታ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ይቅርታ ሁኔታው ሲጣስ ይቅርታው ዋጋ እንዲያጣ የይቅርታ ቦርድ በሰጠው የውሳኔ ሀሳብ መነሻነት የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ይቅርታው ዋጋ እንዲጣ ትዕዛዝ ከሰጡ ይቅርታ ተደርጎለት የነበረው ሰው ትዕዛዙ እንደገና እንዲታይ ትዕዛዙ በደረሰው በ15 ቀናት ውስጥ ለይቅርታ ቦርድ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818-2006
15. አንቀጽ 17/2/
በመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሰፈር ውስጥ በሚከናወኑ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ውሳኔዎች ላይ ቅሬታ ያደረበት ሰው የማረጋገጥ ሂደቱ መጠናቀቁ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ቅሬታ ሰሚ ጉባዔ ማቅረብ ይችላል፡፡
Ethiopian Legal Brief
41-27 tax frr vehicle for the disabled.pdf
2.4 MB
አካል ጉዳተኞች ለግል አገልግሎት የሚውል ተሽከርካሪ ከቀረጥና ታክስ ነጻ የሚያስገቡበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 41-2007
ከ አስር ሺህ አምስት መቶ #(10,500+) በላይ ተከታይ ያለው ፌስቡክ ፔጃችንን ይቀላቀሉን‼️‼️‼️‼️‼️

https://www.facebook.com/lawsocieties/

#join and #share to all #Ethiopian societies‼️‼️‼️‼️
Legal Officer Job at Berhan Insurance S.C – Career Opportunity in Ethiopia

Job title: Legal Officer Job at Berhan Insurance S.C – Career Opportunity in Ethiopia

Company: Berhan Insurance S.C

Job description: ] Jobs at: Berhan Insurance S.C Deadline of this Job: 14 June 2021 Duty Station: Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa…

Expected salary:

Location: Addis Ababa

Job date: Wed, 09 Jun 2021 22:29:38 GMT

https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#ምርጫ2013

በምርጫ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና የሚባሉ ክርክሮች ፦ የመራጮች እና የእጩዎች ምዝገባ ፣ የድምፅ አሰጣጥ ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ የተመለከቱ ናቸው።

እነዚህን ክርክሮች የሚዳኙ ፦

#ተቋማት

- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና በቦርዱ የተቋቋሙ ውሳኔ ሰጪ አካላት
- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

#ሕጎች

- የኢፌዴሪ ህገመንግስት
- የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፷፪/፳፻፲፩
- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፴፫/፳፻፲፩
- አግባባ ያላቸው ሌሎች ሕጎች

#የኢትዮጵያ_የፌዴራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
🔴 የጉዳት ካሳ በኢትዮጵያ ሕግ‼️

1. የጉዳት ምንነት
ጉዳት ማለት በሰዉ ጥቅም ወይም ሀብት ላይ የሚደርስ ጉድለት ወይም ኪሳራ ነዉ ( የአካል ጉዳትንም ጨምሮ)፡፡ በዉል ሕግ ላይ ማብራሪ የፃፉት ፕሮፌሰር ጆርጅ ቺቺኖብችም ጉዳት በሰዉ ጥቅም ላይ የሚደርስ ኪሳራ ነዉ የሚል ትርጉም ሰጥተዉታል፡፡ይህም የገንዘብ ወይም የኅሊና ጥቅምን የሚነካ ወይም የሚያጎድል ሊሆን ይችላል፡፡ የገንዘብ ጉዳት የተጎጂዉን ኪስ ያራቁታል፡፡ የኅሊና ጉዳት ደግሞ የተጎጂዉን ስሜት ይነካል፡፡በተጎጂዉ ላይ የደረሰዉ ጉዳት ሀብቱን ያሳጣዉ ወይም ገቢዉ እንዳይጨምርና ሀብቱ እንዳያድግ ያገደዉ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ጉዳት አሁንኑ የደረሰ ወይም ገና ወደፊት የሚደርስ ጉዳት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- ተጎጂዉ በሬዉ ሞቶበት ወይም ቤቱ ተቃጥሎበት ወይም የሚነግድበት አዉቶብስ ከጥቅም ዉጭ ሆኖበት ወይም ቋሚ የአካል ጉዳት ደርሶበት ሊሆን ይችላል፡፡ባለቤቱ እነዚህን ንብረቶቹን እያከራየ ገቢ ያገንባቸዉ ከነበረ የንብረቶቹ ወጋ ተከፍሎት የማከራቱን ስራ እስኪጀምር ድረስ በየቀኑ ወይም በየወሩ ኪሳራ ይደርስበታል፡፡ጉዳቱ የአካል ጉዳት ከሆነም ሥራ እየሰራ ያገኝ የነበረዉ ገቢ ሊቋረጥበት ይችላል፡፡ይህ ጉዳት የመስራት አቅሙ እስከሚደክም (እስኪያሟጠጥ) ድረስ ላለዉ ዘመን ሁሉ የሚቀጥል ነዉ፡፡ ወደፊት የሚደርስ ጉዳት የምንለዉ እንዲህ ዓይነቱን ጉዳት ሲሆን ጉዳቱ እንደሚደርስ እርግጠኛ ከሆን፣ጉዳቱ እስኪደርስ መጠበቅ ሳያስፈልግ አስቀድሞ ካሳዉ እንዲከፈል ማደረግ ይቻላል፡፡

1.1 የጉዳት መነሻዎችና ምንጮች
በዉል ግንኙነት የመብት ወይም የግዴታ ምንጭ የሰዎች ስምምነት ሲሆን ከዉል ዉጭ ለሚደርስ ኃላፊነት ደግሞ የግዴታዉ ምንጭ ሕግ ነዉ፡፡ በዉል የጉዳት መነሻ የሚሆነዉ የዉሉ አለመፈፀምና የዉል መፍረስ ሲሆን ዉል ባለመፈፀም ስለ ሚደርስ ጉዳት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1790፣ ስለ ዉል መፍረስ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1697 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ዉል ባለመፈፀሙ እና ዉል ሲፈርስ የደረሰዉ ጉዳት ኪሳራ መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ኪሳራዉና ልኩ በፍትሐብሔር ሕግ ከዉል ዉጪ ስለሚደረስ ኃላፊነት በሚለዉ ምዕራፍ በተፃፉት ድንጋጌዎች መሰረት ይወሰናል በማለት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1790 ንዑስ ቁጥር 2 ስር ተደንግጎል፡፡ ሌላዉ ከዉል ዉጭ የሚደርስ ጉዳት ኃላፊነት ምንጮች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2027 ስር እንደተዘረዘረዉ ሶስት ዓይነት የጉዳት ምንጮች (የጉዳት መነሻ ነገሮች) ያሉ ሲሆን እነሱም፡-
 በራስ ጥፋት በሌላሰዉ ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ማድረስ፣
 ጥፋት ሳይኖር የሚደረስ ጉዳት ኃላፊነት ሲኖር እና
 ሌላ ሰዉ ስለሚያደርሰዉ ጉዳት ኃላፊነትን መዉሰድ የሚመለከት ነዉ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ስር የሥራ ስንብት፣ያለ ማስጠንቀቂያ ሥራ መስለቅና መልቀቅ (ከሕግ ዉጪ የሆነ የስራዉል ማቋረጥ) እና በሥራ ላይ የሚደረስ የአካል ጉዳት መነሻዎችና ምንጮች ሲሆኑ የጉዳት ካሳ (ክፍያ) የሚከፈልባቸዉ ናቸዉ፡፡

1.2 የጉዳት ዓይነቶች
በፍትሐብሔር ሕግ ዉስጥ ጉዳት ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች እና የኅሊና ጉዳት በመባል በሁለት ተከፍሎ እናገኛለን፡፡
1.2.1 ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች
ጉዳት የደረሰበት ወገን በንብረቱ አላያም የገንዘብ ጥቅሙ በቀጥታ የሚነካ ሊሆን ይቻላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በሀብትና ንብረቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ ይኸዉ ሀብትና ንብረት በገንዘብ ተተምኖ ወይም ተመሳሳይ ንብረት በመመለስ ይካሳል፡፡ አን/.ደሰዉ በደረሰበት የአካል ጉዳት ምክንያት የደረሰዉን ጉዳት ወደነበረበት ለመመለስ አለያም ለማገገም የተለያዩ ለሕክምና የሚወጡ ወጭዎች ይኖራሉ ( የአልጋ፣የመድኃኒት፣ የአልሚ ምግብ እና የትራንሰፖረት) ፡፡ ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች በሁለት የሚከፈሉ ሲሆን እነርሱም የደረሱ ጉደቶችና ወደፊት የሚደርስ ጉዳት ይባላሉ፡፡

