" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።
የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።
ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።
የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል።
#ሪፖርተርጋዜጣ
@Etstocks