አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለሁሉም መደበኛ እና ተከታታይ ትምህርት ድጋሚ ተፈታኞች
የህግ መውጫ ፈተና የምዝገባ እና የፈተና ቀናት ስለማሳወቅ

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክኒያት በ2012 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የህግ ት/ቤት መውጫ ፈተና ወደ 2013 ዓ.ም መሸጋገሩ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትወስዱ የምዝገባ ቀን ከመስከረም 20 - ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ፈተናውን በድጋሚ መፈተን የሚፈልጉ ተማሪዎች የነፍስ ወከፍ ክፍያ 664 (ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር) ይዛችሁ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ት/ቤት በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ እንዲሁም ፈተናው የሚሰጥባቸው ቀናት ከህዳር 1-4 2013 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን፣ ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በተለይ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ይህን አውቃችሁ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እስኪያደርግ ሳትዘናጉ ዝግጅታችሁን እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡፡

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ህግ ት/ቤት
Interested in PG studies?
Mekelle University, School of Law invites potential postgraduate students for the 2013 E.C academic year in the following LL.M programs. The registration is online using the Mekelle University website.
1) International Human Rights Law
2) Criminal Law and Criminal Justice
3) Business Law
4) International Economic Law
5) Tax Law
6) Tax and Investment
7) Natural Resource Governance
8) Alternative Dispute Resolution
9) Legal Drafting and Legislative Studies
10) Constitution and Public Laws
For more please contact the School of Law Postgraduate Coordination Office
email፡ abreha.mesele@mu.edu.et
Tele፡0904387801
via Mekonnen Fisseha

https://t.me/lawsocieties
የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብነትን በተመለከተ
በ፡- ገመቹ መረራ

ግምቱ ተለይቶ የሚታወቅ የፍትሐብሔር ክርክር ጉዳይ በመያዝ በፍርድ ቤት ክስ የሚመሰርት ወይም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የሚያቀርብ ማንኛውም ተከራካሪ በፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 215/1 እና ስለ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል በ1945 ዓ/ም በተደነገገው ደንብ መሠረት የዳኝነት ክፍያ ይከፍላል። በዚህ ክሱን በከፈተበት ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ደግሞ የይግባኝ አቤቱታውን ይግባኝ ለመስማት ሥልጣን ወዳለው ፍርድ ቤት ያቀርባል። ይህ የይግባኝ አቤቱታ እንዲሰማለት ደግሞ በሥር ፍርድ ቤት የከፈለውን የዳኝነት ክፍያ 50% መክፈል ይጠበቅበታል። የዚህ አጭር ማስታወሻ ዓላማም የዚህ የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብ የማይሆንበትን ኹኔታ መጠየቅ ነው።

ፍርድ ቤት በተለያዩ ምክንያቶች (በማስረጃ ምዘና፣ በሕግ አተረጓጎምና አተገበባበር ወዘተ) ለተገልጋዩ/ለተከራካሪው ተገቢውን እና ትክክለኛውን አገልግሎት/ውሳኔ ባለመስጠቱ ምክንያት ተከራካሪው ውሳኔውን ለማሳረም የሚያወጣው የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ አግባብነት በሁለት ተከፍሎ ሊታይ ይገባል። ይኸውም፣ ይግባኝ ባዩ በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሻር ከሆነ፣ ቀድሞውኑ ወደ ይግባኝ የሄደው በሥር ፍርድቤቱ ሥህተት ነውና የከፈለው የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ ተመላሽ ሊደረግለት ይገባል። ነገር ግን የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የሚፀና ከሆነ ይግባኝ ባዩ ላገኘው አገልግሎት የዳኝነት ክፍያውን ሊከፍል ይገባል።

ይህ የይግባኝ የዳኝነት ክፍያ ይግባኝ ባይ ጉዳዩ በይግባኝ ከታየለት በኋላ የረታ ወይም የቀድሞው ውሳኔ የተሻረለት ከሆነ የወጪና ኪሣራ ዝርዝር በማቅረብ ከተረቺው ሊጠይቅ ይችላል የሚል መከራከሪያ ሊቀርብ ይችላል። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ የሕጉ አንድምታ እና የሰበር ውሳኔዎች ትርጓሜ ሁል ጊዜ ተረቺ ወጪና ኪሣራ ሊሸፍን ይገባል የሚባለው ከቅን ልቦና ውጪ ሌላኛውን ተከራካሪ ለወጪ የዳረገ ተከራካሪ ካለ ብቻ ነው እንጂ በሁሉም ጉዳዮች ወጪና ኪሣራ ይሸፍናል ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል። ከዚህ ባለፈም አሁን አሁን በሰፊው እየተለመደ የመጣው «ግራ ቀኙ ወጪያቸውን ይቻሉ» የሚል ትዕዛዝ ይህ እንዳይቻል ያደርጋል።

በመሆኑም፣ ይህ ሀሳብ ቢተገበር ሁለት ጥቅም አለው። አንደኛው ጥቅም አንድ ተከራካሪ ያለጥፋቱ በሥር ፍርድ ቤት በተሰራበት ስህተት በይግባኝ መንገላታቱ ሳያንስ ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረግ የሚያድነው መሆኑ ነው። ከላይ እንደገለፅነው የውሳኔው በይግባኝ መሻር የሚያመላክተው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሥህተት መሆኑን ነው። ሁለተኛው እና ዋነኛው ጥቅም ግን መንግሥት እንደማንኛውም ግለሰብ እና አገልግሎት ሰጪ ሁሉ ራሱ በዘረጋው አሰራር ከገዛ ራሱ ሥህተት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የለበትም የሚለውን መሠረታዊ የፍትሐዊነት ዕሳቤን በመተርጎም የፍትሕ ተደራሽነትን ማጎልበት ነው።

በአጭሩ የዚህች አጭር ማስታወሻ ድምዳሜ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ታይቶ የተሻረ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተከፈለ የዳኝነት ክፍያ ለይግባኝ ባዩ ተመላሽ ሊሆን ይገባል የሚል ነው፤ ምክንያቱም ለዚህ ወጪ የተዳረገው በሥር ፍርድ ቤቱ ሥህተት ነውና።

በጽሑፉ ላይ ያለዎትን አስተያየት ያካፍሉን፤
via Abyssinia Law
Dear Colleagues, 

May this email finds you well and safe. 


This is Mussie, Head of School of Law, from Ethiopian Civil Service University. I kindly invite you and your colleagues in your schools to contribute, up to October 31, 2020, to our newly launched Ethiopian Journal of Legal Studies. The Journal has well-prepared bylaw, policy, and guidelines as well as leading legal scholars as members of its editorial board and international advisory board, both from Ethiopia and abroad. The subject matters of the Journal are generally related to International Law, Comparative Constitutional and Public Law, Federalism Studies, Criminal Law and Justice, and Comparative Business Law, which reflects the five Programs of the School of Law. 


For more information, please see the attached call for paper and kindly share it with your respective law community at your university.  


With best regards, 

___________________________________________________
ETHIOPIA’S COOPERATION WITH OTHER STATES IN THE EXTRADITION OF CRIMINALS: A NORMATIVE AND INSTITUTIONAL ANALYSIS

BY - Meseret Tadese Asrat

This research finds out the normative and practical status of the extradition tool as one form of international cooperation in criminal matters within the Ethiopian context. Furthermore, it examines the work of various national institutions in relation to extradition and those which are involved in the process of implementation, the gaps that exist within the field and tries to substantiate arguments through a legal and factual analysis.

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1958-ethiopia-s-cooperation-with-other-states-in-the-extradition-of-criminals-a-normative-and-institutional-analysis
ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት የሚሰጠው ትዕዛዝ እና አፈጻጸም!
-------------------------------------------------

በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ትዕዛዝ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስትና በሌሎች ህጎችም ጭምር የተረጋገጠ መብት ቢሆንም ትዕዛዙ ሳይፈጸም ሊቆይ የሚችሉበት በሕግ የተደገፉ ምክንያቶች አሉ፡፡

ሰላም የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ ዛሬ የፍርድ ቤት ትእዛዝና አፈፃፀሙን በተመለከተ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዋስትና ተፈቅዶላቸዉ የሚለቀቁበትንና ተጠርጣሪዎች ሳይለቀቁ የሚቆዩበትን አግባብ ህጋዊ ማዕቀፉን መሰረት አድርገን በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጉደታ ቀንዓን አናግረን ያዘጋጀንላችሁን ፅሁፍ ወደ እናንተ ልናደርስ ወደናል መልካም ንባብ! ከሦስቱ የመንግስት አካላት ወይም ክፍሎች መካከል አንዱ የዳኝነት አካል ነው፡፡

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 78 (1) መሰረት የተቋቋሙት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ የዚሁ ህግ አንቀጽ 79 (1) በግልጽ ደንግጎታል፡፡
ፍርድ ቤቶች በዚሁ የዳኝነት ስልጣናቸው አለመግባባቶች በስምምነት ካልተፈቱ ወይም የወንጀል ጉዳይ ክስ ሲቀርብለት ተከራካሪ ወገኖችን በማከራከር መፍትሔ/ውሳኔ የሚሰጡ ሲሆን በፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮችም የፍታብሔር ወይም የወንጀል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ፍርድ ቤት በክርክር ሂደት ዉስጥ ለዉሳኔ አሰጣጥ እንዲመቸዉ የተለያዩ ትዕዛዞችን ይሰጣል፡፡ ትዕዛዞቹ አንድ ሰው ወይም አካል የተጠቀሰውን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም የሚሰጥ አቅጣጫ ሲሆን እነዚህ ትዕዛዛት ተከሳሽ፣ ከሳሽ፣ ምስክር ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ መስጠት፣ የእግድ ትዕዛዝ (ንብረት፣ የሰው እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል፣ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ ወይም ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበዉ እንዲያስረዱ፣ የመያዣ ወይም የመልቀቂያ ትዕዛዝ፣ የአፈፃፀም ትዕዛዝ እና ሌላ ለክስ መስማት ሂደት የሚያስፈልግ ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት ይፈፀማል የሚለዉን ጉዳይ ስንመለከትም ትዕዛዙ በራሱ በፍርድ ቤት ወይም በተከራካሪ ወገኖች ወይም በፖሊስ ትዕዛዙን ለሚፈጽመው ሰው ወይም አካል ሊደርስ ይችላል፡፡ ትዕዛዙ በፍቃደኝነት ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሆኖም በፍቃደኝነት ካልተፈፀመ በማስገደድ (የአስፈፃሚ አካል/ፖሊስ እገዛ በመጠየቅ) የሚፈፀም ይሆናል፡፡

ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ትዕዛዛት ባልተከበሩበት ሁኔታ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ሁሉም አካላት ትዕዛዛቱን የማክበር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በፍርድ ቤት የተሰጠን ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ አለመፈፀም የፍትሐ ብሔር እና/ወይም የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማክበር ለህግ ተገዥነትን ወይም በህግ የበላይነት ማመንን የሚያሳይ ነው፡፡ በተጨማሪም የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማክበር ህብረተሰቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
በተቃራኒው የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አለማክበር የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር እና ህገ-ወጥንት የሚያስፋፋ በመሆኑ ያለ በቂ ምክንያት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አለማከበር በፍትሐ ብሔርና ወንጀል ህጎች ሥነ-ሥርዓት ላይ የተቀመጡ የትዕዛዝ አለማከበር ውጤቶች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለአብነት በማስገደድ ማስፈፀም፣ የእስር እርምጃ (ፍ/ስ/ስ/ህግ ቁ. 389 እንደተቀመጠው) በተለይ በችሎት ጉዳዮች ላይ አለመታዘዝ በፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ሊያስቀጣ ይችላል፡፡

በተጨማሪም በወንጀል ሕግ ላይ የተቀመጡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አለመፈጸምን የሚመለከቱ የወንጀል ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂነትን ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሁንና ተጠርጣሪው የተጠረጠረበት ወንጀል በዋስትና መለቀቅን የማያስፈቅድ ሲሆን ወይም በሌላ በሥነ-ሥርዓት ህጉ በተቀመጡት ምክንያቶች ተጠርጣሪው በዋስትና ከሚለቀቅ በእስር ላይ መቆየቱ ፍትሃዊ ውሳኔ ለማሰጠት የሚረዳ (በቀጣይ ላይቀርብ የሚችል አይነት ሲሆን፣ ወይም ማስረጃ የሚያጠፋ፣ ሌላ ወንጀል ሊፈጽም የሚችል እንደሆነ) ከነኚህ እና ሌሎች ምክንያቶች አንጻር የተጠርጣሪው በዋስትና መለቀቅ ላይ ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ህግ ቅሬታ ያለው እንደሆነ ይግባኙን ጉዳዩን ቀጥሎ ላለው ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ፍርድ ቤቱም ይግባኝ ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ ተገቢ መሆኑን ሲያምን አከራክሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በስር ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረው ትዓዛዝ ሳይፈጸም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ የሆነ እንደሆነ የዋስትና መብቱ ተጠብቆለት የነበረው ተጠርጣሪ በእስር ላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይሁንና ይግባኙን የመረመረው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካጸና ተጠርጣሪው ወዲያውኑ ሊለቀቅ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲለቀቅ የፈቀደለት ተጠርጣሪ በሌላ የወንጀል ጉዳይ የሚፈለግ ወይም በሌላ ወንጀል የተጠረጠረ ከሆነ በማቆያ እንዳለ ሊቆይ ይችላል፡፡

በዚህ ምክንያት በአንድ ወንጀል ተጠርጥሮ የዋስትና መብት ከተፈቀደለት በኋላ ተጠርጣሪው ሳይለቀቅ በመቅረቱ ምክንያት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልተከበረም ሊያስብል አይችልም፡፡ ይሁንና በዚህ ምክንያት በእጁ ያቆየው ፖሊስ ስለ ተጠርጣሪው አቆያየት ትዕዛዝ ለማሰጠት ፍርድ ቤት ሊያቀርበው የሚገባ ስለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከነዚህ ምክንያቶች ውጭ የዋስትና መብቱ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠብቆለት እያለ ትዕዛዙን በመጣስ ተጠርጣሪው በእስር ላይ እንዲቆይ ያደረገ ማንኛውም ሰው ከተጠያቂነት የሚድን አይሆንም፡፡

ስለሆነም ህብረተሰቡ ሊያዉቀዉ የሚገባው ጉዳይ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ የሰጠበት ሰዉ ሕጋዊ በሆኑ ሌሎች ምክንያቶች መሰረት በእስር እንዲቆይ የሚደረግበት ሁኔታ እንዳለ እና ከዚህ ባለፈ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ማጣራት እና በዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተሰጥቶላቸው ያልተለቀቁ ሰዎች በእስር ላይ የቆዩበት ምክንያት ከላይ ከተነሱት ምክንያቶች አንጻር በተገቢው ታይተው እንደሆነ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መንገድ ያለ አግባብ ታስሮ ያለ ሰው ካለ ነባራዊ ሁኔታዎች ቦታዉ ላይ በመገኘት ጉዳዩን ማየትና መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ለአንድ አገር የፍትህ ስርዓት መጎልበት ሕግን አክብሮ መንቀሳቀስ ተገቢ ሲሆን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲኖር ሕጉ በሚፈቅደዉ መሰረት ሕጋዊ እስከሆነ ድረስ መመራት እንደሚያስፈልግና ይህንን አለማድረግ ግን ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን አዉቆ ህጉ በሚፈቅደዉ መሰረት መሰራት አለበት የእንግዳችን መልእክት ነዉ፡፡
Via Federal General Attorney
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties