#NewsAlert
የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ተላለፈ !
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።
ውሳኔው ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡
ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ በዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ የቻለው፡፡
ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ 3 ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል። ውሳኔዎቹ ፦
1ኛ. የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡
2ኛ. የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማት እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3ኛ. የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ አሳልፏል። (ኢቲቪ)
via tikvahethiopia

#Share
#Share
ALE (Alternative Legal Education) All in one, All Law Societies. federal & regional Judges, Prosecutors, Advocates, consultants & law school heads, instructors, deans, Law graduates, Students & NGOs .....for discussion @ALE_lawsocieties
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተቋማት ለሚያዘጋጇቸው መመሪያዎች አገር አቀፍ ቁጥር እየሰጠ ነዉ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የመንግስት ተቋማት ለሚያወጧቸዉ መመሪያዎች አገር አቀፍ ብሄራዊ ቁጥር እየሰጠ መሆኑን በተቋሙ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ በላይሁን ይርጋ ገለፁ፡፡
አቶ በላይሁን ባለፈዉ አመት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካወጣቸዉ አዋጆች መካከል አንዱ የአስተዳደር ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 1183/2012 መሆኑን አስታዉሰዉ አዋጁ በዋናነት ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮችን የያዘ መሆኑንና አንደኛዉ የመመሪያ አወጣጥ ስርአት ምን መሆን አለበት የሚለዉን የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የዉሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን የሚመለከት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
መመሪያ አወጣጥ ስርአትን በተመለከተ ካስቀመጣቸዉ የአስተዳደር ስርአቶች ዉስጥ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተለይተዉ የተሰጡ ሀላፊነቶች ሲሆኑ እነዚህም የሚረቀቁ ህጎች ላይ አስተያየት መስጠትና ህጉን ተከትለዉ የወጡ መመሪያዎች ሲኖሩ አገር አቀፍ ቁጥር መስጠት ዋነኞቹ መሆናቸዉን የገለፁት ዳይሬክተር ጀነራሉ በየ ተቋማቱ የሚወጡ መመሪያዎች የአወጣጥ ስርአታቸዉ ግልፅ ስለማይሆንና የፀደቁና ያልፀደቁ መመሪያዎችን እንዲሁም ምን ያህል መመሪያዎች እንዳሉ ለመለየት የህግ ስርአት ያልነበረ በመሆኑ ምክኒያት መመሪያዎች የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጥሩ እንደነበር አዉስተዋል፡፡
መመሪያ በሰዎች መብቶችና ነፃነቶች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ዉጤት እንዳላቸዉ ገልፀዉ በተቋሙ በኩል አዋጁ ከወጣ በኋላ በየተቋማቱ የሚወጡ መመሪያዎች አዋጁን የተከተሉ መሆን እንደሚገባቸዉ ከወጡ በኋላም በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አገር አቀፍ ቁጥር ሊሰጣቸዉ እንደሚገባና በየተቋማት ድረ-ገጽ ላይ መጫን እንዳለባቸዉ አዋጁ የሚደነግግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚሁ መሰረትም ብዙ ተቋማት የሚያወጧቸዉን መመሪያዎች እንዲመዘገብላቸዉ ጥረት ማድረጋቸዉን የገለፁት ዳይሬክተር ጀነራሉ በሀርድ ኮፒ( በወረቀት) እና በፒዲኤፍ የተላኩ መመሪያዎች ላይ ቁጥር መስጠት አስቸጋሪ እንደሆነና አንዳንድ ተቋማት የዉስጥ አሰራር መመሪያዎችን ወደተቋሙ የማምጣት ክፍተቶች መስተዋሉን ገልጸዉ የአስተዳደር ስነ ስርአት ህጉ በዋናነት የሚመለከተዉ ከዉጭ ባለ ጉዳይ ጋር የሚገናኙትን መሆኑንና መመሪያቸዉን ሲያቀርቡም በፅሁፍ ቀይረዉ በሶፍት ኮፒ (word) መሆን እንደሚገባዉ በማሳወቅ እነዚህን ክፍተቶች እንዲያስተካክሉ ለተቋማቱ የማሳወቅ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
አዋጁ ከወጣ በኋላ በርካታ ተቋማት ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጋር እየተነጋገሩ መመሪያዎችን እያዘጋጁ እንደሆነ የገለፁት አቶ በላይሁን እስካሁን የተመዘገቡ መመሪያዎችም በቁጥር 31 መድረሳቸዉንና ለአብነትም በዚህ ሁለት ቀን ዉስጥ የተመዘገቡ ኮቪድ 19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚስችል በኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩትና በጤና ሚኒስቴር የወጣ መመሪያ ቁጥር 30/ 2013 እና በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 31/ 2013ን ጠቅሰዋል፡፡
