African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ለጠቅላይ ሚንስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ዛሬ ተገምግሟል::

በአስፈጻሚ አካላቱ በዕቅድ የተያዙ ስራዎችና የሪፎርም አተገባበሮች ውጤታማ እንደሆኑ ተመላክቷል::

በቀሪ ሶስት ወራት መፈፀም ያለባቸው ተግባራትን በመለየት በዓመቱ ለማሳካት የተያዙ ትልሞችን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ከስራ ኃላፊዎች ጋር የጋራ መግባባት እንደተፈጠረ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል::

በሪፖርቱ ከቀረቡ ጉዳዮች ውስጥ መልካም ውጤቶችን ማጠናከር፣ ያሉ ክፍተቶችን ማረምና በተያዘላቸው ጊዜ ያልተከወኑ ተግባራትን የማካካሻ ዕቅድ አውጥቶ በመስራት ጠንካራ አፈጻጸምን ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማው ላይ ተገኝተዋል::
👍1
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) በኢትዮጵያ ለጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ የአፍሪካ መሪዎችን በአመራር ልማት መርሃ ግብሮች የማብቃት ፍላጎት እንዳላው ገለጸ፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ አፍሌክስ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዓላማ የሚሟላበት ለየት ያለ ቦታ መሆኑን ጠቁመው፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ምርጥ አመራሮችን በማስተዋወቅ በነባራዊው ዓለም ያለውን ልዩነት ማጥበብ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በአካዳሚው እና በተቋሙ ሰራተኞች ስም የእንኳን ደህና መጡ በማስተላለፍ ስለ አካዳሚው የሪፎርም ፣ የማስፋት እና የሽግግር ፕሮግራም እና የትብብር እቅዶች ላይ ማብራሪያ ሰተዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ስትራቴጂካዊ አቅም በመጠቀም፣ AFLEX ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ ተቋም የመሆን ፍላጎት እንዳለውና፣ የአፍሪካን አመራር ለማሳደግ እና ለማቋቋም ጥረት እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል
የAFLEX ታላቅ አጀንዳ የአፍሪካን ድምጽን ከፍ ለማድረግ እና አህጉሩን ለመቀየር እንደሆነም አክለዋል።
“ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሱሉልታን፣ ልክ እንደ ዳቮስ ስዊዘርላንድ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ማዕከል ማድረግ እና የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን፣ በአፍሪካ ምድር አጀንዳ መሆናቸውን ማረጋገጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለፓን አፍሪካኒዝም እና ለአፍሪካዊነት ዓላማ ቁርጠኛና ፣ ጠንካራ የትምህርት ፣ የእድገት ፣ የምርምር ፣የህትመት እና የአህጉራዊ ፣ የውይይት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግልም ጠቁመዋል፡፡
አቶ ዛዲግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት እና ዘመናዊ ፋሲሊቲ እና ስማርት እርሻን በማቋቋም የአፍሪካ መሪዎችን ለማብቃት እና አህጉሪቱን ለመለወጥ ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ ለማጠናከር ተቋሙ በስራ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው ለቀረበላቸው አጠቃላይ ገለጻ እና ዝርዝር ማብራሪያ አመስግነው በተለይ በኢንዱስትሪ ፖሊሲ ውይይት እና በሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

በመጨረሻም አቶ ዛዲግ በሥነ-ምግባር፣በዲሲፕሊን እና በሃገር ወዳድነት ዙሪያ ኢትዮጵያና አካዳሚው ከጃፓን ብዙ መማር እንደሚፈልጉም አስታውዋል።
"አካዳሚው የአፍሪካን ችግር የሚፈታ ብቁ አመራር ለማፍራት በሚያስችል መልኩ: በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት: በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ ነው"
ዛዲግ አብርሃ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት
Russian Science and Culture Center Officials Visit African Leadership Academy, Discuss Deepening Cooperation.

In a significant move towards strengthening ties between Russia and Africa, officials from the Russian Science and Culture Center visited the head office of the African Leadership Excellence Academy (AFLEX) in Addis Ababa, Ethiopia today.

The delegation, led by the center's director Mr. Alexander Yevsetignev, held a wide-ranging discussion with the president of the AFLEX, Mr. Zadig Abreha.
During the meeting, Mr. Zadig highlighted the long-standing strong relationship between Russia and Ethiopia, noting that the spirit of cooperation between the two countries has been growing in recent years.
👍3
He praised Russia's ancient civilization and the patriotism of its people, stating that Russia had never harbored any colonial ambitions in its history.
"Russia has a rich and storied past, and the people of Russia are deeply patriotic," said Mr. Zadig. "We at the African Leadership Excellence Academy have a great desire to work closely with Russian institutions to further our shared goals."

The Russian delegation expressed delight at the visit, with Mr. Yevsetignev his surprise at the favorable environment for conducting studies and research at the AFLEX training facility in Sululta.

"We were thoroughly impressed by the state-of-the-art infrastructure and the dedicated staff at the Sululta campus," said Mr. Yevsetignev. "The AFLEX is clearly an institution committed to academic excellence and we are excited about the prospect of collaborating with them."

The two parties agreed that the discussion had opened the door for further cooperation, and they concluded the meeting by reaching an agreement to work closely on common issues. This included the possibility of AFLEX offering free education for second and third-degree programs through its educational institutions.

"This is an important step forward in strengthening the ties between Russia and Africa," said Mr. Zadig. "We believe that this partnership will lead to many fruitful collaborations in the years to come."
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራርነት ስልጠና ወሰዱ::

የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ #ትዕግስት_ሃሚድ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት እጅግ ተለዋዋጭና ውስብስብ በሆነው የሳይበር አለም ውስጥ ውጤታማ የአመራር ብቃት መገንባት ወሳኝና ወቅታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለውና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ አመራር የመገንባት ሂደቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከዚህ አኳያ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የተሰጠው ስልጠና ለተቋማዊ አመራር ግንባታ ትልቅ ሚናን እንደሚጫወት ተናግረዋል።

በስልጠና መድረኩ ላይም የአፍሌክስ የለውጥ፣ የማስፋት እና ሽግግር ስትራቴጂ ቀርቧል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሐገሪቱ ቁልፍ የደሕንነት ተቋም እንደመሆኑ መጠን የአስተዳደሩን የአመራር አቅም መገንባት ለሐገር ሰላምና ደሕንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ #ዛዲግ_አብርሃ ገልጸዋል።
👍1
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ጋር ውይይት አደረገ። ውይይቱ አካዳሚው ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንደሚረዳው ተገልጿል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃና እና የሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ የባህል እና ተሳትፎ ምክትል ቻንስለር ፕሮፌሰር ሚካኤል ዌስሊን ወደፊት አብሮ መሰራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ላይ የዙም ውይይት አደረጉ፡፡
ሁለቱም መሪዎች ተቋማቱ ወደፊት በጋራ መስራት የሚችሉባቸውን መንገዶች በመመርመር ፍሬያማ እና ዘላቂ አጋርነት ለማመቻቸት የትብብር ውይይት አድርገዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የሜልበርን ዩኒቨርሲቲ የየራሳቸውን ጥንካሬ እና ኔትዎርክ በመጠቀም ለጋራ የምርምር ውጥኖች እና ሌሎች የትብብር ፕሮግራሞች ላይ አዳዲስ እድሎችን መፍጠር እንደሆነም በውይይቱ ተገልጿል።
ይህ ስትራቴጂያዊ ተሳትፎ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ራሱን እንደ አንድ የአመራር ማዕከል አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ፍላጎት የሚያጎላ ሲሆን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አፍሪካዊ አመራርን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማፍራት እንደሆነም ተነግሯል ።
አካዳሚው በአህጉሪቱ እና ከዚያም በላይ የለውጥ አራማጅ መሪዎችን የሚያበረታታ ትስስር ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
👍1
Consultative workshop meeting #AFLEX African Leadership Excellence Academy and #pl4ge (Public Leadership for Gender Equality).