አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ዛሬ ታኅሣሥ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ስብሰባው ተሻሽሎ በቀረበለት የሽብር ወንጀል የመከላከልና መቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየበት በኃላ በመጨረሻም በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጅ 1176/2012 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ ይህንን ህግ በማዘጋጀት የጎላ ሚና ለነበራቸውን ለየህግና ፍትህ ሪፎርም አማካሪ ምክር ቤት እና የሰራ ቡድኑን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ አጋጣሚ የላቀ ምስጋና ያቀረባል ፡፡
ልዩ የውክልና ስልጣን

በተወካዩ የሚፈጸሙ ተግባራትን እያንዳንዳቸውን በግልፅ የሚያመለክት የውክልና ስልጣን

የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፣ የመለወጥና የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ተወካይ ንብረት በመያዣ አስያዞ በወካዩ ስም ከባንክ የመበደር ስልጣን አለው፡፡
የውክልና ማስረጃ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ በውክልና ማስረጃው ላይ ከተጻፉት ተግባራት በተጨማሪ በውክልና ማስረጃው የተገለፁትን ጉዳዮችና እንደ ጉዳዩ ክብደትና እንደ ልምድ አሰራር በውክልና ማስረጃው የተገለጹትን ጉዳዮች ተከታታይና ተመሣሣይ የሆኑ አስፈላጊ ተግባራትን የመፈፀም ስልጣንን የሚያካትት መሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2206 ንዑስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም በውክልና ማስረጃ ቤት የመሸጥ፣ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ እንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታ እንዳለው “ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንዱን የማይንቀሣቀሥ ንብረትን በእዳ መያዣነት አድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው” ከሚለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3049 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 17320 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 2026/1/፣ 3049/2/

ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራ በቀር ሌላ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዲኖረው አስፈላጊ መሆኑንና ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በቀር የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ለመሸጥ ወይም አስይዞ ለመበደር የማይችል መሆኑ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ንዑስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል፡፡
በወካዩ ስም የሚዘዋወር ንብረት ማናቸውንም ፎርማሊቲ እያሟላ እንዲያዛውር፣ በስሙ እንዲዋዋል የውክልና ስልጣን የተሰጠው ተወካይ በወካዩ ስም የሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ የመለወጥ ስልጣን የለውም፡፡
በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 መሠረት የሚሰጥ ልዩ ውክልና በይዘቱ በልዩ ውክልና የሚፈፀሙ እያንዳንዳቸውን ተግባሮች በግልፅ የሚያመለክት መሆን ይገባዋል፡፡
የውክልና ስልጣን የሚተረጎመው ሳይስፋፋ በጠባቡ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 50985 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2204፣ 2205፣ 2181/3/

የውክልና ሰነዱ ይዘት በግልፅ ውክልና ተቀባዩ የተሰጠው ስልጣን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ስለመሆኑ እየገለፀ ስለልዩ ውክልና አስፈላጊነት የተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2205 በውክልና ስልጣን ሰነዱ ያለመጠቀሱ ውክልናው ልዩ የውክልና ስልጣን አይደለም ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ስለመሆኑ የሚያሳይ የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡ ዋናውና ቁልፉ ነገር ለውክልና ተቀባዩ የተሰጡት ተግባሮች በዝርዝርና ግልጽ ሁኔታ ተጠቅሰው በውክልና ሰነዱ ላይ መገኘት እንጂ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያለመጠቀሳቸው አይደለም፡፡ የሰነዱ ይዘት ግልጽ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በውክልና ስልጣን ሰጪውና በውክልና ስልጣን ተቀባዩ አልተጠቀሱም ተብሎ ሰነዱ ዋጋ እንዲያጣ ማድረግ የተዋዋዮችን ሐሳብ ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በውል አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው የሚሆነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 72337 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2199፣ 2055
የሥራ ውልን በስምምነት ስለማቋረጥ

