African Leadership Excellence Academy
2.14K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#ከአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #የለውጥ_Reform #የማስፋት_Scaling_Up እና #የሽግግር_Transformation ስራዎች መካከል አንዱ ወደ ተግባር ገብቷል።
በሱሉልታ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት የቀድሞ ህንጻዎች የአስተዳደር ቢሮውን በአዲስ መልክ የማደስ ተግባር ተጀምሯል።
ለአስተዳደር ቢሮው እድሳት #የኢትዮጵያ_መንገዶች_ባለስልጣን #ERA አጠቃላይ ወጭውን የሚሸፍን ሲሆን ለዕድሳት ደግሞ #የኢትዮጵያ_ኢንጂነሪንግ_ኮርፖሬሽን #ECC ውል ገብቶ ስራ ጀምሯል።
የህንጻው እድሳት እንደተጠናቀቀም የአካዳሚው ሰራተኞች ወደ አዲሱ ህንጻ ተዛውረው ስራ እንደሚጀምሩ ተጠቅሷል። በዚህም አካዳሚው ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ገንዘብ ከማስቀረቱም በላይ ለአመራር ልማት እና ለጥናትና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
አሁን ላይ በዓለም በተፈጠረው ዘርፈ ብዙ የእርስ በርስ ትስስር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕድገትና ጥቅም ላይ መዋል ዓለም በፉክክርና እና በውጥረት ላይ እንድትጠመድ ማድረጉም ተመላክቷል።
በቅርቡ #በራሺያና #በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ታዳጊ ሀገራት የምግብ ግብአቶችን እና ማዳበሪያን ወደ ሀገራቸው እንዳያስገቡ በማድረጉ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠሩ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያም በተፈጠሩ ዓለም አቀፍ ጫናዎች ውስጣዊ አቅሟን በማጠናከር በተለይ ስንዴንና ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት መቋቋም የተቻለ ቢሆንም በቀጣይም በቀጠናው በተለይ በቀይ ባህር አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ በመረዳት ከጊዜው ጋር የሚመጥን የራሷን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርባትም ነው #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የተብራራው።
አሁን ላይ በኢኮኖሚው እና በውጭ ግንኙነት ረገድ የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት እንደ #ቻይና#ሕንድ#ቱርክና ሌሎች ቀደምት ሥልጣኔ ያላቸው ሀገራት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህ አኳያ #ኢትዮጵያም_ቀደምት_የስልጣኔ_ሀገር ከመሆኗም ባሻገር #በቅኝ_ያልተገዛች#በኢኮኖሚ_እያደገች የመጣችና #የብሪክስ_ሀገራት አባል መሆን የቻለች፣ #ከአፍሪካ ትልቅ ሕዝብና የመልማት አቅም ያላት፣ በቀጠናው ተቀባይነት ያላትና ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነች እንዲሁም ከፍተኛና ጥብቅ ማህበራዊ ትስስር ያላት ሕዝብ ባለቤት እንዲሁም #በአፍሪካ_አንድነት_ጉልህ_ድርሻ ያላት በመሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር የመሆን ዕድሏ ሰፊ መሆኑ ተብራርቷል።
ስለሆነም #ኢትዮጵያ በውስጥ ያሉባትን ትንንሽ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት #ገጽታዋን_መገንባት እና #የውጭ_ግንኙነት_እመርታዋን_ማረጋገጥ እንደሚኖርባት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየቀረበ ካለው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል ።
(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)
#ከአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #የለውጥ_Reform #የማስፋት_Scaling_Up እና #የመሰረታዊ_እመርታ_Transformation ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞ ህንፃዎችን በማደስ ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ተግባር ስራ ተጀምሯል::

በሱሉልታ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት የቀድሞ ህንጻዎች የአስተዳደር ቢሮውን በአዲስ መልክ የማደስ ተግባር ተጀምሯል።

ለእድሳቱም #የኢትዮጵያ_መንገዶች_ባለስልጣን #ERA አጠቃላይ ወጭውን የሚሸፍን ሲሆን ለዕድሳት ደግሞ #የኢትዮጵያ_ኢንጂነሪንግ_ኮርፖሬሽን #ECC ውል ገብቶ ስራ ጀምሯል።

የህንጻው እድሳት እንደተጠናቀቀም የአካዳሚው ሰራተኞች ወደ አዲሱ ህንጻ ተዛውረው ስራ ይጀምራሉ።

በዚህም አካዳሚው ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ገንዘብ ከማስቀረቱም በላይ ለአመራር ልማት እና ለጥናትና ምርምር ስራዎች ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።

የህንፃ እድሳቱ ሲጠናቀቅ የሚኖረውን ገፅታ የሚያመላክተው የ3D ቪዲዮ እንደሚያሳየው ሁሉንም አይነት መሰረተ ልማት ያካተተው ይህ የህንፃ እድሳት በወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል::