ET Securities
692 subscribers
609 photos
7 videos
30 files
310 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።

በዚህ መሰረት፦
- ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
- ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
- ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር 
- የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው የተገኘው።

Source: Tikvah Ethiopia

LinkedIn |𝕏|
Facebook |YouTube Website
Ethiopia's financial future is taking an exciting turn as senior officials of the Ministry of Finance race against time to establish a regulatory framework injecting vitality into the budding capital market. The plan is to incorporate enticing incentives into an income tax law that has gone unchanged for over two decades. The officials' momentum stems from a comprehensive policy proposal by Brook Taye (PhD), former director general of the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA).

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
Source~ Banks Ethiopia
@Etstocks
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት የገቢ ታክስ ህጎችን ማሻሻልን ጨምሮ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለመደገፍ የሚያስችል የቁጥጥር ማዕቀፍ ላይ እየሰሩ ነው።

- ዶ/ር ብሩክ ታዬ የቀድሞ የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ የገበያውን ዕድገት ለማነቃቃት በኮርፖሬት የታክስ መዋቅር ላይ ለውጦች እንዲደረጉ መክረዋል።

- የገበያ ተሳትፎን ለማበረታታት ከካፒታል ትርፍ፣ ከቦንድ ወለድ እና ሼር ፕሪሚየም ተቆራጭ የሚደረጉ ታክሶች እንዲነሱ ክለሳ መደረግ እንዳለበት ተገልጿል።

- የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር ሕጎችን እያሻሻለ ቢሆንም እስካሁን የፊስካል ተጽእኖዎችን ሙሉ በሙሉ አልተረዳም።

- አሁን ያሉት የታክስ ህጎች የካፒታል ገበያን እድገት እንቅፋት እንደሆኑ የካፒታል ገበያ ባለስልጣናት እና አማካሪዎች ተናግረዋል። ባንኮች ለገበያ ዕድገት ወሳኝ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ በካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሰማራት ጥርጣሬ አላቸው።

- ESX 1.51 ቢሊዮን ብር ካፒታል ቢሰበስብም ብዙ ኩባንያዎች እንዲዘረዝሩ ግን የታክስ ማበረታቻዎችን ይፈልጋል።

- ባለሙያዎች ድርብ ታክስን ( Double Taxation ) ለማስወገድ፣ የረጅም ጊዜ ቁጠባዎችን ለማበረታታት እና የኢንቨስትመንት ብዝሃነትን ለማሻሻል የታክስ ማሻሻያዎች መኖር እንዳለባቸው ይገልጣሉ።

- ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በመንግስት የተያዙ ድርጅቶች በESX ላይ ለመዘርዘር ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው።

- ደጋፊ የታክስ ከባቢ አለመኖሩ የካፒታል ገበያውን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ሊገድበው ይችላል ተብሏል።

Source: Addis Fortune

website |LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
👍1
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የዛሬ 30 ዓመት በቀዳሚነት ወደ ገበያ በመግባት የሚጠቀሱት አዋሽ ባንክና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከግል የፋይናንስ ተቋማት ገበያውን በመምራት እየተጓዙ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ሁለቱ እህትማማች የፋይናንስ ተቋማት የተመሠረቱበትን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቁት፣ በኢንዱስትሪው በየዘርፋቸው በገበያው ውስጥ በመሪነት ደረጃ የሚያስቀምጣቸውን አፈጻጸም ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማቱን የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የሁለቱም ተቋማት ሥራ አስፈጻሚዎች ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ በገበያ ውስጥ የያዙት ድርሻ እየሰፋ መምጣቱንም ጠቁመዋል፡፡

የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የአዋሽ ባንክ ሥራ አስፈጻሚው አቶ ፀሐይ ሽፈራው አክለው እንደገለጹትም፣ ‹‹ቀድመው ወደ ባንክና ኢንሹራንስ ክፍለ ኢኮኖሚው በመግባት የመጀመሪያዎቹ የሆኑት እህት ኩባንያዎቹ፣ በዘርፉ ላለፉት 30 ዓመታት አገልግሎታቸውን ከወቅቱ ጋር እያዘመኑ በመሄድ ከፍተኛ ተከታታይነት ያለው ዕድገት አስመዝግበዋል፤›› ብለዋል፡፡

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጂባት ዓለምነህም፣ ኩባንያቸው ከግል መድን ሰጪዎች መካከል በጄኔራል ኢንሹራንስ ዘርፍ ተከታታይ ዓመታት የመሪነት ደረጃውን አስጠብቆ በመጓዝ ሲሆን፣ በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ደግሞ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ግንባር ቀደም ሆኖ የአንደኛነትን ደረጃውን ይዞ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡

እህት ኩባንያዎቹ በተከታታይ ስኬትን በማስመዝገብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የባንክና የኢንሹራንስ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ ገቢያቸውን በማሳደግና በትርፋማነት በመጓዝ ለአገራዊ ኢኮኖሚው የራሳቸውን አበርክቶ እየሰጡ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
ዳዮት ታዮ
2
📌Ethio Telecom to kick off Ethopian stock trading with 10% flotation next week

Source~ Reuters
@etstocks
መንግስት ነዳጅ ላይ ሊያደርግ ባሰበው ፊፎርም ምክንያት የዛሬ አመት አንድ ሊትር ነዳጅ ከ117 ብር በላይ እንደሚሆን ታውቋል

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከቀናት በፊት የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻን በማድረግ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋን በየሶስት ወሩ እንደሚጨምር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ መግለጫ ላይ ይፋ የተደረገው መረጃ "የተሟላ ማስተካከያ" እስከሚደረግ ድረስ ይህ በየሶስት ወሩ የሚደረገው ጭማሪ እንደሚቀጥል ነው።

ከዚህ መግለጫ ጋር አብሮ የተለቀቀ አንድ ሰነድ እንደሚያሳየው የአለም የነዳጅ ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል ቢሆን የዛሬ አመት የነዳጅ ዋጋ 117 ብር ይገባል።
.
.
.
Read More

Source ~ MeseretMedia
@Etstocks
#News | ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።
#ካፒታል
ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።
በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
#Ethiotelecom
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2 ወር  282 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መስጠቱን አስታወቀ!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሐምሌ 22, 2016 እስከ መስከረም 30, 2017 ድረስ ለዋና ዋና ዘርፎች  282,459,436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች መደልደሉ ተገልጿል።

የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ የተሠጣቸው፡-

- መድሃኒቶች እና የህክምና አቅርቦቶች፡ 208.3 ሚሊዮን ዶላር

- ማሽነሪዎች፡ 42.8 ሚሊዮን ዶላር

- ጥሬ ዕቃዎች እና የፍጆታ ዕቃዎች፡ 18.2 ሚሊዮን ዶላር

- የአገልግሎት ክፍያ እና ልዩ ልዩ፡ 13.2 ሚሊዮን ዶላር

ሆኖም ደንበኞቹ የተጠቀሙት 28 በመቶ ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ  አስተዳደር ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ምንጩን ለማሣደግ ተወዳዳሪ የምንዛሬ ተመን በመስጠት እየሠራሁ ነው ብሏል።

ምንጭ ~ ቅዳሜገበያ @Etstocks
አሃዱ ባንክ ያለመያዣ ብድር መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ 

በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ወይም በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ ብድር ለመስጠት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታዉቋል።

ባንኩ እንዳለው የገንዘብ እንቅስቃሴ ወይም (Cash flow) መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ይም "ማሕደር" የተባለ ቀላልና አመቺ የቴክኖሎጂ መተግበሪያን በመጠቀም ተበዳሪዎች የንብረት ዋስትና ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ብድር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በዚህም ባንኩ "ከብዙዎች ለብዙዎች" የሚለውን መርሕ ተግባራዊ በማድረግ በጥቃቅን እና አነስተኛ የስራ ዘርፍ ለተሠማሩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ የብድር አገልገሎት ይሰጣል ተብሏል።

አሃዱ ባንክ አጠቃላይ ከሚሰጠው የብድር መጠን እስከ 25% የሚሆነውን ድርሻ ለዚህ ዘርፍ መመደብ የተገለፀ ሲሆን ይሀንን ተግባራዊ ለማድረግ ባንኩ ከኤስኤንቪ (SNV)፣ የኔዘርላንድ ልማት ድርጅት እና ከኬኤምዲ አፕሲስ (KMD Apsis) ጋር እንደሚሰራ አስታዉቋል ።

Source: capitalethiopia @Etstocks
" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)

ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።

የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።

ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።

የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።

የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል።
#ሪፖርተርጋዜጣ
@Etstocks
👍1
What does dematerialization of equities mean?

Dematerialization of equities refers to the process of converting physical shares of stock into electronic form. This transformation simplifies the trading, holding, and transfer of shares by eliminating the need for physical certificates. Key benefits include:

1. Reduced Risk: Eliminates risks associated with loss, theft, or damage of physical certificates.


2. Efficiency: Facilitates quicker and easier transactions and record-keeping.


3. Cost-Effective: Lowers administrative costs related to the handling of physical shares.


4. Increased Liquidity: Enhances market liquidity as electronic shares can be traded more easily.



Dematerialization is a significant aspect of modern financial markets, enabling more streamlined operations and greater accessibility for investors.

@Etstocks
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 282 ሚሊየን ዶላር አዘጋጅቼ 28% ብቻ ነው የተወሰደው!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር 282,459,436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች ቢደለድልም ካዘጋጀው የውጪ ምንዛሬ ውስጥ ደንበኞቹ የተጠቀሙት በአማካይ 28 በመቶ መሆኑን ገልጿል"፡፡

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ‼️

ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።

አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።

ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።

እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር አስታውሶ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብሏል።
ዳሸን ባንክ 6.4 ቢሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ!!

የዳሸን ባንክ ባለአክሲዮኖች ጉባኤ በሚሊንየም አዳራሽ ሲካሄድ የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዱላ መኮንን ባለፈው በጀት ዓመት በአለም አቀፍ ደረጃ ሃገራት የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ያወጧቸው ፖሊሲዎች፣ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት፣ በቀይ ባህር አካባቢ የሚፈፀመው ጥቃት በአለም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደሯቸውን ተፅዕኖዎች አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የነበረው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ ግጭቶችና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩንም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ጥብቅ የገንዘብ ፓሊሲ ይፋ ማድረጉንም አስታውሰው እነዚህ ለውጦች ባንኮች በሚያቀርቡት የብድር መጠንና ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ዳሸን ባንክ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ 

በበጀት ዓመቱ የዳሸን ባንክ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን የ30.9 ቢሊየን ብር እድገት ማስመዝገቡን፣ አጠቃላይ ተቀማጩ 145.9 ቢሊየን ብር መድረሱን አቶ ዱላ ተናግረዋል፡፡ ከወለድ ነፃ ዘርፍ ለባንኩ ተቀማጭ 11.1 ቢሊየን ብር ማበርከቱንም ጠቁመዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው የዳሸን ባንክ አጠቃላይ ሃብት የ27 በመቶ በማደግ 183.7 ቢሊየን ብር መደረሱን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት 1.44 ሚሊየን አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘቱን፣ በአጠቃላይም ከ6.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትም ተናግረዋል፡፡

ዳሸን ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት እና ከኔዘርላንድ የልማት ባንክ ጋር በፈጠረው አጋርነት የ40 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል፡፡