የሥራ ባህል ሽግግር ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ተፈራርመዋል።
ሁለቱ ተቋማት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት የተስማሙ ሲሆን የዘርፉን የአመራር ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የአመራር ልማት ፕሮግራም፣ የሥራ ባህል ሽግግር ለመፍጠር የሚያግዝ ማከል ግንባታ፣ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት እና ከስር ያሉትን የሚያተጋ የልህቀት ሽልማት እና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት እንዲቻል የጋራ ምርምር ሥራዎችን ለመስራት ተስማምተዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝደንት ዛዲግ አብርሃ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራና ክህሎት ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር የሚያግዝና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሆነ ጠቅሰው በስምምነቱ መሰረት የአመራሮችን ብቃት የማሳደግ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።
የዘርፉ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ሀሳብ የሚያፈልቁበት የስራ ባህል ሽግግር ማዕከል ግንባታ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበትም የመሰረት ልማት ግንባታው የስምምነቱ አንድ አካል እንዲሆንና በቅርቡም የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርዓት እንደሚፈፀም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል::

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ስምምነቱ በሥራና እድል ፈጠራ ዘርፍ የተያዘውን ዕቅድ ከማሳካት ባለፈ ተወዳዳሪ የሰው ሀብት ልማት ማፍራት ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።
በሥራ ዘርፉ ላይ ያሉ አስፈፃሚ አካላትን ለማብቃት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያግዝ ስልጠናዎችን ለማዘጋጀት ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በአካዳሚው ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ::
የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በተቋሙ የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2017 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል::
ፕሬዚዳንቱ በዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ከተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።
አቶ ዛዲግ እንደገለጹት በርካታ ዓለምአቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተቋማት አካዳሚውን በገንዘብና በሀሳብ እየደገፉ መሆኑን ጠቅሰው ያለፈውን አመት አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ በላቀ መልኩ እንዲፈፀም ሁሉም ዘርፎችና የስራ ክፍሎች የተሻለ የዕቅድ አፈፃፀም እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ።
በተያያዘ ዜና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ስልጠና ተሰጥቷል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ሱሉልታ በሚገኘው የተቋሙ አዳራሽ ስልጠና ሰጠ።
የፕሮግራም ዘርፍ አስተባባሪ ዶ/ር እሸቴ አበበ እንደተናገሩት የስልጠናው ዓላማ የስልጠና ተግዳሮቶችን ለመለየት ደንበኛ እና የደንበኞች አገልግሎት ለመለየት እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት የአገልግሎት አሰጣጥ ልክ እንደስሙ የላቀ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል ።
ዶ/ር እሸቴ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቫንት ባህሪ እና ባለ ጉዳይ ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

👍2
#AFLEX_Environmentally_Friendly_Academy
We are determined to keep our environment sustainable and friendly. We have established a treatment plant and recycled the water for our nursery garden and for the neighborhood community as a way of Corporate Social Responsibility.

አካዳሚው 27 ከሚሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሁለት ዙር የSpecialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) እንዳዘጋጀ የሪፎርም ኮሚቴ አስተባባሪው ሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ገለጹ። አቶ ሙሉነህ አባተ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ ናቸው። የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሚያዘጋጀው የJudiciary Specialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) ተቋማቸውን ወክለው ተገኝተዋል። ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ይዘው በስርዓተ ስልጠና (curriculum) ቀረጻው ላይ ሙያዊ አስተያየቶችንና ምክሮችን ሲያቀርቡ ነበር። አቶ ሙሉነህ እንደገለጹልን አካዳሚው የተሟላ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ተግባር ውስጥ ባለድርሻ አካላት መካተታቸው ምሉዕ የሆነ የስርዓተ ስልጠና ሰነድ ለማዘጋጀት መደላድል እንደሚፈጥር ያምናሉ።
በተለይም ደግሞ የፍትህ ዘርፉን አመራር አቅም በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ለመገንባት የሚያስችል ስርዓተ ስልጠና (curriculum) መዘጋጀቱ፤ ለዘርፉ የሚኖረው ፋይዳ በቀላሉ የሚገለጽ እንዳልሆነ የሚጠቅሱት አቶ ሙሉነህ፤ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር ላሉ ሶስት ፍርድ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት አመራር አቅም ግንባታ ላይ መስራት የሚገባ ከሆነ የስርዓተ ስልጠና (curriculum) የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው። ስለ ስርዓተ ስልጠና ምንነት እና አዘገጃጀት ገለጻ ከመስጠት ጀምሮ በቡድን መንፈስ ለመስራት የነበረው ሂደት አዳዲስ ዕውቀቶችንና ልምዶችን እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

በሀገር ውስጥ ያለውን የልምድና የዕውቀት ውስንነት ለመቅረፍ፤ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እያደረገ ያለውን ተግባር የሚያደንቁት አቶ እንድሪስ ናቸው። ከኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ነው የመጡት።
የተዘጋጀ እና ያለቀ የcivil society Specialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) ከመስጠት ይልቅ፤ የዘርፉን ባለቤቶች ጠርቶ ኑ አብረን እንስራ ማለት ትልቅ ትርጉም ያለውና ለውጤታማነቱም መሰረት የሚጥል እንደሆነ አቶ እንድሪስ ይናገራሉ።
በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለመሙላትም የcivil society Specialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) መዘጋጀቱ አመራሩ በሰነድ የታገዘ የዕውቀትና የክህሎት ድጋፍ እንዲያገኝ ያግዛል የሚሉት አቶ እንድሪስ፤ ይህ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ያምናሉ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ጋር በመቀናጀት በስፔሻላይዜሽን የአመራር ልማት ፕሮግራም ዙሪያ በርካታ ተግባራቶችን አያከናወነ እንደሆነ የሚገልጹት ደግሞ በአካዳሚው የሪፎርም ኮሚቴ አስተባባሪው ሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ናቸው።
አካዳሚው 27 ከሚሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በሁለት ዙር የSpecialization Leadership Development Program ስርዓተ ስልጠና (curriculum) እንዳዘጋጀ የሚገልጹት ሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ከነዚህም ውስጥ 15ቱ ቀደም ብለው በመጀመሪያው ዙር የተከናወኑ እንደሆኑና ቀሪዎች 12 ደግሞ በ2ኛው ዙር ከሀምሌ16/2016 እሰከ ሀምሌ 19/2016 ዓ.ም ድረስ እንደተሰሩ ተገልጿል።
በዚህ የስርዓተ ስልጠና ዝግጅት ከአካዳሚውና ከተለያዩ ተቋማት በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ባለሙያዎች ወደ ዝግጅት ከመግባታቸው በፊት በስርዓተ ስልጠና አዘገጃጀትና ሞዳሊቲ ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም ዜሮ ድራፍት ስርዓተ ስልጠናዎች በጋራ መድረክ ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ወደ የተቋማት ተመልሰው በተቋማት ከፍተኛ የበላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ዳብረው፤ አካዳሚው በቀጣይ በሚያዘጋጀው የቫሊዴሽን ወርክሾፕ ቀርበው የመጨረሻ ቅርጻቸውን እንዲይዙ በሚል ስምምነት ላይ ተደርሶ የስርዓት ስልጠናው ዝግጅት እንደተጠናቀቀ የሪፎርም ኮሚቴ አስተባባሪው ሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ተናግረዋል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሥራና_ክህሎት_ሚኒስቴር ያደረጉትን የጋራ መግባቢያ ስምምነት አዲስ ዋልታ ቴቪ እንዲህ ዘግቦታል፦
#አሁን
********
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የ100 ቀናት ሳምንታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተደረገ ነው::
የዘርፍ ሀላፊዎችና ዳይሬክተሮች በሳምንቱ ውስጥ ያከናወኗቸው ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች እየቀረቡ ነው::