ሀ. የደረሱ ጉዳቶች
ይህ ማለት ጉዳት በመድረሱ በተጎጂዉ ላይ በእርግጠኝነት የደረሰዉን የገንዘብ ኪሳራ ለማመልከት ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ለሕክምና ያወጣዉ ወጪ እንዲሁም የንብረት ጉዳት የደረሰበት ሰዉ በጉዳቱ ምክንያት የንብረቱ ዋጋ መቀነስ ወይም መሉ ለሙሉ ዋጋ ማጣት ጉዳት ሊሆን ይቻላል፡፡

ለ. ወደፊት የሚደርስ ጉዳት
በጉዳት ምክንያት ተጎጂዉ ለወደፊቱ የሚያወጣዉ ወጪን የሚመለከት ነዉ፡፡ ለምሳሌ ፡- አንድ ሾፌር በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ሽባ ከሆነ እንደቀድሞዉ ሰርቶ ገቢ የማግኘት ዕድል የለዉም ሊባል ይቻላል፡፡ ስለሆነም ከጉዳቱ በፊት ያገኝ የነበረዉን ገቢ ለወደፊቱ ያጣ ስለሚሆን ወደፊት የሚደርስ ግልፅ ጉዳት ደርሶበታል ይባላል፡፡
በአጠቃላይ ግልፅ የሆኑ ጉዳቶች (የደረሰ እና ለወደፊት የሚደርስ ጉዳት) ካሳ ሊያስከፍሉ የሚችሉ በእርግጠኝነት የሚታዩ ሲሆን ብቻ ነዉ ( የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2102(2) እና 2092)፡፡ እነዚህ ጉዳቶች መኖራቸዉ የሚረጋገጠዉ በማስረጃ ሲሆን በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2041 መሰረት ተጎጂዉ ሕጋዊ ማስረጃን በማቅረብ የደረሰበትንና ለወደፊቱ የሚደርስበትን ጉዳት ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ተከሳሹ ጉዳቱን በግልጽ ባያስተባብልም እንዳመነ ተቆጥሮ ማስረጃ ያልቀረረበበት ጉዳት ካሳ ሊወሰንለት ስለ ማይችል ከሳሹ ጉዳቱን እና የጉዳት መጠኑን የሚያሳይ ማስረጃ አቅርቦ ማረጋገጥ አለበት (የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 83) ይመለከቷል፡፡

1.2.2 የኅሊና ጉዳት
ይህ ጉዳት የተጎጂዉን የገንዘብ አቅም ወይም ኪሱን የሚጎዳ ሳይሆን ሊጎዳ የሚችለዉ ስሜትን ነዉ፡፡ ተጎጅዉ የደረሰበትን ጥልቅ የስሜት መጎዳት ፣ሀዘንና ሀፍረት መሰረት በማድረግ እንደ ጉዳቱ ዓይነትና ባህሪ ደረጃ የኅሊና ጉዳት ካሳ ሊከፈል ይችላል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ባለዉ የኅሊና ጉዳት ካሳ በምንም ቢሆን ከብር 1000.00 (አንድ ሺኅ ብር እንደማይበልጥ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2116 (2) ይገልፃል፡፡ በሌላ በኩል ግን በቅጅና ተዘማጅ መብቶች አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀጽ 34(4) መሰረት የተለያዩ ጽሁፎች፣ሙዚቃዎች እና ፊልሞች በሌላ አካል ከተሰረቀባቸዉ የተሰረቀባቸዉ ዘፋኞች ወይም ደራስያን ከደረሰዉ ጉዳት ጋር በማመዛዘን የሞራል(የኅሊና) ጉዳት ካሰዉ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺኅ ብር) የማያንስ መሆኑን ሲደነግግ በዚህ ዘርፍ ሊደርስ የሚችለዉን የኅሊና ጉዳት ካሳ ከሌሎች የኅሊና ጉዳቶች ካሳ በልዩ ሁኔታ የተቀመጠ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

1.2.3 የአካል ጉዳት
በተጎጂዉ ላይ የሚደርሰዉ የአካል ጉዳት በገንዘብና በኅሊና ከሚደርሱ ጉዳቶች ሁሉ የከፋና የጉዳት ከሳዉንም ለማስላት አስቸጋረዉ ሲሆን የኅሊና ጉዳትንም ከገንዘብ በበለጠ መልኩ የሚያደርስ ነዉ፡፡

