በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት ለተቋሙ ከተሰጡት በተጨማሪ በሌሎች ሕጎች ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች:-
1. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት:-
ሀ. ለሚኒስትሮች የተሰጠውን የወል ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ
ያውላል፤
ለ. ተጠሪ የተደረጉለትን አስፈፃሚ አካላት በበላይነት ይመራል፣
ያስተባባራል፣ አደረጃጀታቸውን የስራ ፕግራሞቻቻውን እና
በጀታቸውን መርምሮ ለሚመለከተው እንዲቀርብ ያደርጋል፤
ሐ. በፌደራል ፖሊስ ምርመራ ዘርፍ የሚከናወኑ የምርመራ ሥራዎችን
በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፤
መ. በምርመራ ሥራ ላይ ለተሰማሩ መርማሪዎችና ኃላፊዎችን የሥራ
ስምሪት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤ የሥራ ሪፖርት እንዲቀርብለት
ያደርጋል፤
2. የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 166/1952 የንግድ ድርጅቶች ኪሣራ ወቅት ጣልቃ መግባት እንዲችል የተሰጠዉን ስልጣን ያከናዉናል፣
3. የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ከመደበኛ የጋብቻ እድሜው ከሁለት ዓመት ያልበለጠ በመቀነስ እንዲጋቡ እንዲሁም ጋብቻው በእንደራሴ እንዲፈፀም ፍቃድ ይሰጣል፣ በዕድሜ፣ በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ፣ በፍርድ በመከልከል ምክንያት የሚፈፀም ጋብቻ ይከላከላል፣
4. የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 590/2000 በብሔራዊ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሕትመትም ሊሰራጭ መሆኑን ሲደረስበት ለፍ/ቤት ማመልከት ወይም ማገድ፣ በመገናኛ ብዙሃን /mass media/ አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰውን በተመለከተ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልገው መሆኑን በመወሰን ለፍ/ቤት እንዲቀርብ የማድረግ ስልጣን፣
5. በምስክሮች እና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699/2003 በአዋጅ ቁጥር 699/2003 መሰረት ለወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች በህግ መሠረት ጥበቃ ይሰጣል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
6. የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻፀም አዋጅ ቁጥር 840/2006 የይቅርታ ጥያቄዎችን መርምሮ ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርበው የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል፣ የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤትን ያደራጃል፣ ለቦርዱ የሚቀርቡ የይቅርታ ማመልከቻዎች ይቀበላል፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ አጣርቶ ለቦርዱ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ ውሳኔዎችን ይቅርታ ጠያቂው ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት ያሳውቃል፣ የይቅርታ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣
7. የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 የኮምፒውተር ወንጀሎችን አስመልክቶ ከፖሊስ ጋር በጋራ ይመረምራል፣ ምረመራውን ይመራል፣ በቁልፍ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል የኮምፒውተር ወንጀል ስለመፈጸሙ ወይም ሊፈጸም ስለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ሲኖር እና አስቸኳይ ሁኔታ ሲያጋጥም የኮምፒውተር ዳታን ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎትን ለመጥለፍ ወይም ክትትል ለማድረግ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈቃድ ይሰጣል፣ የኮምፒውተር ወንጀሎችን አስመልክቶ አለም አቀፍ ትብብርን ያደርጋል፣ የኮምፒውተር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚቋቋመውን ብሔራዊ አስፈጻሚ ግብረ ሀይልን ያስተባብራል ፣
8. በሰዎች መነገድ እና በህገ-ወጥ መንገድ ድንበርን ማሻገር ወንጀል ለመከላከል በመወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 መሰረት፡-
ሀ/ በሰው የመነገድ፣ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና
በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀልን
ተከላካይ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ያደራጃል፣ ያስተባብራል፣
ለ/ በአዋጁ የተገለፁትን ወንጀሎች ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጡ
ህግችን በተመለከተ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥር እና ለፍትህ
አካላት የአቅም ግንባታ ስራ ያከናዉናል፣
9. በፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚያወጧቸውን መመሪዎች ያርማል፣ ይመዘግባል፣ ቁጥር ይሰጣል ፣ በድረ-ገጹ ላይ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
ምንጭ:- ጠቅላይ ዐ/ህግ
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

Where are the lawyers, the natural leaders in Ethiopia!?
Most of the greatest leaders and change agents in the world are Lawyers. The notable ones being Abraham Lincoln, Gandhi, Mandella, Barack Obama, even the President-Elect Joe-all Lawyers.
What about in Ethiopia? Lawyers are busy with rhetorics and opportunism while others play the game (of course, very badly). So, Comrades, it is time to live up to what the discipline is all about-leadership! Come out from your temporary refuge and lead the nation to leave some legacy behind. Or else, you will remain playing Low-year!
By Moges Zewdu Teshome
@lawsocieties

የወንጀል ፍትህ አስተደደር ምክክር መድረክ
***********************************
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የጠቅላይ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት እና የፖሊስ መመሪያ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ጥቅምት 30/2013 ዓ፣ም ምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የተፋጠነ ፍትህ አሰጣጥ (Real Time Dispatch) በፍርድ ቤቱ የተካሄደ ጥናት በሕግ ጥናት እና ድጋፍ ክፍል አስተባባሪ አቶ ቃለእግዚአብሔር ጎሳዮ በኩል የቀረበ ሲሆን ፈጣን ፍትሕ አሰጣጥ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና የወደፊት የአሰራር ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡ በውይይቱም ወቅት ተሳታፊዎች ያነሷቸውን ሀሳቦች በግብአትነት በመውሰድ ሰነዱ የሚዳብር እና በቀጣይነትም ሰነዱ ለፍትህ አካላት አብይ ኮሚቴ የሚላክ መሆኑን መድረኩን የመሩት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ገልጸዋል፡፡ Federal First Instance Court Of Ethiopia

የውርስ ኃብት ማጣራትን የተመለከቱ አንዳንድ ነጥቦች ከሰበር ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
በ፦ ሙሉቀን ሰይድ
በዚህ ጽሑፍ የውርስ ማጣራት ተግባር በምን አግባብ እንደሚከናወን፤ የውርስ አጣሪው ስልጣንና ኃላፊነት እስከምን ድረስ አንደሆነ፤ የውርስ ኃብት ላይጣራ ሚችልባቸው ሁኔታዎች፤ የውርስ አጣሪ ሪፖርትን በማጽደቅ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ ህጋዊ ውጤቱ እስከምን ድረስ እንደሆነና በዚህ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ ተቃውሞ በምን መልኩ ሊቀርብ እንደሚገባ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ አጭር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1963-liquidation-process-in-ethiopia

Sometimes the bravest and most important thing you can do is just show up.‼️‼️‼️
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
#Share
ALE (አለ) law societies
ALE (Alternative Legal Education) All in one, All Law Societies. federal & regional Judges, Prosecutors, Advocates, consultants & law school heads, instructors, deans, Law graduates, Students & NGOs ...for discussion @ALE_lawsocieties
Contact: @LawsocietiesBot

Forwarded from Deleted Account
እውነት ለመናገር ከሆነ ህግ ትምህርት በመማርህ ዘንድሮ በጣም ትፀፅታለህ። የዘንድሮ የህግ Gc ተማሪ ትልቅ ጉዳት ደርሶበታል በተለይ morally, economically ስለዚህ ካሳ ያስፈልገዋል ምሳሌ ካለው የተማሪዎች ሁኔታ አንፃር 1) ቅልለ ያለ የ exit exam ጥያቄዎች መፈትን አለበት,
2) ተምረቀን እንደ ወጣን በተለይ ደግሞ judicial training መግባት አሚፈልግ ተማሪ ያለ ምንም እንግልት መግባት አለበት።
3) judicial training ለማይገቡት ደግሞ በፍጥነት ስራ እንዲጀምሩ ማደረግ አለበት። ይሄ ካልሆነ በስተቀር የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ መቼም ቢሆን ሊካስ አይችልም።
አመሰግናለሁ

Forwarded from ተስፍሽ አቢሢኒያ
ምንድነው ማካበድ? ባገር ለመጣ ችግር መጀመሪያ ሀገራችን ሰላም ትሁን. ወጥተን መግባት, ሰርተን መብላት የምንችልባት ኢትዮጲያ ትሁን. ቴምፖ ዳቦ ይሆናል? exit exam መፈተን ስራ ለማግኘት ዋስትና ይሰጣል? ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ብንሰጥ
ከኢፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ
================================
በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወሰነ፡፡
እንደሚታወቀው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የግልና የመንግስት ተቋማትን ለመጠበቅ ከመከላከያና ከፖሊስ በጡረታና በክብር የተቀነሱ የሰራዊት አባላት የፀጥታ ስራ ላይ ካላቸው ልምድ በተጨማሪ ተገቢውን ስልጠና አግኝተው ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሚሰጣቸውን የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድና ከሌሎች መንግስታዊ ተቋማት የሚፈለገውን መስፈርቶች አሟልተው የመንግስትና የግል ተቋማትን እንዲጠብቁና ሀገራቸውን እንዲሁም ራሳቸውን እንዲጠቅሙ በሚያስችል ሁኔታ መቋቋማቸው ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጡዋቸውን በመመልመል፣ ለተቋም ጥበቃ የተሰጣቸውን የጦር መሳሪያ በማስታጠቅና በማሰማራት በህዝብና በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተደርሶባቸዋል፡፡
ለአብነትም ከአሳለፍነው 2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን እነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላትና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችንና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉና ሲያዘርፉ ቆይተዋል። በዚህም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብና ንብረት ዘርፈዋል፤ እንዲዘረፍም አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሳሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል። እነዚህ ከተልዕኮአቸው ውጭ እንደሚንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ይህም አልበቃ ብሏቸው አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በጁንታው የህዋሃት ወንበዴ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባትና የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ በህብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ መሆኑ ተደርሶበታል።
ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተገለፀው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፦
1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
ለሀገርና ለዜጎች ሰላምና ደህንነት ሲባል ስራቸውን እንዲያቆሙ የተወሰነና እስከአሁን ባለው አገር የማተራመስና ህገ-ወጥ ስራቸው በህግ የሚጠየቁ መሆኑን እየገለጽን ስማቸው ከላይ የተገለፀው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ስራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግስት አካል ከነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈፅም የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በመጨረሻም ከላይ ስማቸው በተገለፀው የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ስር ተቀጥረው ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ሰራተኞችን በተመለከተ ተገቢውን ልየታ በማድረግ ማስተካከያ እስኪወሰድ ድረስ በተመደቡበት ቦታ የጥበቃ ስራቸውን አጠናክረው እንዲሰሩና የሚጠብቋቸው የግልና የመንግስት ተቋማት ኋላፊዎችም በተሰጠው መግለጫ መሰረት ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ሆኖ የዕለት ተዕለት ስራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርና የግል ጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት በማድረግ ቀጣይ በሚሰጡ የስራ መመሪያዎች ብቻ ሊሰሩ እንደሚገባ በጥብቅ እናሳስባለን።
የኢፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ህግ የመተርጎም ተግባር በዘፈቀደ የሚካሄድ እንዳይሆን የህግ አተረጓጎ መርህዎች አስፈላጊ መሆናቸው ተጠቆመ
***************************
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ከብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ህግ የመተርጎም ተግባር በዘፈቀደ የሚካሄድ እንዳይሆን ጥንቃቄ የሚያስፈልግ በመሆኑነ ምክንያት የህግ አተረጓጎምን የሚመለከቱ መርሆዎች መኖር አስፈላጊ ናቸው ሲሉ በራዲሰን ብሉ ሆቴል በህግ ጉዳይ የተጻፉ መጽሐፍት ላይ በተዘጋጀ የትንተና እና የትችት መርሃ ግብር ላይ ገለጹ፡፡
በዳኝነት አካል አማካኝነት የሚከናወን ሕግ የመተርጎም ተግባር ሁለት ዋና ዋና ክንዋኔዎችን ያቀፈ ነው ያሉት ክብርት ፕሬዝደንቷ አንደኛው የተመረጠውን ሕግ ድንጋጌ ዳኝነት ሊሰጥበት ከተዘጋጀው ጉዳይ ፍሬ ነገሮች ጋር በማዛመድ ውሳኔ መስጠት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በህጉ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላት እና ዓረፍተ ነገሮች የግልጽነት መጓደል፣ አሻሚነት፣ የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ፣ ጥያቄ የተነሳበትን ጉዳይ በተመለከተ ከተሰጡ አማራጭ ሃሳቦች መካከል ሕጉ ከታለመለት ዓላማ ጋር አብሮ የሚሄደውን ሃሳብ በመምረጥ ውሳኔ መስጠት ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
የመጽሐፍ ትንተና ፕሮግራሙ የጆናሲዮ አማካሪ ድርጅት ከመሰረት ስዩምና ጓዶቿ የህግ ቢሮ እና ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡
በመጽሃፍ ትንተና ፕሮግራም ላይ በአቶ ተስፋዬ ነዋይ “ሕግ እና አተረጓጎሙ” እና በአቶ አብርሃም ዮሐንስ “የአስተዳደር ህግ መግቢያ” በሚል ርዕስ በተጻፉ መጽሐፍት ላይ ትንተና ተሰጥቷል፤ ትችትም ቀርቧል፡፡
በህግና አተረጓጎሙ መጽሐፍ ላይ በፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ እና በዶ/ር ጌታሁን ካሳ ትንተናና ትችት የቀረበ ሲሆን ሁለቱ የህግ ምሁራን መጽሃፉ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በርካታ ጠቃሚና አወንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ፍሬ ነገሮችን የያዘ መሆኑን ጠቁመው አቶ ተስፋዮ ነዋይ ለተማሪዎችና ለተመራማሪዎች እዲሁም በህግ ዘርፍ ግንዛቤ ለሌላቸው አንባብያን አስተማሪና ሊጠቀስ የሚችል መጽሃፍ በመጻፋቸው እንኳን ደስ አለዎት በማለት ትንተናቸውን/ ትችታቸውን በሁለት እይታ በመክፈል አቅርበዋል፡፡
የተንታኞቹ የመጀመያሪያ እይታ በመጽሃፉ አደረጃጀትና አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን ሁለቱም ተንታኞች መጽሃፉ የፊደል፤ የሰዋስው እና የይዘት አደረጃጀት ቅደም ተከተል መጠነኛ ችግሮች ያሉበት መሆኑን አንስተዋል፡፡ በሁለተኛው እይታቸው በመጽሃፉ ፍሬ ነገር ይዘት ላይ ትኩረት አድርገው ትንተና ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ አንጻር መጽሃፉ ከህግ እና አተረጓጎም ጽንሰ ሃሳብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ይንንም መነሻ በማድረግ በሃገራችን የሰበር ችሎት ህግ አተረጓጎም ነባራዊ ሁኔታ አስረጅ የሚሆኑ ጉዳዮችን ለማሳየት ጥረት ማድረጉ እጅግ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በማጠቃለያውም 11 የሚሆኑ መደምደሚያዎችን ማስቀመጡ ጸሐፊው ሊያስተላልፈው የሚፈልገውን መልእክት ያሳዩ ናቸውም ብለዋል፡፡ አጻጻፉ ከጽንሰ ሃሳብ ተነስቶ ወደ ተግባራዊ ማሳያዎች መምጣቱ ቅቡልነት ያለውና ተመራጭ የአጻጻፍ ስልት መሆኑን ከርእሰ ጉዳዩ ጋር ተስማነት ያለው መሆኑ ተነግሯዋል፡፡
በመጽሃፉ ይዘት ላይ ተንታኞቹ/ተቺዎቹ በመጽሃፉ ውስጥ ቢስተካከል ወይም ቢካተት ያሏቸውን ሃሳቦች የገለጹ ሲሆን አቶ ተስፋዬ በሁለቱ ትንተና አቅራቢዎቹ የተሰጡ የትችት አስተያያየቶችን ወስደው በሚቀጥላው ህትመት የማስተካከያ እና ተጨማሪ ሃሳቦች እንደሚያካትቷቸው ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ አያይዘውም መጽሃፉን የጻፉበት ዓብይ ምክንያት በርእሰ ጉዳዩ ላይ ከእሳቸው የተሻለ ሊጽፉ የሚችሉ ዳኞች፤ የህግ ባለሙያዎችና ምሁራን እንዲጽፉና በዘፍፉ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያሳርፉ ማነቃቃት ነው ብለዋል፡፡
የኢፊዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በትንተና እና ትችት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ይህንን የትችት መድረክ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር እና መሰረት እና ጓዶቿ የህግ ቢሮ ምስጋና ይገባችኋል ብለውል፡፡ እንደዚህ አይነት የህግ መጽሐፍት የሚተነተኑበትና የሚተቹበት መድረኮች በተደጋጋሚ መዘጋጀት የሚገባቸው መሆኑን ጠቁመው የህግ ባለሙያዎች ያካበቱትን እውቀት ለትውልድ እና ለህብረተሰቡ ለማካፈል በመጽሃፍ መልክ እንዲጽፉ እና ለዘርፉ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡
በመድረኩ የሶስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሃላፊዎችና ተወካይ ዳኞች፣ ጠበቆችና የህግ መምህራን በአጠቃላይ የህግ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

በደንበኞች አገልግሎት እና ስነ-ምግባር ላይ የአስተዳደር ሰራተኞቸ ስልጠና
****************************************************
የአዲስ አበባ ከተማ ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት ከፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጋር በመተባበር 160 ለሚሆኑ የፍ/ቤት ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሶች ለ5ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ስልጠናው የተሰጠው የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ክህሎት፣ የስነ ምግባር እሴቶች በስራ ስለሚተገበርበት አግባብ እና ተያያዥ በሆኑ ርዕሶች ላይ ነው፡፡ በቀጣይነትም መሰል ስልጠናዎች በየደረጃው ለሚገኙ ሰራተኞች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Legal Affairs Manager
SAVE
A
ABH Partners P.L.C
Addis Ababa (+1 other)
Apply on Ethiojobs
2 days ago
The National Election Board of Ethiopia (NEBE), re-established by proclamation No. 1133/2011, is the constitutionally mandated body to conduct elections, organize referendum and regulate political parties in Ethiopia. NEBE is undergoing institutional reform to enhance its credibility and capacity and conduct free, impartial, and credible elections. Through the support of the United Nations Development Program (UNDP), NEBE has contracted ABH Partners to provide human resource recruitment and management services. Accordingly, ABH partners would like to invite applicants who meet the below requirements to apply for the position of Legal Affairs Manager . Required number: One Reports to: NEBE Management Board Member HQ of NEBE Duty station: NEBE Head Quarter, Addis Ababa Duration: 12 months with a possibility of extension Expected Start Date: Immediately after concluding the contract Purpose of the Role Reporting to NEBE Management Board Member, the Legal Affairs Manager will be responsible to planning, directing, coordinating, supervising, evaluating, and decision making on the development of rules, regulations, and guidelines that enable the NEBE to achieve its goals of organizing a fair, credible and transparent polls that meet the minimum international elections legal standards. Major Responsibilities Developing rules and regulations that help to implement election Lead the coordination and preparation of NEBE legal documents such as directives, regulations, manuals that will be used by the NEBE to regulate the behaviours of electoral stakeholders such as political parties. . Review and provide international comparative analysis to the NEBE Management Board various legal issues Provide interpretations of published laws/directives and legal procedures in relations to elections; Provide leadership on NEBE’s public consultation meetings on legal issues to ensure transparency and inclusion; Help the NEBE Management Board to prepare to address legal related questions from the public; Manage translations of legal documents and learning materials into different NEBE languages; Design strategy to boost awareness of internal and external actors on election laws and related code of conducts. Manage the development of code of conduct for the board members and staff members; Formulate strategies to implement and oversee effective election dispute resolution systems at various levels, and provide robust support to the rolling out of these systems; Support the NEBE Management Board to manage and address elections disputes handled through the NEBE’s grievance hearing process at various levels; analyse and summarize the types of grievance and share with the NEBE Management Board. Oversee the NEBE’s response to elections dispute that go through the judiciary process; Lead the establishment and execution of an effective electoral case management system Liaise with various relevant agencies to create a system that promotes accountability for individuals and groups committing electoral crime. Plan, guide, coordinate, oversee, and evaluate all tasks of the legal unit. Provide robust and consistent leadership to the legal department employees Facilitate the necessary conditions to build the legal team’s capacity through creating relationship among other departments and stakeholders. Execute the necessary leadership and decisions making based on analysis of reports from the subordinates. Design strategy to boost awareness of internal and external actors on Follow up the execution of orientation regarding election laws and related code code of conducts. Plan, guide, coordinate, oversee, and evaluate all tasks to be discharged under the supervision of the legal unit Participates in higher level management meetings, discuss on issues that requires decisions, make decisions, and let others to decide. Implement other legal tasks assigned by the NEBE Management Board.

Educational Requirements: LLB/ LLM holders For LLM holders: at least 6 years of relevant experience of which 3 years in a leadership position For LLB holders: at least 8 years of relevant experience of which 4 years in a leadership position Experience in the development and delivery of guidelines, rules, and regulations in an election context, or relevant and equivalent experience working with civil society organizations and implementing...
Required Experience:
Senior Level (5+ years experience
Required Experience:
Senior Level (5+ years experience
ለክቡራን የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች
ከዚህ ቀደም ከ1-5ኛ ፎቅ እጣ በወጣባቸዉ 80 የመኖሪያ ቤቶች ዉስጥ የተካተታችሁ ክቡራን የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት የዉል ፎርም እየሞላችሁ ቁልፍ እንድትረከቡ እንገልጻለን፡፡
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት

Forwarded from Transparency International Ethiopia (TIE)
“ችግር ተንታኝ በዝቷል፣ መፍትሔ ሰጪ ነው የጠፋው፤ ሁል ጊዜ ከችግሩ ጋር ሳይሆን ከመፍትሔ ጋር መወገን፣ ችግር ስናይ እኔ የመፍትሔ ኃላፊነት አለብኝ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፣ እኛ አገር ሥራ አይደለም የጠፋው ሰሪ ነው፣ችግር ስናይ በውስጡ እድል ማየትና እያንዳንዱ ችግር ሀሳብ ያጣ እድል እንደሆነ ማሰብ ያስፈልጋል”
ዶ/ር ምህረት ደበበ
@TransparencyEthiopia
@TransparencyEthiopia
ዶ/ር ምህረት ደበበ
@TransparencyEthiopia
@TransparencyEthiopia
Forwarded from Transparency International Ethiopia (TIE)
ፍትህ በደጃችን በቅርቡ..........ሁሉንም ማህበረሰብ ያካተተ እንቅስቃሴ
ለጋራ ጥቅም እንጅ ለግለሰብ ጥቅም እና መበልፀጊያ መሳሪያ አንሆንም የእኛ መተባበር እና አንድ መሆን ለጋራ ሀብታች ዋስትና ይሆናል ........
ሁላችንም የኢትዮጵያ አንድ አካል ሁነን በጋራ አይን: ጀሮ እና እጅ ሀብታችንን እንጠብቅ።
የሀገር ሀብት ደህንነታችን ነው
የሙስና ሀብት ለሀገር ሰላም ጠንቅ ነው።
የጋራ ሀብታችን በግለሰቦች ሲገባ በገንዛ ሀብታችን በገንዛ ወገናችን ሰላማችንን ያናጋሉ ።።።።።
አሁን ግን በተባበረ ክንድ እንቆማለን
እናያለን
እንሰማለን
ተው እንላለን በህብረት ሀይል አለ።
share

Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብሮ ስለመኖር /Irregular Union/
ይህ ፅሁፍ በተጻፈበት ወቅት በተግባር ላይ ባለው የኢትዮጵያ ህግ መሠረት የቤተሰብ ህግ የማውጣት ስልጣን ለክልሎች የተሰጠ ስለሆነ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የአማራ ክልል፤ የትግራይ ክልል፤ የኦሮሚያ ክልል፤ የአማራ ክልል እና የደቡብ ክልል የየራሳቸው የቤተሰብ ህግ ያወጡ ሲሆን እነዚህ ህጎች ጋብቻ ሳይፈጸም እንደባልና ሚስት ስለመኖር በተመለከተ ያወጡት ድንጋጌ ልዩነት የሌለው በመሆኑ ይህ ጽሁፍ የህግ አንቀጾችን ሳይጠቅስ ጋብቻ ሳይፈጸም እንደባልና ሚስት መኖር ከሀገራችን ህጎች አንጻር እንዴት እንደሚታይ በአጠቃይ ገለጻ ማድረግ ላይ ያተኩራል፡፡
1. ትርጉም
ጋብቻ ሳይፈጸም እንደባልና ሚስት መኖር ማለት አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በህግ በሚፀና አኳኋን ጋብቻ ሳይፈጽሙ ነገር ግን እንደ ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት አንድ ወንድ እና ሴት በሀገሪቱ የቤተሰብ ህጎች እውቅና በተሰጣቸው የጋብቻ አፈጻጸም አይነቶች ማለትም በክብር መዝገብ ሹም ፊት /ማለትም በማዘጋጃ ቤት፤ በወረዳ/ቀበሌ አስተዳደር ወይም ሌላ ጋብቻ ለመፈጸም ወይም ለመመዝግብ ስልጠን የተሰጠው አካል/ የተደረገ ጋብቻ፤ ባህላዊ ጋብቻ /ከተጋቢዎቹ በአንዱ ወይም በሁለቱም ባህል ሥርአት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ/ እና ሀይማኖታዊ ጋብቻ /ከተጋቢዎቹ በአንዱ ወይም በሁለቱም ሀይማኖት ሥርአት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ/ ሳይፈጽሙ ነገር ግን እንደ ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ የሚፈጠር ሁኔታ ነው፡፡
እነዚህ እንደባልና ሚስት የሚኖሩት ወንድ እና ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ኖሩ ለመባል ሌሎች ሰዎች ወይም ለሚኖሩበት ማህበረሰብ የሚሳዩት ሁኔታ በህግ ተጋብተው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ መሆን ያለበት ሲሆን ነገር ግን ራሳቸውን ባልና ሚስት እንደ ሆኑ በማድረግ ወይም ባልና ሚስት ነን ብለው ለሌሎች ሰዎች ማስተዋወቅ አይጠበቅባቸውም፡፡ ይህ ሁኔታ ተሟልቶ ባልተገኘበት ሁኔታ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በታወቀና በተደጋጋሚ ሁኔታ የሩካቤ ስጋ ግንኙነት መፈጸማቸው ብቻ ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ኖሩ አያስብላቸውም፡፡
2. ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት መኖር ያሉት ህጋዊ ወጤቶች
2.1 በግል ግንኙነት በኩል
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ መሠረት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት ቤተሰቦች መካከል ህጋዊ ጋብቻ እንደፈጸሙ ሰዎች የሥጋ ዝምድና አይፈጠርምም፡፡ ማለትም የሴቷ እናትና አባት ለወንዱ አማች፤ የወንዱ እናትና አባት ለሴቷ አማች አይሆኑም፡፡ በተመሳሳይ የሴት ወንድምና እህት ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት ዘመድ አዝማድ ከወንዱ የወንዱ ደግሞ ከሴቷ ጋር በህግ የሚፈጠር ዝምድና አይኖራቸውም፡፡
ነገር ግን ወላጆችና ተወላጆች፤ ወንድምና እህት፤ አንድ ሴት ከአጎቷ ወይም አንድ ወንድ ከአክስቱ ጋር ትዳር ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብረው ሊኖሩ አይችሉም፡፡ በተጨማሪም በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ማለትም ከሚስት ወላጆች ወይም ተወላጆች እንዲሁም ሴቷ ከባሏ ወንድም እንዲሁም ወንዱ ከሚስቱ እህት ጋር ጋብቻ ሳይፈጽሙ አብረው መኖር አይችሉም፡፡
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች ህጋዊ ጋብቻ እንደፈጸሙ ሰዎች የጋራ ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደየአቅማቸው አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸው፡፡
2.2 በንብረት በኩል
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት ለ3 /ሶስት/ አመት ያላነሰ ጊዜ አብረው ከኖሩ በዚህ ጊዜው ውስጥ ያፈሯቸው ንብረቶች በሙሉ የጋራ ሀብት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ወንድ እና ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ አብረው የኖሩት ከ3 አመት ያነሰ ከሆነ ግንኙነቱ ሲቋረጥ ሁለቱም በስማቸው የተመዘገቡ ንብረቶችን ብቻ ይዘው የሚቆዩ ሲሆን 3 አመት ቢቆዩም አንዳቸዉ ከግንኙነቱ በፊት ያፈሩትን ሀብት ሌላኛው ሰው የመካፈል መብት የለውም፡፡
እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች በጋራ በሁለቱም ስም ወይም በየግል ስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ እና ያላቸው ንብረት በሙሉ ወንዱ እና ሴቷ አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት የተገኘ መሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ እንደሆነ ንብረቱን አብረው በነበሩ ጊዜ ያገኙት ነው በሚል የህግ ግምት ይወሰዳል፡፡
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች የጋራ ንብረት በተመለከተ ህጋዊ ጋብቻ ያላቸው ሰዎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ህጎች ሁሉ ለእነርሱም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት የጋራ ንብረት ለመሸጥ፤ ለመለወጥ፤ በመያዣ ለማስያዝ፤ ወይም ሌሎች ሰዎች በጋራ ንብረታቸው ላይ መብት እንዲያገኙ ለማድረግ፤ ከብር 500.00 /አምስት መቶ/ በላይ የሆነ ገንዘብ ለማበደር፤ ለመበደር ወይም ዋስ ለመሆን፤ ከብር 100.00 /አንድ መቶ/ በላይ የሆነ ንብረት ወይም ገንዘብ በስጦታ ለመስጠት የሁለቱም ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ የሁለቱም ፈቃድ ሳይኖር ከላይ የተደረጉት ነገሮች ተፈጽመው ቢገኙ ፈቃዱን ያልሰጠው ወገን የተፈጸመው ተግባር ወይም የተገባው ግዴታ ፈራሽ ወይም ቀሪ እንዲሆን መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህንን ጥያቄ ለፍርድ ቤት ማቅረብ የሚቻለው ፈቃዱን ያልሰጠው ወገን ተግባሩ መፈጸሙን ባወቀ በ6 ወር ጊዜው ወይም ተግባሩ በተፈጸመ በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
በተጨማሪ ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች የጋራ ንብረታቸውን ከሁለት አንዳቸው ብቻ እንዲያስተዳድሩ በግልጽ ስምምነት ካላደረጉ በስተቀር ወንዱ እና ሴቷ በጋራ ንብረታቸው አብረው የሚያስተዳድሩ ሲሆን ከሁለቱ አንዳቸው ይህንን ማድረግ እንዳይችሉ የሚደርጋቸው ሁኔታ ከመጣ አንደኛቸው ብቻ ንብረቱን ያስተዳድራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ንብረቱን የሚያስተዳደረው ወገን ለሌላኛው ሰዉ መረጃ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ገቢያቸውን በተመለከተ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች ገቢያቸውን ወንዱ ሴቷ እንድትቀበልለት ወይም ሴቷ ወንዱ ገቢዋን እንዱቀበልላት ሥልጣን መስጠት የሚችሉ ሲሆን ለሌላኛው ወገን ገቢ የሚቀበለው ወገን ለሚቀበለው ገንዘብ ደረሰኝ እንዲሰጥ በፍርድ ቤት ሊታዘዝ ይችላል፡፡
የጋራ ሀብት አስመልክቶ የሚደረገው ንብረት ክፍፍል በህግ አኳያ በህግ የተጋቡ ሰዎች ፍቺ ሲፈጽሙ ከሚያደርጉት ንብረት ክፍፍል የማይለይ ሲሆን ሁለቱም በግንኙነቱ ውስጥ የነበሩት ሰዎች የጋራ ንብረት ግማሽ ይደርሳቸዋል፡፡ ነገር ግን ግንኙነቱ የተቋረጠው በአንዱ ወገን ጥፋት ሲሆን ማለትም ወንዱ ወይም ሴቷ ታማኝ ባለመሆናቸው ወይም በሌላኛው ላይ ሌላ በደል በማድረሳቸው ምክንያት ሲሆን እና ይህ በተጨማጭ ማስረጃ ከተረጋገጠ ጥፋት የፈጸመው ወገን ለተበዳዩ ወገን ካሳ እንዲከፍል ሊገደድ ይችላል፡፡ ይህ ካሳ የሚወሰነው በትርእ /Equity/ የተወሰነ ገንዘብ እንዲከፍል በመወሰን ወይም ከጋራ ንብረት ላይ አብላጫውን ድርሻ ለተበደለው ወገን በመስጠት ሊሆን ይችላል፡፡
እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች ለልጆቻቸው ለማሳደጊያ ለሚውሉ ወጪዎች ወይም የራሳቸውን ኑሮ ወጪዎች ለመሸፈን በሚል አላማ ብድር የሚበደሩ እንደሆነ ህጋዊ ጋብቻ እንደፈጸሙ ሰዎች ሁሉ ይህ ብድር የጋራ እዳቸው ሆኖ ሁለቱም በአንድነት እና በነጠላነት የእዳው ሀላፊ ይሆናሉ፡፡ ይህ ሲባል አበዳሪዎች እዳዉን በምርጫቸው ወንዱን ወይም ሴቷን ብቻ ከፈለጉ ደግሞ ሁለቱንም በጋራ እንዲከፍሏቸው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ይህ እዳም ከሁለቱም የጋራ ንብረት ላይ፤ የጋራ ንብረቱ እዳዉን ለመክፈል በቂ ካልሆነ ደግሞ ከወንዱ ወይም ከሴቷ የግል ሀብት ላይ ተከፋይ ይሆናል፡፡ የግል እዳን በተመለከተ ደግሞ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ሰዎች አሁንም ከህጋ

ዊ ባልና ሚስት ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታቸው የግል እዳ ካለባቸው እዳው ከግል ንብረታቸው የሚከፈል ሲሆን የግል ንብረታቸው እዳውን ለመክፈል በቂ ካልሆነ ግን ከጋራ ንብረታቸው ላይ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ልጆችን በተመለከተ አንድ ወንድ እና ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት በሚኖሩ ወቅት የተረገዙ እና የተወለዱ ልጆች አባት ወንዱ ሴቷ ደግሞ እናት መሆናቸው የህግ ግምት ይወሰዳል፡፡ በእርግጥ ይህ የህግ ግምት በህክምና ወይም ሌላ አሳማኝ ማስረጃ በማቅረብ ቀሪ ሊሆን የሚችል ነው፡፡
3. ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት መኖር ግንኙነት ስለማቋረጥ
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ግንኙነታቸው እንዲቋረጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት በህግ አግባብ ጋብቻ እንደፈጸሙ ሰዎች በሚለያዩበት ወቅት በፍርድ ቤት ቀርበው ፍቺ ማስወሰን ሳያስፈልጋቸው አብረው መኖር ማቆም እና ግንኙነታቸው ማቆም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከሁለቱ አንዱ በሚሞቱ ጊዜ ይቋረጣል፡፡ ነገር ግን ግንኙነቱ የተቋረጠው በወንዱ እና/ወይም በሴቷ ፍላጎት ወይም በሁለቱ አለመጣጣም ሆነ በአንዳቸው ሞት ምክንያት ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የመኖሩ ግንኙነቱ በሚቋረጥ ጊዜ ከጋራ ንብረት ላይ ድርሻቸው ለመካፈል ለፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ ክፍፍል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
4. ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደ ባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት ስለመኖሩ ለመስረዳት ስለሚቀርብ ማስረጃ
ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ወንድ እና ሴት ከላይ በተገለጸው መሠረት ግንኙነታቸውን ማስረዳት አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ይህንን የሚያስረዱት “የግንኙነት ሁኔታ’’ እንዳለ በማስረዳት ነው፡፡ የግንኙነት ሁኔታ ማስረዳት ሲባል ወንድ እና ሴቷ ምንም እንኳን ጋብቻ ባይፈጽሙም ነገር ግን የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመዶቻቸው እና የሚኖሩበት ማህበረሰብ እንደተጋቡ ሰዎች ነው የሚኖሩት ብለው ሲገምቷቸው ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ምክንያት እንደባልና ሚስት መኖር እንዳለ ማስረዳት የፈለገ ወገን የግንኙነት ሁኔታ መኖሩን በሰው ምስክር አሊያም ሌላ ሊያስረዳ ይቻላል የሚለው የሰነድ ማስረጃ ካለ ይህንን በማቅረብ ሊያስረዳ ይችላል፡፡ ማስረዳት የፈለገው ወገን በአሳማኝ ማስረጃ ይህንን ካረጋገጠ በወንዱ እና በሴቷ መካከል ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት የመኖር ግንኙነት አለ ተብሎ የህግ ግምት ይወሰዳል፡፡ ይህንን የህግ ግምት ግን ማንኛውም አይነት አስተማማኝ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ ወይም ግንኙነት እንደሌለ ማስረዳት ይቻላል፡፡
በሶስቱ የጋብቻ ሥርአት አይነቶች ከተፈጸመ ጋብቻ እና ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከመኖር ግንኙነት ውጪ በወንድ እና ሴት መካከል ያሉ ግንኙነቶች በህግ በኩል ምንም አይነት ወጤት አይኖራቸውም፡፡
በታምሩ ያዕቆብ - የህግ አማካሪና ጠበቃ
ጥቅምት 2013 ዓ.ም.
@Ethiopian_Legal_Advocate
https://t.me/Ethiopian_Legal_Advocate