African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራርነት ስልጠና ወሰዱ::

የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ #ትዕግስት_ሃሚድ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት እጅግ ተለዋዋጭና ውስብስብ በሆነው የሳይበር አለም ውስጥ ውጤታማ የአመራር ብቃት መገንባት ወሳኝና ወቅታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለውና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ አመራር የመገንባት ሂደቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከዚህ አኳያ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የተሰጠው ስልጠና ለተቋማዊ አመራር ግንባታ ትልቅ ሚናን እንደሚጫወት ተናግረዋል።

በስልጠና መድረኩ ላይም የአፍሌክስ የለውጥ፣ የማስፋት እና ሽግግር ስትራቴጂ ቀርቧል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሐገሪቱ ቁልፍ የደሕንነት ተቋም እንደመሆኑ መጠን የአስተዳደሩን የአመራር አቅም መገንባት ለሐገር ሰላምና ደሕንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ #ዛዲግ_አብርሃ ገልጸዋል።