African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የብር ሜዳልያ ለኢትዮጵያ!!

የፓሪስ ኦሎምፒክ 800 ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።
እንኳን ደስ አለን!!
👍5
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከአስተዳደር ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አከናወኑ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከአስተዳደር ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራርና አባላት ጋር በመተባበር የበጎ አድራጎት ማህበረሰብ ተሳትፎ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ሱሉልታ ከተማ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ተከናውኗል።
የአካዳሚው ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሠ ዶ/ ር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የሴቶች ሊግ የአረንጓዴ አሻራ መልዕክት አካል በመሆናቸው ኩራት እንደተሠማቸው ተናግረዋል ።
በስደተኞች ተመላሽ አገልግሎት የአስተዳደር ወረዳ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ አባት እንደተናገሩት የአስተዳደር ወረዳ ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር የሆነ ከአስራ ስድስት ተቋማት ጥምረት የተመሰረተ እንደሆነና አራት መቶ ሀምሳ የሴት ሊግ አባላት እንዳሉት ገልፀዋል፡፡
ኃላፊዋ እንደገለፁለት አስተዳደሩ የአቅም ግንባታ፣ የበጎ አድራጎት ለዝቅተኛ ሰራተኞች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የማድረግ ስራና የደም ልገሳ እንዲሁም ለፅዱ ኢትዮጵያ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡
በዛሬው እለትም የተከናወነው መርሀግብር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር የአየር ንብረት አሉታዊ ተፅዕኖን ለመከላከል የሚችሉ ሀገር በቀል ችግኞችን ለመትከል የተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በቀጣይም ከመትከል ባለፈ መፅደቃቸውን አንደሚንከባከቡና በአረንጓዴ አሻራ ልማቱ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 2500 ችግኝ እንደተተከለም ተናግረዋል፡፡
👍2
#AFLEX_President Engages in Productive Dialogue with #UN_Under_Secretary_General_and_Executive_Secretary_of_ECA on Partnership and Leadership Development Programs
In a significant move towards fostering collaboration and enhancing leadership capabilities across Ethiopia and Africa, The African Leadership Excellence Academy President, #Zadig Abreha and UN Under-Secretary-General and, Executive Secretary of ECA, #Claver_Gatete, engaged in a fruitful discussion on potential #partnerships and collaborative efforts aimed at #Ethiopian and #African leaders' Development Program, Africanization project, Joint research, and facility sharing for Global meetings and convention.
During the meeting, President Zadig Abreha outlined various partnership areas that could effectively unlock the best Ethiopian and African potentials for senior leaders' capacity building. His vision emphasized the importance of creating sustainable pathways for leadership development, the Africanization project and The African Davos program which he believes is critical for the region's progress.
"I am excited about the potential for our partnership to cultivate and develop Ethiopian and African leaders who can drive thought leadership and positive change in their countries," Zadig Abreha stated. "By transforming and scaling up AFLEX Visions, we can enhance the capabilities of our leaders and effectively address the pressing challenges that our leaders face."
UN Under-Secretary-General and, Executive Secretary of ECA, Claver Gatete, expressing his appreciation for the President's comprehensive presentation, highlighted the critical need for such collaborative efforts. He commended the AFLEX for its forward-thinking initiatives and noted his institution’s eagerness to work closely with the African Leadership Excellence Academy to realize these ambitious goals.
"I am genuinely impressed by the strategic areas of partnership outlined by President," said Claver Gatet. "I firmly believe that together, we can design an impactful Leadership Development curriculum and foster exchange programs that will position our senior leaders for success.
The dialogue underscored a shared commitment to building the capacity of leadership across various sectors, paving the way for innovative solutions and impactful change.
Both leaders agreed to continue exploring avenues for collaboration, with plans to establish a framework for developing leadership development programs tailored to the specific needs of senior leaders in the region.
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከደቡብ ለደቡብ ትብብር ድርጅት ጋር ውይይት አካሄደ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የደቡብ ለደቡብ ትብብር ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች የትብብር ስምምነትን ወደ ተግባር መቀየር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ በቅርቡ መፈራረማቸውን አስታውሰው ፣ የስምምነቱን አተገባበር በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣትና ዝርዝር ተግባራትን በማዘጋጀት መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በትብብር የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ በሚያስችላቸው ሌሎች ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።

ስምምነቱ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመቀናጀት አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ማዘጋጀት፣ የአመራር ልማት ፕሮግራም ሞጁሎችን በጋራ ማዘጋጀት እና የአመራር ልማት ስራዎችን በመጠቀም የትብብር ህብረቱን ሀገራት የመንግስት ፖሊሲ አውጪ አካላትን ማብቃት እንደሆነ ተነግሯል።

ሁለቱም ወገኖች ስምምነታቸውን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለማስተካከል በየጊዜው መገናኘታቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

ይህ የትብብር ጥምረት የሁለቱን ተቋማት ጥንካሬዎች በማጎልበት እና ዘላቂ ልማትን በክልሉ ውስጥ በመፍጠር ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን እንደሚያጎለብት ተጠቅሷል።

የደቡብ ለደቡብ ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ፣ አገር በቀል ዕውቀት፣ ባህልና ሰፊ ልምድ እንዳላቸው ይታወቃል።
👍2
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲና ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ንቅናቄ ጉዳዮች ላይዛሬ ነሀሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየመከሩ ነው፡፡

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጉዳይ የብሄራዊ ደህንነት፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ የዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ምላሽ የሚጠይቅ መሆኑን የኢ.አ.ስ.ሥ.አ.ኮ. ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማሪያም የምክክር መድረኩን ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የሚዲያን የኮሙኒኬሽን አካላት የተዋናይነት ሚና እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሙያዊና አገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣትም የአደጋ ስጋር ሥራ አመራር ፖሊሲ ጉዳዮችን አውቀው የማህበረሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሽፈን የአገራችንን ሉዓላዊነት ሙሉ በማድረግ በኩል ሰፊ ሚና መኖሩም ተገልጿል፡፡ ምክክሩም ለሁለት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የሚቆይ ይሆናል፡፡
እንኳን ደስ አለን!!

አትሌት ታምራት ቶላ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኘ

በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በወንዶች ማራቶን የፍጻሜ ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ታምራት 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ26 ሴኮንድ በርቀቱ የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን አሻሽሏል።

አትሌት ደሬሳ ገለታ አምስተኛና አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
👍3
እንኳን ደስ አለን!!

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ወድድር በሴቶች ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡
👍4