አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#Tigray

ዛሬ በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ምንድን ነው የተከሰተው ? 

እንስት ዘውዱ ሃፍቱ ከሁለት ዓመት በፊት በግፍ ከተገደሉት ሴቶች አንድዋ ናት።

የሟችዋ ጉዳይ በፓሊስ ተጣርቶ መዝገቡ ወደ ፍርድ ደርሶ ለሁለት ዓመት ያህል ውሳኔ ሳያገኝ በይዋል ይደር ረጅም ጊዜ መውሰዱ የተበዳይዋ ቤተሰብና የፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ በእንዲህ አንዳለ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በፊት የመጨረሻው ውሳኔ ለመስጠት ችሎት ይቀመጣል።

ፍርድ ቤቱ በግድያ ወንጀሉ በተጠረጠሩት ላይ የመጨረሻ ያለውን የጥፋተኝነት የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል።

ይህንን ተከትሎ ችሎቱ በሚከናወንበት አዳራሽ የነበሩት ብዛት ያላቸው የተጠርጣሪ ወገኖች ጠረጴዛ በመደብደብና የተለያዩ ድምፆች በማሰማት ረብሻ ይጀምራሉ።

ከረብሻ በዘለለ ዳኞቹን " እናንተም  እንደመስሳቹሃለን ፤ ቀናችሁን ጠብቁ " የሚሉ የስድብ ናዳና ዛቻ ያወርዳሉ።

በችሎት አዳራሹ በቂ የሆነ ስርዓት አስከባሪ ባለመኖሩና ዳኞቹ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እና አስፈሪ በመሆኑ ምክንያት ውሳኔውን ሳይቋጩ ለግንቦት 18/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥተዋል።

የችሎት መድፈር ተግባሩ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ሰፊ መነጋገሪ ሆኖዋል።

ጠበቃ ሚኪኤለ ፍስሃ የተባሉ የሟች ጠበቃ " በፍርሃት ስራዬን አላቋርጥም፤ የተበዳይን እንባ ለማበስ ነገም ዛሬም እሰራለሁ " ሲሉ በማህበራዊ ሚድያ የትሰስር ገጻቸው ላይ ሀሳባቸውን አስፍረዋል።

በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የህግ ልዕልና እንዲከበር አገልግሎት በሚሰጠው ፍርድ ቤትና ዳኞች ላይ የተፈፀመ ድፍረት በምሬትና በቁጣ ሲያወግዙት ተስተውለዋል።

የመቐለ ማእከላይ ፍ/ቤት በያዝነው ሳምንት ብቻ የእንስት ዘውዱን ጨምሮ 4 በግፍ የተበደሉ ሴቶችን ጉዳይ መመልከቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከቦታው መረጃውን አድርሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia 
" ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " - ፅ/ቤቱ

ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል።

ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት።  

የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል " ብሏል።

" በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል " ሲል ገልጿል።  

" የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ  የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከነገ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia 
" የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት ነው " - ማህበራቱ

ነባር ተራ እስከባሪዎችን በመተካት የተርሚናል አስተዳደር እና ቁጥጥር ስልጠና የወሰዱ ከ 80 በላይ በሚሆኑ ማህበራት(ኢንተርፕራይዝ) የተደራጁ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ዛሬ ከሰአት ስራ ጀምረዋል።

ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣የአዲስ አበባ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በተገኙበት የተመረቁት 996 የታክሲ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ከሰአት በኋላ ስራ መጀመራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ነባሮቹን ተራ አስከባሪ ወጣቶች በመተካት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ የገቡት ወጣቶች በየወረዳው የተደራጁ ሲሆን በከተማዋ በሚገኙ 87 ተርሚናሎች ወደ ስራ ገብተዋል።

የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ቲክቫህ ያነጋገራቸው የማህበራቱ አባላት ገልጸዋል።

ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል ከትላንት ጀምሮ የተበተነው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው በራሪ ወረቀት የተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በየትኛውም መነሻ እና መድረሻ ላይ 10 ብር መሆኑን በመግለጽ ክፍያውንም በዲጂታል መንገድ ብቻ እንዲፈጸም ይጠይቃል።

በተጨማሪም ከተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በላይ የከፈለ አሽከርካሪም ሆነ ረዳት 4000 ብር እንደሚቀጡ ይገልጻል።

ነባር ተራ አስከባሪዎች በመረጡት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia