አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ያቀረባቸውን የቃል ምስክሮች በዛሬው ዕለት ማዳመጥ ጀምሯል።

ፍርድ ቤቱ ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ አሉኝ ያላቸውን የቃል ምስክሮች ከግንቦት 21 ጀምሮ እንዲያሠማ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህ መሰረትም በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው የቃል ምስክሮች በሁለቱ ተከሳሾች ላይ መስክረዋል።

Via #fbc
የአልኮል መጠጦችን በቴሌቪዥን፤ በሬዲዮ እና በግዙፍ የአደባባይ ሠሌዳዎች ማስተዋወቅን የሚከለክለው «የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ» ከዛሬ ግንቦት 21 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚኾን የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዐስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በግዙፍ ሠሌዳዎች ላይ በአደባባይ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ክልከላውን በማናቸውም መንገድ የሚተላለፉ አካላት ካሉ ኅብረተሰቡ በ«8482» ላይ ደውሎ እንዲጠቊም ሚንሥትር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል። የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ፌስቡክ ገጽ ላይም ጥቆማ ማድረግ እንደሚቻል የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዶክተር አሚር አማን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

አንዳንድ የግል መገናኛ አውታሮች ከማስታወቂያ የሚያገኙት ገቢ እጅግ የሚቀንስ በመኾኑ የሠራተኛ ቅነሳ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገልጠዋል።

Via #DW
ፎቶ፦ የጤና ጥበቃ ሚንሥቴር ዶ/ር አሚር አማን ትዊተር ገጽ
የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ዋቁማ ጡሪ እንዳስታወቁት በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ ውስጥ በምትኖረው ተከሳሽ ወይዘሮ እልፍነሽ በቀለ ጅራታ ላይውሳኔው የተላለፈው ባሏን አቶ አዳነ አሰፋውን በመርዝ መግደሏ በመረጋገጡ ነው።

ሟች ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከተበደሩት 86ሺህ ብር ውስጥ 10ሺህ ብር እንዲሰጣት ጠይቃ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ቂም ይዛ መርዝና አይብ በማደባለቅ መጋቢት 01/2011ዓ.ም ከምሽቱ በግምት አራት ሰዓት አካባቢ እንዲመገብ አድርጋለች።

ወደ መኝታ ክፍል እንደገባም በሩን በውጭ በኩል ዘግታ መሞቱን ካረጋገጠች በኋላ ራሱን በራሱ የገደለ ለማስመሰል ’’ፀፀት’’ ተብሎ የተፃፈና ሁለት ገጽ ያለው ወረቀት በደረቱ ላይ አስቀምጣ መኖሪያ ቤቱን በመዝጋት ንብረት ስታሸሽ መያዟን አመልክተዋል።

የተከሳሿ ድርጊት በዞኑ ዓቃቤ ሕግየሕግ ምሥክሮች በመረጋገጡ፣ ራሷም የፈጸመችውን ድርጊት ማመኗንና የመከላከያ ማስረጃም የለኝም ማለቷን አቶ ዋቁማ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግንቦት 21/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ ሆን ብላ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት ተዘጋጅታ የፈጸመችው ድርጊት በመሆኑ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

Via #ENA
Yabsra M.:
Human right record yalachew tebaberugn!

Degmo ewedachwalew
@lawsocieties @lawsocieties
በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ሲቂ ማሪያም አካባቢ የአስገድዶ #መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ #በእስራት ተቀጣ፡፡

የክሱ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ጫኔ ተሾመ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 620/2/ሀ/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ለአካለ መጠን ያልደረሰች የባለቤቱን እህት በቢላዋ እገልሻለሁ በማለት አስፈራርቶ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ዐቃቤ ሕግ የግል ተበዳይን ጉዳት የሚያስረዳ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተከሳሹ በሰራው ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 09 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡን መርመሮ ተከሳሹ ምንም አይነት ወንጀል ሰርቶ እንደማያውቅና የቤተሰብ አስተዳደሪ መሆኑን በማቅለያነት በመያዝ ተከሳሹን ያርማል በማለት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@lawsocieties @lawsocieties
Helo i'm mahder 3rd year student from aksum university......can i get procedure exist exam of this year?
Abdella Jewaro:
I want property law shortnote
Abdella Jewaro:
please dear group mates could l got supreme court cessation decision benches on possession which is changed into English version from volume 16_22(I want only one or two cases). thanks
Walelign Wondie:
please send short note on the difference between OAU and un
mele መሌ:
Share 'Evidence Code.doc'
Ëštíph:
Selam ye ale beteseb ebakachu sample yetesera legslativ drafting workers code of conduct kale
Lily Zewdie:
marital rape is a very necessary agenda that the law making organ should take in to consideration. but i believe that it could be abused by the spouses and easily used as a tool of revenge. also it will make the evidentiary system difficult, hence it is a domestic violence. what do u all think?
Mekdi:
conflict of law party autonomy material felge neber share argugh.
#ማስታወቂያ ለፍሪ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አምስተርዳም የLLM ድግሪ ተማሪዎች በሙሉ
______________________

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፍሪ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አምስተርዳም ትብብር እየተሰጠ ባለው በህግ የሁለተኛ ድግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር ትምህርታችሁን እየተከታተላችሁ የምትገኙ ተማሪዎች የመጀመርያው ኮርስ ፈተና የሚሰጠው ትምህርት ከጀመረበት ቀን አንስቶ በ10ኛ ሳምንት ላይ መሆኑን ገልጸን እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁንና በተለያዩ ክልሎች በመስክ ስራ ያሉ የመርሃ-ግብሩ ተማሪዎችን ሁኔታ ከግምት በማስገባት ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ እንዲፈቀድ ዩኒቨርሲቲው ተጠይቆ ምላሹን ልኮልናል፡፡

በዚሁም መሰረት ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ቅዳሜ ጁን 29 / 2019 GC ወይም ሰኔ 22 ቀን 2011 ዓ/ም መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ተብላችኋል፡፡

መረጃውን Share በማድረግ ሁሉም ተማሪ ጋር እንዲደርስ ትብብር ያድርጉ
GEDA .B GUMi:
Hello ALEs family I am from haramaya university college of law . I wann to have journal article on divorce
Kefe Tadesse:
Any one who have note on criminal procedure
Could you send me.Statment of claim and statement of defence examples.
@lawsocieties @lawsocieties

🛑የአልኮል ማስታወቂያዎችን ማሰራጨት፣ የትንባሆና የሺሻ ምርቶችን ማዘዋወር፣ መሸጥና ማስጠቀም እስከ 2 መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል።🔴

የአልኮል ማስታወቂያዎችና በተከለከሉ የትንባሆና የሺሻ ምርቶች ዝውውርና ሽያጭ ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ህብረተሰቡ እንዲያግዝ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጠየቀ።

የባለስልጣኑ የሕግ አማካሪ አቶ ደረጄ ሽመልስ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 60 ንዑስ አንቀጽ አራት እና አምስት፣ እንዲሁም በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ አምስት ላይ ስለ ቁጥጥሩ የተቀመጡ የተለያዩ ድንጋጌዎች አሉ።

ለተፈፃሚነቱም ባለስልጣኑ ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከደንብ ማስከበር፣ ከክልሎች፣ ከከተማ መስተዳደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥር ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።

በአዋጁ አንቀጽ 60 ንዑስ አንቀጽ አራትና አምስት “ማንኛውንም የአልኮል ምርት በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የተከለከለ መሆኑንና የአልኮል መጠጥን ከሎተሪ ዕጣ ወይም ከሽልማት ጋር በማንኛውም መንገድ በማያያዝ ወይም አልኮልን በቢልቦርድ የማስተዋወቅ ተግባር መከልከሉን” አስረድተዋል።

በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ አምስት ደግሞ የሺሻን ምርት ማምረት፣ ወደ ሀገር ማስገባት፣ ማከፋፈል፣ ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ የተከለከለ ነው።
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
ሺሻንም ሆነ ማንኛውንም ዓይነት የትምባሆ ምርት ለማስጨስ ወይም ለማስጠቀም የሚዘጋጅ የንግድ ሥራ መገደቡንም አቶ ደረጄ ገልፀዋል።

ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከደንብ ማስከበር፣ ከክልሎች፣ ከከተማ መስተዳደሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተወጣጣ ግብረ ሃይል በማቋቋም አዋጁን ተፈጻሚ የማድረግ ሥራ እንደተጀመረም ነው የገለፁት።

ሕጉን የማስከበሩ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የተናገሩት የሕግ አማካሪው ኅብረተሰቡ በድርጊቱ ባለመሳተፍ እና የሺሻ ምርት የሚያመርቱ፣ ወደ ሀገር የሚያስገቡ፣ የሚያከፋሉ፣ ለሽያጭ የሚያቀርቡ ወይም ሺሻንም ሆነ ማንኛውንም ዓይነት የትምባሆ ምርት የሚያስጨሱ አካላትን በነፃ የስልክ መስመር 84 82 ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
🛑🛑🛑🛑🛑
አዋጁ በክፍል ስምንት አንቀጽ 65 ንዑስ አንቀጽ 23 ላይ “ማንኛውም ሰው የተከለከለ ይዘት ያለው ትምባሆ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ የገባን ምርት ሺሻን ወይም የኤሌክትሮኒክ ኒኮቲን መስጫ መሳሪያን ወይም ሌላ ከሲጋራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ለኒኮቲን መስጫ የሚያገለግል የቴክኖሎጂ ምርት ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያከፋፈለ፣ ያከማቸ ወይም የሸጠ እንደሆነ ከሦስት ወር እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር 1 ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ይቀጣል" ሲል ያትታል።

በዚሁ አዋጅ 1112/2011 ማንኛውንም የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት ማስተዋወቅም ሆነ በቢልቦርድ የአልኮል ማስተዎቂያን መስቀል ከግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ መከልከሉን መዘገባችን ይታወሳል።🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties