#ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውጪ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን ተጠያቂ እናደርጋለን-ፖሊስ
ሰመራ-ሰኔ 16/2013 (አ.ብ.መ.ድ)
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውጪ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፤ በመዲናዋ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን እና ድምጽ የተሰጠባቸው የምርጫ ቁሳቁሶች ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ምርጫ ክልሎች መጓጓዛቸውን ገልፀዋል።
ምርጫው በከተማው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ብሎ የተደረገው ዝግጅት እገዛ ማድረጉን ገልፀው ፖሊሰ ገለልተኛ ሆኖ ለየትኛውም ቡድን ሳያዳላ አገልግሎቱን መስጠቱን ነው የተናገሩት።
በቅድመ፣ በምርጫው እለት እና በድህረ ምርጫ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን ቀድሞ በመተንተን የፀጥታ ሃይሉ ዝግጅት ማድረጉን አስረድተዋል።
በዚህም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስችሏል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
በድህረ ምርጫም ሂደቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በዚሁ ሂደት የምርጫ ውጤት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መገለጽ እንዳለበት በህግ የተደነገገ በመሆኑ ከዚህ ውጭ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን ፖሊስ በህግ ተጠያቂ ያደርጋል ብለዋል።
በአንዳንድ ህገ ወጥ የሚለቀቁ ያልተረጋገጡ ውጤቶች ፍፁም ህጋዊነት የሌላቸው እና በምርጫ ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚያደርጉ መሆኑንም ነው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር የነበረው ትብብር የላቀ እንደነበርም ጠቅሰዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለፖሊስ ላደረገው የሎጀስቲክ ድጋፍም ኮሚሽነር ጌቱ አመስግነዋል።
#AMN

#አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃር ኢብራሂምን ከንቲባ አድርጎ ሾመ፣፣
ሰመራ-መስከረም 19, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃር ኢብራሂምን ከንቲባ አድርጎ ሾመ፣፣
በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድሬዳዋ ህዝብን ይሁንታ ያገኙ ተወካዮች ባካሄዱት የምስረታ ጉባዔ አሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩ አመራሮች ተቀብሎ ሾሟል::
በዚህም አቶ ከድር ጁሃር የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾመዋል::
ለመጪዎቹ 5 ዓመታት ከተማዋን እንዲመሩም በምክር ቤቱ ይሁንታ አግኝተዋል::
አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከከንቲባው ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ፈቲያ አደም ዑመርን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ እንዲሁም ወ/ሮ ከሪማ አሊን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሾሟል::
ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባልነት በተካሄደው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም 186 መቀመጫዎች ማሸነፉ ይታወሳል::
ቀሪ 3 የምክር ቤቱ መቀመጫዎችም መስከረም 24 በሚደረግ ምርጫ የሚሟሉ ይሆናል::

#የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሌሊት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በመንግስታቱ ድርጅት 7 ሰራተኞች ላይ የወሰደውን ከሃገር እንዲወጡ የማድረግ እርምጃ በተመለከተ ምክክር አድርጓል።
ሰመራ-መስከረም 27, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሌሊት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በመንግስታቱ ድርጅት 7 ሰራተኞች ላይ የወሰደውን ከሃገር እንዲወጡ የማድረግ እርምጃ በተመለከተ ምክክር አድርጓል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ እንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ ከመንግስታቱ ድርጅት ህግ በተፃረረ መልኩ ውሳኔ አስተላልፋለች ሲሉ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ አቅርበዋል።
በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ታዬ አቅፀስላሴ በበኩላቸው በዋና ፀሐፊው ጉተሬዝ የቀረበው ሀሳብ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
አምባሳደር ታዬ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት 7ሰራተኞች ላይ የወሰደችው እርምጃ የአለም አቀፍ ህግጋትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀው አንድ ሉዐላዊ ሀገር ህግን ተከትሎ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ይህ ጉባኤ ለምክክር መቀመጡ እንዳስገረማቸውም አስረድተዋል።
የተመድ ሰራተኞችንም ሆነ ዲፕሎማቶችንና ሌሎች መልዕክተኞችን ምክንያቱ በተገለፀ እና ባልተገለፀበት ሁኔታ አንዲት ሉዓላዊነት ሀገር ከድንበራ እንዲለቁ ስትወስን ኢትዮጵያ የመጀመሪያ አለመሆኗን የገለፁት አምባሳደር ታዬ የተመድ ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ለውይይት ተቀምጦ እንደማያውቅም አስታውሸዋል።
በተመድ ህግ መሰሠት የኢትዮጵያ መንግስት በ7ቱ ሰራተኞች በወሰደው እርምጃ ማብራሪያ የሚጠየቅበት አግባብ የለም። በምክር ቤቱ የስነምግባር መርሆዎች (General guiding principles for humanterian assistance 46/182) መሰረት የሀገራት የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሙሉ ለሙሉ መከበር እንዳለበት ይደነግጋል። በዚህ መሰረት በአንድ ሉዓላዊነት ሀገር ውስጥ ማን መግባት ፣ መቆየት እና መውጣት እንዳለበት የመወሰን ስልጣን ያለው ሀገሩ ነው በማለት አምባሳደሩ አብራርተዋል።

#የብልፅግና ፓርቲ ሲያካሂድ በነበረው የመጀመሪያው የፓርቲ ጉባኤ 45 አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል። በዚህ መሰረት፦
1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ዴላሞ
5. ደ/ር ፍፁም አሰፋ
6. አቶ አብረሀም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሃሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡመድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሐመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሃጂ አወል አርባ
16. ሃጂ አሴ አደም
17. አቶ አወሎ አብዲ
18. አቶ ሳዳት ነሻ
19. ወ/ር አዳነች አቤቤ
20. ደ/ር እዮብ ተካልኝ
21. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
22. ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
23. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
24. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
25. አቶ መላኩ አለበል
26. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
27. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
28. አቶ ኤሌማ አቡበከር
29. ወ/ሮ ሃለሞማ ሃሰን
30. አቶ ሙስጠፌ መሐመድ
31. አቶ አህመድ ሺዴ
32. ዶ/ር ነጋሽ ዋኔሾ
33. አቶ ፀጋዬ ማሞ
34. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
35. አቶ ተስፋዬ በልጂጌ
36. አቶ ርስቱ ጥርዳው
37. አቶ ተስፋ ይገዙ
38. አቶ ሞገስ ባልቻ
39. አቶ ጥላሁን ከበደ
40. አቶ መለሰ አለሙ
41. አቶ ሽመለስ አብዲሳ
42. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
43. ዶ/ር አለሙ ስሜ
44. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ
የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።
#AMN
1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ዴላሞ
5. ደ/ር ፍፁም አሰፋ
6. አቶ አብረሀም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሃሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡመድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሐመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሃጂ አወል አርባ
16. ሃጂ አሴ አደም
17. አቶ አወሎ አብዲ
18. አቶ ሳዳት ነሻ
19. ወ/ር አዳነች አቤቤ
20. ደ/ር እዮብ ተካልኝ
21. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
22. ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
23. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
24. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
25. አቶ መላኩ አለበል
26. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
27. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
28. አቶ ኤሌማ አቡበከር
29. ወ/ሮ ሃለሞማ ሃሰን
30. አቶ ሙስጠፌ መሐመድ
31. አቶ አህመድ ሺዴ
32. ዶ/ር ነጋሽ ዋኔሾ
33. አቶ ፀጋዬ ማሞ
34. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
35. አቶ ተስፋዬ በልጂጌ
36. አቶ ርስቱ ጥርዳው
37. አቶ ተስፋ ይገዙ
38. አቶ ሞገስ ባልቻ
39. አቶ ጥላሁን ከበደ
40. አቶ መለሰ አለሙ
41. አቶ ሽመለስ አብዲሳ
42. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
43. ዶ/ር አለሙ ስሜ
44. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ
የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል።
#AMN