አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በሀገራችን የሚገኙ ከ 17 ሚሊዮን በላይ ብዛት ያላቸው አካል ጉዳተኞችን የሚገጥሟቸዉ የማህበረሰቡ የአመለካከት እና የአካባቢ ተግዳሮች ልዩ ችሎታቸዉን እንዳይጠቀሙ ማነቆ መሆኑን በመረዳት ሁሉም ልዩ ድጋፍና ትኩረት ሊሰጣቸዉ ይገባል።
በዚህ ረገድ በርካታ ተቋማትና ግለሰቦች የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ሲጥሱ አስተማሪ ቅጣት የሚሰጡ የህግ ማውቀፎች የላሉ መሆናቸዉና የወጡ ህጎችም በተገቢዉ ባለመተርጎማቸዉ በአካል ጉዳተኖች ላይ ብዙ በደሎች እየተፈጸሙ ይገኛል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን በወጣት አብርሃም ዱሬሳ ላይ የተፈጸመዉ ድርጊት ሰብአዊነት የጎደለዉ መሆኑን በመግለጽ መንግስት አስፈላጊዉን ክትትል እንዲያደርግ እና ድርጊቱን ህዝቡ እንዲያወግዘው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን አጥብቆ ጠይቋል።
በወጣቱ ህልፈተ ህይወቱ የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።
****************************************************************************************
ታሪኩ በአጭሩ!
የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት ቤት ያገኘ ሲሆን ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር።
የመውጫ ፈተናውን ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሀሙስ በሰላም ተፈትኖ የመጨረሻው የፈተና ዕለት ማለትም አርብ የመፈተኛ ኮዱን ረስቶ ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ ይሄዳል። ካለ መፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ የመፈተኛ ኮዱን ይዞ ሲመጣ የመፈተኛ ሰዓት አልፏል ይባላል።
ፈተናው ከጠዋቱ 3፡30 የሚጀመር ሲሆን አብርሃም ግን አስር ደቂቃ ዘግይቶ 3፡40 ይደርሳል። ሱፐርቫይዘሩ መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ይሞክራል። ተማሪ አብርሃም_ዱሬሳም በተለያየ መንገድ ይማፀናል። አይነ_ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም ፈተናውን እንዲወስድ ግን አልፈቀዱለትም ።
ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ ፥ ሲበሳጭ ይውላል። ምሽት ላይ ወደ ቤቱ በመግባትም ቤቱን ዘግቶ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ ከፍተኛ ቃጠሎ እንደደረሰበትና በኋላም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና ቢያገኝም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱ ማለፉ ታውቋል!!
ለአካል ጉዳተኞች ጥንቃቄን እናድርግ!
ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሴት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው
-----------------------------------

ስልጠናው ሴቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለማዳበር የጎላ ሚና እንዳለው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዳልካቸው ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የመሪነት ክህሎት ላይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰጥ ሲሆን ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከፍተኛ አመራሮች የተጠርጣሪዎችን የሰብአዊ መብት አያያዝን ሲጎበኙ።📕📕📕
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከፍተኛ አመራሮች የተጠርጣሪዎችን የሰብአዊ መብት አያያዝን ጎበኙ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፍትሐ ብሄርና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ገለታ ስዩምን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በልደታ ክፍለ ከተማና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመገኘት የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ ምን እንደሚመስል ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ገለታ ስዩም እንዳሉት የኮሮና ቫይረስን በሚመለከት በፖሊስ ጣቢያዎች እየተሰሩ ያሉ ተግባራትንና ተጠርጣሪን ከመያዝ ጀምሮ መጠበቅ ያለባቸዉ የሰብአዊ አያያዝ ሂደት ምን እንደሚመስል መመልከት በዋናነት ጉብኝቱ ትኩረቱን ያደረገባቸዉ ጉዳዮች መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

የክፍለ ከተሞቹ የፖሊስ መምሪያ ሀላፊዎች በምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሀጉ የተነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ስላለዉ ሁኔታ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በተቻለ መጠን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የዉሀ ችግርና ተጠርጣሪን ለማቆየት በተለይም የፍርድ ቤት ታሳሪዎች የሚቆዩበት ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ መጨናነቅ እየተፈጠረ መሆኑ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተነሱ ችግሮች ሲሆኑ ተጠርጣሪዎቹ የኮቪድ ምርመራ እየተደረገ አለመሆኑ ደግሞ በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያ በኩል የተነሱ ችግሮች ናቸዉ፡፡

በሌላ በኩል በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በኩል ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ተጠርጣሪዎች በየ ሳምንቱ ምርመራ እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ አንስተዉ ሆኖም ግን ቅድመ መከላከልን አስመልክቶ በፊት ሲቀርቡ የነበሩ ቁሳቁሶች ባለመቅረባቸዉ ምክንያት መዘናጋት እንደተፈጠረ አንስተዋል፡፡

በፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በበኩላቸዉ በተለይም ወደ ጣቢያዉ ሲያመጡን በአንዳንድ አባላት ተደብድበናል፣ የምግብ አቅርቦትና የንፅህና ችግሮች አሉብን ሲሉ ያነሱ ሲሆን የተነሱ ችግሮችን አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ለተነሱ ችግሮች መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዉ `በተለይም የሰብአዊ መብትን ከአያያዝን በሚመለከት በተጠርጣሪዎች የተነሱ ቅሬታዎች በትኩረት በማየት አጣርቶ በዚህ ተግባር የተሳተፉ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከኮቪድ ምርመራ ጋር በተያያዘም ከጤና ጥበቃ ጋር በመነጋገር ምርመራ መካሄድ እንደሚገባዉና ተጠርጣሪዎች ወደ ጣቢያዉ እንደመጡ መመርመር ቢችሉ እንዲሁም አዲስ የገቡትን ምርመራ እስኪደረግላቸዉ ድረስ በክፍል መለየት ቢቻል የሚሉ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በዋናነት ያጠፋ አካል ላጠፋበት ወንጀል መጠየቁ እንዳለ ሆኖ የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ግን ትኩረት መሰጠት እንደሚገባዉ ተገልጧል፡፡

ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ አብረዉ መስራት የጀመረቱም በዋናነት እነዚህንና መሰል የሰብአዊ መብት አያያዝ ችግሮችን ለማስቀረት መሆኑም በጉብኝቱ ተጠቁሟል፡፡
If you are on this table, please dont take this behaviour into 2021.

My mum had a friend, she lost her husband shortly after they got married. She has little children and her in-laws did not treat her nicely.

She started a small business, selling food stuffs. One day I went to buy things from her and as usual if I notice she is moody I would cheer her up like my mum did.

She told me a lady came to her shop and mocked her with widowhood. They had an argument that had nothing to do with widowhood so I wondered why the lady brought it up.

Two years later, the mocker became a widow and her in laws threw her our of their mansion on the grounds that they were not legally/traditionally married.

The woman lost weight in a week and left the area.

In all your dealings with people, do not mock their predicament. Everything you have is a gift and it can be taken away from you anytime.

Be nice.
https://t.me/lawsocieties
Via YALI network face to face
Forwarded from Yoseph Mesele
Selam bro esit sile special mitigating and special aggravating circumstances yemyawera note kalehe asichukay nw ke yikrta gar
Forwarded from Deleted Account
ሰላም ሰላም.. የወንጀልም የፍታብሔርም የስነስርዓት ህግ ማብራሪያ ካለህ እስቲ ላክልኝ...
ረቂቅ የንግድ ሕግ ላይ ግብዓት የማሰባሰብ ውይይት ከባለድርሻ አካለት ጋር ተካሄደ
***

