General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የንግድ ሐሳብ ፈጠራ ውድድር
ሐሙስ፡- ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የተመራቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ሁኔታ መከታተያ ጥናት ግኝት ቀረበ!!

የ2016 ተመራቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል መከታተያ ጥናት ግኝት /graduates tracer study findings/ ቀረበ።

ጥናቱ በኮሌጁ ጥናትና ምርምር ቡድን አባላት ተሰርቶ የቀረበ ሲሆን የተመራቂ ሰልጣኞችን የስራ ሁኔታ በዲፓርትመንት፣ በፆታ እና በስራ ዓይነት ተንትኖ ያቀረበ ነው።

በዚህ ጥናት መሰረት ምን ያህሉ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እንደተቀጠሩ፣ ስንቶቹ በራሳቸው ስራ እንደፈጠሩ፣ ምን ያህሉ የሚሰሩት ስራ ከሰለጠኑበት ሙያ ጋር ዝምድና እንዳለውና የትኞቹስ ከስራ ወጪ እንደሆኑ መረጃ የሰጠ ነው፡፡

ጥናትና ምርምሩ ሲቀርብ ሀሳብ ያዋጡ ዘንድ ከፍተኛ ሙያና የካበተ ልምድ ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የጥናት ሰነዱን በአስተያየት እንዲያዳብሩ ተደርጓል፡፡

በኮሌጁ የ2016 ዓ.ም አጠቃላይ ተመራቂዎች ዉስጥ ከ91 ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት ወደ ስራ የገቡ ሲሆን አብዛኛዎቹ በተማሩት የሙያ መስክ መሰማራታቸው ተረጋግጧል።

ተመራቂዎቹ በመንግስት መስሪያ ቤት እና በኢንዱስትሪዎች በመቀጠር እንዲሁም በግላቸው እና ተደራጅተው በመስራት ወደ ክፍለ ኢኮኖሚው አበርክቶ መግባታቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል ጥናቱ በአሰልጣኞች፣ በሰልጣኞች እንዲሁም በትብብር ስልጠና ሰጭ ድርጅቶች ያለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች ተንትኖ አሳይቷል።

የተመራቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ሁኔታ መከታተያ ጥናትና ምርምር በየዓመቱ የሚደረግ ሲሆን የተመራቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ሁኔታን ለማወቅና ኮሌጁ ለሚሰጣቸው ስልጠናዎች የገበያው ፍላጎትን ለመዳሰስ ነወ፡፡

"በላቀ አገ ልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"