General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ቅዳሜ፡- ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

15ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ተጀመረ፡፡

15ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች ዕይታ ክፍት ተደረገ፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ #አዳነች #አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ #ጥራቱ #በየነን ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ የመዲናይት ከንቲባ በመልዕክታቸው "ችግር ፈቺ ተኪ ምርቶችን በማምረት ሂደት  የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው" ብለዋል።

ክብርት ከንቲባዋ አያይዘውም በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት  ውድድር በከተማ አስተዳደሩ  አጠቃላይ አሸናፊነት በመጠናቀቁ የዘርፉን አመራሮችና ባለሙያዎች  አመስግነዋል።

መንግስት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለዘርፉ ልዪ ትኩረት በመስጠትና በአዳዲስ እሳቤ በመቃኘት ለሀገራዊ ዕድገትና ብልፅግና መረጋገጥ ዋስትና እየሆነ መጥቷል ያሉት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  ኃላፊ ክቡር #አቶ #ጥራቱ #በየነ ናቸው፡፡

በዚህ ኤግዚቪሽን ላይ በ15ቱ የመንግስት ኮሌጆች በሚገኙ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች  የተሰሩ ከ150 በላይ  ችግር ፈቺ የማምረቻ እና የምርት  ቴክኖሎጂ ውጤቶች በአውደ ርዕዩ ላይ ቀርቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ የተሰሩ 5 የማምረቻ እና 6 የምርት ውጤቶች ለጎብኝዎች ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም በኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የሚደረግላቸው 2 ኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ምርታቸውን ይዘው ተገኝተዋል፡፡

ኤግዚቪሽኑ ''ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ለ5 ተከታታይ ቀናት በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተስተናገደ ለጎበኝዎች ክፍት ተደርጎ እንደሚቆይ ተነግሯል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
እሁድ፡- ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ የፋሽን ሾው ትርኢቱን በዛሬ ዕለት አቀረበ!!

የ15ኛው ቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ አካል የሆነውን የፋሽን ሾው ትርኢት ውድድር የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አቀረበ፡፡

ከትናንት ቅዳሜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች እይታ ክፍት የተደረገው 15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ የማምረቻ እና የምርት ፈጠራ ስራዎችን ለተመልካቾች ከማቅረብ ባሻገር በልዩ ልዩ ትርኢቶች እና አዝናኝ ውድድሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም በተካሄደው የፋሽን ሾው ትርኢት በኮሌጆች የተሰሩ የፋሽን ዲዛይኖች የተመልካቾችን ቀልብ የሰረቁ አስደማሚ ስራዎች የታዩ ሲሆን የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክስታይ ሌዘር ጋርመንት ዲፓርትመንት አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች እጃችሁ ይባረክ ያስባለ ፈጠራዎችን ለመድረክ አብቅተዋል፡፡

ዲፓርትመንቱ በጋርመንት እና በሌዘር ዘርፎች ያዘጋጃቸውን ቅንጡ የወንድ እና የሴት ፋሽን ልብሶችን ለታዳሚዎች እና በመድረኩ ለተሰየሙት ዳኞች በማራኪ አቀራረብ አሳይቷል፡፡

ከዲዛይነሮቹ ፍሸና ጋር የሞደሎቹ ውብ አቀራረብ ተዳምሮ የመድረኩን ታዳሚ ቀልብ በመግዛት እውነትም ዊንጌት የከተማይቱ የቴክኒክና ሙያ ድምቀትና ኩራት አስብሎታል።

በቴክኖሎጂ ረገድ በከተማ ደረጃ በዚህ ዐውደ ርዕይ በተለያዩ የሙያ ዓይነቶች ከ150 የማምረቻ፣ የምርት፣ የሀገር በቀል እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተሰርተው ለጎብኝዎች መቅረባቸው ታውቋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ሰኞ፡- ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ ሰራተኞችና ሰልጣኞች ለኤግዚቪሽን የቀረቡ ቴክኖሎጂዎችን ጎበኙ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በ15ኛው ቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ላይ የቀረቡ ቴክኖሎጂዎችን በዛሬው ዕለት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

3ኛ ቀኑን ባስቆጠረውና በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች እይታ ክፍት በተደረገው 15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ላይ ከ150 በላይ የማምረቻ፣ የምርት፣ የሀገር በቀል እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ለተመልካቾች ቀርበዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች እንዲሁም ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተጋበዙ ተማሪዎች በአሰልጣኞችና በሰልጣኞች የተሰሩ አስደናቂ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጎበኙና በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ ምርቶችን ደግሞ እንዲያዩ ከፈለጉም እንዲሸምቱ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከቴክኖሎጂ ጉብኝት ባሻገር ከደጃዝማች ገረሱ ዱኪ /ከቀድሞው አዲስ ከተማ/ ኢንዱስትሪል ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለጎብኝዎች የሻይ፣ ቡና ዝግጅት በማድረግ የበዓሉን ድባብ ለማሳመርና የተመልካችን ቀልብ ለመሳብ ተሞክሯል፡፡

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክነክ ኮሌጅ ከ10 በላይ ቴክኖሎጂዎችን ለዕይታ ያቀረበ ሲሆን በትናንትና ዕለት ደግሞ በቴክስታይ ሌዘር ጋርመንት ዲፓርትመንት አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች የተሰሩ ቅንጡ የወንድ እና የሴት ፋሽን ልብሶችን በፋሽን ሾው ትርኢት መድረክ ላይ ለተመልካቾች ማሳየቱ አይዘነጋም፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››