ቅዳሜ፡- ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
15ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ተጀመረ፡፡
15ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች ዕይታ ክፍት ተደረገ፡፡
በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ #አዳነች #አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ #ጥራቱ #በየነን ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የመዲናይት ከንቲባ በመልዕክታቸው "ችግር ፈቺ ተኪ ምርቶችን በማምረት ሂደት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው" ብለዋል።
ክብርት ከንቲባዋ አያይዘውም በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት ውድድር በከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ አሸናፊነት በመጠናቀቁ የዘርፉን አመራሮችና ባለሙያዎች አመስግነዋል።
መንግስት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለዘርፉ ልዪ ትኩረት በመስጠትና በአዳዲስ እሳቤ በመቃኘት ለሀገራዊ ዕድገትና ብልፅግና መረጋገጥ ዋስትና እየሆነ መጥቷል ያሉት ደግሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር #አቶ #ጥራቱ #በየነ ናቸው፡፡
በዚህ ኤግዚቪሽን ላይ በ15ቱ የመንግስት ኮሌጆች በሚገኙ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ ከ150 በላይ ችግር ፈቺ የማምረቻ እና የምርት ቴክኖሎጂ ውጤቶች በአውደ ርዕዩ ላይ ቀርቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ የተሰሩ 5 የማምረቻ እና 6 የምርት ውጤቶች ለጎብኝዎች ቀርበዋል፡፡
በተጨማሪም በኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የሚደረግላቸው 2 ኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ምርታቸውን ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ኤግዚቪሽኑ ''ብሩህ አዕምሮዎች፤ በክህሎት የበቁ ዜጎች'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ለ5 ተከታታይ ቀናት በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተስተናገደ ለጎበኝዎች ክፍት ተደርጎ እንደሚቆይ ተነግሯል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››