አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የአልኮል መጠጦችን በቴሌቪዥን፤ በሬዲዮ እና በግዙፍ የአደባባይ ሠሌዳዎች ማስተዋወቅን የሚከለክለው «የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ» ከዛሬ ግንቦት 21 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚኾን የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዐስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በግዙፍ ሠሌዳዎች ላይ በአደባባይ የተሰቀሉ የአልኮል ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ክልከላውን በማናቸውም መንገድ የሚተላለፉ አካላት ካሉ ኅብረተሰቡ በ«8482» ላይ ደውሎ እንዲጠቊም ሚንሥትር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል። የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ፌስቡክ ገጽ ላይም ጥቆማ ማድረግ እንደሚቻል የጤና ጥበቃ ሚንሥትር ዶክተር አሚር አማን በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

አንዳንድ የግል መገናኛ አውታሮች ከማስታወቂያ የሚያገኙት ገቢ እጅግ የሚቀንስ በመኾኑ የሠራተኛ ቅነሳ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ገልጠዋል።

Via #DW
ፎቶ፦ የጤና ጥበቃ ሚንሥቴር ዶ/ር አሚር አማን ትዊተር ገጽ