አሠሪውና ሠራተኛው በስምምነት ያደረጉትን የሥራ ውል በማንኛውም ጊዜ በስምምነት ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን የሥራ ውል የተለየ ፎርም ባያስፈልገውም ለማቋረጥ የሚደረገው ስምምነት በጽሐፍ ካልሆነ አይፀናም፡፡a በጽሑፍ ሲባል ውሉን ለማቋረጥ ግራ ቀኙ ያላቸውን ሀሳብ በፊርማቸው ያረጋጡበት ሰነድ ሊኖር እንደሚገባ ያስገነዝበናል፡፡ ስለሆነም ሠራተኛው የተለያዩ ክፍያዎችን ተቀብሎ መሄዱ የሥራ ውሉን በስምምነት የማቋረጥ ውጤት አይኖረውም፡፡ በሰ/መ/ቁ 37575(አመልካች ቃሊቲ ባሌስትራ ማምረቻ እና ተጠሪ ብርሃኑ ልደት ወልዴ ህዳር 2 ቀን 2001 ዓ.ም ቅጽ 8) ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ሲሰራ ቆይቶ የአገልግሎትና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ተቀብሎ ከሄደ በኋላ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራ እንዲመለስ ካልሆነም ክፍያ እንዲፈፀምለት በመጠየቅ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት አግኝቶ የሥራ ውሉ ከህግ ውጭ እንደተቋረጠ በስር ፍ/ቤቶች የተወሰነ ሲሆን ጉዳዩን በሰበር ያየው የሰበር ችሎትም “በስምምነት የሚጠበቅበኝን ክፍያ ፈጽሜ አሰናብቸዋለሁ” በማለት በአመልካች በኩል የቀረበውን ክርክር የሥራ ውል በስምምነት የሚቋረጠው ስምምነቱ በጽሑፍ ሲደረግ እንደሆነ በመግለፅ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡
The law applicable to foreigners in Ethiopia-Summary of the legal provisions (Part I)
by Abrham Yohannes
The law applicable to foreigners in Ethiopia-Summary of the legal provisions (Part I) This Article is neither a commentary nor an analysis of the legal regime governing the rights and duties of foreigners in Ethiopia. Rather, it is a summary of the legal provisions directly or indirectly related to foreigners in Ethiopia so as to […]
https://chilot.blog/2013/01/the-law-applicable-to-foreigners-in-ethiopia-summary-of-the-legal-provisions-part-i/
አለሕግAleHig ️
https://chilot.blog/2013/02/effect-of-formalities-on-the-enforcement-of-insurance-contracts-in-ethiopia/
Effect of Formalities on the Enforcement of Insurance Contracts in Ethiopia

Fekadu Petros

(LL.B, LL.M; Arbitration Tribunal Manager, Ethiopia Commodity Exchange; Part-time Lecturer at AAU Faculty of Law)

Introduction

The problems addressed in this article are related to the functions, purposes, and effects of non-observance of legal formalities in contracts of insurance in Ethiopia. Failure to meet the formality requirements provided in the law entails nullity of a contract. However, this paper attempts to explore and examine the various perspectives of this proposition with regard to insurance contracts. To this end, the writer has reviewed literature, conducted extensive interviews and analyzed cases.

The first section deals with formalities in Ethiopian contract law in general, and makes a general overview in respect of all types of formal contracts. It attempts to show the broad social and institutional purposes and justifications of formalities beyond narrower immediate effects viewed in the context of individual cases and present needs. The last two sections are devoted to analysis of insurance formalities both in the law and in the practice.
https://telegram.me/lawsocieties

PROCLAMATION No. 807/2013

@lawsocieties

PROCLAMATION TO AMEND THE CAPITAL GOODS LEASING BUSINESS PROCLAMATION

@lawsocieties

WHEREAS, it has became necessary to amend the Capital Goods Leasing Business Proclamation No.103/ 1998;

NOW, THEREFORE, in accordance with Article55 (1) of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby proclaimed as follows:

1. Short Title

This Proclamation may be cited as the “Capital Goods Leasing Business (Amendment) Proclamation No. 807/2013”.

2. Amendment

The Capital Goods Leasing Business Proclamation No. 103/ 1998 is hereby amended as follows:

@lawsocieties

DOWNLOAD FULL TEXT
https://chilot.blog/2013/10/capital-goods-leasing-business-amendment-proclamation-no-8072013/

Following the issuance of the new amendment the National Bank of Ethiopia has issued two directives for its implementation.

Clink the links below to download. https://chilot.blog/2013/10/capital-goods-leasing-business-amendment-proclamation-no-8072013/

LICENSING AND SUPERVISION OF THE BUSINESS OF CAPITAL GOODS FINANCE COMPANIES

Requirements for Licensing of Capital Goods Finance Business Directives No. CGFB /02/ 2013    DOWNLOAD

https://chilot.blog/2013/10/capital-goods-leasing-business-amendment-proclamation-no-8072013/

LICENSING AND SUPERVISION OF THE BUSINESS OF CAPITAL GOODS FINANCE COMPANIES

Minimum Paid Up Capital Requirement Directives No.CGFB /01/ 2013      DOWNLOAD

https://chilot.blog/2013/10/capital-goods-leasing-business-amendment-proclamation-no-8072013/
መልካም እሁድ።
rozi:
any one who have volume 23 cas decision
When life seems hopeless, rearrange things for a dose of dopeness.

The truth is, unless you let go, unless you forgive yourself, unless you forgive the situation, unless you realize that the situation is over, you cannot move forward.
No matter how much we want things to stay the same, life is all about change. Sometimes change is for the better, and sometimes it’s not.
But no matter why things are changing, we need to be able to let go and move on. Whether it’s the death of a loved one, a painful breakup, a business failure, or a treacherous betrayal, holding onto pass pain and resentment will only hold you back.
Some of us think holding on makes us strong, but sometimes it is letting go. You don’t need strength to let go of something. What you really need is understanding. You’ve gotta know when it’s time to turn the page. Life moves on and so should we. Letting go does not mean you stop caring. It means you stop trying to force others to.
I think that the power is the principle. The principle of moving forward, as though you have the confidence to move forward, eventually gives you confidence when you look back and see what you’ve done
Via Christina Mishell
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
Vol 23.pdf
3.8 MB
sisay:
Sisay WKU
አንድ የሕግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ
ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች።
በዚህም የሕግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት
ዓይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች።
አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች። በዚህን
ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው።
ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ ...
"ያለህን ገንዘብ፣ የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ
ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰክብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ
ላሉት ሁሉ በመንገር እጮሃለሁ" አለችው።
የሕግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና
እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ጻፈላት ...
"ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ
ወረቀት ላይ ጻፊልኝ።
"ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።
የሕግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ
ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው
"አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"
***
የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም
አስፈላጊ ነው።
Forwarded from ሕግ ቤት
ለሕግ ትምህርት ቤት ዲኖች በሙሉ

ጉዳዩ፡-  ትብብር ስለመጠየቅ

የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ሕብረት ከጥር8-9/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አመታዊ ስብሰባውን  እና አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መምረጥ በማስፈለጉ የፍትሕና የሕግ ምርምርና ስልጠናን ኢንስቲትዩትን የጠየቁና የተፈቀደላቸው በመሆኑ ሁሉም የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳንት እና አንድ የሴት ተወካይ እያንዳንዱ ዩንቨርስቲ ሁለት ተወካዮች እንዲሳተፉ ተፈልጓል፡፡

ስለዚህም የህግ ትምህርት ቤት ዲኖች ተማሪዎቹ ስብሰባውን እንዲካፈሉ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግና መሳተፍ መቻላቸውን እስከ ጥር 2 /2012 ዓ.ም ድረስ በተጠቀሰው ኢሜይል አድራሻ mikiasmelak@gmail.com
Or
mesfinjlsri@gmail.com
 እንድታረጋግጡልን እየጠየቅን መሳተፋቸውን በቀነ ገደቡ ያላሰወቁንን ማሳተፍ የማንችል መሆናችንን ከወዲሁ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

 

መስፍን እሸቱ   

https://telegram.me/EthiopianLawStudentsUnion