አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍243👏1🙏1
" በስም ከተለዩት ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎችም ይገኙበታል " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጿል፡፡

እግድ የተጣለባቸው 62 ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ዕዳቸውን ለመክፈል  ፈቃደኛ ያልሆኑ ናቸው ተብሏል።

" በስም ከተለዩት ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎችም ይገኙበታል ዕዳቸውን የማይከፍሉ ከሆነም አዋጁ በሰጠን ሥልጣን መሰረትም በቀጣይ የንብረት እግድ እና ንብረታቸውን በሃራጅ የመሸጥ እርምጃዎች ይወሰዳሉ " ሲሉ የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቢሮው በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ እግድ የተጣለባቸው ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡

የ62ቱ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተላከው በትላንትናው ዕለት ነው።

አቶ ሰውነት " በህጉ መሰረት የተቀመጠ ቀነ ገደብ አለ በአዋጁ በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት መጥተው እስካልከፈሉ ድረስ ለእዳው ማካካሻ በሚሆን መሰረት ንብረታቸው በሃራጅ ተሽጦ እዳው ይሸፈናል " ብለዋል።

ቢሮው የግብር ዕዳቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በ2017 በጀት ዓመት እንደ አዲስ አዋቅሯል።

በዚህም መሰረት ባለፉት 6 ወራት ከ 6.4 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ እዳ መሰብሰቡን አቶ ሰውነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#tikvahethiopia
Welcome to Mikias Melak & Associates Law Office!

🔹 Facebook: AlehigOfficial
🔹 Telegram Channel: AleHig
🔹 Website: alehig.com
📧 Email: mikiasmelak.mm@gmail.com

📞 Direct Contact:
WhatsApp: +251920666595
Telegram: @MikiasMelak

For legal consultations and inquiries, feel free to reach out. We’ll get back to you as soon as possible!
👍181