 ጊዚያዊ የአካል ጉዳት
ይህ የአካል ጉዳት ጊዚያዊ የሆነ ሕመምና ስቃይ ቢያስከትልም እንኳ ቁስሉ የሚድንና ስብራቱም ከትንሽ ጊዜ በኋላ የሚጠገን በመሆኑ ሥራን እንደወትሮዉ ሁሉ ለማከናወን የሚስችል ነዉ፡፡ በጥገና ወደነበሩበት የሚመለሱ የእጅና የእግር ስብራት፣ በራስ አካባቢ ያለ ፍንክት የመሳሰሉት ጊዜያዊ የአካል ጉዳቶች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ነበሩበት የሚመለሱ ናቸዉ፡፡ በአጠቀላይ ጊዜያዊ የአካል ጉዳት ማለት ሠራተኛዉ ሥራዉን በተወሰነ ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል ለማከናወን እንዳይችል የሚያደርገዉ የአካል ጉዳት ነዉ፡፡
 ዘላቂ ከፊል የአካል ጉዳት
ይህ የአካል ጉዳት ሥራን አንደ ድሮዉ አቀላጥፎ ለመስራትና እንደልብ ለመደሰት የሚያስችል ነዉ፡፡ በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያሉ ሥራዎችን ከመስራት አይከለክልም፡፡ እንደ የመስማት ችግር፣ የአንድ እጅ ወይም እግር መቆረጥ እና የአንድ ዓይን መጥፋት ከዚህ ክፍል የሚመደቡ ናቸዉ፡፡ እነዚህ ጉዳቶች ዘላቂ ሲሆኑ ነገርግን ሙሉ በሙሉ ሥራን ለመስራት ከልካዮች አይደሉም፡፡

 ዘላቂ ሙሉ የአካል ጉዳት
ዘላቂ የአካል ጉዳት ማለት ጉዳቱ የደረሰበትን ሠራተኛ የመስራት ቻሎታ የሚቀንስ፣የማይድን ጉዳት ማለት ነዉ፡፡ ይህ ከሁለም የጉዳት ዓይነቶች ከባዱ ነዉ፡፡ በመሆኑም ማንኛዉንም ዓይነት ሥራ ለመሥራት አያስችልም፡፡ ይህ ዓይነት ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ዕድሜ ልኩን የግል ህይወቱን ለመምራት ስለማይችል የሌሎች ሰዎች እርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ በአጠቃላይ አነጋገር አንድ ሰዉ ሙሉ የአካል ጉዳት ደረሰበት ሲባል ግለሰቡ በጊዜያዊነትም ሆነ በዘላቂነት ለዕለት ኑሮዉ ማድረግ የሚገባዉን እንደወትሮዉ ለማከናወን ተደስቶና በተፈጥሮ በመጠኑም ቢሆን እረክቶ ለመኖር ይቸገራል፡፡
2 የጉዳት ካሳ
ስለ ጉዳት ኪሳራ በ1952 ዓ.ም በወጣዉ የኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 13 ምዕራፍ 1 ክፍል 3 ንዑስ ክፍል 1 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ከዉል ወይም ከዉል ዉጭ ለሚደርስ የጉዳት ኃላፊነት ሕግ ዓላማዉ ከዉል ወይም ከዉል ግንጉነት ዉጭ በሆነ ሁኔታ በአንድ ሕግ በተጠበቀ መብት ላይ ጉዳት ሲደርስ ጉዳት አድራሹ ወይም ለጉዳቱ ሕጉ ኃላፊ የሚያደርገዉ ሰዉ ጉዳቱን እንዲያስተካክለዉ ማድረግ ነዉ፡፡ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2090(1) እና 2090 ስር ከተቀመጠዉ ድንጋጌ ካሳ ለአንድ ጉዳት ለደረሰበት ሰዉ የጉዳት መጠኑ ተተምኖ ለዚያ ጉዳት መጠን የሚሰጠዉ ጥቅም ወይም ገንዘብ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ለተጎጂዉ የሚሰጠዉ ጥቅም ለጉዳቱ ፈንታ ሆኖ ጉደቱን ለማስተካከል ሲባል ነዉ፡፡

ከዚህ በኋላ እንደምንመለከተዉ የካሳ ዓይነቶች የተለያዩ ቢሆኑም ዋናኘዉ የካሳ አይነት ከጉዳቱ ጋር ተመዛዛኝ የሆነ በገንዘብ የመካስ ዘዴ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል በተጎጂዉ ላይ የደረሰዉን ጉዳት በትክክል ለመገመት የማይቻል በሆነ ጊዜ በርትዕ የካሳዉን ልክ መወሰን ስለሚቻል ተጎጂ በደረሰበት ጉዳት የገንዘብ ካሳ እንዲያገኝ ከመወሰን ሌላም በሌሎች አማራጮች ጉዳቱ መካስ እንደሚቻል በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2118-2123 ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ ለምሳሌ የተወሰደዉን ዕቃ ለተጎጂ በመመለስ ወይም በዓይነት መመለስ ወዘተ…፡፡

2.1 የካሳ ዓይነቶች
በአብዛኛዉ የጉዳት ካሳ የገንዘብ ጉዳት ከሳ እና የአካል ጉዳት ካሳ በመባል ይታወቃሉ፡፡ የአካል ጉዳት የሚደርሰዉ የገንዘብ ኪሳራን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

2.1.1 ጉዳቱን ለማስተካከል የሚወጣዉ ወጪ
ተጎጂ የተጎዳዉን አካል አሳክሞ ለማዳን የሚከፈለዉን እንደቁስሉ አዳጋ በኋላም ቢሆን የደረሰዉ የአካል ጉዳት ላስከተለባቸዉ ችግሮች ማቅለያ የሚከፈለዉን ገንዘብ ሲሆን እንደሕክምና፣ ትራንስፖረት፣ለአልሚ ምግቦች እና ለመሳሰሉት አስፈላጊ ነገሮች የሚደረገዉን ክፍያ ያጠቃልላል፡፡ ይህ ገንዘብ ከተጎጅዉ ሀብት ላይ እየተቀነሰ የሚከፈል ነዉ፡፡ ይህ ከኪስ የሚከፈል ወጪ አብዛኘዉን ጊዜ በደረሰኞች ሊደገፍ ስለሚችል አስልቶ ለተጎጂዉ ማስከፈል እምብዛም አያስቸግርም፡፡

2.1.2 የገቢ ማጣት ኪሳራ
ይህ ኪሳራ በትክክል አስልቶ ለተጎጂዉ ካሳ ማስከፈል በጣም አስቸጋሪነዉ፡፡ በዋናነት የአካል መጉደል የሚያስከትለዉ ገቢ ማጣት ወይም መቋረጥ ነዉ፡፡ የአካል ጥቅሙ ሥራን ሰርቶ ገቢማስገኘት ብቻ ነዉ ባይባልም ገቢማስገኘቱ የታወቀ ስለሆነ በጉዳት ወቅት ያለዉ ገቢ ይቋረጣል፡፡

የአካል ጉዳት ካሳ ደግሞ ተቀጥሮ ወይም በደመወዝ ይተዳደር ለነበረ አካልጉዳተኛ የመከፈል ካሳ ፣በግል ሥራ ይተዳደር ለነበረ የሚከፈል ካሳ፣ ሥራ ለሌለዉ አካል ጉዳተኛ የሚከፈል ካሳ፣ ሥራ ለመስራት ለማይችል አካል ጉዳተኛ የሚከፈል ካሳ እና በአደጋ ሰዉ ሲሞት የሚከፈል የመተዳደሪያ ቀለብ ይባላሉ፡፡

3 ካሳ ለማግኘት መሟላት የሚገባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች
ከዚህ ላይ ካሳ ጠያቂዎች ሊገነዘቧቸዉና ሊያሟላቸዉ የሚገቡት ጉዳዮች ጉዳቱ የደረሰዉ በሕጋዊ ጥቅም ላይ መሆን ያለበት መሆኑን፣ተጎጂዉ ያገኝ የነበረዉና የተቋረጠበት ጥቅም ሕገ ወጥ ወይም ለኅሊና ተቃራኒ ከሆነ፤ ለምሰሌ ገቢዉ በቁማር ወይም በሴተኛ አዳሪነት ወይም በኮንትሮ ባንድ ንግድ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ካሳ ለጠይቅ የማይችል መሆኑን፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2029 ስር እንደተመለከተዉ ጥፋት ታስቦ ወይም በቸልተኝነት እንዲሁም ተግባርን በመፈፀም ወይም ለመፈፀም ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህም ጉዳት ይደርሳል በጥፋቱ ጉዳቱን ያደረሰዉ ሰዉ ተጎጂዉን የመካስ በሕግ ኃላፊነት አለበት፡፡ ካሳ ለማግኘት ጉዳት መድረሱን ማስረዳት የሚያስፈልግ መሆኑን ፡፡ አንድ ጉዳት በገንዘብ ሊተመን በሚችል ጥቅም ላይ ሲደርስ የደረሰዉን ጉዳት ለማመጣጠን ወይም ኪሳራዉን ሙሉ ለማድረግ ቀላል ሲሆን በሌላ በኩል የደረሰዉን በገንዘብ መተመን በማይቻል መብት ወይም ጥቅም ሲሆን ግን ካሳዉን ለማመጣጠን እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ምክንያቱም የደረሰዉ ጉዳት በገንዘብ በመካስ ሊመለስ የማይችል በመሆኑ ነዉ፡፡የጉዳት ካሳዉ ከደረሰዉ ኪሳራ እኩል መሆን አለበት ተብሎ ቢደነግግም የአካል ጉዳት በደረሰበትና ህይወት ባለፈበት ጉዳይ የኪሳራዉን መጠን እርግጠኛ በመሆን ይህን ያህል ነዉ ብሎ መገመት አስቸጋሪና የማይቻል ነዉ፡፡

4 የጉዳት ካሳ ጠያቂዎች
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2141 ስር እንደተመለከተዉ የደረሰበትን ጉዳት ልክና የጉዳት አድራሹን ኃላፊነት በማስረዳት ክስ ማቅረብ የሚችለዉ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ነዉ፡፡ በሕጉ መሰረት ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ሲባል ተጎጂ የተባለዉ በቀጥታ ጉዳት ያረፈበት ሰዉ ወይም ይህ ሰዉ በመጎዳቱ ምክንያት በተዘዋዋሪ ጉዳቱ የሚያገኛቸዉ ሌሎች ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ (የፍትሐብሔር ሕግ ቁትር 2095 እና 2144 ይመለከቷል)፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2142 መሰረት የካሳ ጥቄ ከሳሽ የደረሰበትን ወይም የሚደርስበትን ጉዳት ልክ ብቻ ሳይሆን የጉዳት አድራሹንም ኃላፊነት የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡

5 የጉዳት ካሳ የመክፈል ኃላፊነት
የጉዳት ካሳ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርባቸዉ የጉዳት ካሳ ሕጉ ኃላፊ የሚያደርጋቸዉ ሰዎች የደረሰዉን ጉዳት በካሳ መልክ ለማስተካከል የጣለባቸዉ ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ተሸከርካሪ በሌላ ሰዉ ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ቢያደርስ አሽክርካሪዉ ወይም (እና) የተሽከርካሪዉ ባለቤት የጉዳት ካሳ ኃላፊነት የኖርባቸዋል፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2081(1) መሰረት መኪና ወይም ባለሞተር ተሸከርካሪዉ ለሚያደርሰዉ ጉዳት ባለመኪናዉ ኃላፊ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡ የተሸከርካሪዉ ባለቤት ከደረሰዉ የጉዳት ኃላፊነት ማምለጥ የሚችለዉ ከሚከተሉት ሶስት አማራጮች አንዱ ሲሆንለት ብቻ ነዉ፡፡
• በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2081(2) መሰረት መኪናዉ ጉዳቱን ባደረሰበት ጊዜ የተሰረቀ መሆኑን በማስረዳት፣
• በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2982 መሰረት በደረሰበት ወቅት ለሌላሰዉ ጥቅም በሌላ ሰዉ እጅ የነበረ መሆኑን በማስረዳት፣
• በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2088(2) መሰረት ጉዳቱ የደረሰዉ በተጎጂዉ ወይም በተከሳሹ ሙሉ ጥፋት መሆኑን ባስረዳት ነዉ፡፡
በአጠቀላይ ስለ ጉዳት ካሳ ልንረዳዉ የሚገባዉ ጉዳይ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ የግድ መካስ እንደለበት ሲሆን ጉዳት በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 2090 እና 91 ስር እንደተተደነገገዉ በመሰረቱ ተመጣጣኝ በሆነ የገንዘብ መጠን ነዉ የሚካሰዉ፡፡ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ተካሰ ሚባለዉ ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ወደ ነበረበት ቦታ ሲመለስ ነዉ፡፡ ተጎጂዉን ወደ ነበረበት ቦታ ለመመለስ ለጉዳቱ ኃላፊ የሆነዉ ሰዉ ከጉዳቱ እኩል የሆነ ካሳ እንዲከፍል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምርሁም ጉዳት እኩል ሆናል ካሳ ስለሚል፡፡ የደረሰዉ ጉዳት ካላይ እንዳየነዉ ገንዘብ በመክፈል ሊሆን ይችላል ወይም ምትክ ንብረት በመስጠት ወይም በሌላ አኳኋን ሊፈፀም ይችላል፡፡
ኤፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties