African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.53K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ ነው"
---- የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ----
የሀገራችንን ህልም እውን ለማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አሳሰቡ።
👍13
የምክር ቤት አባላት በሀገራችን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይቀለበስ እና ዳር እንዲደርስ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ከመታገል ባሻገር በዕውቀትና በሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ በማፍራት ለሀገራቸው ብልፅግና አሻራቸውን እንዲያስቀምጡም ጥሪ አቅርበዋል።
የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ይህን ያሉት "የሥነ-ምግባራዊ እመርታ፤ ከሞራል ብልሹነት ወደ ግብረገባዊ አርኣያነት" እና "ሰብአዊ ዕመርታ" በሚሉ ርዕሶች ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች በተሰጠው ሥልጠና ዙሪያ ከሠልጣኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው።
የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ለለውጡ መምጣት ገፊ ከሆኑት ምክንያቶች ውስጥ የሥነ-ምግባርና ብልሹ አሰራሮችን ተከትለው የመጡ የፍትሕ፣ የፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ችግሮች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦት ተጠቃሽ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከለውጡ በፊት የልማት ባንክን እና የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶ ለሙስናና ምዝበራ ተጋልጠው እንደነበረ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አስታውሰዋል።
አሁን ላይ መንግስት እነዚህን ተቋማት መልሶ በማደራጀት ከኪሳራ እየታደጋቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት። ይህ ሲባል ግን በለውጡ መንግሥት ምንም አይነት የሥነ-ምግባር እና የሙስና ችግር የለም ማለት እንዳልሆነ እና አልፎ አልፎ በአንዳንድ ግለሰቦች፣ በውስን አመራሮችና በተቋማት የሚታዩ ትንንሽ ችግሮች የሉም ለማለት አይቻልም ብለዋል።
ይሁን እንጂ እዚህም እዛም የሚታዩ ትንንሽ ችግሮች ስጋት እንዳይሆኑ የምክር ቤት አባላት በሚያደርጉት የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ብልሹ አሠራሮች እንዲስተካከሉ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
"እኛም የምክር ቤት አባላት" አሉ የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ሙስናንና ኢፍትሐዊ አሠራርን ለመታገል መንግሥት ቁርጠኛ በመሆኑ እንደ አባልና እንደ አመራር በቁርጠኝነት ልንታገል ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል ።
ስለዚህም ጥቃቅን ችግርችም ቢሆኑ በእንጭጭነታቸው መቀጨት እንዳለባቸው መንግሥት ስለሚያምንና ቁርጠኛም በመሆኑ በሺህ የሚቆጠሩ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ፣ የሀብት ምዝገባ እና ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደ ሥራ መገባቱንም ነው በምላሻቸው ያስገነዘቡት።
በመጨረሻም የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ይህ የመንግሥት ዕቅድ እንዲሳካ የምክር ቤት አባላት በሕግ ማዕቀፍ፣ በክትትልና ቁጥጥር ሥራቸው ውስጥ በማካተትና በትኩረት በመስራት ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አሳስበዋል።
(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)
👍16
#ዜና_ሹመት

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #ወ_ሮ_መሠረት_ደስታን #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ምክትል_ርዕሰ_አካዳሚ እንዲሆኑ ሹመት ሰጥተዋል።

የአካዳሚው አመራር እና ሰራተኛ መልካም የስራ ዘመንን ይመኛል።
👍22
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ሆነው የተመደቡት ወ/ሮ መሰረት ደስታ ከዘርፉ ዳይሬክተሮችና ከተቋሙ የሪፎረም ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ።
በውይይቱ ላይ ወ/ሮ መሰረት ደስታ እንደጠቀሱት በግል እና በመንግስት ተቋማት ላይ በብዙ ዘርፎች እንዳገለገሉ ገልጸው ወደዚህ አካዳሚ ከመመደባቸው በፊት በጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ እንዳገለገሉም ተናግረዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ አካዳሚዋ የአፍሌክስን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ከተቋሙ አመራር እና ሰራተኛ ጋር ለመስራት እንደሚተጉ ተናግረው፤ ተቋሙ በህግ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲያሳካ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
የአካዳሚው የሪፎርም ኮሚቴ አባላትና የዘርፉ ዳይሬክተሮች በበኩላቸው ለምክትል ርዕሰ አካዳሚዋ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተው፤ በተቋሙ ውስጥ የሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ጠቅሰው፤ ወደፊት መከናወን ያለባቸው ስራዎች ላይ ማብራሪያና ገለፃ አድርዋል፡፡
ወ/ሮ መሰረት ደስታ ከውይይቱ በቂ ግንዛቤ እንደወሰዱ ተናግረው፤ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት አካዳሚው ብዙ መስራት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
👍19
ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉ ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡

*********************

“የሚዲያ ሚና ለትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዘጋጅነት ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 18/2017 ዓ/ም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥተጀምራል፡፡

"ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ ላይ ገለጻ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉን ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው መሥራት እንደሚጠበቅባቸውና ሃገር የሚገነባው በአዎንታዊ ትርክቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሥራ ትርክትን እንደሚቀይር የተናገሩት አማካሪ ሚኒስትሩ ባዶ ትርክት እንደማይጸናና ተግባራዊ ሥራ ሲሰራ ትርክቶች ይለወጣሉ ብለዋል። ትላንት የነበረው የአባይ ውሃ ዛሬ ህዳሴ ግድብን ሰርተን ስናጠናቅቅ ትርክቱ ተቀይሯል በማለት ሥራ ተግባርን እንደሚቀር አመላክተዋል፡፡

ትርክቶች አካታች መሆን እንዳለባቸው ፣ልሂቃን የሚገቡ ትርክቶች መቃናት እንዳለባቸው ያነሱት አማካሪ ሚኒስትሩ ትርክት ለነገ ሲባል የትላንቱን የሚተወውን ትተን፣ የዛሬንም ይቅር ብለን ነገን የምንገነባበት ሊሆን ይገባል ብለዋል በገለፃቸው፡፡

ትርክት የአብሮነት ታሪካዊ መሰረት እንደሆነ፣ ሰዎች ከየት ተነስተው እና ወደየት እንደሚሄዱ እና የት እንደሚደርሱ የሚመለከቱበት መሆኑንም ዲያቆን ዳንኤል አክለዋል፡፡

ለመገናኛ ብዙሃን "ሚዲያ ለብሔራዊ ትክርክትና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ስልጠና ለሶስት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ይቀጥላል፡፡
👍12
በመንግሰት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት እና በአካዳሚው 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመንግሰት የ2017 የመጀመሪያ 100 ቀናት እና በአካዳሚው 1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ውይይት አካሄደ፡፡

በአካዳሚው የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በአለም አቀፍ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አዝማሚያና ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው አንድምታ፣ የሪፎርሙ ተጠባቂ ፋይዳዎች የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ፤ የዘርፎች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት እና የመንግስስት አገልግሎትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል:: ምክትል ርዕሰ አካዳሚው የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይም ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በበኩላቸው፣ ተቋሙ እቅዱን በመፈተሸ፣ ተግዳሮትን በመለየት፣ የተቋቋመበት ተልዕኮ ላይ አተኩሮ መስራት እንዳለበትና መሪነት የሚታይበት እና መሪ ፈፃሚ መሆን እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡
👍17