#የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሌሊት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በመንግስታቱ ድርጅት 7 ሰራተኞች ላይ የወሰደውን ከሃገር እንዲወጡ የማድረግ እርምጃ በተመለከተ ምክክር አድርጓል።
ሰመራ-መስከረም 27, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሌሊት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በመንግስታቱ ድርጅት 7 ሰራተኞች ላይ የወሰደውን ከሃገር እንዲወጡ የማድረግ እርምጃ በተመለከተ ምክክር አድርጓል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ እንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ ከመንግስታቱ ድርጅት ህግ በተፃረረ መልኩ ውሳኔ አስተላልፋለች ሲሉ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ አቅርበዋል።
በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ታዬ አቅፀስላሴ በበኩላቸው በዋና ፀሐፊው ጉተሬዝ የቀረበው ሀሳብ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል።
አምባሳደር ታዬ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ በመንግስታቱ ድርጅት 7ሰራተኞች ላይ የወሰደችው እርምጃ የአለም አቀፍ ህግጋትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀው አንድ ሉዐላዊ ሀገር ህግን ተከትሎ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ይህ ጉባኤ ለምክክር መቀመጡ እንዳስገረማቸውም አስረድተዋል።
የተመድ ሰራተኞችንም ሆነ ዲፕሎማቶችንና ሌሎች መልዕክተኞችን ምክንያቱ በተገለፀ እና ባልተገለፀበት ሁኔታ አንዲት ሉዓላዊነት ሀገር ከድንበራ እንዲለቁ ስትወስን ኢትዮጵያ የመጀመሪያ አለመሆኗን የገለፁት አምባሳደር ታዬ የተመድ ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ለውይይት ተቀምጦ እንደማያውቅም አስታውሸዋል።
በተመድ ህግ መሰሠት የኢትዮጵያ መንግስት በ7ቱ ሰራተኞች በወሰደው እርምጃ ማብራሪያ የሚጠየቅበት አግባብ የለም። በምክር ቤቱ የስነምግባር መርሆዎች (General guiding principles for humanterian assistance 46/182) መሰረት የሀገራት የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ሙሉ ለሙሉ መከበር እንዳለበት ይደነግጋል። በዚህ መሰረት በአንድ ሉዓላዊነት ሀገር ውስጥ ማን መግባት ፣ መቆየት እና መውጣት እንዳለበት የመወሰን ስልጣን ያለው ሀገሩ ነው በማለት አምባሳደሩ አብራርተዋል።
#AMN