ታህሳስ 23/ 2013 ዓ.ም ለኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተመራው ረቂቅ የንግድ ሕግ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች እና የተለያዩ የባለድርሻ አካለት በተገኙበት ግብዓት የማሰባሰብ ውይይት ተካሄዷል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዬን ጢሞቲወስ በውይይት መድረኩ ባደረጉት ንግግር ረቂቅ የንግድ ሕጉን ለማዘጋጀት የአገራችን የሕግ ባለሙያዎች እና ሙህራን ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን አፍስሰው ከብዙ ጥረት በኃላ የተዘጋጀ መድብል መሆኑን ጠቁመው በስራው ሂደት ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ባለሙያዎችና ተቋማትን ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አክለውም ረቂቅ የንግድ ሕጉ ዘመናዊ የሆነ የንግድ ስራ እንቅስቃሴን ቀልጣፋ እንዲሆን ለማድረግ እና አነስተኛ እንዲሁም ከፍተኛ ሀብት የሚያንቀሳቅሱ የሀገር ውስጥ ብሎም የውጭ ባለሀብቶች ምቹ የሆነ የንግድ ስራ እንቅስቃሴ የሚደረግበትን መደላድል በማመቻቸት ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ማሰደግም የመንግስት አላማ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር ጌዱዬን አያይዘውም አንድን ሀገር ከድህነት ማውጣት እና ሀብት መፍጠር የሚቻለው በምኞት፡ በንግግር ሳይሆን በስራ፣ ምርትና አገልግሎትን በመሸጥ፣ በንግድ ስራ በመሳተፍ ሲሆን ዜጎች በንግድ ስራ እንዲሳተፉ መንግስት የተለያዩ የሕግ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

በረቂቅ ሕጉ የግል ድርጅቶች አመሰራረትና አደረጃጀት አስመልክቶ ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋ እና ቀላል ያሉ ሕግ ድንጋጌዎችን እንዲኖሩ፣ አነስተኛ አክስዮን ድርሻ ያላቸውን ባለአክሲዮኖች በሚሳተፉበት ድርጅትና ማህበር መብታቸው እና ጥቅማቸው የሚከበርበት ሥርዓት እና ከኪሳራ እንዲሁም ከኪስራ ሂደት ጋር በተያያዘ ሥርዓቱን ቀልጣፉ፣ ወጪ ቆጣቢ በማድረግ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎትን ለማስጠበቅ የሚረዱ ድንጋጌዎች የተካተቱ መሆኑን እና ረቂቅ ሕጉ ከ50- 60 ዓመታት እንዲያገለግል ጥራት ያለው ተጨባጭ የሆነ ውጤትና ለውጥ የሚያመጣ እንዲሆን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ረቂቅ የንግድ ሕጉን በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና ያላቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ በላይሁን ይርጋ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን የሆኑት ዶ/ር ስዩም ዩሐንስ እና ዶ/ር ታደሰ ሌጮ ከ1952 ዓ.ት ጀምሮ ያገለገለውን የንግድ ሕግ ድንጋጌ ክፍተቶች፣ የአዲሱን ሕግ መሰረታዊ እሳቤዎች እና ከኪስራ ንግድ ጋር በተያያዘ በሕጉ ውስጥ የተጠቀሱ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ አጠቃላይ ገለፃ አድርገዋል።

በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በረቂቅ የንግድ ሕጉንለማዳበር በጥንካሬ እንዲሁም ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያለቸውን ሀሳቦች እና ጥያቄዎችን በማንሳት ዉይይት በማድረግ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
Forwarded from Kira Abigaro
ዓይነ ስውሩ የሕግ ተመራቂ ስለምን ራሱን በእሳት አቃጠለ?
***


የዛሬ ሳምንት አርብ ታኅሳስ 16/2013 ዓ.ም አንድ ዓይነ ሥውር የሕግ ተማሪ ራሱን በእሳት አቃጥሎ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

አብርሃም ዱሬሳ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዳገኘ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና በመውሰድ ላይ እንደነበር ጓደኛው ጣሰው ሃብታሙ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ፈተናው ባለፈው ዓመት በ2012 ዓ.ም ይሰጥ የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት በመራዘሙ ለረጅም ጊዜ ለፈተናው ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ያስታውሳል።

ከአብርሃም ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ ተከራይተው መኖር ከጀመሩ አምስት ዓመት እንደሆናቸው የሚያስታውሰው ጣሰው፣ ሲዘጋጅበት የነበረውን የመውጫ ፈተና ማክሰኞ ዕለት መውሰድ መጀመሩን ይናገራል።

የመውጫ ፈተናውን ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ በሰላም ተፈትኖ እንደነበር የሚናገረው ጣሰው ደስተኛም እንደነበር ለቢቢሲ ያስረዳል።

የመጨረሻው የፈተና ዕለት፣ ማለትም አርብ፣ ረፍዶበት ስለነበር የመፈተኛ ኮዱን [የመለያ ቁጥሩን] ረስቶ በችኮላ ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ መሄዱን ያስታውሳል።
ፈተናው የሚሰጠው ስድስት ኪሎ ኤፍ ቢ ተብሎ በሚታወቀው ካምፓስ ስለነበር ወደ ውስጥ ዘልቆ መፈተኛ ኮዱን መርሳቱን እና ይፈትኑት እንደሆነ ቢጠይቅም፣ "ያለእርሱ አይሆንም፣ ሄደህ አምጣ" በመባሉ ወደ ቤቱ መመለሱን ጓደኛው ጣሰው ያስረዳል።

ካለመፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ፣ ከትራንስፖርት ከወረደ በኋላ ወደ ቤቱ የሚያቀናውን የእግር መንገድን አቋርጦ፣ የመፈተኛ ኮዱን በመያዝ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ሲደርስ ፈተናው መሰጠት ከጀመረ የተወሰኑ ደቂቃዎች ማለፉን ጣሰው ለቢቢሲ ተናግሯል።

"ፈተናው አላለቀም ተማሪዎች አልወጡም ቢያንስ ከ20 ደቂቃ በላይ ይቀር ነበር" ብሎኛል ሲል የሟች አብርሃም የቅርብ ወዳጅ ጣሰው ለቢቢሲ የነበረውን ሁኔቴ አስረድቷል።

የፈተና ተቆጣጣሪዎችን ለማሳመን እና ልባቸውን ለማራራት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም የሚለው ጣሰው፤ ነገር ግን ምንም ፍሬ እንዳላፈራለት ይናገራል።

"መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ቢሞክርም፤ "በቀረችው 20 ደቂቃ አብቃቅቼ እሰራለሁ" እያለ ዓይነ ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም፣ ቢያለቅስም፣ ፈተናውን እንዲወስድ ግን አልተፈቀደለትም።"

የሟች አብርሃም ጓደኛ ጣሰው፣ ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ፣ ሲበሳጭ መዋሉን ያስታውሳል።

ጓደኞቹ ሊያጽናኑት ቢሞክርም "በቃ የእድሌ መጨረሻ ነው፣ ዓይነ ስውር ካልተማረ ውጤታማ አይሆንም" እያለ ያለቅስ እነደነበር ይናገራል።

ምሽት ላይ ወደ ቤቱ ሲገባ ወዳጆቹ የመሰላቸው እረፍት ሊያደርግ ቢሆንም፣ እርሱ ግን ቤቱን ዘግቶ፣ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ፣ በዙሪያዎቹ ተቀጣጣይ ነገር በማኖር ራሱ ላይ እሳት መለኮሱን ጣሰው ገልጿል።

ግቢ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተረባርበው የቤቱን በር በመገንጠል እሳቱን አጥፍተው፣ ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ሕክምና ቢያገኝም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ቅዳሜ ማለዳ 3፡00 ላይ ህይወቱ አልፋለች።

የአብርሃም ቤተሰብ

አብርሃም ዱሬሳ ባለትዳር ሲሆን ባለቤቱ ነፍሰጡር በመሆኗ መስከረም ወር ላይ ለመውለድ ትግራይ ወደ ሚገኙት ቤተሰቦቿ መሄዷን ጓደኛው ጣሰው ለቢቢሲ ተናግሯል።

አብርሃም ብቻውን ለመኖር የተገደደው በተፈጠረው ችግር ምክንያት በረራ ተቋርጦ ስለነበር ባለቤቱ ልጃቸውን ክርስትና አስነስታ መምጣት ስላልቻለች በመዘግየቷ ነበር።

"ለብቻው የሆነው ለዚህ ነው እንጂ ከሚስቱ ጋር ነበር የሚኖረው" የሚለው ጣሰው በጓደኛው ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል።

በየካቲት 12 ሆስፒታል አብረውት የነበሩት አቶ አሸብር ገብረ ሕይወትም ቅዳሜ ዕለት ሆስፒታል ሲደርሱ አብርሃም ነፍሱ እንደነበረችና ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሎ ማየታቸውን ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ወሰን አለሙ፣ በማኅበሩ ሦስት ዓመታትን አንዳገለገሉ ገልፀው፤ ከዚህ ቀደም በድሬደዋ ከተማ ከኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ ጋር በተያያዘ አንድ ዓይነ ስውር በተመሳሳይ ሁኔታ ራሱን አቃጥሎ መሞቱን ያስታውሳሉ።

አቶ ወሰን፣ "በአብርሃም ዱሬሳ አርፍዶ በመምጣቱ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አትችልም መባሉ ሕግን ካለማወቅ የመጣ ነው" ይላሉ።

"የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን ተመጣጣኝ ሁኔታን ማመቻቸት ይላል" በማለትም ይህ ማለት የሰዓት፣ የቦታ ማስተካከያ ማድረግ ሊሆን እንደሚችል ያብራራሉ።

አብርሃም ቀደም ባሉት ሦስት የፈተና ቀናት በሰዓቱ ተገኝቶ መፈተኑን ከግንዛቤ በማስገባት፣ ያለ ኮድ ማስተናገድንም ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳሉ።

"ይህ በግልጽ ስህተት ነው" የሚሉት ፕሬዝዳንቱ "ፈተናውን የሚያከናውነው አካል እንዲህ አይነት ሥርዓቶችን መዘርጋት ነበረበት" ብለዋል።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ በተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ላይ የተፈጸመዉ ክልከላ "ሰብአዊነት የጎደለዉ በመሆኑ መንግሥት ክትትል አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ" ሲል ጠይቋል።

ቢቢሲ ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ቢደውልም ጉዳዩ እነርሱን እንደማይመለከት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ይመለከተዋል የተባለው የፈተናዎች ኤጀንሲም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

# BBC Amharic
የሰ/መ/ቁ 22891 - በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ ምክንያት የተፈጠረ ዕዳ ለጋራ ጥቅም መዋሉ በተረጋገጠ ጊዜ የዕዳው ወደ የጋራ ንብረት ወይም ወደ ሌላኛው ተጋቢ የግል ንብረት በመሄድ ሊከፈል የሚችለው በፍርድ አፈፃፀም ላይ ስለመሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘ በሌላኛው ተጋቢ ላይ ዕዳውን መሠረት በማድረግ ክስ ሊመሰረትበትም ሆነ ፍርድ ሊሰጥበት የማይገባ ስለመሆኑ በጋብቻ ወቅት ለጋራ ጥቅም የዋለ እዳ ከግል ወይም ከጋራ ንብረት ሊከፈል የሚችልበት ሁኔታ እና ክስ ሊመሰረት የማይቻልበት አግባብ
http://negari.abyssinialaw.com/judgments?id=1148
ጥብቅና የተከበረ ሙያ ነው። የዛሬ ችሎት ውሎዬና ትዝብቴ:-

ጠበቃ - ውሉ ህገወጥ ነው

ዳኛ -ህገወጥነቱን ያስረዱ

ጠበቃ- ሁሉም ነገር ህገወጥ ነው

ዳኛ -ለምሳሌ

ጠበቃ - ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው
ህገወጥ ነው።
ዳኛ - እስቲ አንዱን እንኳ ይጥቀሱ ? ክቡር ጠበቃ
ውሉ የህግ ጉድለት ነው ያለበት ወይስ ዋጋ
አልባ ውል ነው የሚሉት ?