መመሪያዎችን በማስመዝገብ በኩል አዋጁ ከወጣ በኋላ ያለዉ እንቅስቃሴ መልካም መሆኑን የገለፁት ሀላፊዉ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጁ ከመዉጣቱ በፊት ወጥተው የነበሩትን መመሪያዎች በ90 ቀናት መመዝገብ አለባቸዉ የሚለዉ በአዋጁ የተቀመጠዉ መመሪያ መተግበር ላይ ክፍተት መኖሩንና ተቋማት አዋጁ ከመዉጣቱ በፊት አዉጥተዋቸዉ የነበሩ መመሪያዎችን ልከዉ እንዲያስመዘግቡ በደብዳቤ ማሳወቃቸዉ አስታዉሰዉ ይህ ሳይሆን ቀርቶ መመሪያዎችን ልከዉ የሚያስመዘግቡ ካልሆነ ግን መመሪያዎቹ የህግ ዉጤት እንዳይኖራቸዉ የሚደረጉ መሆኑን ማወቅ እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም መመሪያዎችን እያረቀቁ ያሉ ተቋማት የአስተዳደር ስነ ስርአት ህጉን በጥንቃቄ እንዲያዩትና መመሪያ ሲዘጋጅ መከተል የሚገባዉን መስፈርቶች አይተዉ ማዘጋጀት እንዳለባቸዉ የገለፁት አቶ በላይሁን መስፈርቱ ተሟልቶ ከተገኘና አገር አቀፍ ቁጥር ከተሰጠዉ በኋላ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግና በየተቋማቱ ድረ-ገጾች ተጭኖ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆን እንዳለበት በመግለፅ ይህ መሆኑም በተለይም በዋናነት በተገልጋዩ ማህበረሰብ ዘንድ መልካም አስተዳደርን በማስፈን በኩል የማይተካ ሚና እንዳለዉ አክለዉ ገልፀዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅን እና የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መራ
*****
መስከረም 28፣ 2013
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅን ከመረመረ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ለንግድና ለኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡
ምንጭ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረ-ገጽ
https://t.me/lawsocieties
*****
መስከረም 28፣ 2013
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሕግ ረቂቅ አዋጅን ከመረመረ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ለንግድና ለኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለህግና ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡
ምንጭ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረ-ገጽ
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
የፌደራል ጠቅላይ ዕቃቤ ሕግ
የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection) ሲባል ምን ማለት ነው?
______________________
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው? ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን ተከታተሉን፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡ይህም ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡
በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
• ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
• በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
• ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡በወንጀል ህግ አንቀጽ 219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡
• ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣
• ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
• በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣
• ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡
ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው አስፍሯል፡፡
ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ውድ አንባቢያን ለዛሬ ካዘጋጀንላችሁ ጥንቀር በጉዳዩ ዙሪያ ዕውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ እናደርጋለን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ ተመኝን ሰላም፡፡

መደበኛ ላልሆናችሁ ለሕግ መዉጫ ተፈታኞች በሙሉ የመፈተኛ ክፍያ የሚፈጸመዉ የምትፈተኑበት የፈተና ጣቢያ ወይም ዩኒቨርስቲ መሆኑን አውቃችሁ በግላችሁ በፈተና ኤጀንሲው አካዉንት ማሥገባት ተቀባይነት የሌለዉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን።
መስፍን እሸቱ
https://t.me/lawsocieties
መስፍን እሸቱ
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ሰላም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌስ-ቡክ ገጻችን ተከታታዮች ይህ የናንተን የህግ ግንዛቤ ለማሳደግ በየሳምንቱ አርብ የምናቀርብላችሁ የህግ ማብራሪያ ሲሆን በዛሬው ጽሁፋችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ድርጊት የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበንላችኋል መልካም ንባብ!
1. የማህበራዊ ሚዲያ ጽንሰ ሃሳብና በአገራችን ስላለዉ የአጠቃቀም ሁኔታ
በኢንተርኔት ላይ ከምንጠቀማቸው እጅግ በጣም ዝነኛ ከሆኑ መካነ ድሮች መካከል የማኀበራዊ ሚዲያዎች ይገኙበታል። ፌስቡክ ከቢሊዮን በላይ፣ ኢንስታግራም እና ትዊተር እያንዳንዳቸው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አሏቸው። ማኀበራዊ ሚዲያዎች የተገነቡት የተለያዩ ሃሳቦችን፣ ፎቶግራፎችን እና የግል መረጃን ለማጋራት ነው። ይሁን እንጂ አሁን ላይ አገራችንን ጨምሮ በተለያዩ የአለመ አገራት ዉስጥ ሰዎች እነዚህን ድረገጾች ለታለመላቸዉ በጎ ተግባራት ከማዋል በተቃራኒዉ ለእኩይ ተገባረት ለምሳሌ የጥላቻ ንግግሮችን እና የሃሰት መረጃዎችን ለማሰራጨት ሲጠቀሙት ይሰተዋላል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ኃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሐሰት ወሬዎች በተለይ እንደፌስቡክ ባሉ የማህበራዊ ድረ ገጾች አንድን ቡድን፣ ብሔር የሚያንቆለጳጵሱ፣ የሌላውን ብሔር ዝቅ የሚያደርጉ፣ የሚዘልፉ፣ የሚያዋርዱ ከፋፋይ አጀንዳዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ናቸዉ፡፡
2. የማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ገደብ በኢትዮጵያ
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው በቅርቡ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185 ጸድቆ ስራ ላይ ዉሏል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ዕውቅና ከተሰጣቸው መብቶች አንዱ አንቀጽ 29 ላይ የተደነገገው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ቢሆንም ይህ መብት በሕገ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶችም ጭምር ገደብ የሚጣልበት ነዉ፡፡ በመሆኑም ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተግባራዊ ሲያደርጉ ሰብዓዊ ክብርን፣ የሌሎችን ደኅንነትና ሰላም አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ አዋጅ ስለ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ምንነት እንዲሁም ድረግቶቹን ፈጽሞ የተገኘ ሰዉ ስለሚቀጣዉ የወንጀል ቅጣት እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡
የጥላቻ ንግግር ማለት በአንድ ሰዉ ወይም የተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፡ብሄረሰብንና ህዝብን፣ ሀይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር ሲሆን ንግግሩ በቃል፣ በጽሑፍ፣ በምሥልና ሥዕል፣ በቅርጻ ቅርጽ እና በሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች መልእክትን የማሰራጨት ተግባርን በመጠቀም የተደረገ ሊሆን ይችላል፡፡
በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 4 እና 7(1) መሰረት የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለና ይህን የተከለከለዉን የጥላቻ ንግግር ማድረግ እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት ነዉ፡፡(አንቀጽ 7(2) በሌላ በኩል ደግሞ በአንቀጹ ንሁስ አንቀጽ 4 መሰረት ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱ እስከ ሶስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እና ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይሆናል፡፡
ከጥላቻ ንግግር በተጨማሪ አዋጁ ሃሰተኛ የሆነ መረጃ ማሰራጨትንም በወንጀልንት የከለከለ ሲሆን ሀሰት የሆነና የመረጃውን ሀሰተኝነት በሚያውቅ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን እዉነተኝነት ለማጣራት በቂ ጥረት ሳይደረግ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የሚያነሳሳ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የሚያደርግ እድሉ ከፍ ያለ የሀሰት ንግግር ነው በሚል ትረጉም ተሰጥቶታል፡፡ በአንቀጽ 5 እና 7(3) መሰረት የሐሰት መረጃን በአደባባይ ስብሰባዎች በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለና ይህን ተግባር የፈጸመ ሰዉ እስከ አንድ አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም ከብር 50,000 ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱ እስከ ሶስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እና ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይሆናል፡፡(አንቀጽ 7(4) በሌላ ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ከሆነ፣ ሁከት ወይም ግጭት የተከሰተ እንደሆነ ቅጣቱ ከሁለት እስከ አምስት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት የሚሆን ሲሆን ምንም ጉዳት ካልደረሰ ጥፋተኛውን ለማረም የተሻለ ነው ብሎ ሲያምን ፍርድ ቤት በእስራት ምትክ የግዴታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራን በአማራጭ ቅጣትነት ሊወስን ይችላል።(አንቀጽ 7(5)(6))
ከለይ የተቀመጡት ተጠያቂነቶች እንዳለሆነዉ በአዋጁ አንቀጽ 6 ስር ንግግሩ የሌላ ሰዉ ሆኖ ለትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ጥናት አካል ለማድረግ፤ንግግሩን በተመለከተ የዜና ዘገባ ወይም ትንታኔ ለመስራት ወይም የፖለቲካ ትችት ለመስጠት፤የኪነጥበብ ፣ ትወና ወይም መሰል የስነጥበብ ውጤት በማድረግ ህብረተሰብን ለማስተማር፤ ወይም የሃይማኖት አስተምህሮት አካል እንደሆነ እንዲሁም ንግግሩን ያሰራጨው ወይም ያደረገው ሰው የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱ ሁኔታ ካለ ሰው የሚጠበቀውን ምክንያታዊ ጥረት ያደረገ እንደሆነ እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም የሃሰት መረጃ ስርጭት የማይወሰድ ስለመሆኑ በልዩ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡
3. በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት
በመሆኑም ህብረተሰቡ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃን ማሰራጨት በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ከመረዳት ባለፈ ተግባሩ እጅግ በጣም አስነዋሪና ለሀገር መፈራረስ ምክንያት መሆኑን በመገንዘብ ሃሰብን በነጻነት የመግልጽ መብቱን በአግባቡ መጠቀም አለበት፡፡
በመንግስት በኩልም ለነዚህ የጥላቻ ንግግሮች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃ ስርጭቶች ምክንያት የሆኑትን በህብረተሰቡ መካከል ለተፈጠሩት ቁርሾዎች እና አለመግባባቶች ብሄራዊ መግባበቶችንና እርቆች እንዲፈጸሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም ህጉን በሚጥሱ ግለሰቦች ላይም ተገቢዉን እርምጃ መዉሰድ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ከዚህም ባለፈ ለማህበረሰቡ በተለይም ለወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል በጉዳዩ ላይ ሰፊ የሆነ የ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የመስከረም ወር ዜና መጽሄት ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://drive.google.com/file/d/1T-GuwgtiDzATrqFd2SmVDLVUx1jZnzbe/view?usp=sharing
Share‼️

Celebrating Graduation at Oromia Justice Sector Training and Legal Research Inistitute (Adama) with Tedros Legesse.N, Tewodros Legesse.A, Sintayehu Teshome, Gosa Adugna, Kaleab Dejene........‼️‼️‼️‼️
Congratulation ‼️‼️‼️❤️
via Mebratu Getahun
Congratulation ‼️‼️‼️❤️
via Mebratu Getahun
ድምፁ የማይሰማው የምስኪኑን አርሶ አደር መሰረታዊ ፍላጎት ሲነጠቅ እያየን ዝም ማለት ከሰውነት ተራ መውጣት ነው። ❓❓❓
አንድ አንበጣ ባናባርርለትም አንዴ ሸር አድርገን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለአርሶ አደሩ ድምፅ እንሁን‼️‼️
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
አንድ አንበጣ ባናባርርለትም አንዴ ሸር አድርገን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለአርሶ አደሩ ድምፅ እንሁን‼️‼️
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ የሥነምግባር መርሆዎች ተገዢ ሊሆኑ እንደሚገባ ተገለጸ
******************************************
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታ ሊያተርፉ የሚችሉት ሥራቸውን የዳኝነት የሥነምግባር ደንቡን እና ዓለም አቀፍ የዳኝነት የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት አድርገው ሲያከናውኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተሾሙ 40 ዳኞች እና 10 ረዳት ዳኞች ከመስከረም 26-30 ቀን 2013 ዓ.ም ሲካሔድ የቆየው የሥራ ማስጀመሪያ ሥልጠና ማጠናቀቂያ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት እና በሥልጠናው ላይ በአሠልጣኝነት የተሳተፉት ክቡር አቶ ቀነዓ ቂጣታ በሰጡት አስተያየት ነው፡፡
በፌደራል የፍትሕና የሕግ ምርምር ሥልጠና ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀውና ለአምስት ቀናት የቆየው ሥልጠና በምርጫ ሕግ፣ በተሻሻለው የወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ ረቂቅ እንዲሁም በዳኝነት ሥነምግባር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡
የሥልጠናው ዓላማ ለፍርድ ቤቱ አዲስ የተሾሙ ዳኞች በሥልጠናው ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ቀደም ሲል በነበራቸው የዳኝነት የስራ ልምድ ላይ ተጨማሪ የዳኝነት እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ በሥነምግባር የታነጹ እንዲሆኑ እንዲሁም ተገልጋይን ማዕከል ያደረገ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንዲገነቡ ለማስቻል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ማንኛውም ሙያ የራሱ የሆኑ የሥነምግባር መርሆዎች ያሉት መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ዳኛ ቀንዓ፣ እነዚህ የሥነምግባር መርሆዎች ተዋቅረው የሚቀመጡት በሥነምግባር ደንብ መሆኑን በመግለጽ በተለይ በዳኝነት ሙያ ላይ የተሰማሩ ዳኞች እና ሌሎች ባለሙያዎች የዳኝነት ሙያ ምንድን ነው? ሙያው ምን ይጠይቃል? የሙያው ሥነምግባር ምንድን ነው? በሚሉት ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ በመሆኑ ሥልጠናው በዚህ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አሠልጣኖቹ ሕግ በማርቀቅ ተሳትፎ ያላቸውና በከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት በሕግ መምህርነት የሰሩ እንዲሁም በዳኝነት ሙያ ላይ እየሰሩ የሚገኙ ናቸው፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባከሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በዚህ ሥልጠና ላይ የተሳተፉ 40 የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞችን ሹመት ያፀደቀ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ምንጭ:-ፌ/ጠ/ፍ/ቤት