ጠበቃ - ሁለቱም ። በህገመንግስቱ መሰረት
ህገፕወጥ ነው

(ችሎት ውስጥ ቁጭ ብለን እስክንጠራ የምንጠባበቅ ጠበቆች አጉረመረምን፣ ተንሾካሸክን)

ዳኛ - ፀጥታ አሉና ይቀጥሉ ክቡር ጠበቃ አሉ

ጠበቃ- ያው ቀደም ሲል እንዳልኩት ህገወጥ ነው
ውል ክፍል አልተፈረመም
ዳኛ - ውል ክፍል ባይፈረምስ? ለመሆኑ ምንድን
ነው ውል ክፍል ማለት ?

ጠበቃ - እኛ የምንለው ውሉ ህገወጥ ነው ብለን
ነው የምንፋለመው ?

ዳኛ - ክርክራችሁ መፋለም ነው ወይስ ውል
ይፍረስልኝ ነው ?
ጠበቃ - ሁለቱንም ። እንፋለማለንም ውልም
ይፍረስልን
ዳኛ - ክቡር ጠበቃ የይዞታው ባለቤት እኛ ነን ነው
የምትሉት ወይስ ውሉ ህገ ወጥ ነው
የሚሉት ?
ጠበቃ - (ከጀርባቸው ቁጭ ያከው የችሎት ታዳሚ
ጠበቆች ጉርምርምታና ሹክሽክታ
ያሳቀቃቸው ይመስላል ። ) እኛ እንግዲህ
በህገ መንግስቱ መሰረት ንብረት የማፍራት
መብት አለን።

ዳኛ - ታዲያ ማን ንብረት እንዳታፈሩ ከለከላችሁ ?
(ሙድ የያዙ ይመስላሉ)

ጠበቃ - ተከሳሽ ?
ዳኛ - እንዴት?
ጠበቃ - ህገወጥ ውል ይዘው ____ ብለው ዝም
አሉ።
ዳኛ - ጨረሱ ?

ጠበቃ - አዎ ጨርሻለሁ ክቡር ፍ/ቤት አሉ ። ወደ
ኃላ እኛን ዞር ብለው እየተመለከቱ

ዳኛ - ተከሳሽ ይቀጥሉ

የተከሳሽ ጠበቃ - ገልበው ገልበው ልክ አስገቡልኝ።

NB - *** ለካ
ሁሉም ሰው ጠበቃ መሆን ይችላል ።
By: Birhanu Assefa
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
@LawsocietiesBot
Forwarded from Abrham Tadesse
With regard to Abrhama Deressa's suicide case, What kind of code is that ? As far as I know it was only 4digit code and also it was posted on each exam room no need to go back to home even there was nothing given to the examinee in hard copy code so what kind of code was that???
I was one of the examinee there
Forwarded from Deleted Account
በዐ/ሕግ ሙያ 13 ዓመት አገልግያለው በታናሽ ወንድማችን የሕግ ባለሙያ አብርሃም ዱሬሳ ምናልባትም ከኔ በተሻለ የለበስኩትን ጥቁር በቀይ ጋወን ተረክቦኝ ፍትሕ ሊያስከብር የሚችለውን ጀግናችንን በደረሰበት አሰቃቂ በደል አተነዋል...እጅግ..ያንገበግበኛል...ይህ አልበቃ ብሎ በሱ ዙሪያ የተሰ ምላሾችም እጅግ ደካማ መሆናቸው ደግሞ ይበልጥ ያስቆጫል...ግን ጥቁር በቀይ ጋዎን ለብሼ በምከራከርበት ችሎት በቆምኩበት ለጀግናው ወንድማችን የሕግ ባለሙያ አብርሃም ዱሬሳ ልዩ ክብር አለኝ......"ፍትሕ ለጀግናው ወንድማችን አብርሃም ዱሬሳ"......ዐ/ሕግ
አእምሮ አልባ ዳኛ

በክፉ ህሊና እድልህን ዘግቶ በጉዳት ያጠቃህ፣
ታታሪውን ወጣት የነገን ተስፈኛ ለህልፈት ያበቃህ፤
ማን ይሆን ያ ክፉ ርህራሄ ያጣ?
ለምን ፈቀድክለት ደንብን ተከልሎ በጉዳተኛ ላይ ቂሙን እንዲወጣ?
እንዴት ዘነጋሃው አብራሃም ወንድሜ ግብግብ መሆኑን የኔና ያንተ እጣ?
ልብህ እያወቀው በምቀኞች መንደር በክፎዎች አንባ ልንኖር ተወልደን፣
ኮረኮንቹን መንገድ የጉዞን ጋሬጣ እሾሁን ተራምደን፣
የህብረተሰብ ሸጋታ አስተሳሰብ የሚቆልለውን የመከራ ቋጥኝ በጀግንነ አልፈን፣
በየህይወት ዘርፉ በትምህርት በስራ የገፉንን ሁሉ በወኔ አሸንፈን፤
ለድል የምንበቃ የእድሜልክ ታጋዮች መሆናችንን ልብህ እያመነው፣
አብራሃም ወንድሜ በክፉዎች ወጥመድ በእኩያኑ ሴራ መውደቅህ ለምነው?
ዳገት ቁልቁለቱን ያን ሁሉ መከራ አልፈኸው በብርታት፣
በአንዲት እርጉም አፍታ በከፋ ሰው ድርጊት በድንገት መረታት?

እስቲ ይሁን በቃ፣
በእውቀት አቅምህ ሳይሰንፍ አእምሮህ ጎልብቶ ሙሉ ሆኖ ልብህ፣
ማየት ብቃት ሆኖ ህሊና አልባ ዳኛ ሞት አስፈረደብህ።
ግን አይዞህ አልሞትክም ቃል ገብተንልሃል ሞትክን ላለመርሳት፣
በልባችን ነዷል ያቃጠለህ እሳት።

አይን አእምሮ በሚመስላቸው የእውቀትና ህሊና ድሆች ፍርደገምድል ፍርድ ራሱን ላጠፋው አይነስውር ወንድሜ አብራሃም ዱሬሳ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ ብዬ የፃፍኩት።

የህግ ባለሙያ እና የቀድሞው የፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የአይነ ስውራን ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት #አቶ ካሳሁን ይበልጣል።
ፍትህ የየሚመጣው በሁላችን ተሳትፎ ነው።
Ethical and corruption free society that upholds integrity and accountability
Contact Us via
@Transparency_Ethiopia_Bot
and
ethiopiatransparency@gmail.com
ከመድሎ የፀዳች አገርን እንፍጠር‼️‼️
ኢትዮጵያ ለ50 ዓመታት የተጠቀመችበትን የንግድ ሕግ ልትቀይር ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረውን የንግድ ሕግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ አዲስ ሕግ ልትቀይር መሆኑ ተገልጿል።
አገሪቷ ከምትጠቀምባቸው መድኃኒቶች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆነው በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ መሆኑም ተጠቁሟል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ምስጋኑ አረጋ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ኢትዮጵያ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ስትጠቀምበት የነበረው የንግድ ሕግ ከዘመነ ቴክኖሎጂ ጋር የተናበበና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በአዲስ ሕግ ልትተካ ነው።
አገሪቷ እያካሄደች ያለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ መርህ በዋናነት በማክሮ ኢኮኖሚ፣ መዋቅራዊ እና የዘርፍ ማሻሻያ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፣ በዚህም በአሁኑ ወቅት ሁለንተናዊ ለውጦችን ለማምጣት ከመቼውም በላይ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትር ድኤታው ገለፃ፤ እየተደረጉ ካሉ ማሻሻያዎች መካከል 50 ዓመታትን በሥራ ላይ የነበረው የንግድ ሕግ ዘመኑ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ የማሻሻል እና ሕግ ሆኖ የማውጣት ሂደቱ ከጫፍ መድረሱን አብራርተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ማግኘት ትችላላችሁ፡፡